Tuesday, July 22, 2014

የጤና ባለሞያዋ ወይዘሪት ተክለ ደስታ ከስራ ተባረረች።

  • 551
     
    EmailSha
ethsat

               የታዋቂው ፖለቲከኛና ጸሃፊ አብርሃ ደስታ እህት ከስራ ታገደች

ሐምሌ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአረና የወጣው መረጃ እንደሚያሳየው ወይዘሪት ተክለ ደስታ የኣብራሃ ደስታ እህት በመሆንዋ ብቻ ከስራዋ ታግዳለች ።

 ወይዘሪት ተክለ ደስታ የጤና ባለሙያ ስትሆን የህወሓት ኣባልና የራያ ዓዘቦ ወረዳ የጤና ፅህፈት ቤት ምክትል ሃላፊ ሁና ታገለግል ነበር።የወረዳው ባለስልጣናት “አንቺ እንደ ወንድምሽ ዓረናነሽ ፣ ላንቺ የሚሆን የህወሓት ሃላፊነትም ይሁን የሞያ ስራ የለንም፣ ላንቺ እንኳን ስራ፣ መሬቱም እሳት ሆኖ ያቃጥልሻል ” በማለት ከስራዋም ከህወሃት አባልነትም እንዳባረሩዋት ድርጅቱ አስታውቋል።

የህወሓት ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ኣባይ ወልዱ ታላቅ ወንድም የሆነው ኣቶ ኣውዓሎም ወልዱ የዓረና መስራችና ኣመራር ኣባልነው።ይህ በእንዲህ እንዳለ ወይዘሮ ኣልጋነሽ ገብሩ በህወሓት መንግስት “ኣሸባሪ” ተብላ ከተከሰሰች ጀምሮ 3ቱ ህፃናት ልጆቿ የጎዳና ሂወት መምራት መጀመራቸውን ከድርጅቱ የተገኘው መረጃ አመልክቷል።ህፃናቱ ኣባታቸውን  ከ9 ዓመት  በፊት  በሞት  ያጡ  ሲሆኑ፣  ጠላ እየጠመቀች ታስተዳድራቸው የነበረችው እናታቸውን በእስር ምክንያት ካጡ ብሗላ ትምህርታቸው ኣቋርጠው ፣የጎዳና ሂወት መግፋት ጀምረዋል።

እናታቸው  በ”ኣሸባሪነት” ተፈርጃ  በእስር ያጡ  ህፃናትን ለመንከባከብ በህብረት ባንክ መቐለ ቅርንጫፍ በ202 041 606 379 3018 የሚልየአካውንት ቁጥርተከፍቷል።
የሂሳብ ደፍተሩ የተከፍተው በወይ ዘሮ ኣልጋነሽ ታናሽ እህት ወይዘሮ ፅጌ ገብሩነው።

Thursday, July 3, 2014

(Breaking News) Dr. Brehanu Nega Speaks After Yemen handed over Andargac...

(ሰበር ዜና) የየመን መንግስት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን አሳልፎ ሰጠ

andargachew
  • 685
     
    EmailShare

) የደረሰን ዜና እንደሚያመለክተው፣ የግንቦት ሰባቱ ዋና ጸሃፊና የድርጅቱ ሞተር የሚባሉት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ  ለኢትዮጵያ መንግስት አሳልፈው ተሰጥተዋል። አቶ አንዳርጋቸው ለትራንዚት ሰንዓ የመን በቆዩበት ጊዜ በየመን ደህንነት ሃላፊዎች  ከአሥር ቀናት በፊት የታገቱ ሲሆን፣ ድርጅታቸው ግንቦት ሰባት እርሳቸዉን ለማስፈታት ዉስጥ ዉስጡን በርካታ ጥረቶች ሲያደርግ እንደቆየም ከድርጅቱ የወጣዉ መግለጫ ይጠቁማል።
አቶ አንዳርጋቸውን ለመጎብኘት ጥረት ያደረገው የእንግሊዝ ኤምባሲ፣ በየመን አቶ አንዳርጋቸውን ለማግኘት እንዳልቻለ የገለጸዉ የደረሰን ዘገባ፣ አቶ አንዳርጋቸው ለኢትዮጵያ መንግስት አሳልፈው የተሰጡት፣ በየመን መንግስት መያዛቸው በድርጅታቸው ለሕዝብ ይፋ ከመሆኑ በፊት እንደሆነም ለማረጋገጥ ችለናል።

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከግንቦት ሰባት አባላት ዉጭ በበርካታ ኢትዮጵያዉያን ዘንድ በቆራጥነታቸውና ሐሳብ አመንጪነታቸው የሚታወቁ ናቸው። በምርጫ ዘጠና ሰባት ወቅት ፣ በቅንጅት ዉስጥ ትልቅ ተሳትፎ ያደርጉ የነበሩት አቶ አንዳርጋቸው፣ ለሰላማዊ ትግሉም መጽሃፍ ጽፈው ያበረከቱ አገር ወዳድ ሰው ናቸው። በወቅቱ የኢሕአዴግ መንግስት አቶ አንዳርጋቸውን በዝዋይ አስሮ የነበረ ሲሆን፣ በዚያም በደረስባቸው ድብደባ አይናቸው ላይ ጉዳት እንደደረሰም በወቅቱ መዘገቡ ይታወሳል። አቶ አንዳርጋቸው አገዛዙ በሰላም አይወርድም በሚል ሁለገብ ትግል አደርጋለውሁ የሚለው የግንቦት ሰባት ከፍተኛ አመራር አባል ሆነው ሲሰሩ የነበሩ ታጋይ ናቸው።

Tuesday, July 1, 2014

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን ባለሥልጣናት እገታ ላይ መሆኑን በማስመልከት የወጣ መግለጫ

          


የግንቦት 7፣ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓም ለሥራ ጉዳይ በየመኒያ አየር መንገድ አይሮፕላን ተጉዞ በትራንዚት ሰንዓ ከተማ እያለ በየመን መንግሥት ፀጥታ ኃይሎች በሕገወጥ መንገድ ታግቷል። አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የመን የጉዞው መዳረሻ አልነበረም፤ ከየመን ጋርም የሚያገናኘው ምንም ጉዳይ አልነበረውም። የየመን መንግሥት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን አግቶ ለአንድ ሰዓት እንኳን ለማቆየት ምንም ምክንያት የለውም። በዚህም ምክንያት ያለአግባብ የታገተብን የንቅናቄያችንን አመራር በአስቸኳይ እንዲፈታ በተለያዩ መንገዶች ላለፈው አንድ ሣምንት ያደረግነው ጥረት እስካሁን አልተሳካም። እንዲያውም የየመን ባለስልጣናት አምባገኑን ወያኔ ለመርዳት ባለው ፍላጎት ሳቢያ መሪያችንን አሳልፎ ሊሰጠው ይችላል የሚል ከፍተኛ ስጋት አድሮብናል።http://www.ginbot7.org/wp-content/uploads/2013/05/g7-logo.jpg

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ በሀገራችን በኢትዮጵያ ውስጥ ፍትህ፣ ነፃነትና ዲሞክራሲ እንዲሰፍን ጊዜውን፣ እውቀቱንና ጉልበቱን ብቻ ሳይሆን ሕይወቱን አሳልፎ ለመስጠት የተዘጋጀ፤ ዝግጁነቱንም በተግባር ያሳየ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ነው። የየመን መንግሥት ከዘረኛውና ፋሽስታዊው ወያኔ ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ታጋይ መሪያችን ላይ እየፀመ ያለውን ደባ የጉዳዩ ባለቤት የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲያውቅ የንቅናቄዓችን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ወስኗል።
ትግላችን መስዋትነት እንደሚያስከፍል እናውቃለን። ከዚህ በፊትም ብዙ ጓዶቻችን መስዋዕትነት ከፍለዋል፤ ወደፊትም ብዙ መስዋዕትነት መከፈሉ የማይቀር ጉዳይ ነው። አሁን በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ የደረሰውና ወደፊትም ሊደርስ የሚችለው ጉዳት ምሬታችን በማብዛት፣ ቁጣችንና ዝግጁነታችን ከማጠንከር በስተቀር ቅንጣት ታክል እንኳን ወደ ኋላ እንድናፈገፍግ እንደማያደርገን ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ለአባሎቻችንና ለደጋፊዎቻችን ሁሉ መግለጽ እንወዳለን።

መንግሥታት ይመጣሉ፣ ይሄዳሉ። ኢትዮጵያና የመን ግን ጎረቤታሞች ሆነው መቆየታቸው የማይቀር ነው። የየመን መንግሥት የወያኔ እድሜ አጭር መሆኑ የተገነዘበ አይመስልም። በዚህም ምክንያት የየመን መንግሥት የሁለቱን አገሮች ሕዝቦች የቆየ ወዳጅነት የሚያደፈርስ እርምጃ ወስዷል። የየመን መንግሥት የየመንን የወደፊት የረዥም ጊዜ ጥቅም እንዲያሰላና ያገተብንን መሪ በአስቸኳይ እንዲፈታ እንመክራለን። ይህ ሳይሆን ቀርቶ በመሪያችን ላይ ጉዳት ቢደርስ ወይም ለወያኔ አሳልፎ ቢሰጥ የመን ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር የማይሽር ቂም ውስጥ የምትገባ መሆኑን የየመን መንግሥት አውቆ በጥብቅ እንዲያስብበት እናስጠነቅቃለን።
በየመን መንግሥት አልሰማ ባይነት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ለፋሽስቱ የወያኔ አገዛዝ ተላልፎ ቢሰጥ በአካሉና በሕይወቱ ለሚደርሰው ሁሉ የወያኔ ፋሽስቶችን ዋጋ የሚያስከፍል መሆኑ ከአሁኑ እናስጠነቅቃለን። በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ አካል፣ መንፈስና ሕይወት ላይ የሚደርሰው ማንኛውም ጥቃት ለነፃነታቸው ለመሰዋት ዝግጁ የሚሆኑ እልፍ አዕላፍ ታጋዮችን እንደሚፈጥር ጥርጥር የለንም። በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ አካል፣ መንፈስ እና ሕይወት ላይ ለሚደርሰው ጥቃት ሁሉ በማንኛውም መንገድ በማንኛውም ቦታ የምንበቀል መሆኑንና ብዙ የወያኔ ሹማምንት ዋጋ የሚከፍሉበት እንደሚሆን እንዲያውቁት እናስጠነቅቃለን ።

Saturday, June 28, 2014

በአ.አ ዩኒቨርሲቲ 52 ተማሪዎች ክስ ተመሰረተባቸው ።

በአ.አ ዩኒቨርሲቲ 52 ተማሪዎች በ”ዲሲፕሊን” ሰበብ ፖለቲካዊ ክስ ተመሰረተባቸው (ዝርዝራቸውን ይዘናል)

  • 1466
     
    EmailShare
 በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመብት ጥያቄ አንስተው በሃገራዊ ጉዳይ ነቃ ያለ ተሳትፎ የሚያደርጉ 52 ተማሪዎች ላይ የዲሲፕሊን ክስ መመስረቱ ተሰማ። የዲሲፕሊን ክስ የተመሰረተባቸውን ተማሪዎች ስም ዝርዝር የያዘውን ወረቀት በማህበራዊ ድረገጾች ላይ የለቀቁት የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ክሱ የተመሰረተባቸው ሰኔ 21 ቀን 2006 ዓ.ም ከጠዋቱ በ2 ሰዓት በተማሪዎች ጽ/ቤት እንዲገኙ ት ዕዛዝ ተሰጥቷል።
ምናልባትም እነዚህ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ትኩረት አድርገው የሚንቀሳቀሱት ተማሪዎች ላይ በዲሲፕሊን ሰበብ ፖለቲካዊ እርምጃ ሊወሰድባቸው እንደሚችል የቅርብ ምንጮች  ያስታወቁ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው ይህን እርምጃ ከወሰደ ሌላ የተማሪዎች አመጽ እንዲነሳ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ታዛቢዎች ይናገራሉ።
በዲሲፕሊንክ ክስ ሰበብ የፖለቲካ እርምጃ ሊወሰድባቸው የተዘጋጁት ተማሪዎች ስምዝርዝር የሚከተለው ነው፦
students 1

students 2

Friday, June 27, 2014

የህወሓት ባለስልጣናት የመቀሌውን ሰላማዊ ሰልፍ ለማስቆም ሽርጉድ በማለት ላይ ናቸው።

ህወሓቶች የመቐለን ሰለማዊ ሰልፍ ለመከልከል ወስነዋል። 

(አብርሃ ደስታ)

  • 68
     
    Share
mekeleትናንት ሐሙስ ማታ (ከምሽቱ 4:30) አንድ የህወሓት ባለስልጣን ደውሎ እንደነገረኝ ከሆነ ህወሓቶች የመቐለን ሰለማዊ ሰልፍ ለመከልከል ወስነዋል። ትናንት ማታ አስቸኳይ ስብሰባ የተጠራው “ሰልፉ በመቐለ እንዳይካሄድ፣ እንዳታዋርዱን፣ የህዝቡን ስሜት መረዳት እንዴት ያቅታችኋል? ነገሮች ሳይበላሹ ሰልፉ በሆነ ምክንያት እንዲቀር አድርጉ! ተብሎ ተደውሎልናል” ብሎ ነገረኝ። ማን ለማን ነው የሚደውልለት? አልነገረኝም። ግን ከአዲስ አበባዎቹ ይሆናል ብለን እንገምት።

ህወሓት ሰልፉን ለመከልከል ወስኖ ከሆነ በጣም የሚያሳፍር ተግባር ነው። ከመጠን በላይ ፈርቷል ማለት ነው። የመቐለ ህዝብ ሰልፍ የማድረግ መብቱ ተነፈገ ማለት ነው። ድሮምውም ኮ የህዝብ ስሜት የሚያጤኑ የደህንነት ሰዎች በዝተዋል። ህዝቡ እንደሚሰለፍ ስለተረዱ ይሆናል። መረጃው ትክክል ከሆነ በቃ የትግራይ ህዝብ ሰለማዊ ሰልፍ የማድረግ መብት የለውም ማለት ነው።
ግን ሰልፉን መከልከላቸው በደብዳቤ እስኪያሳውቁን ድረስ ሰልፉ እንደሚካሄድ ነው ታሳቢ የምናደርገው። ዉሳኔው ትክክል ስለመሆኑ የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ያስፈልገናል። እውነት ግን ሰልፉ አይደረግም ብለው ደብዳቤ ሊሰጡን? አላምንም። ደብዳቤ ካልሰጡን ደግሞ ሰልፉ ይደረጋል። ስለዚህ እናያለን።

Monday, June 16, 2014

(ሰበር ዜና)

 ከ1000 በላይ የሚሆኑ ዜጎች ቤታችን ፈረሰ በሚል ኢሰመኩ ደጃፍ ተቃውሞ ወጡ

  • 1237
    Share
(ዘ-ሐበሻ) በአሁኑ ሰዓት በአዲስ አበባ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን መስሪያ ቤት ደጃፍ ከ1000 በላይ የሚሆኑ ዜጎች ቤታችን ፈረሰ፣ የምንሄደበት አጣን በሚል ለተቃውሞ መውጣታቸውን የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች በፎቶ ግራፍ አስደግፈው ዘገቡ።
ከ1000 በላይ የሚሆኑት እነዚሁ ተሰላፊዎች መንግስት አንድ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ለመጠየቅ በኢሰመኮ ደጃፍ ላይ በመስፈር መፍትሄ ካላገኘን አንነቃነቅም እንዳሉ ነው። አካባቢውን ፌደራል ፖሊስ ከቦታል ሕዝቡ ግን ካለምንም ፍራቻ ተቀምጦ መብቱን እየጠየቅ እንደሚገኝ የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች አስታውቀዋል።
ፎቶዎችን ተመልከቱ፤ ተጨማሪ መረጃዎች እንደደረሱን እንመለሳለን። ዘ-ሐበሻ የትኩስ መረጃ ምንጭ።