Sunday, November 24, 2013

የተማራቂ ተማሪዎች “ጌት ቱጌዘር”

በጎንደር ዩንቨርስቲ ውጥረቱ እንደቀጠለ ነው .አንድ ተማሪ በታጣቂዎች ተገድሏል

ነገሩ የተፈፀመው የተማራቂ ተማሪዎች “ጌት
ተጌዘር” አዘጋጅተው ያንን ፖሮግራም ጨርሰው ከምሽቱ ሁለት ሰአት ተኩል አካባቢ ወይም ከዛ ረፈድ ብሎ በቁጥር ወደ
ሀምሳ የሚሆኑ ተማሪዋች ወደ ዩኒቨርስቲው በር አካባቢ ሲደርሱ ሞች እና በወቅቱ ከሟች ጋር አብራ የነበረች ተማሪ ቀድመው
ወደ ጥበቃ በመድረሳቸው ጥበቃው እንዲቆሙ በሚያዛቸው ወቅት ሟች የለም ከግቢው በር ውጭ ልታስቆመን መብቱ
የለህም እንደውም መታወቂያህን አሳየኝ በማለት በመባባል ነገሩ እንደተጀመረ እና በወቅቱ ተማሪዎቹ መጠጥ መቀማመሳቸውን
፣ ሟችም በስካር መንፈስ ሆኖ ግብግብ መፈጠሩን ጥበቀውም ከሟች ጋር የነበረችውን ምንዋን እንደመቱዋት
ባልታወቀ ሁኔታ እራሱዋን መሳትዋን እና መውደቁዋ ፣ በዚህ መሀል ተማሪዋቹ ለማገላገል በሚጠበጉበት ወቅት ጥይት
በመተኰሱ በድንጋጤ (ሶሰት ግዜ መተኰስሱን ልብበሉ) መበታተናችወን እና ጠዋት ሟች በተባለው ቦታ ደም ፈሶት
ሟቶ ስለመገኘቱ በጉንደር ዪኒቨርሰቲ የሳስተኛ አመት ማርኬቲንግ ተማሪ የሆነው እና በወቅቱ ቦታው ላይ የነበረው ወንድሜ
የነሀረኝን ሳልጨምር ሳልቀንስ!! በጣም የሚያመውና
የሚያቆስለው ሟች የተገደለው እርስ በርስ በጩቤ ተወጋግተው ነው በማለት አንድን ተጠርጣሪ ነፍሰ ገዳይ
ዘበኛ ለዛውም የህክምና እርዳታ ቢያገኝ ሊድን የሚችልን ልጅ እንደውሻ ጐትተው ወንዝ ዳር በመጣል የጭካኔ አገዳደል የገደለን ለማድበስበስ
መመኮራቸው ሳያንስ ይህን ለመቃወም ሰልፍ የወጡትን ተማሪዋች በፈደራል አስደብድበው የሰአት እላፊ አውጅው አስረዋቸዋል
ወጣት አንተነህ አስፋው ለገሰ  የማርኬቲንግ ማኔጅመንት የ፫ኛ ዓመት የድግሪ ተማሪ ነበር
source: freedom4ethiopian

አንድ ጊዜ ሆድ ብሶኝ ራሴን ለማጥፋት ሞክሬ ነበር....!!

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/9831

Friday, November 22, 2013

የዜጎቻችን እንባና ደም በግደለሽነት አንየው...!!!

(ራሄል ኤፍራም)
November 22.11.2013
ስቃያቸው እንደ ወንዝ ጅረት ለበዛው እና እንደ ቀልድ እየተደፈሩ የትም ለቀሩት ህቶቻችን እንዲሁም  ሂወታቸው በየቦታው እንድዋዛ ለረገፈው ወንድሞቻችን፣ ሀዘናችው ውስጣችንን እያቃጠለው፣እያንገበገብው  ፍትህ እስከምናገኝ መቀመጫ ያልሰጠን የወገኖቻችን ጉዳይ ፖለቲካ ሳይሆን የማንነት ጥያቄ መሆኑን ሁላችንም ልንገነዘብ ይገባል።
  ማንነታችን ተደፍሮ ፣ተንቀን ፣ተዋርደን ፖለቲካ ነው እያልን የምንሸሽ ካለን ስህተት ነው። ወገኖቻችን በሰው ሀገር መደፈር ፣መደብደብ ፣መሰቃየት ፣መዋረድ እና መገደል የሁላችንም ህልውና የሚነካ ሲሆን ይሄንን የስፖርት ቤተሰብ የወገኖቻችንን ስቃይና ጉዳት እንዲሁም በአሰቃቂ ሁኔታ መሰቃየታቸው እና መገደላቸው እንደወገን ሊሰማቸው የገባል።
ጉዳታቸው ጉዳታችን ፣ስቃያቸው ስቃያችን ፣ ውርደታቸው የሁላችንም ውርደት በመሆኑ ይህንን በመገንዘብ በስቃይና በመከራ ወስጥ ያለውን የወገኖቻችንን ድምፅ ማሰማት የኢትዮጵያዊነት ግዴታችን ነው።

በእርግጥ አንድ እውነት አለ የዚህ ሁሉ የወገኖቻች መሰቃየት ፣ የህቶቻችን መደፈር ፣የወንድሞቻችን መደብደብ በተለያየ መንገድ ሂወታቸውን ማጣታቸው ዋንኛው ምክንያት ስልጣንን ከህሊናቸው በማስበለጥ ለሃገራቸው ሳይሆን ለጥቅማቸው ሲሉ እንድ እባብ በሆዳቸው እየሄዱ መርዛቸውን እየረጩ እነሱ እየኖሩ ሌላሁን የስደት ቁራኛ በማድረግ ከመኖረም በላይ በህዝቦቻቸ ደም ላይ አንደዚ እየተሳለቁ ወገን ሲዋረድ ሀገር አቀርቅራ ስታለቅስ እነሱ ሽቅብ እየሳየቁ ወገኖቻቸን ችግር ከምንም ባልቆጠሩት ቱባ ያገራችን ባለስልጣናት ምክንያት መሆኑ ግልፅ ነው ።
ሆኖም ግን ጥያቄው በዜጎቻችን ላይ የሚደርስው ጥቃትንና አሰቃቂ ግድያ እንዲያቆም እና ፍታዊ እርምጃ እንዲወሰድ እንጂ ፍጹም ከፖለታካ ጋር የሚያያይዘው አንድም ነገር አለመኖሩ እንዲሁም ባገኘነው አጋጣሚ ለወገኖቻችን መጮህ እንዳለብን ድምፃቸው እንዲሰማ የግላችንን አስትዋፆና ጥረት በማድረግ ፍትህ የሚያገኙበትን መንገድ በመፍጠር ለወገኖቻቸን መቆማችንን በታላቁ እሩጫ ላይ ጥቁር ሪቫን በማሰር አዘናችንን እና የተሰማንን የወገናዊነት  እናሳይ ።

Thursday, November 21, 2013

የኢትዮጵያዊያን ሴቶች አሰቃቂ ሂወት በሀገር ውስጥ እና በስደት ኣውደርዕይ

(ምስራቅ መንበሩ)
በሃገራችን ኢትዮጵያ ወያኔ ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ  በኣስከፊ ሁኔታ አየተባባሰ የመጣው የዜጎች መብት ረገጣ ፣ በተለይም በዚ ስርአት ዋነኛ ተጎጂ የሆኑት ሴት አህቶቻችን በሀገር ውስጥ በመንግስት አካላት በሚደርስባቸው ጥቃት ለ አካል አና ስነልቦና ጉዳት ሰለባ የተዳረጉትን እና ገዢው ፓርቲ ባመቻቸው አና በከፍተኛ ሁኔታ አየተስፋፋ የመጣው ህገወጥ የሰው ዝውውር ዘመናዊ ባርነት ወደ አረብ ህገራት በዜጎች ላይ እያደረሰ ያለው ከፍተኛ ሰቃይ፣ አንግልት፣ አስር፣ ሞት አና የመሳሰሉት ችግሮች በየጊዜው የምንሰማው እና እልባት ያልተገኘለት መራር አውነት የሚያሳይ የፎቶ ኣውደርዕይ እና ገለጻ  በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የሴቶች ክፍል ኣዘጋጅነት በኦስሎ ከተማ ተደረገ ።
በዝግጅቱ ላይ ከቀረቡት ፎቶዎች መሀከል ሴቶች በሀገር ውስጥ የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊ ናቹ በሚል በመንግስት ኣካላትeth women2የሚደርስባቸው አሰቃቂ ድብደባ በአካላቸው ላይ የደረሰባቸው ጉዳትን የሚያሳ፥ ገዢው መንግስት በልማት ሰበብ ነዋሪዎችን ያለምንም ቅድመ ዝግጅት ከመኖሪያቸው በማፈናቀል ለጎዳና ህይወት መዳረጋቸው በየሜዳው መበተናቸው የሚያሳይ (እነዚህ ዜጎች መጠለያ በማጣት ለጎዳና ህይወት መዳረጋቸው ሴቶች ለተለያየ ጾታዊ ጥቃቶች፣ መደፈር፣ ላልተፈለገ እርግዝና፣ ለተለያዩ በሽታዎች እንዲጋለጡ ብሎም ሴተኛ ኣዳሪነት አንዲስፋፋ እና ለስደት ለህገወጥ ዝውውር ምክኒያት መሆኑ ይታወቃል)።
የዚህ ዝግጅት ዋነኛ ክፍል የነበረው በህገወጥ መንገድ በተለይም ወደ አረብ ሀገራት ለርካሽ የጉልበት ስራ ብዝብዛ  በሚሰደዱበት ሀገር የሚደርሰባቸው ሰቃይ አና አሰቃቂ ሞት የሚያሳዩ የተለላዩ ፎቶውች ናቸው ።
(በ100,000  የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ሴቶች አብዛኛዎቹ እድሜአቸው ከ18 በታች የሆኑ ህጻናት ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በህገወጥ መንገድ ለጉልበት ስራ ዘመናዊ ባርነት ወደ አረብ ሀገራት ይሰደዳሉ። በተሰደዱበት ሀገር ህጋዊ ጥበቃ ከኢትዮጵያ መንግሰትም ሆነ ከተሰደዱት ሀገር መንግስት ባለማግኘታቸው ከአቅም በላይ የሆነ የጉልበስራት በቀን ከ18  ሰዓት በላይ አንዲሰርሩ በመገደድ ፣  የሚደርስባቸው ከፍተኛ ስቃይ እና እንግለት፣ ድብደባ፣ በኣሰሪዎቻቸው በተደጋጋሚ መደፈር፣ በአካል አና ስነልቦና ጉዳት ብዙዎች ለአይምሮ ህመም በሽታ በመዳረጋቸው እና ክትትል የሚያደርግልቸው ባለማግኘታቸው በባእድ ሀገር በየጎዳናው ወድቀዋል።
ይህ ስቃይ ከኣቅማቸው በላይ የሆነባቸው ሰሚ ያጡ ዋይታዎች፣ ድብደባ መቛቛም ያቃታቸው፣ በመደፈር ባዛት የደከሙ የጨቅላ ገላዎች፣በደል የበዛባቸው ብዙ እህቶች፤ መርዝ በመጠጣት፣ ከፎቅ በመፈጥፈጥ፣ በመታነቅ ሂወታቸውን ያጠፋሉ።
ከመነሻው ለዚህ ችግር ምክኒያት የሆነው ገዢው መንግስት በዜጎቸ ላይ የሚደርሰውን እንግልት እና የግፍ ሞት ግዴለሽ በመሆኑ እና ባለመጠየቁ ዛሬ ኢትዮጵያዊነት ወንጀል እስኪመስል ድረስ በሳውዲ በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለውን ስቃይ አንገልት እንዲባባስ ምክኒያት በመሆን ብሎም ለህዝቡ ያለውን ከፍተኛ ንቀት አያሳየ ይገኛል።)
በዘግጅቱ ላይቁጥራቸው በዛ ያለ   ሰዎች የተገኙ ሲሆን ተጋባዥ አንገዶችም  ንግግር ኣድርገዋል።

Tuesday, November 19, 2013

"ለመላዉ ኢትዮጲያዊያን፡- ከሰማያዊ ፓርቲ የተላለፈ ጥሪ"

Posted on 

ለመላዉ ኢትዮጲያዊያን፡- ከሰማያዊ ፓርቲ የተላለፈ ጥሪ
በሳዑዲ ለሚሞቱና ለሚንገላቱ ወገኖቻችን ያለንን ተቆርቋሪነት
አሁንም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት፡፡ ሰሞኑን በአዲስ አበባዉ
ሰልፍ የተፈፀመዉን መንግስታዊ ሽብር ሁላችንም በሀዘን
አልፈነዋል፡፡ ነገር ግን ለብሔራዊ ቡድናችን ያደረግነዉ ጥሪ
በቸልተኝነት መታለፉ ፣ በሀይማኖት ተቋማትም የሚፈለገዉን
ያህል ጥሪዉን ባለመቀበላቸዉ የዘንን ቢሆንም ህዝቡን ከጎናችን
በማቆም የደረሰበትን ነገር ሁሉ በፅናት መቀበሉ አኩርቶናል፡፡
በቀጣይነትም የተለያዩ ስራዎችን ለመስራት ታስቧል፡፡ ከነዚህ
ዉስጥ በመጪዉ እሁድ ህዳር 15 ቀን በአዲስ አበባ በሚካሄደዉ
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጲያ ላይ የምንሳተፍ ሰዎች ጥቁር ሪቫኖችን
አድርገን እንድንሳተፍ፤ በአንድነት መንፈስም አጋጣሚዉን በሳዑዲ
ስለሚሞቱና ስለሚንገላቱ ሰዎች ድምፃችንን የምናሰማበት
ሀዘናችንን የምንገልፅበት እንዲሆን ሰማያዊ ፓርቲ በግፉአን
ወገኖቻችን ስም ጥሪ ያስተላልፋል፡፡
የሰማ ላልሰማ ያሰማ!!