Tuesday, October 15, 2013
UNITY IS POWER: Nhatty Man & Jacky Gosse - Fim Esat [NEW! Music Vi...
UNITY IS POWER: Nhatty Man & Jacky Gosse - Fim Esat [NEW! Music Vi...: በጣም ተወዳጅ የሆነው የ ናቲና የ ጃኪ ፍም እሳት የሚለውሙዚቃ በስተመጨረሻ ክሊፑ ተለቋል። በኔ አመለካከት የሙዚቃው መልእክት በኢትዮጵያ የእግር ክኳስ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረገውና ባሁኑ ወቅት በጣም ከፍተ...
ተሸላሚ ያጣው የሞ ኢብራሂም ሽልማት
በመልካም አስተዳደር ለተመረጡ የአፍሪቃ መሪዎች ለሚሰጠው የሞኢ ኢብራሂም ሽልማት በዚህ ዓመት ተሸላሚ እንዳልተገኘ ድርጅቱ ዛሬ ለንደን ውስጥ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል ።
ሞኢ ኢብራሂም የተባለው ድርጅት በመልካም አስተዳደር ለተመረጡ የአፍሪቃ መሪዎች ለሚሰጠው ሽልማት በዚህ ዓመት መስፈርቱን ያሟላ መሪ አለማግኘቱን አስታወቀ ። ድርጅቱ ዛሬ ለንደን ውስጥ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ በዚህ ዓመት ተሸላሚ እንደሌለ አስታውቋል ። ከ52 የአፍሪቃ ሃገራት መሪዎች መካከል የድርጅቱን መስፈርት ያሟላ መሪ አለመገኘቱ በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አነጋጋሪ ጉዳይ ነበር ። ድርጅቱ ለአፍሪቃ ሃገራት የሰጠው የመልካም አስተዳደር ደረጃም ዛሬ ይፋ ሆኗል ። የለንደኑ ዘጋቢያችን ድልነሳ ጌታነህ ዝርዝሩን ልኮልናል ።
ድልነሳ ጌታነህ
ሂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ
ከሊቢያ ለጉዞ የተዘጋጁ ስደተኞች
አፍሪቃ
ኣንዳንድ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ስደተኞች ታጉረው ከሚገኙበት ወይንም ተደብቀው ጀልባ ከሚጠባበቁበት የትሪፖሊ ማጎሪያ ቤት ለዶቸቬሌ አነጋግሯቸዋል።
እንደተናገሩትም በሱዳን በኩል ኣድርገው ሊቢያ እስኪደርሱ በዚህ ረጅም የበረሃ ጉዞ የደረሰባቸውስቃይ ሳያንሳቸው ኣሁንም የባህር ላይ ኣሰቃቂ ጉዞ ይጠብቃቸዋል። በእርግጥ ስደተኞቹ እንደሚሉት ያ ከሁለት መጥፎ ይሻላል ብለው የመረጡት የተሻለ መጥፎ በመሆኑ እዚያው ሊቢያ ውስጥ በፖሊሶች የሚደርስባቸውን ዘረፋ እና እስራት ነው ይበልጥ የሚያማርሩት።
ከ UNHCRየጀኔቫ ቢሮ ቃል ኣቀባዩ ሚ/ር ዳን ሚክኖኣፓኔ እንደሚሉት ለችግሩ መፍትሄ ለመሻት የሚደረገው ጥረት ማነጣጠር ያለበት መነሻው ላይ ነው።
ይህ ግን ጊዜ የሚፈጅ በመሆኑ ሚ/ር ዳን እንደሚሉት የኣውሮፓ ህብረት እና ሌሎችም ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ስደተኞች ተገን የሚጠይቁበትን ቦታ እና የሚያገኙበትን ሁኔታ እንደገና ሊመረምሩ ይገባል። ከዚሁ ጎን ለጎን ደግሞ የባህር ላይ ቁጥጥሩም በእርግጥ ሊጠናከር ይገባል ባይ ናቸው ሚ/ር ዳን።
ጃፈር ዓሊ
ሸዋዬ ለገሰ
Sunday, October 13, 2013
ስብሃት ነጋ በአሁን ሰአት በፖሊስ እየታደኑ ነው !
በአሌክሳንደሪያ ቨርጂኒያ ከአንድ ሰአት በፊት ስብሃት ነጋና አብሯቸው የነበረ ግለሰብ በአንድ ኢትዮጲያዊ ላይ ከፍተኛ ድብደባ ፈፅመው ማምለጣቸውን ማረጋገጥ ተችሏል። መስፍንsebehat nega one of the founders of TPLF የተባለው ኢትዮጲያዊ በአሁኑ ሰአት በሆስፒታል የሚገኝ ሲሆን የሲቪሊቲ ሩም ፓልቶክ አዘጋጅ አባ መላ በስልክ አግኝቶት ስለሁኔታው ያነጋገረው ሲሆን፤ መስፍን እንደገለፀው በድብደባው ጅርባው እንደተጎዳና ብዙ ደም እንደፈሰሰው ገፆዋል። እነስብሃት ድብደባውን ሲፈፅሙ በቅርብ ርቀት ቪዲዮ እየተቀረፁ እንደነበረና ይህኑን ማስረጃ ለፖሊስ መስጠታቸው ታውቋል። ድርጊቱ ከተፈፀመ በኋላ ፖሊስ በአካባቢው ፈጥኖ የደረሰ ሲሆን፣ በአሁን ሰአት እነስብሃትን ለመያዝ ፖሊስ መሰማራቱ ታውቋል።
ከኢየሩሳሌም አርአያ
Saturday, October 12, 2013
ከስክሪን ጅርባ በመሆን የሰዎችን እቅድ ለምታደናቅፉ የወያኔ ጀሌሆች
በዚህ እድገታችን እጅግ ፈጣን በሆነበት 21ኛዉ ክፍለ ዘመን እየኖርን አስተሳሰባችን እጅግ የላቀንና የማስተዋል ችሎታችን እጅግ የፈጠነ በሆነበት ሰዓት ፡ ከስዎች ጋር ተነጋግረን መረዳዳት አንደውም ጉለታችንን መማማር በምንችልብት በዚ ጊዜ፡
ከስክሪን ጅርባ በመሆን የሰዎችን እቅድ ለምታደናቅፉ የወያኔ ጀሌሆች፡ እሊና እንዳለው ሰው ሁኔታዎችን እንዳትመለከቱ ወያኔ በላቀ ደረጃ ሚናሁን እየተጫወተባችሁ ይገኛል።
አብዛኞዉን ኢትዮዺያዊ እየተራበ እና እተጠማ ባለበት በዚ አስቸጋሪ ሰዓት፡
ወያኔ እንደራሳቸዉ ህሊና የሌላቸዉን ለመለምለም ሆዳችሁን ብቻ እየሞላ እሊናቸሁ ግን ባዶ አንዲሆን ጊዜ ወስዶ ሲቀርፃችሁ ነበር።
አዉንም የሆድ አዳሪሁን ተግባር ለሟሟላት ለምትራራጡ እና በተለያየ መንገድ የሰሆችን ስራ ለማበላሽት ከምስኪኑ ሕዝብ ተነጥኮ ለናንተ ይሄንን ስራ እንድታከናሁኑ የተከፍላችሁ አሁን ምንም መሄጃ ስለሌላችሁ ለህለናችሁ መኖርን ብትመረጡ ይሻላችዋል።
ከጀግናዉ ወገኖቻችን ጋር እጅ ለእጅ በመያያዝ ልክ እንደ ጥንቱ እንደልማዳችን ለህሊና እና ለወገን የምንኖርበትን መንገድ ማንም ለያስቆመን ስለማይችል ከንቱ ልፋታችሁን ብታቆሙ ይመረጣል።
፦ ራሄል ኤፍሬም ከኖርዌይ
Friday, October 11, 2013
የናቁት ያደርጋል እራቁት
ታሪክ አንዳስቀመጠልን በሃገራችን ሰው የሚኖርበትን ኣካባቢ ለቆ የሚሰደደው የተሻለ ትምህርት ለማግኘትና የሄደበትን አላማ ሲጨርስ ሀገሩን ለማገልገል እንደሆነ የታሪክ ምንጮች ይገልጻሉ።
ዛሬ በተለያየ መንገድ ተሰደው የተለያዩ አሰቃቂ ችግሮች የሚደርስባቸው ሴት እህቶቻችን በ አረብ ሀገር ውስጥ የሚደርስላቸውን አጥተው እንደወጡ የሚቀሩት፣ በደቡብ አፍሪካ ስንት ወገኖቻችን የእንስሳት ሆድ መሙያ የሆኑበት፣ የሰሀራ በረሀ ስንት ወገኖቻችንን አፍኖ ያስቀረበት፣ በተለያዩ ሀገሮች እንዲህ ነው ሊባል የማይችል ስቃይ እየደረሰባቸው ሰሚ አጥተው በወጡበት የቀሩት ወገኖቻችን ማን ነው የሚያየው?
ማነውስ የሚደርስላቸው?
የላምፐዱሳ ደሴት ውጦ ጸጥ ያለውን የወንድሞቻችን እና የእህቶቻችንን እንዲሁም ምንም የማያውቁ ህጻናትንስ ማን ነው የሚያድነው? ማነውስ በቃ የሚለው?
እሬሳቸው ሀገርና ወገን እንደሌለው ወድቀው ለሚገኙት እና የስደት መከራ በየግዜው ለሚያሰቃየን፣ ሀገራቸው ውስጥ የነጻነት መብታቸውን ተነጥቀው፣ ፍትህን አጥተው በእስር እየተሰቃዩ ላሉት፣
በሀገራቸው የመኖር መብታቸውን ተቀምተው ለሚንከራተቱት፣ ነጻነት እና ዲሞክራሲ እንደውሃ ከጠማው ህዝባችን ጋር በፍቅር እጅ ለእጅ ተያይዘን ሆድ እንጂ ጭንቅላት የሌለውን የዚህ ሁሉ ወገኖቻችን እልቂት፣ ስቃይ፣ መከራና መንከራተት ምክንያት የሆነውን ይህንን ባንዳ ከናዚ ባልተናነሰ መንገድ ሀገራችንን በተለያየ መንገድ ደብዛዋን ሊያጠፋ ቆርጦ ለራሱ ቃል የገባውን ቆርጠን ተነስተን የስልጣን ፍቅሩን በውርደት ኣስለቅቀን ለፍርድ ማቅረብ የምንችልበት ግዜ አሁን ነው!!
አንድ ላይ በመሆን የናቁት እንዴት እንደሚያስቀር እራቁት በተግባር ለማሳየት የድሮው ይበቃል ብለን ቆርጠን መነሳት ይኖርብናል።
ራሄል ኤፍሬም ከኖርዌይ
የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ወደ ፖሊስ ጣብያ ተወሰዱ
October 11, 2013
በአሁኑ ወቅት በመነን አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ በቁጥጥር ስር የነበሩት የፓርቲ አመራሮች ወደ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ መወሰዳቸዉን አሁን የደረሰን መረጃ ይገልፃል፡፡
***
ጉዳዩ እንደዚህ ነው መንግስት ነኝ ባዩ በስራው ግን ከማፍያ ቡድን እምብዛም የማይለየው ህወሀት/ኢህአዴግ በተለየም የሰማያዊ ፓርቲ እና የአንድነት ፓርቲ አጠናክረው የቀጠሉት የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴ ስጋት ውስጥ ጥሎታል።
“ሳይቃጠል በቅጠል” እንዲሉ ይህን ህዝብ ውስጥ በፍጥነት እየሰረጸ የመጣውን እንቅስቃሴ ድምጽ በሌለው መሳሪያ ለማዳከምና ብሎም ለማምከን ህወሀት/ኢህአዴግ እየተከተለ ያለው ስልት ቡድኑ ምን ያህል “የሞራል የበታችነት” እንደተላበሰ የሚያሳይ ነው።
የሰማያዊ ፓርቲ የካቲት 12(መነን) አካባቢ አዲስ የተከራየውን ጽህፈት ቤት ለመረከብ ጥቅምት 1/2006 ዓ.ም በቦታው ይገኛል። ይሁንና ቀድመው በቦታው የተገኙ የህወሀት/ኢህአዴግ ሰዎች ቤቱን እኛ ቀደም ብለን የተከራየነው ስለሆነ የሚገባው ለኛ ነው በማለት ወዝግብ ያነሳሉ… እንግዲህ አንባብያን እራሱን መንግስት ብሎ የሚጠራው ሀይል የሰፈር “ጢቦ” ሆኖ መጣ ማለት ነው…
ይህ በዚህ እንዳለ ነው አሁን በቅርቡ የክፍለ ከተማዉ ፍትህ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ጌታሁን አማረ ፤ የወረዳዉ አስተዳደር ሃላፊዎች ፤- የወረዳ 3 ስራ አስፈፃሚ አቶ አማረ ቤካ ፤ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ አማረ አቡጤ ፤ መነን አካባቢ ፖሊሶች ፤ ፌደራል ፖሊሶች እና ሲቪል የለበሱ የደህንነት አካላት በጋራ በመሆን ኢንጅነር ይልቃልን ጨምሮ ሌሎች የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችችን ወደ ወደ መነን አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የወሰዷቸው።
የሰማያዊ ፓርቲ ሁኔታውን እንዲህ በማለት በፌስ-ቡክ ገጹ ላይ ጠቅሶታል፣
የኢህአዲግ አፈና በሰማያዊ አመራሮች እና አባላት ላይ ተጠናክሮ ቀጥሏል!!!
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ዉስጥ ለሰማያዊ ፓርቲ ጽህፈት ቤት ተከራይቶ የነበረዉን ቤት ከዛሬ ጥቅምት 1 2006 ጀምሮ ለመጠቀም በሄዱበት ጊዜ የክፍለ ከተማዉ ፍትህ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ጌታሁን አማረ ፤ የወረዳዉ አስተዳደር ሃላፊዎች ፤- የወረዳ 3 ስራ አስፈፃሚ አቶ አማረ ቤካ ፤ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ አማረ አቡጤ ፤ መነን አካባቢ ፖሊሶች ፤ ፌደራል ፖሊሶች እና ሲቪል የለበሱ የደህንነት አካላት በጋራ በመሆን በማይመለከታቸዉ ጉዳይ የፓርቲዉን ከፍተኛ አመራሮች
1. ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት(ሊቀ መንበር)
2. አቶ ስለሺ ፈይሳ (ምክትል ሊቀመንበር)
3. አቶ ይድነቃቸዉ ከበደ (የህግ ጉዳይ ሃላፊ)
4. አቶ እንዳሻዉ እምሻዉ (የጽህፈት ቤት ሃላፊ)
5. አቶ በቃሉ አዳነ (ምክር ቤት አባል )
6. አቶ ዮናስ ከድር (የምክር ቤት አባል)
7. አቶ ብርሃኑ ተክለ-ያሬድ (አባል)
ወደ መነን አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደዋል፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)
