Tuesday, August 5, 2014

በጅዳ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ካድሬዎች የአቶ በረከትን ገበና አጋለጣችሁ በሚል ጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት ሲያዋክቡ ዋሉ።

አዲስ መረጃ በአቶ በረከት ዙሪያ፡ ምስጢር አወጡ የተባሉትን የጂዳ ቆንስላ ጽ/ቤት እያመሰ ነው

ሰበር ዜና አቶ በረከት ስሞኦን ዛሬ August 5, 2014 የሆስፒታል ቀጠሮቸውን ያጠናቅቃሉ !
« በአቶ በረከት ጉዳይ ካድሬዎች ጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤትን ሲያምሱ ዋሉ »

bereket alamudi demeke
ሳውዲ አረቢያ በህክምና ላይ የሚገኙት አቶ በረከት ስሞኦን ከህመማቸው አገግመው ሼክ አላሙዲን ወደ አዘጋጁላቸው ሚስጥራዊ ሆቴል ካቀኑ ወዲህ እኚህ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን ስላሉበት የጤነነት ሁኔታ በእርግጠኝነት መናገር ባይቻለም ከሁለት ቀን በፊት የሼክ አላሙዲን ወደ አሜሪካ ማቅናት ተከትሎ የአቶ በረከት ስሞኦን የ ጤንነት ሁኔታ በመላካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ መረጃዎች ያመላክታሉ ። አቶ በረከት ስሞኦን እስካሁን ሳውዲ አረቢያ ከሚገኙ ዲፕሎማቶች ጋር በስልክም ሆነ በአካል እንዳለተጋናኙ የሚገልጹ እነዚህ ምንጮች እኚህ የመንግስት ከፍተኛው ባለስልጣን ያረፉበት ሆቴል ምሲጥራዊነቱ በከፍተኛ ጥንቃቄ የተጠበቀ መሆኑን ይናገራሉ።
 
የአቶ በረከት የጤንነት ሁኔታ በማህበራዊ ገጾች መነጋገሪያ ከሆነ ወዲህ ጭቀት ውስጥ የገቡት ሼክ አልሙዲን የተለያዩ ሆቴሎችን እየቀያየሩ እኚህን የመንግስት ባለስልጣን ደብቀው ሲያስታምሙ እና አሰፈላጊውን ድጋፍ ሲያደርጉላቸው መክረማቸውን ለማውቀ ተችሏል። አቶ በረከት ከሆስፒታል ከወጡ ወዲህ የተለያዩ ሆቴሎች እንዳረፉ የሚገልጹ መረጃዎች ሼኩ ወደ አሜሪካ ከማቅናታቸው በፊት በግል ከተከራዩላቸው ምርጥ ሆቴሎች ምናልባተም የመጨረሻ የአቶ በረከት ሚስጥራዊ ማገገሚያ ይሆናል ተብሎ ከሚነገርለት ሆቴል ነገ ወደ «ቡግሻን» hospital በማቅናት የመጭረሻ የህክምና ቀጠሮአቸውን ካጠናቀቁ በሃላ በአጭር ቀን ውስጥ፡ ወደ ሃገር ይመለሳሉ ተብሎ ይጠበቃል። በተያያዘ ዜና በህክምና ላይ የምትገኘው የ6 አመቷ የአቶ በረከት ልጅ ህጻን ህሊና በረከት በመልካም ጤነት ላይ መሆኗን የኢትዮጵያ ሃገሬ የሆስፒታል ምንጮች አረጋግጠዋል ።

ይህ በዚህ እንዳለ በጅዳ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ካድሬዎች የአቶ በረከትን ገበና አጋለጣችሁ በሚል ጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት ዛሬ የመጡ ኢትዮጵያውያን ሲያዋኩቡ መዋላቸው በጅዳ እና አካባቢው ኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ዘንድ ከፍተናኛ ቁጣን ማስነሳቱ ን ለማረጋገጥ ተችሎል ። ጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት የተለያዩ ጉዳዮቹን ለማስፈፀም በጠራራ ጸሃይ ሲነፍሩ የነበሩ ኢትዮጵያዊያንን እንደ ዜጋ አዝነው በአግባቡ ከማስተናገድ ይልቅ አቶ በረከት መታመማቸውን መረጃ ያወጣችሁት እናንተ ናችሁ የተቃዋሚ ወሬ አቀባዩች እናተን ሰብስቦ ማቃጠል ነበር በሚል ዛቻ ፍጹም ኢትዮጵያዊ ነኝ ከሚል የድርጀት አባል በማይጠበቅ ቃላት በኢ.ህ.ዴ.ን ካድሬዎች እና የህወሃት ካድሬዎች ሲያዋክቡ ሲዋከቡ መዋላቸውን በደሉ የተፈፀመባቸው ወገኖች ገልፀውልናል። በተለይ እራሳቸውን ብቸኛ በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት ፈላጭ ቆራጭ አድርገው ያስቀመጡት የህወሃት የቀድሞ ታጋይ አቶ ገሬ እና መዝገብ ቤት ሃላፊ የሆነው የትግራይ ተወላጁ የቀድሞው የህወሃት ታጋይ አቶ ሽፋ ባለጉዳዮችን ሲያንገራግሩ ከነበሩ መሃከል ግንባር ቀደም እንደነበሩ ታውቋል።
የጅዳ ቆንስል ሃላፊ የነበሩትን ቆንስል ዘነበን በተጽዕኖ ያስነሱት እንዚህ የጅዳ ኢህአዴግ ካድሬዎች የጅዳን ቆንስላ ጽ/ቤት በመቆጣጠር ደካማ ዲፕሎማቶችን በመናቅ እንዳሻቸው በማድረግ ከማድረጋቸውም በላይ ለጉዳይ የመጣውን ኢትዮጵያዊ ማጉላላት እና ፓስፖርት እስከ መንጠቅ የደረሱ ወንጀለኞች መሆናቸው በአብዛኛው የጅዳ ማህበረሰብ ዘንድ ይነገራል። ከዚህ መሰሪ ተግባራቸው ያልታቀቡት እንዚህ ግለሰቦች የአቶ በረከትን ለህክምና መምጣትን መረጃ አወጣችሁ የሚሏቸውን ወገኖች ወደ ቆንስላው ግቢ ሲገቡ በመተናኮል ሁከት ቀሰቀሱ ብለው ለማሳሰር በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ከጽ/ቤት የወጡ መረጃዎቻችን ጠቁመዋል።

Monday, August 4, 2014

ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማሪያም ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራውን በስልጣን ጥመኝነት ከሰሱ!!

አንድነት ከቲፎዞ ነጻ የሆነ ምርጫና መሪ ያስፈልገዋል!!….hqdefault

በቅርቡ ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሊቀመንበር ለመሆን በዕጩነት ቀዳሚ ሆነው ማለፋቸው የፓርቲው ልሳን የሆነው ፍኖተ ነጻነት አስታውቋል፡፡በዚህ ጉዳያ ያልተናደደና ያልተበሳጨ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ይኖራል ብሎ መገመት ይከብዳል፡፡ በተለይ ያእቆብ ሀ/ማሪያም በግንቦት 25/2005 በሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ ላይ በኩባ አደባባይ ለሰልፈኛው አቅርበውት በነበረው ንግግቸው ላይ “እኛ አባቶች ከእንግዲህ ሀላፊነት ለወጣቶች በመስጠት በምክርና የተለያየ ተሞክሯችን በመስጠት ከጎናቸው መቆም አለብን፣ከእንግዲህ የእኛ ሀላፊነት ወንበሩን ለወጣቱ ለአዲሱ ተውልድ መልቀቅ ነው፣ “ብለው ነበር፡፡ኢንጂነር ግዛቸው ግን እንዲህ ቅዱስ ነገር ለመስማት ፍላጎትም ያላቸው አይመስልም፡፡ኢህአዴግም የእሳቸው ወደ ፊት መምጣት እንደ ሰማይ መና የሚቆጥረው ነገር ነው፡፡ ለምን?

፣ሰውዬው ታሰረው ከነበሩትና በኋላም በይቅርታ ከተለቀቁት የቅንጅት አመራሮች አንዱ ነበሩ፡፡እና ምን አለበት ሊባል ይችላል፡፡በጣም ከባድ ችግር ነው ያለበት፡፡ዋናው ነገር ምን አይነት ይቅርታ ጠይቀው ነው የወጡት የሚለው ነው፣ እንዲህ የሚል ነው

….ህገ መንግስቱንና ህገመንግስታዊ ስርአቱን በሀይልና በአመጽ ለመናድ በህገወጥ መንገድ ተንቀሳሰናል በዚህም ምክንት ብዙ ጥፋትና ውድመት ተከስቷል፤እንዲህ አይነት ነገሩ ውስጥ በማድረግ ህዝባችንና መንገስታችንን በመበደላችን አጥፍተኛል ተጸጽተናል፣ከእንግዲህም አይለመደንም ይቅርታ ይደረግልን… የሚል አይነት ነበር፡፡


ኢህአዴግ በእንዲህ አይነት ሁኔታ ይቅርታ እንዲጠይቁ ያደረገው በትክክል የተባለው ነገር ስለፈጸሙ ሳይሆን፣፣ከእስር ትፈታላችሁ ነገር ግን ካሁን በኋላ እኔ ከምላችሁ አንዳች ፍንክች ብትሉ ተመልሳችሁ ትገቧታላችሁ ማለቱ እንደሆነ ትርጉሙ ግልጽነው፡፡ለዚህም የብርቱካን ሚደቅሳ ነገር ማየት ረዘም ተደርጋ እንዳተሰረች ዶሮ እንጂ እኝደወፍ እንድትበር አልተፈቀደላትም፡፡ስዊድን ሀገር ሄዳ ኢህአዴግ የማይፈቅደው ነገር ተናግራ ወደ ሀገር ቤት ስትመጣ ብዝብ ፊት ይቅርታ ጠይቂ አለበለዛ በተስማማስ መሰረት ወደነበርሽበት ትመለሻለሥ ጠባለች፡፡እምቢ አለች፡፡ተመለሰች፡፡በወቅቱ አብዛኛው የአንድነት አመራሮች በፊርማ የወጡ ስለነበሩ ለምን ብለው ሊከራከሩላት አልቻሉም፣እንዳውም የሚሉሽን አትሰሚምና የእጅሽን ነው ያገኘሽው በሚል አይነት ሁኔታ በብዙ መንገድ ሊኮንኗትና ሊያሳጧት ሞክረዋል፡፡

በወቅቱ ደግሞ ድርጅቱን በሀላፊነት ይመሩ የነበሩት ዛሬ ቲፎዞ አሰልፈው የመጡት ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው ነበሩ፡፡እኚህ ሰው በወቅቱ ብርቱካን የታሰረችው እስርቤት የገባችውን የፊርማውን ቃል ስላቃለለች ነው የሚል በሚመስል የብርቱካንን ስም የሚያነሳ ሁል በድንጋይ ሳይቀር እስከማስደብበብ ደርሰዋል ውሸታም የሚለኝ ያ አይመስለኝም፡፡ከድርጅቱ አግደዋል አባረዋል፡፡ለዚህም የዛሬዎቹ የሰማያዊ ፓርቲ መሪዎችና አባላትን መጥቀስ ይቻላል፡፡ሰውዬው ድርጅቱን ይመሩት እስርቤት የፈረሙትንነገር በህልማቸውና በቅዠታቸው እየመጣባቸው ነበር፡፡ ለኢህአዴግ የገቡትን ቃል ለማክበር ብዙ የደርጅቱን ወጣቶችና ስም አባክነዋል፡፡ዘሬም ያ ፍርሀታቸው ደብቀው በፍርሀት ሊመሩት ከነቲፎዟቸው ብቅ ብለዋል፡፡በነገራችን ላይ ይህ ሰው በ97 ምርጫ ወቅት ፓርላማ እንግባ አንግባ በሚባልበት ወቅት እንግባ (ኢህአዴግ የሰጠንን ተቀብለን እንግባ) ብለው ይከራከሩ የነበሩ ከዚህም የሀገር ፍቅር ይኖራቸው ይሆናል እንጂ ወደፊት ገፍቶ ኢህአዴግን ለመታገል የሚጎላቸው ነገር እንዳለ ማወቅ ይቻላል፡፡ለጫማው በኋላ ይታሰብበታል ላሁኑ ማምለጥ ነው የሚሉ አይነት ሰው ናቸው፡፡


እና ምን ለማለት ነው ? ሰውዬ የአንድነት መሪ ቢሆኑ ድርጅቱን የሚመሩት ያኔ በፈረሙት ፊርማ ታስረውና ተሸብሽበው ነው፡፡አንዷል አተራጌ አፌን ሞልቼ ስለነጻነት አወራለሁ ሲል አትችል እንዲህ ማድረግ እንደማትችል እስርቤት ፈርመሀል ተብሎ ይኀው የትእንዳለ እናውቃለን፡፡ዶ/ር ብርሀኑ ነጋ የፈረው ፊርማ በሀገር ቤት የትም እንደማያደርሰው አውቆ ይኸውየት እንዳለ እናውቃለን፣እዛም አልቀረለትም የሞት ፍርድ ተፈርዶበታል፡፡ዶ/ር ያእቆብ ቃሊቲ እያለሁ የፈረምኩት ፊርማ እያሰብኩኝ የኢትዮጵያን ህዝብ ትግል ከምጎዳ አርፌ ብቀመጥ ይሻላል ብለው ይመስላል ይኸው መሪ አይደለም የየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባልም አይደሉም፡፡ብርቱካንም በውሸት ታስራችሁ በተጭበረበረ መንገድ የፈረማችሁት ፊርማ እፈራችሁ የምትኖሩ ከሆነና ሌላውም ሲታሰር ፍርዳችሁና ና ምላሻችሁ ይሄ ከሆነ ብላ ሀገሩም ትግሉም ጥላ ተደብቃ እየኖረች ነው፡፡

ኢንጂነር ሀይሉሻውል መለስን ጎንበስ ብለው እጅ ነስቻለሁ ያሉት ወደው አይደለም፣ የፈረሙት ፊርማ ምን ያህል ቀልባቸውና ቅስማቸውን እንደሰበራቸው መገመት ይቻላል፡፡ያኔ ታስረው የነበሩ ጋዜጠኞች ሀገር ጥለው ያሉት ቃሊትን ብቻ ሳይሆን የፈረሙትንም ፊርማ ስለሚፈሩ ጭምር ነው፡፡ኢህአዴግ ሰማያዊ ፓርቲ በአደረጃጀትም ሆነ በዐጣቃላይ ጥንካሬ ከአንድነት ስለሚበልጠው አይደለም እንዲህ ልቡ የተሸበረው፣የቀሊቲን ፊርማ እያሰቡ የሚመሩ ሰዎች ስላልሆኑ ጭምር ነው፡፡

ስለዚህ ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው የአንድት መሪ ሆኑ ማለት ድርግቱ ክንፍ ብቻ ያለው የማይበር የታሰረ ዶሮ ከመሆን ውጪ ምንም አያመጡም፡፡ ስለዚህ በገዛ ፈቃዳቸው በቃኝ ብለው ከጎን ሆነው የትግል ልዳምቸውና ምክርብቻ ማካፈል አለባቸው፡፡ ደግሞም ባለፈው 22 ውስጥ ፖለቲካ ውስጥ ብዙ ጊዜጣቸውን ያሳለፉት እንደ በየነ ጴጥሮስና ዶ/ር መራራ ጉዲና በድርጅት አመራርነት በተለያየ ቦታ ተለጥፈው ተጣብቀው ነው ነው፡፡ለኢህአዴግ የጣሉት እንጂ ያስጣሉት ነገር የለም፡፡ሸክም መሆን ብቻ፡፡መአድ ውስጥ አመራር ውስጥ ነበሩ፣መኢአድ ውስጥ እንዲሁ፣ቅንጅት ውስጥ የታሰሩት አመራር ላይ ስለነበሩ ነው፣አንድነት እሰካሁን የሚያሳማውን ስም ያሰጡትም አመራር ላይ ስለነበሩ ነው፡፡አይተናቸዋል ፣በቃ አሁን ቦታውን ለሌላ ይልቀቁ!!በተለይ የእሳቸው ወደ ስልጣን መምጣት ድርጅቱን እንደእነ ቡልቻ ባሉ “የበራላቸው” ሰዎች በብሄር (በተለይ መዐአድ ውስጥ የነበሩ ሰው ከመሆናቸው አንጻር)በጣም የሚያሳማና ኢህዴግም የያኔው አንዳንድ የቅንጅት ስህተቶችን እያነሳ ህዝብ የሚያስትበት አጀንዳ ናየትግል መግደያ ከመሆን አያልፉም!!

ኃይለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ ሌሎች የአፍሪካ መሪዎች አሜሪካ ከመግባታቸው በፊት የኢቦላ ቫይረስ እንደሚመረመሩ ተገለጸ

 ሰሜን አሜሪካ ከነገ ጀምሮ በሚደረገው ትልቅ ስብሰባ ላይ የሚሳተፉ ኃይለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ የአፍሪካ መሪዎች ስብሰባው ውስጥ ከመግባታቸው አስቀድሞ ከኢቦላ ቫይረስ ነፃ መሆናቸውን ምርመራ እንደሚያደርጉ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ አስታወቁ።

Ethiopian Prime Minister Hailemariam Desalegn speaks during an interview with Reuters inside his office in the capital Addis Ababa
ከ729 ሰዎች በላይን የገደለውና በርካቶችን በቫይረሱ ተጠቂ ያደረገው ኢቦላ በአሁኑ ወቅት የታማሚዎች ቁጥር ከ 1 ሺህ 200 በላይ እንደሚሆንና ቫይረሱም ከአገራቱ አልፎ በስፋት በመሰራጨት የአህጉሪቷ ብሎም የዓለም ስጋት ሊሆን እንደሚችል ባለሙያዎች የሰጡትን አስተያየት በመጥቀስ ሲኤን ኤን መዘገቡ አይዘነጋም።
በጊኒ፣ በሴራሊዮን እና ላይቤሪያ በርካቶችን እየፈጀ ያለውና የአፍሪካም ትልቁ ስጋት እንደሆነ የሚነገርለት ይኸው በሽታ ወደ ስሜን አሜሪካ እንዳይሰራጭ መንግስታቸው በሰፊው እየሰራ እንደሚገኝ ያስታወቁት ባራክ ኦባማ ይህ ለ3 ቀናት በዋሽንግተን ዲሲ የሚደረገው በዚህ ትልቅ ስብሰባ ላይ ከ50 በላይ የአፍሪካ መሪዎች የሚገኙ ሲሆን ሁሉም የኢቦላ ምርመራ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።

ይህ ሰሚት (ስብሰባ) ነገ ኦገስት 4 ተከፍቶ ኦገስት 6 ቀን 2014 ዓ.ም ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሲዲሲ የተባለው የአሜሪካ የጤና ተቋም ባለፈው ሰኞ በሰጠው መግለጫ፣ በአገሪቱ ይህ ነው የሚባል የኢቦላ ወረርሽኝ ስጋት እንደሌለ አረጋግጧል፡፡ ይህም ሆኖ ግን በሽታው አደገኛ በመሆኑ መጠንቀቅ ይበጃል ብሏል ተቋሙ፡፡ በሽታው ከተከሰተባቸው የአፍሪካ አገራት የሚመጡ መንገደኞችን ወደ አሜሪካ አለማስገባት ሁነኛ መከላከያ መላ ነው ይላሉ- የሲዲሲ ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት ዶ/ር ማርቲ ሴትሮን፡፡ በቅርቡ ከእነዚያ አገራት የመጡና የኢቦላ ምልክቶች የተሰሟቸው ሰዎችም፣ ዛሬ ነገ ሳይሉ በአፋጣኝ ወደ ህክምና መሄድ እንደሚኖርባቸው ዶክተሩ መክረዋል፡፡ በአገራቱ የሚኖሩ ዜጎችም፣ የበሽታውን መተላለፊያ መንገዶች ጠንቅቀው በመረዳት ራሳቸውን እንዲጠብቁ ተናግረዋል፡፡
  • 532
     
    EmailShare
(ዘ-ሐበሻ)

Saturday, August 2, 2014

በዋሽንግተን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሊኢ ህ አ ዴ ግ ባለስልጣናት አንመችም አሉ..


non_pulsating_econ_caption

ይቺ አባባል ራሷ ቀላል ተመቸችኝ እንዴ፤ ትላንት በዋሽንግተን ዲሲ በአንዱ ምግብ ቤት ደረታቸውን ነፍተው ሊበሉ ሊጠጡ ተከስተው የነበሩት የንግድ ሚኒስትሩ አቶ ከበደ ጫኔ አንዳች ጫን ያለ ነገር ገጥሟቸው፤ ሳይበሉ ሳይጠጡ ጎንበስ ብለው እንደወጡ ተሰማ፤
ባለስልጣኑ የገጠማቸው ነገር ሳይወዱ በግዳቸው ልክ ልካቸውን መስማት ሲሆን፤ ይህንን ያደረጉ የዲሲ ወጣቶች የ ኢ ህ አ ዴ ግ ባለስልጣናት በተገኙበት ቦታ ሁሉ፤ በህዝብ ምግብ ቤትም ይሁን በህዝብ መጽዳጃ ቦታ እየጠበቁ ልክ ልካቸውን መንገር እና የሁላችንም ሃላፊነት ነው ሲሉ ይናገራሉ።
ይህንን ማድረግ ፋይዳው ምንድነው… ሲል እሳት የላሰው የኢሳት ጋዜጠኛ መሳይ ከበደ በጠየቃቸው ጊዜም፤ ”እነርሱ በኢትዮጵያ ላሉ ወንድሞቻችን አልመች እንዳሉ ሁሉ እኛም እንርሱን ምቾት መንሳት ዋናው አላማችን ነው” ሲሉ መልሰውለታል።
የኢ ህ አ ዴ ግ ባለስልጣናት ባለፈው ጊዜ በአቶ መልስ ላይ የደረሰውን ነገር ረስተውታል መሰለኝ ሰኞ በአሜሪካ ዋሽንግተን ለአንዳች ስብሰባ ልዑካን ልከዋል አሉ። ዘንድሮ ደግሞ ማን ደንግጦ ሊሞት ይሆን እያልን እየተጨነቅን ባለበት በዚህ ሰዓት የዲሲ ወጣቶች ለባልስልጣኖቹ ኮረኮንች መንገድ ሆነው አልመች ብለዋቸዋል። (ባለስልጣኖቹም ምን አለኝ ኮብል ስቶኔ… እያሉ መስሪያ ቤታቸውን እና መሳሪያ ታጣቂዎቻቸውን እየናፈቁ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው)
በዚህ አጋጣሚ ሰኞ በዋሽንግተን እና አካባቢዋ ይሚገኙ ኢትዮጵያውያን ባለስልጣኖቹ ላይ የተቃውሞ ቁጣቸውን ለማሰማት ተቀጣጥረዋል። ባለስልጣኖቻችን እንግዲህ ቆፍጠን ነው! ብለን እንምከር ወይስ ይቻሉት…! ?

Tuesday, July 22, 2014

የጤና ባለሞያዋ ወይዘሪት ተክለ ደስታ ከስራ ተባረረች።

  • 551
     
    EmailSha
ethsat

               የታዋቂው ፖለቲከኛና ጸሃፊ አብርሃ ደስታ እህት ከስራ ታገደች

ሐምሌ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአረና የወጣው መረጃ እንደሚያሳየው ወይዘሪት ተክለ ደስታ የኣብራሃ ደስታ እህት በመሆንዋ ብቻ ከስራዋ ታግዳለች ።

 ወይዘሪት ተክለ ደስታ የጤና ባለሙያ ስትሆን የህወሓት ኣባልና የራያ ዓዘቦ ወረዳ የጤና ፅህፈት ቤት ምክትል ሃላፊ ሁና ታገለግል ነበር።የወረዳው ባለስልጣናት “አንቺ እንደ ወንድምሽ ዓረናነሽ ፣ ላንቺ የሚሆን የህወሓት ሃላፊነትም ይሁን የሞያ ስራ የለንም፣ ላንቺ እንኳን ስራ፣ መሬቱም እሳት ሆኖ ያቃጥልሻል ” በማለት ከስራዋም ከህወሃት አባልነትም እንዳባረሩዋት ድርጅቱ አስታውቋል።

የህወሓት ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ኣባይ ወልዱ ታላቅ ወንድም የሆነው ኣቶ ኣውዓሎም ወልዱ የዓረና መስራችና ኣመራር ኣባልነው።ይህ በእንዲህ እንዳለ ወይዘሮ ኣልጋነሽ ገብሩ በህወሓት መንግስት “ኣሸባሪ” ተብላ ከተከሰሰች ጀምሮ 3ቱ ህፃናት ልጆቿ የጎዳና ሂወት መምራት መጀመራቸውን ከድርጅቱ የተገኘው መረጃ አመልክቷል።ህፃናቱ ኣባታቸውን  ከ9 ዓመት  በፊት  በሞት  ያጡ  ሲሆኑ፣  ጠላ እየጠመቀች ታስተዳድራቸው የነበረችው እናታቸውን በእስር ምክንያት ካጡ ብሗላ ትምህርታቸው ኣቋርጠው ፣የጎዳና ሂወት መግፋት ጀምረዋል።

እናታቸው  በ”ኣሸባሪነት” ተፈርጃ  በእስር ያጡ  ህፃናትን ለመንከባከብ በህብረት ባንክ መቐለ ቅርንጫፍ በ202 041 606 379 3018 የሚልየአካውንት ቁጥርተከፍቷል።
የሂሳብ ደፍተሩ የተከፍተው በወይ ዘሮ ኣልጋነሽ ታናሽ እህት ወይዘሮ ፅጌ ገብሩነው።