Wednesday, October 9, 2013

Photos of Ben Salam Khaled | responsible for the Lampedusa tragedy.

Ben Salam is likely to be charged with human trafficking and with multiple counts of voluntary manslaughter, the prosecutor said. As the skipper, Ben Salam was responsible for allowing too many people aboard the boat and witness accounts indicate that it was he – or someone acting on his instructions – who set a piece of cloth on fire in a bid to attract attention from other vessels once the boat began taking on water near Lampedusa, Di Natale said. source - http://www.raimoq.com/photos-of-ben-salam-khaled-responsible-for-the-lampedusa-tragedy/

ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች አድማ መቱ !

በማይ አይኒ እና አድሃሩሽ (ጸለምት ወረዳ )ኢትዮጵያውያ የሚገኙ የኤርትራውያን ስደተኞች የተቃውሞ ድምጻቸውን በማሰማት ላይ ናቸው ። ኤርትራውያን ስደተኞች ድምጻቸውን ማሰማት ከጀመሩ ሶስት ቀን አልፎታል እስካሁን የወያኔ ፖሊስ በወሰደው እርምጃ ሶስት ኤርትራዊያን ስደተኞች ህይወታቸው አልፏ ። የተቃውሞው መነሻ የስደተኛው አያያዝ እንደሆነ ይነገራል ። የኤርትራውያን ስደተኞች ከኢትዮጵያ ወደ ሱዳን ከሱዳን ወደ ሊቢያ በመሄድ ለአሰቃቂው የባህር ላይ እልቂት የሚጋለጡ በኢትዮጵያ እና በሌሎች የአፍሪካ ሃገር በሚደርስባቸው የተበላሽ የስደተኛ አያያዝ እንደሆነ ብዙ የችግሩ ገፈት ቀማሽ ወገኖች ይናገራሉ ። ከዚህ በታች የሚገኘውን ሊንክ በመጫን የ አካባቢው ያለው ድባባ ይመልከቱ ። http://www.youtube.com/watch?v=J2yhldbm1YA

Tuesday, October 8, 2013

ሞዴስ ወንዶችንም ለሞት ሊያበቃ ለሚችል በሽታ ይዳርጋል

ሴቶች የወር አበባቸውን የሚያዩበት ዕድሜ በአኗኗር ሁኔታ፣ በአመጋገብና በአካባቢያዊ ሁኔታዎች ሊለያይ የሚችል ቢሆንም በአብዛኛው ከ14 ዓመት ዕድሜያቸው ጀምሮ የወር አበባቸውን ያያሉ፡፡ ምቾት ባለበት አኗኗር ውስጥ የሚያድጉ ልጆች፤ ከዚህ ዕድሜ ቀደም ብለው የወር አበባቸውን ሊያዩ ይችላሉ፡፡ ይህ ቀደም ባሉት ዓመታት የነበረው የወር አበባ ማያ የዕድሜ ገደብ ዛሬ ዛሬ እየወረደ መጥቶ ታዳጊ ሴት ህፃናቱ፣ በዘጠኝና በአስር ዓመት ዕድሜያቸው ላይ የወር አበባ ማየታቸው እየተለመደ መጥቷል፡፡ ህፃናቱ የሰውነታቸው ዕድገት ፈጣን እንደመሆኑ ሁሉ የውስጣዊ አካላቸው ዕድገትና ለውጥ እንዲሁ ፈጣን ነው፡፡ እነዚህ ታዳጊ ህፃናት የወር አበባ ምንነትና ሒደቱ በሰውነታቸው ላይ ስለሚያስከትለው ተፈጥሮአዊ ለውጥ ግንዛቤ ባላገኙበት ዕድሜያቸው ላይ ይህ ክስተት ሲገጥማቸው ለከፍተኛ ድንጋጤና የሥነልቡና ጫና መዳረጋቸው የማይቀር ነው፡፡ ችግሩ እንዳይከሰት ቤተሰብ በተለይም እናቶች ለሴት ታዳጊ ልጆቻቸው ስለወር አበባ ምንነትና የወር አበባ በሚመጣ ጊዜ ሊደረጉ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች እንዲሁም በወር አበባ ወቅት የግል ንጽህናን በአግባቡ መጠበቅ እጅግ አስፈላጊነ መሆኑን በጊዜ ማስተማርና ልጆቻቸውን ማዘጋጀት እንደሚኖርባቸው የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ። ልጆቹ ያላወቁትና ይከሰትብኛል ብለው ያላሰቡት ነገር ሲገጥማቸው ከፍተኛ ድንጋጤና የሥነልቡና ችግር እንደሚደርስባቸውም ባለሙያዎቹ ይገልፃሉ። ቀደም ባሉት ዘመናት እናቶች የወር አበባቸው በሚመጣበት ጊዜ ከነጠላና አሮጌ ቀሚሶች ቅዳጅ እየቆረጡ በሚያዘጋጇቸው ጨርቆች የወር አበባቸውን እየተቀበሉ ንጽህናቸውን ይጠብቁ ነበር። ጨርቆቹ እየታጠቡ ከአንድ ጊዜ በላይ አገልግሎት እንዲሰጡ ይደረጉ ነበር፡፡ አሁንም ቢሆን በአገራችን በርካታ አካባቢዎች ጥቅም ላይ እየዋለ ነው። ሴቶች የወር አበባቸው በሚመጣበት ወቅት የሚጠቀሙበትና ንጽህናቸውን የሚጠብቁበት መንገድ በአብዛኛው ባህላዊና ተለምዶአዊ ነው፡፡ ዘመናዊነቱ እየተስፋፋ፣ ቴክኖሎጂው እያደገ ሲሄድ ለሴቶች የወር አበባ መቀበያነት የሚያገለግሉና የሴቶቹና ንጽህና የሚጠብቁ ሞዴሶች ተሰርተው ገበያ ላይ መዋል ጀመሩ፡፡ የእነዚህ ምርቶች ገበያ ላይ መዋል ሴቶች በወር አበባ ወቅት የሚሰማቸውን የህመም እና ያለመመቸት ስሜት በእጅጉ ከመቀነሱ ባሻገር፣ ንጽህናቸው በአግባቡ ባልተጠበቁ ጨርቆች ሳቢያ የሚከሰቱ ችግሮችን ለማስቀረት አስችሏል፡፡ በፋብሪካ ደረጃ እየተመረቱ በጥቅም ላይ የሚውሉ ዘመናዊ የወር አበባ መቀበያ ፓዶችም ሆኑ የወር አበባ መቀበያ እራፊ ጨርቆቹ እጅግ አደገኛ የሆኑ ችግሮችን እንደሚያስከትሉ ጥናቶች ጠቁመዋል፡፡ “ጆርናል ኦፍ ኢንፌክሽን ዲዚዝ” ይፋ ባደረገው መረጃ፤ በወር አበባ መቀበያ ሞዴሶች ሳቢያ የሚራቡት አደገኛ ባክቴሪያዎች ከሴቶችም አልፈው ወንዶችን ለህልፈተ ህይወት እየዳረጉ ነው፡፡ በወር አበባ ወቅት በሚፈሰው ደም ውስጥ ጉሉኮስን የመሰሉ ለባክቴሪያ መራባት እጅግ አስፈላጊና ምቹ የሆኑ ነገሮች ይገኛሉ፡፡ እነዚህም በወር አበባ መቀበያ ሞዴስ ውስጥ በመግባት በቀላሉ ለመራባትና ለመሰራጨት ይችላሉ፡፡ ስታፈሎከሰስ የተባሉት እጅግ አደገኛ ችግር ሊያስከትል ለሚችል በሽታ ምክንያት የሚሆኑት ባክቴሪያዎች “ቶክሲክ ሽክ ሲንድረም” የተባለና እስከ ሞት ሊያደርስ የሚችል አደገኛ የፍትወተ አካል ኢንፌክሽን ይፈጥራሉ፡፡ በአብዛኛው ችግሩ የሚከሰተው ረዘም ላለ ጊዜ ጥቅም ላይ በሚውሉ (በወር አበባ ወቅት በሴቷ ብልት ላይ ረዥም ሰዓት በሚቆዩ) ሞዴሶች ወይንም ንጽህናቸው በአግባቡ ባልተጠበቀና በተደጋጋሚ በጥቅም ላይ በሚውሉ የወር አበባ መቀበያ ጨርቆች አማካኝነት መሆኑንም መረጃ አመልክቷል፡፡ ችግሩን እጅግ የከፋ የሚያደርገው ሌላው ጉዳይ፤ ይህ በሞዴሱ ሳቢያ የሚከሰተው አደገኛ በሽታ ለወንዶችም መትረፉ ነው፡፡ የችግሩ ሰለባ ከሆነች ሴት ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት የፈፀሙ ወንዶችም “በቶክሲክ ሾክ ሲንድረም” መጠቃታቸው አይቀሬ ነው፡፡ ችግሩ በወቅቱ ታውቆ ተገቢው ህክምና ካልተደረገለትም ለሞት ሊያደርስ እንደሚችል መረጃው አመልክቷል። የወር አበባ መቀበያ ሞዴሶች በሴቷ ሰውነት ላይ መቆየት የሚገባቸው ከ3-4 ሰዓታት መሆን ይገባዋል ያለው መረጃው፤ ከዚህ ለበለጠ ጊዜ የሚቆይ ከሆነ ለባክቴሪያ መራቢያ ምቹ ሁኔታዎች ስለሚፈጠሩ ይኸው ስታፍሎኮከስ ኦርስ የተባለው ባክቴሪያ ይራባና ”ቶክሲክ ሾክ ሲንድረም” የተባለውን አደገኛ በሽታ ሊያስከትል እንደሚችል ገልጿል፡፡ ይህ እጅግ አደገኛና በግብረሥጋ ግንኙነት ሳቢያ ከአንዱ ወደ አንዱ የሚተላለፍ በሽታ ከመከሰቱ በፊት ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባና ሴቶች በወር አበባ ወቅት የሚጠቀሙበትን ሞዴስ በንጽህና ሊጠቀሙበት እንደሚገባ “ጆርናል ኦፍ ኢንፌክሽን ዲዚዝ” አሳስቧል። addis admas

ከሜዲትራንያኑ የባህር አደጋ የተረፈው ኢትዮጵያዊ አጭር የቪዲዮ ምስክርነት

ከሜዲትራንያኑ የባህር አደጋ የተረፈው ኢትዮጵያዊ አጭር የቪዲዮ ምስክርነት http://www.youtube.com/watch?v=05dBIYSrduU

Ethnic apartheid regime of the TPLF

Ethnic apartheid regime of the TPLF is not a formidable foe when we utilize our collective strength. As we do, we do not need the permission of TPLF/EPRDF or their supporters—inside or outside Ethiopia—in order for us to come together. We also can do it at the time of our own choosing! This is not the same old game. The rules of operation have changed. The rules of change means tolerating some degree of division as part of a process of sorting out the best ways to get to a common goal. New leadership, where the leaders put humanity before ethnicity, will automatically produce some inner tensions between the goals, values and tactics of these new leaders and those who believe in ethnic divide and conquer politics. TPLF uses Article 39 for its own advancement at the cost of the destruction of the country. People are supposed to think they have autonomy, but they are under the control of the TPLF. TPLF/EPRDF does not want all the varied groups with their different approaches to have a dialogue and to come up with common goals. Yet, dialogue and compromise is the best means to be used to restore peace and harmony to Ethiopia. Because of this, we in the SMNE, and others are determined to work as hard as possible to accomplish such solidarity. We will try to make sure that all these political, civic and religious groups come together in the same room and have a dialogue for a lasting peace in Ethiopia. An atmosphere of peace is just the beginning of the road to building a future for a New Ethiopia. source -Obang Metho

የኢትዮጵያ ስደተኞች እና የላምቤዱዛው እልቂት አዲስ ዘገባ

የኢትዮጵያ ስደተኞች እና የላምቤዱዛው እልቂት አዲስ ዘገባ አንድ N R K የሚባል የኖርዎይ ቴሌቪን በላምቤዱዛው የባህር ላይ እልቂት አስመልክቶ ባወጣው ዘገባ አሳዛኝነቱ በተጨማሪ አንድ ነገር ትኩረቴን ሳበው ። ነገሩ እንዲህ ነው ብዙ የመገናኛ ብዙሃን የሚዘግቡት የኤርትራውያን ስደተኞች እያሉ ነው ። ነገር ግን N R K እንደዘገበው ከተረፉት 150 ሰዎች መቻከል 43 ቱ እድሚያቼው ከ 11 እስከ 17 የሚሆን ነው ። ከእነዚህ ውስጥ ብዙሃኑ ከኢትዮጵያ የመጡ ስደቶኞች ናቸው ሲል ዘግቡዋል ። 41 children survived the refugee boat with over 500 people on board capsized. They were between 11 and 17 years and most are from Ethiopia. Now, Save the Children helps them to move on alone. ሙሉ ዘገባውን ለማገኘት የሚከተለውን ሊንክ ከፍተው ይተርጉሙ http://www.nrk.no/verden/vil-til-norge-etter-bathavari-1.11285143 የሞቱትን ኢትዮጵያዊ እና ኤርትራዊ ወገኖቻችንን ነፍሳቸውን ይማር ። ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እመኛለሁ !

Monday, October 7, 2013

መሬት የማን ነው? (ክፍል አንድ) ፕ/ር መሰፍን ወ/ማርያም

አገር ማለት በአባቶች፣ በአያቶችና በቅድማያቶች አጥንትና ደም ተገንብቶ የታጠረ መሬት ነው፤ የዶር. በድሉ ዋቅጅራን ዋይታ እየኮረኮረ የሚያወጣውና የሚያስተጋባው የፍቅር ስሜት ምንጭ ነው። የተከሰከሰውና ተፈረካክሶ አፈር የሆነው አጥንትና የወረደው የአያቶችና የቅድማያቶች ደም እየፈሰሰ መሬቱ ላይ በሚገኙ ወንዞች ውስጥ ሁሉ ገብቶአል፤ እንዲያውም እነዚህ ወንዞች ወስደው በቀይ ባሕር፣ በሜዲቴራንያን ባሕርና በሕንድ ውቅያኖስ ጨምረውታል፤ Prof. Mesfin Woldemariam ይህ በአጥንትና በደም የታጠረ መሬት የማን ነው? በመሬቱ ላይ የባለቤትነት መብትን ለማስከበር ከውጭ ኃይሎች ጋር የተጋደሉት ጥንታውያን ነፍጠኞች ቅድሚያን የሚያገኙ ይመስለኛል፤ እነዚህ ጥንታውያን ነፍጠኞች ብቻቸውን አልነበሩም፤ ለምግብ የሚሆናቸውን ሁሉ የሚያመርቱ ገበሬዎች ነበሩ፤ ለልብስ የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ የሚፈትሉና የሚሸምኑ ባለሙያዎች ነበሩ፤ ልጆቻቸውን የሚንከባከቡና የሚያሳድጉም ለዘማቹ ምግብ የሚያቀብሉ እናቶች ነበሩ፤ በአጠቃላይ የሕዝቡን መንፈሳዊ ጤንነት ለመጠበቅ በቤተ ክርስቲያኖችና በመስጊዶች የሚጸልዩ ሰዎች ነበሩ፤ ሰላምን የሚያስከብሩና የሚያስተዳድሩ ሰዎች ነበሩ፤ … አንድ ማኅበረሰብ ለተለያዩ የመደጋገፍ ሥራዎች የሚያስፈልጉት የሰዎች ዓይነት ሁሉ ነበሩ፤ እነዚህ ሰዎች ሁሉ በአንድ ላይ አጥሩን ለመገንባት አስተዋጽኦ አድርገዋል፤ ስለዚህ መሬቱ የእነዚህ ሰዎች ሁሉ ነው። ታሪካችንን በተግባር በኩል ስንመረምረው ግን መሬቱን እኩል እንዳልተካፈሉት እናያለን፤ ዛሬ ነፍጠኛ የሚባሉት መሣሪያ የታጠቁት ሰዎች ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ እንደሚባለው ሰፋፊ መሬት የመያዝ ዝንባሌ ነበራቸው፤ ነገር ግን ለማረስ የነበራቸው የሰው ጉልበትና የጥንድ በሬ ቁጥር የተወሰነ በመሆኑ ራሱንና ቤተሰቡን ለማስተዳደር ብቻ ለሚፈልገው ገበሬ በቂ መሬት ይደርሰው ነበር፤ ሰፋፊ መሬት የያዙት ጉልበት አጥሮአቸው ሲቸገሩና ትናንሽ ማሳ ያለው ገበሬ ሰብሉ ቀንሶበት ሲቸገር በመጋዞ በማረስ ይረዳዱ ነበር (ገበሬዎችና ከብት አርቢዎችም ላሚቱ ስትወልድ ሴት ከሆነች ለከብት አርቢው፣ የከብት አርቢው ላም ወንድ ስትወልድ ለገበሬው እየተሰጣጡ ይረዳዱ ነበር፤) ሰፋፊ መሬት ያዙትም በጉልበት እጥረት ምክንያት፣ ትናንሽ ማሳ የያዙትም በትንሽነታቸው ምክንያት ከአስፈላጊው በላይ ስለማያመርቱ ትርፍ ምርት ቢኖርም በጣም ትንሽ ነበር፤ ከላይ እሰከታች ያለው ሰው ሁሉ የሚተዳደረው በመሬት ስለነበረ በጣም ጥቂት ለሆኑ ሰዎች (ቀጥቃጮች፣ አንጣሪዎች፣ ሸክላ ሠሪዎች፣ ሸማኔዎች … ወዘተ.) ለጉልበት ዋጋ ከሚከፈለውና ለአስተዳዳሪዎች ከሚከፈለው ግብር በቀር አብዛኛው ምርት ለቤት ፍጆታ ነበር። እዚህ ላይ በመሬት ጉዳይ ላይ ለመታረም ያስቸገሩ ሁለት ስሕተቶችን ሳላመለክት ለማለፍ አልፈልግም፤ ብዙ ጊዜ እንዲታረሙ ብጥርም ፈረንጆች በብዙ ሰዎች አእምሮ ውስጥ በሙጫ አጣብቀውት ሊፋቅ አልቻለም፤ አንደኛ ገባር ማለት ባለመሬት ማለት ነው እንጂ ጪሰኛ ወይም መሬት የሌለው ሰው ማለት አይደለም፤ መሬት የሌለው ገባር አይባልም፤ መገበር ማለት የባለመሬት ግዳጅ ነው፤ ገባር ማለት ግብር ወይም ታክስ የሚከፍል ባለመሬት ነው፤ ጉዳዩን አጣርተው ያልተገነዘቡት ፈረንጆች በራሳቸው አገር የመሬት ስሪት ዓይነት እንደተረጎሙት ለኢትዮጵያውያን ወጣቶች አስተማሩ፤ እነዚያም ያንኑ እንደገደል ማሚቶ እያስተጋቡ ስሕተቱን አራቡት፤ ‹‹ፊውዳሊዝም›› የሚለው ቃልም ከዚህ ስሕተት ጋር የተያያዘ ነው፤ አውሮፓ የነበረው ፊውዳሊዝም የሚባል ነገር በኢትዮጵያ ኖሮም አያውቅ። ሁለተኛው ከመሬት ጋር የተያያዘ ቃል ጉልት ነው፤ ጉልት በመሬት ላይ ያለ መብት ሳይሆን በመሬቱ ከፊል ምርት ላይ የተሰጠ መብት ነው፤ ዱሮ ገንዘብ አልነበረምና በጥሬ ገንዘብ የሚከፈል ዋጋ አልነበረም፤ ለወታደሮችም ቢሆን በደመወዝ ፈንታ የሚሰጣቸው ገባሮች ነበሩ፤ ዛሬ ባለመሬቶች በጥሬ ገንዘብ ለመንግሥት ይከፍሉና ገንዘቡ ተሰብስቦ ለወታደሮችም ሆነ ለሌሎች የመንግሥት ሠራተኞች ይከፈላል፤ ጥንት ግን ግብር ከፋዩን (ማለት ገባሩን) በቀጥታ ከመንግሥት አገልጋዩ ጋር ያገኛኙትና በእህል እንዲቀልበውና በጉልበት እንዲረዳው ይደረግ ነበር፤ ይህ ሥርዓት አልተበላሸም ለማለት አይቻልም፤ ሆኖም የመንግሥት አገልጋዮች በገባሩ መሬት ላይ ምንም መብት አልነበራቸውም፤ እንዲሁም ጉልት የተሰጣቸው የመንግሥት ባለውለታ የሆኑ መሳፍንትና መኳንንት፣ ሴት ወይዘሮዎችም በመሬቱ ላይ ሳይሆን ለመሬቱ በሚከፈለው ግብር ላይ ነበር፤ የጉልት ሥርዓት እያሉ የሚጽፉ ወይም የሚናገሩ ሰዎች አለማወቃቸውን እያራቡ ነው። የኢትዮጵያን የመሬት ስሪት ውስብስብነት በትንሹም ቢሆን ለመረዳት ሌላ ቢቀር የብላቴን ጌታ ማኅተመ ሥላሴን ዝክረ ነገር ይመልከቱት፤ የጥንቱን እንተወውና በቅርብ ዓመታት ኢትዮጵያ ከሶማልያ ጋር ቢያንስ ሁለት ጊዜ ተዋግታለች፤ ከኤርትራ ጋር የተደረገውን ጦርነት ደግሞ ብዙ ወጣቶችም የሚያውቁት ነው፤ እነዚህ ጦርነቶች የተደረጉት በመሬት ምክንያት ነበር፤ ምናልባትም ከሶማልያ ጋር ሁለት ጊዜ ከተደረጉት ጦርነቶች ይልቅ ከኤርትራ ጋር በተደረገው ጦርነት የተገደሉት የኢትዮጵያውያን ቁጥር በጣም የላቀ ሳይሆን አይቀርም፤ ከዚያም በላይ ከኤርትራ ጋር ጦርነት የተደረገበት ምክንያት ከሶማልያ ጋር ከተደረጉት ጦርነቶች ምክንያት በጣም ያነሰ ነው፤ በአጠቃላይ አገሪቱን በሙሉ ለመውረር የመጣውንም ሆነ አንዲት ትንሽ መንደር የወረረውን እኩል በመዋጋት ሀብትንና የሰው ሕይወትን ማቃጠል የማሰብ ችግር ውጤት ነው፤ ለጊዜው ዋናው ነጥባችን በነዚህ ጦርነቶች የሞቱት ሰዎች መሬቱ የኛ ነው፤ አንሰጥም፤ በማለት ነው፤ በሌላ አነጋገር የመሬቱ ባለቤት፣ የመሬቱ ባለመብት እኛ በመሆናችን ያለፈቃዳችን ሌላ አይወስደውም በማለት ነው። ባለቤትና ባለመብት ሆኖ የሞተውና በየሜዳው ላይ ሬሳው ወድቆ ሳይቀበር ለጅብና ለአሞራ ምግብ የሆነው ኢትዮጵያዊ መሬትን እንኳን ለኑሮ ለመቃብርም አላገኘም፤ በሆነው ባልሆነው መጫወቻ የሆነው መስዋእት የሚባል ቃል ትክክለኛ ትርጉሙ ይህ ነው፤ እንግዲህ ይህ ሰው መስዋእት የሆነው ለምን ዓላማ? ለማን ዓላማ ነው? የሚለው ጥያቄ መሠረታዊ ነው፤ ማንም ሰው ለመሞት በቆረጠበት ጊዜ ‹‹የምሞተው ለምን ዓላማ ነው?›› ብሎ መጠየቅ አለበት።