ESAT Menalesh Meti interview with Mr. Obang Dec 5 2013
http://ethsat.com/video/esat-menalesh-meti-interview-with-mr-obang-dec-5-2013/
Saturday, December 7, 2013
ከሳውዲ ተመላሽ ዜጎች ንብረታቸው በጉምሩክ እንደተወሰደባቸው ተናገሩ
7 בDecember 2013
ህገወጥ ናችሁ ተብለው ከሳውዲ አረቢያ ወደ አገራቸው የተመለሱ ኢትዮጵያዊያን፤ ለበርካታ አመታት ለፍተን ያፈራነውን ንብረት ይዛችሁ መግባት አትችሉም ተብሎ ተነጥቀናል፡፡ የፍተሻ ሰራተኞች
ኤሌክትሮኒክስና ለቤተሰቦቹ ያመጣውን ልብሶች ቀረጥ ከፍለህ ነው የምትወስደው በመባሉ፣ ለሁለት ቀን በስደት ተመላሾች በተዘጋጀው ድንኳን ውስጥ ያለምንም ፍራሽና ልብስ ተኝቶ ንብረቱን ቢጠብቅም ማግኘት እንዳልቻለ ገልጿል፡፡ “ሳዑዲም እዚህም ሀገራችን ስንደርስ እየበደሉን ያሉት ሃበሾች ናቸው” ያለው መሃመድ፤ መንግስት በሚዲያ በተሟላና በተደላደለ መንገድ እንደሚቀበለን ቢገልፅም እዚህ የጠበቀን ግን ሌላ ነው ሲል ቅሬታውን ገልፆ “ሌላው ቢቀር እስካሁን ተመላሾቹን የሚያመላልሰው እንኳን የሳዑዲ እንጂ የኢትዮጵያ መንግስት አይደለም” ብሏል፡፡ ከሳኡዲ ካመጣችው ወርቅ ላይ ሃምሳ ግራሙን ብቻ እንደምትወስድ የተነገራት ተኪያ ሙሃመድን ያገኘናት በቁጭት መሬት ላይ እየተንከባለለች ነበር፡፡
ተኪያ እያለቀሰች እንደነገረችን፤ ለ14 ዓመት ሰርታ ከሶስት መቶ ሃምሳ ግራም በላይ ወርቅ እንዳጠራቀመች ገልፃ፤ በተፈጠረው ችግር ምክንያት ከሳውዲ እንድትወጣ ከመገደዷ በፊት ሙሉ ንብረቷን አስቀድማ ብትልክም እስካሁን እንዳልደረሰላት ትናገራለች፡፡ አሁንም፤ ከተመለሰች በኋላ የያዘቻቸውን ሻንጣዎች ለመውሰድ እንዳልቻለች የምትገልፀው ተኪያ፤ በፍተሻ ስም ሰራተኞቹ ሻንጣዋን በርብረው በማየት፣ ያመጣቻቸውን የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችና ሶስት ሞባይሎች መውሰዳቸው ሳይንስ፣ ሶስት መቶ ግራም የሚመዝን የወርቅ ንብረቷን እንዳታስገባ መከልከሏን በጩኸት ትናገራለች፡፡ ለምን ንብረቷን እንደከለከሏት ስትጠይቅም “እናንተ ነጋዴዎች ናችሁ፤ በስደተኞች ስም ያለቀረጥ ንብረት ለማስገባት ትፈልጋላችሁ” በማለት ሰራተኞቹ እንደመለሱላት ገልፃ፤ ጉዳዩን ለአለቆቻቸው ለማመልከት ብትፈልግም የሚያናግራት ሰው አለማግኘቷን ጠቁማለች፡፡ በዚሁ ስፍራ ያገኘናቸው በርካታ ተመላሾች፤ የንብረታቸው ጉዳይ እንዳሳሰባቸው ይናገራሉ። ንብረታቸውን ሳይዙ ወደቤተሰቦቻቸው ላለመቀላቀል በሚል የተሰበሰቡበት ካምፕ፣ ምንም ለማረፊያ የተመቻቸ አገልግሎት ባለመኖሩ መቸገራቸውንም ገልፀዋል፡፡ መንግስት የሚሰጣቸውን 900 ብር፣ በትራንስፖርትና በስልክ አገልግሎት እንደሚጨርሱ አክለው ተናግረዋል፡፡
በርካቶች በእቃዎቻቸው መታገድ በመበሳጨታቸው ጭቅጭቅና አላስፈላጊ ውዝግብ ውስጥ ለመግባት መገደዳቸውን ተመላሾቹ ይናገራሉ፡፡ “ስንመጣ የሚሰጠንን ሊሴ ፓሴን አይተው ማስተናገድ ሲገባቸው እነሱ ግን ንብረታችንን እየወሰዱብን ነው” በማለት የሚናገሩት ተመላሽ ዜጎቹ፤ “ምናልባትም ንብረት የላቸውም ብለው አስበውን ይሆናል፤ ነገር ግን በርካታ አመታት ስንቆይ መቼም ባዶ እጃችንን አንመጣም” በማለት በምሬት ይናገራሉ፡፡ “ዛሬ እቃችንን የከለከሉን ነገ ምን ተስፋ ይዘን ነው ተደራጅታችሁ ስራ ስሩ ለሚሉን?” የሚሉት እነዚህ ተመላሾች፤ “በመንግስት ላይ አመኔታ የጣልነው ሳውዲ ድረስ በተወካዮቹ አማካኝነት መጥቶ ባናገረን መሰረት ነበር፤ ነገር ግን የተገባልን ቃል ታጥፏል” ይላሉ፡፡ መንግስት ለጉዳዩ ትኩረት ባለመስጠቱ እና ለቤተሰብ መርዶ ባለመነገሩ፣ ለሚያውቋቸው ቤተሰቦች መርዶ ለመንገር ጭንቀት ላይ መሆናቸው ሌላ ችግራቸው እንደሆነ የተናገሩት ተመላሾች፤ አሁንም ቢሆን ሳውዲ ላይ ሃበሻዎችን በመኪና እየገጩ መግደል የሳውዲ ፖሊሶች የቀን ተቀን ስራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ታዲያ በዚህ አጣብቂኝ ውስጥ አምልጠው የሚመለሱ ዜጐችን ንብረት መቀማት ምን የሚሉት ተግባር እንደሆነ አልገባንም፤ በማለት አማርረዋል-ተመላሾቹ፡፡ ምናልባትም የፖለቲካ ማራመጃ ሊያደርጉን ነው በማለትም ስጋታቸውን አንፀባርቀዋል፡፡
ተመላሾቹ የተሟላ መጠለያ ተዘጋጅቶላችኋል በተባለበት ቦታ ሳይቀር፣ መተኛ ሥፍራ እንኳን እንዳልተዘጋጀ ሲረዱ ተስፋ መቁረጣቸውን እና ንብረታቸውን እንዳያስገቡ ሲከለከሉ፣ ተመልሰው በህገወጥ መንገድ ለመሰደድ ሙከራ መጀመራቸውን ይገልፃሉ፡፡ በጉዳዩ ላይ መልስ እንዲሰጡን የጠየቅናቸው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በበኩላቸው፤ “ተመላሾቹ ስለንብረት የሚያነሱትን ጥያቄን በተመለከተ፤ እኛ ተመላሾች በሙሉ ንብረት እንደሌላቸው ነው የምናውቀው“ በማለት ተናግረዋል፡፡ አምባሳደሩ አልፎ አልፎ ባዶ እግራቸውን ከሳዑዲ የተመለሱ እንዳሉ ጠቁመው፤ በሳኡዲ መንግስት ጓዛችሁን ይዛችሁ እንዳትወጡ ተከልክላችኋል በመባላቸው፣ መጀመሪያውኑም ንብረት ይዘው ባለመምጣታቸው ነው፤ ብለዋል፡፡ እነዚህ ዜጎች ከመደበኛ የአየር መንገዱ ተጓዦች እኩል እንደማይስተናገዱና ለብቻቸው ተጠብቀው እንደሚስተናገዱ ገልፀው፤ ምናልባት ከነዚህ ዜጎች ጋር ተቀላቅለው የሚመጡ ሌሎች ሰዎች ስለሚኖሩ እሱን ለማጣራት ንብረታቸው ይፈተሻል እንጂ ማንም የእነሱን ንብረት የሚወስድ እንደሌለ የተናገሩት አምባሳደሩ፤ እንኳን በሀገር ውስጥ የገባ ንብረት፣ ሳዑዲ ያለውንም የላባቸውን ውጤት ለማስመጣት እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡
የሟቾችን ቁጥር እና ለቤተሰቦቻቸው መርዶ አለመንገርን በተመለከተ አምባሳደሩ በሰጡት ምላሽ፣ አሁን ሙሉ በሙሉ ትኩረታችን በህይወት ያሉ፣ ንብረታቸውን ያጡ እና ጉዳት የደረሰባቸው ላይ ነው፤ ብለዋል፡፡ የሟቾቹን ቁጥር በተመለከተ ግን መንግስት ከገለፀው በኋላ፣ የተፈጠሩ ነገሮች መኖራቸውን አምነው፤ ነገር ግን ቁጥሩ ላይ ተመላሾች የሚሉትና አንዳንድ ሚዲያዎች የሚያወሩት ትክክል ሊሆን ቢችልም የተጣራ ነገር እስካላገኘን ድረስ የሞቱበትን ሁኔታ ለማወቅ ያስቸግራል፤ ብለዋል፡፡ የሳውዲ አየር መንገድ እንጂ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመመለሱ ሂደት ምንም አስተዋፅአ ለስደተኞቹ አላደረገም ለተባለው አምባሳደሩ መልስ ሲሰጡ፡- የሳውዲ አውሮፕላን የሚያመላልሰው እራሱ በማባረሩ ምክንያት ነው፤ ወጪውን የሚችለውም እራሱ ነው ብለዋል፡፡ addisadmas
Friday, December 6, 2013
በቦንጋ መምህራን አድማ ሊጠሩ ነው
ህዳር ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በከፋ ዞን በቦንጋ ከተማ የሚገኙ መምህራን ፣ መንግስት ለአባይ ግድብ በማለት ያለፈቃዳቸው የቆረጠባቸውን ደሞዝ በአስቸኳይ ካልመለሰ ሰኞ የስራ ማቆም አድማ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል።
መምህራኑ ዛሬ ወርሀዊ ደሞዛቸውን ለመቀበል ወደ ባንክ ሲሄዱ ለአባይ ግድብ በሚል ደሞዛቸው ተቆርጦ ተሰጥቷቸዋል። በሁኔታው የተበሳጩት መምህራን ወደ ትምህርት ጽህፈት ቤት ሲያመሩ መስተዳድሩ ያዘዘው በመሆኑ ምንም ማድረግ አንችልም የሚል መልስ ተሰጥቷቸዋል። መምህራኑም አፋጣኝ መልስ የማይሰጠን ከሆነ፣ ከሰኞ ጀምሮ የስራ ማቆም አድማ እናደርጋለን በማለት ለመስተዳድሩ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።
የመስተዳድሩ ባለስልጣናት በበኩላቸው፣ ውሳኔውን የሚቃወም መምህር ስራውን በራሱ ፈቃድ እንደለቀቀ ይቆጠራል በማለት የማስፈራሪያ ደብዳቤ ልከዋል።
ከዚህ ቀደም በጋሞጎፋ ዞን የሚገኙ መምህራን ተመሳሳይ ተቃውሞ በማሰማታቸው የተቆረጠባቸው ደሞዝ በፍጥነት እንዲመለስላቸው መደረጉን መዘገባችን ይታወሳል።
አሁን የውሸት ወይም ድራማዊ ለቅሶ ሳይሆን፤ የእውነት ሃዘን የምናይበት ጊዜ ይሆናል።
ኔልሰን ማንዴላ እና ኢትዮጵያ!!
December 6, 2013
የነጻነት ታጋዩ ኔልሰን ማንዴላ በ95 አመታቸው ከዚህ አለም ሲለዩ፤ የተለያዩ አገሮች እንደየራሳቸው ግንኙነት የራሳቸውን ታሪክ ሲያወሩ ነበር። የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ሃዘናቸውን ሲገልጹ ከማንዴላ ጋር የነበራቸውን ግንኙነት በመግለጽ ነበር። እኔ በምኖርበት አትላንታ ከተማ ዜናው ሲቀርብ፤ ኔልሰን ማንዴላ አትላንታ በመጡበት ወቅት፣ ከነአንድርው ያንግ ጋር ሆነው የማርቲን ሉተር ኪንግ ማዕከልን ስለመጎብኘታቸው ነበር – ዋናው ዜና። ሁሉም አገር ስለማንዴላ የየራሱ ትዝታ አለው። ኢትዮጵያውያንም ስለኔልሰን ማንዴላ የራሳችን ታሪክ እና ትዝታ አለን። እናም ማንዴላ የዛሬ 51 አመት ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ስለነበረው ጉዳይ በማውጋት ታሪካችንን እንጀምራለን።
በዳዊት ከበደ ወየሳ
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር የነበሩት አቶ ከተማ ይፍሩ በ1962 ዓ.ም አራተኛው የፓን አፍሪካ ስብሰባ በኢትዮጵያ እንዲደረግ ጃንሆይን ፍቃድ ጠየቁ። ጃንሆይ በጉዳዩ ተስማሙና በፌብሩዋሪ 1962 ዓ.ም የአፍሪካ ታዋቂ የነፃነት ታጋዮች ወደ ኢትዮጵያ መጡ። ከእነዚህም መሃከል ሚስተር ኦሊቨር ታምቦ፣ ሚስተር ሮበርት ሙጋቤ፣ ሚስተር ኬኔት ካውንዳ እና ሚስተር ኔልሰን ማንዴላ ይገኙበታል። (በኋላ ላይ እነዚህ ወጣት ታጋዮች የየአገራቸው ፕሬዘዳንት ሆነዋል) ይህ ጉዞ በተለይ ለኔልሰን ማንዴላ በህይወታቸው ውስጥ ልዩ ስፍራ የሚሰጡት ነው።
የኔልሰን ማንዴላን ወደ ኢትዮጵያ ጉዞ ያሰናዱት የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አቶ ከተማ ይፍሩ ነበሩ። በወቅቱ በአፓርታይድ የዘረኝነት ቀንበር ስር የነበረችው ደቡብ አፍሪካ ጥቁር ዜጎችዋ ያለፈቃድ አገሪቱን ለቀው እንዳይወጡ የሚያዝ ህግ አውጥታ ነበር። ይህ ህግ ለኔልሰን ማንዴላ ጉዞ አስቸጋሪ ሁኔታን ፈጠረ። በመሆኑም አቶ ከተማ ይፍሩ ለኔልሰን ማንዴላ የኢትዮጵያ ዲፕሎማት መሆናቸውን የሚገልፅ ፓስ ፖርት ካዘጋጁላቸው በኋላ ነበር፤ በፌብሩዋሪ 1962 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ የመጡት። ማንዴላ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት፤ ወቅት ወታደራዊ ስልጠና ለማድረግ ነበር ወደ ኢትዮጵያ የመጡት።
በወቅቱ ለኔልሰን ማንዴላ የተዘጋጀው ፓስፖርት ላይ ማንዴላ እንደጋዜጠኛ ሆነው፤ ስማቸው ዴቪድ ሞሳማይ ተብሎ ነበር የተጻፈው። ስሙን የተጠቀሙት ደቡብ አፍሪካ እያሉ አብሯቸው ከነበረው ጓደኛቸው ነው።
ወደ ኢትዮጵያ ስለነበረው ጉዞ እናውጋ። ኔልሰን ማንዴላ “Long Walk To Freedom” በሚለው መፅሃፋቸው የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚንስትር አየር መንገድ ድረስ መጥተው እንዴት እንደተቀበሏቸው ገልፀዋል። እንዲህ በማለት ይቀጥላሉ ኔልሰን ማንዴላ…
ለንደን የነበሩትን ጓደኞቼን በወዳጅነት ስሜት ተሰናብቼ ወደ አዲስ አበባ- ኢትዮጵያ ተጓዝኩ። እስካሁን ባለው ህይወቴ ለማላውቀው ወታደራዊ ስልጠና ነው የምሄደው። የስድስት ወር ወታደራዊ ስልጠና ለማድረግ በያዝኩት ፕሮግራም መሰረት ነው ወደ ኢትዮጵያ የምጓዘው። አዲስ አበባ ስደርስ መጀመሪያ ተቀብለው ያነጋገሩኝ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ከተማ ይፍሩ ነበሩ። ሞቅ ያለ አቀባበል አደረጉልኝ። ከዚያም “ኮልፌ” ወደሚባለው አንድ የከተማው ክፍል ወሰዱኝ።
የኢትዮጵያ አድማ በታኝ ፖሊስ የሚሰለጥነው እዚህ ኮልፌ የሚባለው ሰፈር ነው። የባታሊዮኑ ዋና መስሪያ ቤት የሚገኘው ከዚህ ነው። አኔ ወታደራዊ የሳይንስ ጥበብ እንድማር የተመደብኩበትም ስፍራ እዚህ ነው። እስካሁን ባለኝ ልምድ ጀማሪ ቦክሰኛ ከመሆን ውጭ ስለጦር ሜዳ ፍልሚያ የረባ እውቀትም የለኝም። አሰልጣኜ መቶ አለቃ ወንድሙ በፍቃዱ ይባላል። በጣልያን ወረራ ግዜ የደፈጣ ተዋጊ የነበሩ ልምድ ያላቸው ወታደር ናቸው።
በአዲስ አበባ መውሰድ የጀመርነው የስልጠና ፕሮግራም ጥብቅ ነው። ከጠዋቱ 2፡00 ሰአት እስከ 7፡00 ሰዓት ድረስ ስልጠና ላይ እንቆያለን። ከዚያ የምሳ ሰዓት ነው። ከዚያ ከሰዓት ከ8፡00 እስከ 10፡00 ስልጠናው ይቀጥላል። ከ10፡00 ሰዓት በሁዋላ እስከምሽቱ ድረስ ስለ ወታደራዊ ሳይንስ የንድፈ ሃሳብ ገለጻ ይደረግልናል። ይህንን ስልጠና የሚያደርጉልን ኮሎኔል፤ የፖሊስ ረዳት ኮሚሽነር ናቸው። በንጉሱ ላይ የተደረገው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ እንዲከሽፍ ትልቅ አስተዋፅኦ አድርገዋል።
በስልጠናው የአውቶማቲክ መሳሪዎች እና የሽጉጥ አጠቃቀምን ተማርኩ።
መጀመሪያ ኮልፌ ከዚያም ከኮልፌ 50 ማይልስ የምትርቅ ቦታ ከወታደሮቹና ከንጉሱ የክብር ዘበኛ አባላት ጋር ሄጄ የኢላማ ተኩስ ተለማመድኩ። የሞርታር ተኩስና እንዲሁም የቦንንብ አሰራሮችን፤ ፈንጂዎችን የማክሸፍ ዘዴንም ተማርኩ። አሁን እያደር ወታደር እየሆንኩ ስሄድ ይታወቀኛል። እንደ ወታደር ማሰብ ለመድኩኝ። ወታደር መሆን እንደ ፖለቲከኛ ከማሰብ የሚለይበት የራሱ መንገድ አለው።
እዚህ ቦታ ላይ በጣም የወደድኩት ጠዋት ተነስተን የምናደርገው የማለዳ ጉዞ ነው። ጠመንጃ፣ ጥይትና ጥቂት ውሃ እንይዛለን። እናም በተሰጠህ ጊዜ ውስጥ ያንን ርቀት ተጉዘህ የታዘዝከውን ፈፅመህ መድረስ አለብህ። በዚህ ወታደራዊ ጉዞ የአገሪቱን ገጠራዊ ክፍሎች ለማየት እድሉን አገኘሁ። የመሬቱ አቀማመጥ በጣም ቆንጆ ነው። ጥቅጥቅ ያለ ደንና ከፍተኛ ቦታዎችን አየሁ። ገጠሩ በጣም ሁዋላ ቀር ነው። ሰዎች በእንጨት መቆፈሪያ ነው የሚያርሱት። ምግባቸውም ትንሽና በቀላሉ የሚዘጋጅ ነው። እቤት የሚጠመቅ ቢራ ወይም ጠላ አላቸው፤ ኑሯቸው እዚህ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ካሉ መከረኞች ጋር ተመሳሳይ ነው። መቼም ደሃ ሰዎች የትም ቢኖሩ ኑሯቸው አንድ አይነት ነው፤ ብዙም አይለያዩም።
በስልጠናዬ ወቅት ኮሎኔል ታደሰ ብዙ ጉዳዮችን እያነሱ ያስተዋውቁኛል። ስለ ደፈጣ ውጊያ፤ ሃይል እንዴት ማዋቀር እንደሚቻል አንድን ጦር እንዴት ማዘዝና መምራት እንደሚቻል፤ በጦር ውስጥ ወታደራዊ ስነ ስርአትን ለማስፈን ምን ማድረግ እንደሚገባ ያስተምሩኛል።
አንድ ምሽት እራት ላይ ለደቡብ አፍሪካ ትግል ምን አይነት ጦር እንደሚያስፈልገንና የሰራዊቱ ባህሪ ምን መሆን እንዳለበት አጫወቱኝ። “ይኸውልህ ማንዴላ… አንተ የምትመሰርተው ነፃ አውጪ ሃይል እንጂ መደበኛ ጦር አይደለም። የናንተን ጦር ሰዎች የምትቀርፅበት ስልት ከመደበኛው ጦር አሰራር የተለየ ነው። አንተ መመስረት ያለብህ ነፃ አውጪ ጦር ነው። በትግል ላይ ስትገባም የምትመራቸው ተከታዮችህ ፍፁም እርግጠኝነት እንዲሰማቸውና ሁሉም ሃሳብህን እንዲከታተሉ ማድረግ መቻል አለብህ። ይህ በመደበኛው ጦርም ውስጥ ያለ ነው። ከስራ በሁዋላ በእረፍት ሰዓትህ ማድረግ የሚገባህ ግን ከመደበኛው ደንብ ውጪ ይለያል። አንተና የመጨረሻው ተራ ተዋጊ እኩል መሆናችሁን የሚያሳይ አቀራረብ ሊኖርህ ይገባል። የሚበሉትን ትበላለህ፤ የሚጠጡትን ትጠጣለህ። ምግብህን ወደ ግል ክፍልህ መውሰድ የለብህም። እራስህን ገለል አታድርግ፤ እዚያው አብረሃቸው ሁን።” አሉኝ። የኮሎኔልን ሃሳብ ተረድቻለሁ። ሃሳቦቹ የሚደነቁና መልዕክት ያዘሉ ናቸው። እንደነዚህ ያሉ ቁም ነገሮችን በየፕሮግራሙ መሃል ይነግሩኝ ነበር።
ወደ አዲስ አበባ የመጣሁት ለስድስት ወር ስልጠና ነው። ስምንት ሳምንት እንደሆነኝ ግን ከድርጅቴ ‘የአፍሪካ ኮንግረስ’ አንድ የቴሌ ግራም መልዕክት ደረሰኝ። ባስቸኳይ ወደ ደቡብ አፍሪካ እንድመጣ የሚጠይቅ ነው። የዚያን ጊዜ የነፃነት ትግሉ መፋፋም ጀምሯል። እናም የግንባሩ አዘዥ እዚያው ቦታው ላይ መገኘት ስላለበት ነው የጠሩኝ። ኮሎኔል ታደሰ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ካርቱም የምሄድበትን መንገድ ቶሎ አዘጋጁልኝ። ስንሰነባበት አንድ ሽጉጥና ሁለት መቶ ጥይት ስጦታ አበረከቱልኝ። ስለ ስልጠናውም ሆነ ሰጡኝ ትምህርት ትልቅ አክብሮት እንዳለኝ ገለጽኩና ጉዞዬን ጀመርኩ። መሳሪያ ተሸክሞ ረዥም መንገድ መጓዝን ብለማመድም የተሰጠኝ መሳሪያ ከባድ ነው። ሁለት መቶ ጥይት ጀርባ ላይ መታጠቅ ህጻን ልጅ በጀርባ እንደማዘል ነው የሆነብኝ።
ኦገስት 5 ቀን፣ 1962 ላይ… ኔልሰን ማንዴላ ወደ ደቡብ አፍሪካ ኤርፖርት ሲደርሱ ጥብቅ ፍተሻ ተደረገባቸው። ከጦር መሳሪያው በተጨማሪ በኪሳቸውም ውስጥ የኢትዮጵያ ዲፕሎማት መሆናቸውን የሚገልጽና የአቶ ከተማ ይፍሩ ፊርማ ያለበት ፓስፖርት ተገኘባቸው። በኢትዮጵያ መቆየታቸውን የሚገልጽ የጃንሆይ ማስታወሻና የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ከተማ ይፍሩ አነስተኛ ፎቶ ነበር። እነዚህን ጨምሮ 173 መረጃዎች በሪቮንያ የአፓርታይድ ችሎት ላይ ቀረበባቸው – 1963።
እነዚህና ሌሎች መረጃዎች በሪቮንያ ፍርድ ቤት ቀርቦ በኔልሰን ማንዴላ ላይ የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸው፤ በዚሁ አመት በ1963 ሮቢን ደሴት ላይ ወደሚገኘው ወህኒ ተወረወሩ።
ከብዙ ውጣ ውረድና የ27 አመታት ትግል በኋላ ማንዴላ ከእስር ተፈቱ። እናም መጀመሪያ ከጎበኟቸው አገሮች አንዷ ኢትዮጵያ ነበረች። በፓስፖርታቸው ላይ ያሉት የመጀመሪያ ቪዛዎችም የሚያሳዩት ይህንኑ ነው። መጀመሪያ ከጎበኟቸው አገሮች መካከል ኢትዮጵያ አንዷ ሆነች። በኋላ ላይ በመጽሃፋቸው ላይ ሲጽፉ፤ “ኢትዮጵያ በኔ ውስጥ ልዩ ስፍራ አላት። በፈረንሳይ፣ በእንግሊዝ እና በአሜሪካ ያደረኳቸው ጉብኝቶች ቢደመሩ እንኳን፤ በኢትዮጵያ ከነበረኝ ቆይታ አይበልጡም።” በማለት ለኢትዮጵያ ያላቸውን ልዩ ስሜት ገልጸዋል። (በነገርዎ ላይ የኔልሰን ማንዴላን የህይወት ታሪክ የሚገልጽ፤ በኢትዮጵያ ያሳለፉትንም ወታደራዊ ስልጠና ህይወት የሚያሳይ ትልቅ ፊልም ተሰርቷል)
ኔልሰን ማንዴላ ከ እስር ቤት ከወጡ በኋላ ዳግም ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ። በወቅቱ እነ ጄነራል ታደሰ ብሩ በህይወት አልነበሩም። ጊዜውም ተለውጧል። ቆየት ብሎ ኔልሰን ማንዴላ በህይወት ካገኟቸው ሰዎች መካከል አቶ ከተማ ይፍሩ አንዱ ነበሩ።
ከሰላሳ አመት በፊት አብረው የተነሱት ፎቶ ማንዴላን ለእስር እንዳላበቃቸው፤ አሁን ግን በነፃነት እንደገና ተገናኝተው የመታሰቢያ ፎቶ ለመነሳት በቁ። (አቶ ከተማ ይፍሩም ከጥቂት አመታት በፊት አልፈዋል)
ከመሰናበታችን በፊት… በአንድ ነገር እንሰነባበት። የኔልሰን ማንዴላ የልደት ቀን ሲመጣ፤ ተማሪዎችን ጨምሮ ህዝቡ በሙሉ ልደታቸውን ያከብራል። ለኔልሰን ማንዴላ ትልቁም ትንሹም “ማዲባ ሃላላ፣ እንወድሃለን አባባ” እያሉ ይዘምሩላቸዋል።
Madiba, Halala
Happy birthday to you!
Happy birthday to you!
Happy birthday dear Tata!
We love you Tata
Happy birthday to you!
Happy birthday to you!
Happy birthday dear Tata!
We love you Tata
We love you Tata
Nelson Mandela. Ha hona
Ya tshwanang le wena (there is no like you)
Yeep yeep!
Hooray!
Nelson Mandela. Ha hona
Ya tshwanang le wena (there is no like you)
Yeep yeep!
Hooray!
እኛም በዚሁ ስንሰናበት፤ አንድ ነገር ለማለት ወደድን። አሁን የውሸት ወይም ድራማዊ ለቅሶ ሳይሆን፤ የእውነት ሃዘን የምናይበት ጊዜ ይሆናል።
ነፍስ ይማርልን!
Wednesday, December 4, 2013
ወያኔ የአፄ ምኒልክ 100ኛ አመት መታሰብያ በዓል እንዳይከበር ፍቃድ ከለከ
December 4, 2013
የሰማያዊ ፓርቲ የአፄ ምኒልክ 100ኛ አመትን በተለያዩ ዝግጅቶች አስቦ ለመዋል በጃንሜዳ የመሰብሰብ ፍቃድ እንዲሰጠው ጥያቄ አቅርቦ ነበር፣ ይሁንና መንግስት ጥያቄውን ተልካሻ ምክንያቶችን በመደርደር ውድቅ ማድረጉን የሚገልጽ ደብዳቤ ለሰማያዊ ፓርቲ ልኳል።
የፊታችን ታህሳስ 3 የእምዬ ምኒልክን 100ኛ እረፍት በሰማያዊ ፓርቲ አዘጋጅነት እንደሚዘክር የታወቀ ነዉ፡፡ በፕሮግራሙ ላይም በርካታከሀገር ዉስጥና ከዉጪ ሀገር ምሁራን ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች ይገኛሉ ተብሉ ይጠበቃል፡፡ የፕሮግራሙ አዘጋጅ ሰማያዊ ፓርቲ ለዝግጅቱ በሚያስፈልጉ ጉዳዩች ላይ ስራ እየሰራ ይገኛል! በስብሰባና ሰላማዊ ሰልፍ አዋጅ መሰረትም ስብሰባ እንደሚያደርግ ለስብሰባና ሰልፍ ማሳወቂያ ክፍል ደብዳቤ በትናንትናዉ እለት ያስገባ ሲሆን ዘሬ በደብዳቤ የተመለሰዉ መልስ እጅጉን አስቂኝና አጠያያቂ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡
በደብዳቤዉ ላይ ለምታደርጉት ስብሰባ እዉቅና ልነሳጥችሁ አንችልም ምክንያቱም የፖሊስ ጥባቃ መመደብ አንችልም የሚል ነዉ፡፡ የሚገርመዉ ደግሞ የፅፈት ቤቱ ሀላፊ ተብዬዉ አቶ አሰግድ በንቀት ደግሞ ማናችሁና ምኒልክ ምናምን የምትሉት ደግሞ ምኒልክ ማነዉ በሚል በእብሪት የመለሰዉ መልስ ነበር፡፡
እንኳን ድንኳን ጥሎ ለመሰብሰብ ይቅርና ጎዳና ሙሉ ህዝብ በመላበት የሩጫ የሰልፍ መሰል የገዢዉ ፓርቲ መልካም ፈቃድ ያገኙ ፕሮግራሞች ከህዝቡ እኩል ፌደራል ፖሊስ ለጥበቃ እንደሚታዘዝላቸዉ እየታወቀ ፤ በሌላ መልኩም በድፍረት እንወጣለን ብለን በተለያየ ምክንያት በተጠሩ ሰልፎች ላይ ለድብደባ የሚላከው ቁጥር ስፍር የሌለዉ የፀጥታ ሀይል አሁን ምን ቢውጠው ነዉ የጥበቃ የሚሆን የሰዉ ሀይል ልናስተባብር አንችልም ስለዚህ ዝግጅታችሁን እዉቅና አንሰጠዉም መባሉ??? ይህ ከእብሪት በላይ ምን ሊሆን ይችላል!!!?
ያም ሆነ ይህ ዝግጅቱ በታቀደለት ምልኩ እንደሚፈፀም በተለመደ ቁርጠኝነት ላይ ነን! ሲፈልጉ ለጥበቃ የከለከሉትን ሀይል ለድብደባ ይላኩት!!! እኛ የምንዘክራቸዉ ፍርሃት ካልፈጠረባቸዉ ሞተዉም መንፈሳቸዉ ካልተለየን እምቢ ባይ አባቶቻችን ተወልደናል፡፡
ድል ለኢትየጵያ ህዝብ!!!
ድል ለኢትየጵያ ህዝብ!!!
Monday, December 2, 2013
የወያኔ አገዛዝ በመልዕክተኞቹ በኩል ላቀረበው የ“እንደራደር” ጥያቄ ከግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የተሰጠ ምላሽ
ወያኔ ኢትዮጵያ ዉስጥ የገነባዉ ሥርዓት በከፍተኛ ችግሮች የተወጠረ ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የመሪው ሞት በወያኔ መሀል ያስከተለው ቀውስ፤ የሕዝብ ሁለገብ ትግል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎለበት መሄድ የፈጠረበት ስጋት እና ምርጫ በደረሰ ቁጥር የሚደርስበት ጭንቀት መጨመር ተደማምረው ውጥረቱን ወደ ከፍተኛ ደረጃ እያደረሱት መሆኑን የሚያሳዩ በቂ ምልክቶች አሉ። የእስካሁኑ ተሞክሮዓችን እንደሚያሳየው ወያኔ ውጥረት ሲበዛበትና መዉጪያና መግቢያዉ ሲጠፋዉ ፣ ተቃዋሚ ድርጅቶችን “እንወያይ፣ እንደራደር” በማለት ለውጥረት ማስተንፈሻ ጊዜ የሚገዛ መሆኑን ነው። ሰሞኑን በወያኔ አገዛዝ መልዕክተኞች በኩል የደረሰንን “የእንደራደር” ጥያቄ ንቅናቄያችን በዋናነት ያየው ወያኔ እንደለመደው ድርድርን ለውጥረት ማስተንፈሻነት ለመጠቀም እየሞከረ መሆኑን ነው።
የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚመኘው ዲሞክራሲያዊ ለውጥ በሰላማዊ መንገድ በሚደረግ ትግልና በጠረጴዛ ዙሪያ በሚደረጉ ዉይይቶች ቢመጣ የግንቦት 7 ምርጫ መሆኑን ንቅናቄያችን በተደጋጋሚ ግልጽ አድርጓል። ግንቦት 7ን ሁለገብ ትግል ውስጥ እንዲገባ ያስገደደው የወያኔ እምቢተኝነትና እብሪት ብቻ ነው።
የግንቦት 7 ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የሰሞኑ የወያኔ የእንደራደር መልዕክት እንደደረሰው በጉዳዩ ዙሪያ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ይህ ጉዳይ የኢትዮጵያን ሕዝብ ባጠቃላይ እንጂ ግንቦት 7ን ብቻ የሚመለከት ጉዳይ እንዳልሆነ ከድምዳሜ ላይ ደርሷል። ይህ ጉዳይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ከሚያደርገው ትግልና እየከፈለ ካለው መስዕዋትነት ጋር በቀጥታ ግንኙነት አለው። በመሆኑም፤ ለቀረበልን ጥያቄ ግልጽ መልስና፤ ድርድር ስለሚባለው ጉዳይም ያለንን አቋም ጉዳዩ በቀጥታ ለሚመለከተው የኢትዮጵያ ሕዝብና የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ሁሉ ለማቅረብ የሚያስችል ተጨማሪ አጋጣሚ አድርገን ወስደነዋል። በዚህም መሠረት ለቀረበልን ጥያቄ የሰጠነዉን መልስና አቋማችንን በድርጅታችን ድረ ገጽ ላይና በሌሎች መገናኛ ብዙሀን በኩል በይፋ ለመግለጽ ወስነናል።
በድርድር ስለሚመጣ ለውጥ ያለን የመርህ አመለካከት:
ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ግልጽ እንዳደረግነው ድርጅታችን ከምሥረታው ጀምሮ የትግል ስልቱን ሲወስን እምነቱ አድርጎ የተነሳው ዴሞክራሲያዊ ለውጥ በሀገራችን በሰላማዊ መንገድና በድርድር ቢመጣ በእጅጉ የሚፈልገውና የሚመኘው መሆኑን ነው:: ድርጅታችንን ወደ ሁለንተናዊ ትግል የገፋው በመግቢያው ላይ እንደገለጽነው የወያኔ እብሪት ብቻ ነው:: የቀረበልን ምርጫ በባርነትና በውርደት መኖር ወይም ለነፃነት እየታገልን መሞት ቢሆን ኖሮ ንቅናቄያችን የሚመረጠው ምን ግዜም ለነፃነትና ለአገር አንድነት ታግሎ በክብር መሞት መሆኑን በተደጋጋሚ ለሕዝብ ግልጽ አድርገናል። ይህ የማይናወጥ አቋማችን ደግሞ ለይምሰል የተቀመጠ አቋም ሳይሆን ከልባችን የምናምንበትና ኢትዮጵያን ጨምሮ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ አባላቶቻችንን ያሰባሰብንበት አቋም ነው። ዛሬ በትግሉ ግንባር የምንንቀሳቀሰውና ወደ ግባችን የሚወስደንን ተጨባጭ እርምጃዎች እየወሰድን ያለነውም በዚሁ አቋማችን ዙሪያ ነዉ።
ይህ አቋማችንና እምነታችን በአንድ ላይ ጎን ለጎን የሚሄዱ ሁለት መርሆችን አጣምሮ የያዘ ነዉ። አንደኛው፣ ሂደትን በሚመለከት ሁሌም ለድርድር ክፍት መሆኑን የሚያመለክት ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ፣ ይህ የድርድር ሂደት እንዲያው ለለበጣ የሚደረግ ሳይሆን ወደሚፈለገው ነጻነት በአነስተኛ መስዕዋትነት ሊያደርስ ይችል ከሆነ በሩን ላለመዝጋት እንጂ፣ በምንም አይነት ዋና ውጤቱን፤ ማለትም ኢትዮጵያን እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሀገር ማድረግን፤ የሚቀይር ወይንም ከዚያ ያነሰ ውጤትን ለመቀበል መፍቀድን ፈጽሞ የማያመለክት መሆኑን ነው::
በእኛ በኩል ድርድሩን አስፈላጊና ጠቃሚ የሚያደርጉት መነሻ የፖለቲካ እሳቤዎችም ከእነኝሁ ሁለት መንታ ገጽታዎች የሚመነጩ ናቸው:: በድርድር ለሚገኝ ፍትሀዊና እውነተኛ ውጤት ክፍት መሆናችንን ሁሌም እናሳያለን፤ ነገር ግን ይህን የምናደርገው የሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነት የተረጋገጠባትን ኢትዮጵያን እውን ማድረግ የሚጠይቀውን ማንኛውንም መስዋዕትነት መከፈል አለበት የሚለውን መሠረታዊ የአካሄድ መርህ በመመርኮዝ እንጂ መርሀችንን ለድርድር ለማቅረብ እንዳልሆነ በግልጽ መታወቅ ይኖርበታል::
ስለዚህም:
ሀ) የድርድሩ ውጤት የኢትዮጵያን ሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነት ያረጋገጠ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን በአስቸኳይ እውን ማድረግ መሆን ይኖርበታል:: ይህ ዋናው ግብ ሆኖ ከዚህ በመለስ የሚኖሩ በሂደት የሚገኙ አነስተኛ ግቦች ሊኖሩ ይችላሉ (ለምሳሌ የፖለቲካ እስረኞች ማስፈታት…ወዘተ):: ሆኖም በምንም አይነት ለእነኝህ መለስተኛ ግቦች ተብሎ ዋናውን ግብ የሚያሳጣ ወይንም ጊዜውን ያላግባብ የሚያስረዝም ድርድር፣ ድርድር ነው ብሎ ድርጅታችን አይቀበልም። ስለዚህም ዋናው የድርጅታችን ዓላማና ግብ የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነት ፣ በፍጹም ለድርድር የሚቀርብ ጉዳይ አይደለም:: በሥልጣን ላይ ባለው ኃይል በኩል ወደዚህ ግብ ለመድረስ ቁርጠኝነቱ በሌለበት ሁኔታ በሚደረግ ማንኛውም አይነት ድርድር ውስጥ ግንቦት 7 አይሳተፍም::
ለ) በግንቦት 7 እምነት ማንኛውም ድርድር ወያኔ ከግንቦት 7 ጋር በተናጠል የሚያደረገው ሳይሆን ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ሁሉንም የፖለቲካ ኃይሎች ያካተተ መሆን ይኖርበታል:: ድርጅቶችን በተናጠል እየለያዩ “እንደራደር” ማለት በራሱ ጊዜያዊ የፖለቲካ ጥቅም ስሌትን የያዘ እሳቤ እንጂ፣ በዘላቂነት አገሪቱን እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ አገር ለማድረግ መፈለግን አያመለክትም:: ለአንድ ድርጅት ለብቻው የሚመጣ ወይም የሚጠቅም ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የለም:: ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የመፍጠር ፍላጎት ያለው ድርድር በአገሪቱ ያሉትን የተለያዩ የፖለቲካም ሆነ የሲቪክ ኃይሎችን ያካተተና ያመኑበት መሆን ይኖርበታል:: የሚደረገው ድርድርም ማን በስልጣን ላይ ይውጣ ወይንም የፖለቲካ ስልጣንን ባሉት ኃይሎች መሀከል እንዴት እናከፋፍለው የሚል የስልጣን ቅርምት ድርድር ሳይሆን፤ ሕጋዊና የሕዝቡን የሥልጣን ሉዓላዊነት ባረጋገጠ ሁኔታ የፖለቲካ ስልጣን እንዴት እንደሚያዝ ፍትሀዊ የሆነ ሂደትን ለማስጀመር የሚደረግ ድርድር መሆን አለበት::
ሐ) ቀደም ብለን እንደጠቀስነው ይህ ጉዳይ የሚመለከተው አንድን ድርጅት ወይንም የፖለቲካ ድርጅቶችን ብቻ ሳይሆን መላውን የኢትዮጵያን ሕዝብ ነው:: ይህ እስከሆነ ድረስ እንዲህ አይነት ድርድር ከሕዝቡ በተደበቀ ሁኔታ በሚስጥር የሚካሄድበት ምንም ምክንያት የለም::
2) ከዚህ በፊት ከወያኔ ጋር ከተደረጉ ድርድሮች ያገኘናቸው ተመክሮዎችና ከዚህ በመነሳት ወደፊት በሚደረጉ ምንም አይነት ድርድሮች እንዳይደገሙ ለመጠበቂያ የሚሆኑ ከአሁኑ መወሰድ ያለባቸው እርምጃዎች
ከማንኛውም ወገን ጋር የሚደረግ ድርድር የተደራዳሪዎቹ ምንነት፤ ውስጣዊ ባህርያቸውን፤ ከተለምዶ ተግባራቸው ያላቸውን ተአማኒነትና ወደዚህኛው ድርድር ያመጣቸውን ምክንያቶች በበቂ ከመገንዘብ ጋር ተያይዞ የሚታይ ጉዳይ ነው:: ቃሉን አክባሪና ተዓማኒ ከሆነ ሰው ጋር የሚደረግ ድርድርና ያለፈው ታሪኩ ምንም አይነት የተዓማኒነት ባህርይ ከማያሳይ ቡድን ጋር የሚደረግ ድርድርም ሆነ ለድርድሩ የሚደረግ ዝግጅት ለየቅል ናቸው:: ይህ ማለት ግን ተዓማኒነት ካለው ኃይል ጋር ብቻ ነው ድርድር የሚካሄደው ማለት አይደለም:: በፍጹም ተዓማኒ ካልሆነ ኃይል ጋር የሚደረግ ማንኛውም ድርድር ግን ድርድሩ በእርግጥም ተግባራዊ ሊሆን የሚችል መሆኑን የሚያሳዩ ጠንካራ መጠበቂያዎች (System of Verification) እንዲሁም ግልጽ የመተግበሪያ ሥርዓቶች (Implementation Mechanism) ሲደረጉለት ብቻ ነው ከምር ሊወሰድ የሚችለው:: ከዚህም ባሻገር ግን መጀመሪያውኑ ወደ ድርድር የሚመጣው ለጊዜያዊ የፖለቲካ ጥቅም ሳይሆን በእዉነተኛ መንፈስ ከድርድር የሚመጣውን ውጤት በመፈለግ መሆኑን የሚያሳዩ “የመተማመኛ” ምልክቶች ሲያሳይ ነው በእርግጥም ወደ ድርድር የመጣው ከልቡ ድርድሩንና ከድርድሩ የሚመጣዉን ዉጤት ፈልጎ መሆኑን ለማመን የሚያስችለው::
ወያኔ ከተቀናቃኝ ወገኖች ጋር “ድርድር” ሲያደርግ የመጀመሪያ ጊዜዉ አይደለም:: እኛ እስከምናውቀው ድረስ ምናልባት በኃይል ይበልጡኛል ብሎ ከሚያምናቸው ወገኖች ጋር ካልሆነ በስተቀር፣ በረሃ ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ በማንኛውም ጊዜ ለቃሉ ታማኝ፤ ለመርሁ እውነተኛ፤ ለደረሰበት ስምምነት ተገዢ ሆኖ አያውቅም:: ይልቁንም ሶስተኛ አደራዳሪ ወገኖችን በሚያሸማቅቅና በሚያሳፍር መልኩ ውሸትን እንደ አዋቂነት፤ ማጭበርበርን እንደ ብልጠት፤ የተስማማበትን በገሀድ ማፍረስን እንደ የአመራር ብልሀት አድርጎ የሚያይ፤ ምንም እፍረትና ጨዋነት የሚባል ነገር ያልፈጠረበት እኩይ ኃይል ነው:: ከራሱ የድርጅት ጥቅምና በስልጣን ከሚገኝ የዝርፊያ ሀብት ማካበት ባሻገር፤ ለአገር ዘላቂ ጥቅም ብሎ የራሱን ጥቅም አሳልፎ የሚወስደው ምንም እርምጃ እንደሌለ በተግባር በተደጋጋሚ ያረጋገጠልን ኃይል ነው:: በግንቦት 7 ውስጥ ያለን ወገኖች ይህንን የወያኔ ባህርይ በንድፈ ሀሳብ ደረጃ ሌሎች ጽፈውት ያነበብነው ሳይሆን፣ እራሳችን በተግባር በተሳትፈንበት ሂደት ያገኘነው ጥልቅ ግንዛቤ ነው:: ይህንን ደግሞ በአንድ አጋጣሚ ብቻ ሳይሆን ከድርጅቱ ታሪክ ጋር የተጣበቀ፤ በአመራር አባላቱ ላይ እንደ ግል ባህርይ የሰረጸ መሆኑን እስክንገነዘብ ድረስ በተደጋጋሚ የተመለከትነው ነው:: ስለዚህም ከዚህ ኃይል በኩል የሚመጣን የ “እንደራደር” ጥያቄ ከዚህ በፊት እንዳደረገው ለገባበት የፖለቲካ ውጥረት ማስተንፈሻ፣ ለውሸት ፕሮፓጋንዳው መጠቀሚያ፤ ለጊዜያዊ የፖለቲካ ትርፍ መሰብሰቢያ፤ የዴሞክራሲ ታጋዮችን ትጥቅ ማስፈቺያና ወኔ መስለቢያ አድርጎ እንዲጠቀምበት በፍጹም አንፈቅድለትም:: ስለዚህም ከላይ በመርህ ደረጃ ከጠቀስናቸው ሶስት ጉዳዮች በተጨማሪ ምንም ዓይነት ድርድር ከመደረጉ በፊት ወያኔ ጉዳዩን ከምር የወሰደው መሆኑን የሚያሳዩ “የመተማመኛ” እርምጃዎች መውሰድ አለበት ብለን እናምናለን::
እነኝህም፣
ሀ) ሁሉንም የፖለቲካ እስረኞች፤ ጋዜጠኞች፤ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መፍታት:: ይህ ደግሞ በግልጽ የሚታወቁ እስረኞችን ብቻ ሳይሆን በድብቅ የተቋቋሙ ማጎሪያና ማሰቃያ ቤቶች ያሉትን ሁሉ ማጠቃለል አለበት።
ለ) በሕዝብ በተለይ በተቃዎሚ ኃይሎች ላይ ወያኔ በየቀኑ እያካሄደ ያለውን ወከባና እንግልት ባስቸኳይ ማቆም፣ ሰብዓዊና የዜግነት መብታቸውን ማክበር አለበት።
ሐ) በፖለቲካ ምክንያት ከዚህ በፊት የተወሰዱ ሁሉም ዓይነት ፍርድ ተብዮ ውሳኔዎች እንዲሻሩ ማድረግ፤ በሂደት ላይ ያሉ ከፖለቲካ ጋር የተያያዙ ምንም አይነት ክሶችን ማቋረጥ አለበት።
መ) ሕዝብን በፍርሃትና በስጋት ለማቆየት ሆነ ተብለው የወጡ አፋኝ ህጎችን በአስቸኳይ ማንሳት አለበት።
ሠ) ማንኛውም ድርድር ገለልተኛ የሆኑ ሶስተኛ ወገኖች ባሉበት፤ የድርድሩ ሂደት በምስልና በድምጽ ተቀርጾ በገለልተኛ ወገኖች እጅ ብቻ የሚቀመጥ፣ የድርድሩ ቦታም የተደራዳሪ ወገኖች በጋራ በሚስማሙበት ቦታ መሆኑን መቀበልና ይህንንም በግልጽ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ማሳወቅ አለበት።
እነኝህ ከላይ ያስቀመጥናቸው በወያኔ በኩል የሚወሰዱ “የመተማመኛ” እርምጃዎች ለተቃዋሚዎች ተብሎ የሚወሰዱ እርምጃዎች አይደሉም:: ወያኔ እነዚህን እርምጃዎች ለመውሰድ ቁርጠኝነት ሳይኖረው ለእውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መመስረት የሚደረግ ድርድር ላይ ከምር ይሳተፋል ብለን ማመን በፍጹም ስለማንችል ነው ::
እስከዚያው ድረስ ግን ግንቦት 7ም ሆነ ሌሎች ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መመስረት በቁርጠኝነት የምንታገል ኃይሎች፣ ወያኔ እነኝህን የመተማመኛ እርምጃዎች እስኪወስድና ቀደም ብለው በተቀመጡት መርሆች መሠረት በሚደረግ ድርድር በተግባር ሊመነዘር የሚችል ስምምነት፣ አልፎም ለምንም አይነት ማጭበርበርና መንሸራተት እድል የማይሰጥ ጠንካራ መጠበቂያዎች መኖራቸው እስኪረጋገጥ ድረስ፣ የጀመርነውን ትግል ይበልጥ አጠናክረን የምንገፋበት እንጂ በምንም አይነት ለአንድ አፍታም ቢሆን በድርድር ስም የማንዘናጋ መሆኑን አበክረን እናስታውቃለን::
የግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ፣
ኅዳር 23፣ 2006 ዓ:ም
Subscribe to:
Posts (Atom)
