Tuesday, August 19, 2014

የመከላከያ ሰራዊቱ ሊከዳ ይችላል በሚል ስጋት የወያኔ ጄኔራሎች ሲመክሩ ውለዋል።

ሻእቢያ ከከረን እና ከአስመራ ጦሩን ወደ ተሰንይ ማስፈሩን ተከትሎ ወያኔ ተጨማሪ ጦር ሲያጓጉዝ ዋለ።

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
የመከላከያ ሰራዊቱ ሊከዳ ይችላል በሚል ስጋት የወያኔ ጄኔራሎች ሲመክሩ ውለዋል።
ከሩሲያ ጋር የጦር ልምምድ ስምምነት እንዳደረገ የሚነገርለት የኤርትራ ገዥ ቡድን ሻእቢያ ከባለፉት ወራቶች ጀምሮ ጦሩን ወደ ደቡባዊ የኤርትራ ግዛቶቹ በመሰብሰብ ላይ መሆኑን ተከትሎ ወያኔም እንዲሁ ባለፈው ካሰፈረው ሰራዊት በተጨማሪ ከትላንትና ጀምሮ ከባድ የጦር ተሽከርካሪዎችን እና ተጨማሪ የጦር ሰራዊት በአከባቢው በማስፈር ላይ መሆኑ ታውቋል።
Ethio-army2 (1)
አሜሪካ እና ሩሲያ በአከባቢው ያላቸውን የበላይነት ለመቀዳጀት ፉክክር በገቡበት በዚህ ወቅት አከባቢው የጦርነት ቀጠና እንደሚሆን ቀድማ አሜሪካ በበረራ ደህንንነ ሰበብ ሹክ ባለችበት ሰአት እንዲሁም የሻእቢያ ተቃዋሚ ሃይሎችን ወያኔ በገንዘብ እና በቅስቁስ እየረዳ ባለበት ጊዜ በተጨማሪም በአግል ወያኔያዊ ትእቢት እየዛተ እንዳለ ሲሆን ለወያኔ ከፍተኛ ስጋት የሆኑበት ኢርታራ ውስት የመሸጉ ተቃዋሚ ሃይላት ስለሆኑበት በጭቆና የተምረረው ምከልከያ ሰራዊት ተቃዋሚዎችን ይቀላቅላል የሚል ከባድ ስጋት በሕወሓት ጄኔራሎች ላይ መከሰቱን ምንጮች ጠቁመውል።
ወያኔ በቅርቡ ከዩክሬይን ያስገባችቸን ቲ-72 ዘመናዊ ታንኮች በጦርነት ላይ ለማሰለፍ ወደ ሰሜን እያጓጓዘ ሲሆን ሻእቢያ በበኩሉ ሩሲያ ሰራሽ የሆኑ ዘመናዊ ታንኮች ሚሳኤሎች እና ከባባድ መሳሪያዎች፡ጸረ አይሮፕላን መድፎችን በአከባቢው አስፍሯል። ወያኔ ዘመናዊ መሳሪያ እና በታንክ ላይ የተጠመዱ መድፎችን ቢያምጣም በመክላከያ ሰራዊቱ ላይ ምንም አይነት መተማመን እንዳሌለው እየተናገረ ሲሆን በሰሜናዊ ትግራይ ብግብርና ሙያ ላይ ከነሙሉ ትጥቃቸው ያሰፈራቸውን የቀድሞ ታጋዮች እየቀሰቀሰ መሆኑ ሲታወቅ ህዝቡ ጦርነት እንደተሰላቸ እና ባለው ስርአት ላይ እምነት እንዳጣ በግልጽ እየተናገረ መሆኑ ታውቋል።

በሰራዊቱ ያልተማመነው ወያኔ አንድ የወሰደው እርምጃ ከሱዳን ጋር ያደረገውን የሰራዊት ቅልቅል ሲሆን ይህም ተቀላቅሎ መስራት በሰራዊቱ መኮንኖች ዘንድ ተቀባይነት አለማግኘቱ ታውቋል። የምዕራብ ኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን ለመስጠት ያሰበውን አገር የማጥፋት ሴራ ተግባራዊ ለማድረግ መሆኑን እና ሰራዊቱም ይህንን ተረድቶ ላገሩ ክብርና ታሪክ እንዲቆም ህዝቡ እየትናግረ ሲሆን የተደረገው የሰራዊት ውህደት ሱዳን በዳርፍርና ምስራቅ ሱዳን እንዲሁም ከደቡብ ሱዳን አቅጣጫ ላለበት ጦርነት በስምምነታቸው መሰረት የኢትዮጵያ ወታደሮች እንዲዋጉለት ለማድረግና ወያኔም በዚህ ጉዳይ ላይ መስማማቱን እናም በመከላከያ ሰራዊት ያለ የኢትዮጵያ ወጣት በጎረቤት አገሮች የበረሃ ሲሳይ ከመሆን ራስን እንዲታደግ አስተያየት ሰጪዎች አሳስበዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከአዲስ አበባ የሚወጡ ዘገባዎች መጭውን የወያኔ የጦርነት ዝግጅት ተከትሎ የመከላከያ ሰራዊቱ በመክዳት ከተቃዋሚ ሃይሎች ጋር ሊቀላቀል ይሽላል በሚል ስጋት ስብሰባ ተቀምጠው መዋላችውን ምንጮች ጠቁመዋል። በኤርትራ የሚንቀሳቀሱ የተቃዋሚ ሃይሎች የሚያወጡት መግለጫ በሰራዊቱ ላይ የሚፈጸመው ዘረኝነት እንዲሁም ብዝበዛ እና ከሃገሪቱ ጥቅሞች አንጻር እየተደረገ ያለው ብሄራዊ ውርድት በእጅጉ አሳሳቢ ደረጅ ልይ መድረሱ ሕዝቡ ለስር አቱ ያለው ጥላቻ መበራከቱ እንዲሁም ከዚህ ቀደም በባድመ ጉዳይ የተፈጸሙ መንግስታዊ ማጭበርበሮች እና የመሳሰሉት ግኡዳዮች ሰራዊቱ ይከዳል የሚል ከባድ ስጋት ያላቸው መሆኑን ያወሱት ጄኔራሎቹ በመከላከያ ሰራዊቱ ላይ እምነት በማጣትቸው ትግራይ ያለው የሕወሓት ታጣቂ ሃይል ከጀርባ እንደ ደጀን እንደ መተማመኛ እንደሚወስዱት መክረዋል።
ሰራዊቱ ያለውን ስርአት በተመለከት ደስተኛ ስላልሆነ እንዲሁም ሕዝቡ የሚፈልገው ለውጥ እንጂ ጦርንት ስላልሆነ ወያኔ በመጭው ሊያደርገው ያሰበው ጦርነት ከባድ ኪሳራ ያስክትልበታል ተብሎ ተገምቷል።

ወጣት ጥላዬ ታረቀኝ ዛሬ ፍድር ቀርቦ የዋስትና መብቱ ሳይጠበቅ ለዓርብ ቢቀጠርም የትግርኛ ሙዚቃ ለምን ተከፈተ ብሎ በሰው ላይ ጉዳት አድርሷል በሚል 2ኛ የክስ መዝገብ ተከፍቶበታል፡፡


ፍኖተ ነፃነት

10606390_684528351632102_6265250781347686507_n
በ4/12/06 እሁድ ማታ በደህንነት ኃይሎች በቁጥጥር ስር የዋለውና በእስር ላይ የሚገኘው ወጣት ጥላዬ ታረቀኝ በዛሬው እለት ፍርድ ቤት ቢቀርብም ፖሊስ ከሳሹን ስላላገኘሁትና የህክምና ማስረጃውን ስላልደረሰልኝ የጊዜ ቀጠሮ ይፈቀድልኝ ያለ ቢሆንም ወጣት ጥላዬ መርማሪው የምርመራ ስራን እየሰራ አይደለም ይልቁንም ራሱ ቢሮ የያዙኝ ደህንነቶች እየመጡ መርማሪው ባለበት ከእኛ ጋር ለመስራት ፈቃደኛ እስካልሆንክና የምንሰጥህን ተልዕኮ እስካልፈፀምክ እዚህ ትበሰብሳለህ እንጂ አትወጣም እያሉ እንደሚዝቱበት ለፍርድ ቤቱ ቢያስረዳም ፍ/ቤቱ ፖሊስ ለ16/12/2006 ፖሊስ መረጃዎቹን አጠናቆ እንዲያቀርብ እስከዛ የዋስና መብቱ ተቀባይነት አለማግኘቱን ብይን ሰጥቷል፡፡

ወደ እስር ቤት ሊሄድ በሚዘጋጅበት በድጋሚ ተጠርቶ 2ኛ የክስ መዝገብ እንደተከፈበት እና ክሱም በ12/10/2006 ዓ.ም ከምሽቱ 4፡30 ላይ የትግርኛ ሙዚቃ እንዴት ይከፈታል በማለት በሰላም የሚዝናኑ ግለሰቦች ላይ ጉዳት አድርሶ ተሰውሯል የሚል ሲሆን ስለቀቀረበበት ክስ የተጠየቀው ጥላዬ እኔ ከአካባቢዬ አልተሰወርኩም ሲይዙኝም ከቤቴ በር ላይ ነው እስከዚህ ሰዓትም አላመሽም ፖሊስ እያቀረበ ያለው ክስ ከሳሽ በሌለበት ራሱ እየፈጠረ መሆኑን ፍርድ ቤቱ እንዲረዳልኝ እና የአንድነት ፓርቲ አባል በመሆኔ ባለኝ የፖለቲካ አመለካከት ጫና ለማሳደር የተወጠነ ውጥን መሆኑን መርማሪው ራሳቸው ያውቃሉ በማለት አስረድቷል ፡፡

ፖሊስ ለምን ጉዳት የደረሰበትን ግለሰብ እንዳላቀረበና 2ወር ሙሉ ፖሊስ የት ነበራችሁ ብሎ ፍ/ቤቱ ቢጠየቅም ከሳሽ ለጊዜው እዚህ ስለሌለና ልናገኘው ባለመቻላችን የህክምና ማስረጃውን እንድናቀርብ ይፈቀድልን በማለቱ ፍርድ ቤቱ የፖሊስን ማስረጃ ለመመልከት በ2ኛው ክስ ለ14/12/2006 ዓ.ም ለ3፡00 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ ፖለስ እስካሁን በጥላዬ ላይ ክስ የመሰረተውን ከሳሽን ሊያቀርብ ካለመቻሉም ባሻገር ፍ/ቤቱን የህክምና ማስረጃ እንዳቀርብ ይፈቀድልኝ ማለቱ አግራሞትን ጭሯል፡፡

Monday, August 18, 2014

የወያኔው ኢንሳ በአዲስ መልክ የፌስቡክ ስም አጥፊ ፔጆችን/ገጾችን ሊያደራጅ ነው።

ነቢል አህመድ ዘገፈርሳ


 ወያኔ የኢትዮጵያን ሕዝብ አንድነት እና ነጻነት ለመሸራረፍ ብሎም ለመበታተን ከሚጠቀምባቸው ዘዴዎች አንዱ በማህበራዊ ድህረገጹ ያሰማራቸውን ከተቃዋሚ ሃይላት ጋር ተመሳስለው የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት መስለው የተቃዋሚ ሃይሎችን ሎግ በመጠቀም እንዲሁም ለሽፋንነት በየመሃሉ የተቃዋሚ ድርጅቶችን መግለጫ እንደወሽመጥ በማስገባት በማታለል እና በማጭበርበር ላይ ተመስርተው ሲሰሩ የነበሩ ስም አጥፊ ገጾችን/ ፔጆችን በአዲስ መልክ ለማደራጀት በዚህ ሳምንት እረፍት እንዲወስዱ ያደረጋቸው መሆኑ ታውቋል።
 
ስም በማጥፋት ለውጥ ፈላጊ ሃይሎች በተለያዩ አክቲቪስቶች ላይ መጠራጠር እንዲያሳድሩ እና ጠቃሚ የተባሉ ጦማርያንን እንዲያጡ እና ትግሉ አቅጣጫውን እንዲስት በስፋት አዲስ የአሰራር ዘይቤ ለመቀየስ የተሳዳቢዎች የተዛልፊዎች እና የስም አጥፊዎች የማህበራዊ አካውንት እና ፔጆች እረፍት ላይ መሆናቸውን እና በተጠናከረ መልኩ ወደ ስራ እንደሚመለሱ በቅርብ የሚያውቋቸው ወዳጆቻቸው ተናግረዋል።
በዚሁም መሰረት በዜጎች መካከል ከባድ ጥርጣሬን ያጭራሉ የተባሉ የፈጠራ ጽሁፎች እና የሞቱ ሰዎች ፎቶዎችን በመጠቀም የተለያዩ የፌክ ወንጀሎችን በመጻፍ እንድሁም ከብልግና እና የሰውን ክብር ከሚያዋርዱ አዳዲስ ብካይ የሃሰት መረጃዎች ጋር ወዘተ ተያይዘው ወደ ማህበራዊ ድህረገጾች እርፍታቸውን ጨርሰው እንደሚመጡ ታውቋል።

Sunday, August 17, 2014

A must Watch Interview ESAT Bezih Samint Part 2


 ESAT Bezih Saminte with Tamagne Beyene, Ermias Legesse, Wendimagegne Gashu, August 10 2014, Part 2 | ESATTUB

ESAT Bezih Saminte with Tamagne Beyene, Ermias Legesse, Wendimagegne Gashu, August 10 2014, Part 2 

አንድ መንግስት እንደ መንግስት ከሚያሳዩት ነገሮች አንዱ በህዝቡ ላይ ስጋት የሚሆኑ ነገሮች እንዳይከሰቱ መከላከል ነው።

የኢትዮጵያ መንግስት ኢቦላን ለምን ፈለገው…!?


የኢትዮጵያ መንግስት ኢቦላን ለምን ፈለገው…!
ትላንት እነ ዮሃንስ ሞላ (ዮሃንስ ሞላ የብርሃን ልክፍት መድብል አሰናጅ ነው) እነርሱ የሚቀኙላትን ቅዳሜን የመሰለች ቀን ራሴን ክፉኛ ታምሜ አሳለፍኳት። ከመዕራብ አፍሪካ የመጣ ሰው ጋር ባለመገናኘቴ እንጂ የትኩሳቴ ነገር በሌላ የሚያስጠረጥር ነበር። (ሌላ የተባለው ኢቦላ ነው… ደጋግሞ በመጥራት ራሱ ይመጣብን ይሆን እንዴ እያልን ተሳቀን ሞትን እኮ ጃል…!
ከትላንት በስቲያ አይደል እንዴ… አየር መንገዳችን ከዩንጋንዳ ካምፓላ የመጣ አንድ ሰውዬ የበዛ ትኩሳት ታይቶበታል ብሎ ለኢቦላ መመርመሪያ ጣቢያ በተዘጋጀ ልዩ ስርፋ አስገብቶ የበዛ ምርመራ ሲያደረግለት ያየነው…!
እኔ የምለው እንዲህ ምልክት የሚመስል ነገር ሲታይ አፋጣኝ ምርመራ ማድረጉ ባልከፋ… ነገር ግን አየር መንገዳችን እስካሁንም ድረስ በመጨባበጥ ሁላ የሚተላለፈው አደገኛ ቫይረስ ወደተቀሰቀሰብት ምዕራብ አፍሪካ በረራ ማድረጉ ምኑን ተማምኖ ነው.. እንደሆነ ለምን አይነገረንም…!
በርካታ ሀገሮች፤ ለዛው በህክምናውም በመከላከሉም ዋዛ ያልሆኑቱ፤ ወደ ምዕራብ አፍሪካ ድርሽ አንልም ብለው ሲታቀቡ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ድርስ ምልስ፣ ድርስ ምልስ… እያለ እንደ ውሃ ቀጂ ሲመላልስ ብናይ የምርም ”የኢትዮጵያ መንግስት ኢቦላን ለምን ፈለገው…!” ብለን እየተጨነቅን እንገኛለን። መንግስት ኢቦላን አልፈለገውም ብሎ የሚሞግተን አካል ቢመጣ እንኳ ቢያንስ ነገር ሲፈልገው እያየን ነው ብለን እማኝነታችንን መስጠታችን አይቀሬ ነው…
እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ ነገር ከገባ በቀላሉ አይወጣም። እንኳንስ ኢቦላ ይቀርና ኢህአዴግም እንኳ አልወጣ ብሎናል… (ልል ነበር ”ጽንፈኛ ዲያስፖራ ተቃዋሚ…” እንዳልባል ብዬ ትቼዋለሁ…) እውነቱን ለመናገር ግን አንድ መንግስት እንደ መንግስት ከሚያሳዩት ነገሮች አንዱ በህዝቡ ላይ ስጋት የሚሆኑ ነገሮች እንዳይከሰቱ መከላከል ነው። ሆን ብሎ በክፉ ልቦና ተነሳስቶ፤ አልያም ደግሞ በድንገት እና በነዋይ ፍቅር ተሳስቶ ህዝቡን ለስጋት የሚዳርግ ከሆነ መንግስት ሳይሆን መቅሰፍት ነው ብለን ከመደምደም ወደኋላ አንልም።
እናም አየር መንገዳችን፤ በበኩሌ ሳልናገር ብዬ እንዳይጸጽተኝ፤ ይሄ ኢቦላ የተባለ ክፉ ደዌ ወደ ሀገር ቤት ቢገባ ካንተ ራስ አንወርድም እና ካሁኑ ወደ አደገኛ ሀገሮች ከመብረር ክንፍህን ሰብስብ ለማለት እወዳለሁ!
 ከአቤ ቶክቻው

Saturday, August 16, 2014

በሰማያዊ ፓርቲ የአርባ ምንጭ አስተባባሪዎች የተጀመረው እስር ተጠናቅሮ ቀጥሏል ፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ እንደዘገበው፦

blue party
ከአሁን ቀደም አራት የሰማያዊ ፓርቲ የአርባ ምንጭ አስተባባሪዎች በሽብርተኝነት ስም መታሰራቸው ይታወቃል፡፡ እነዚህን እስረኞች ያሉበትን ሁኔታና የዞኑን አደረጃጀት ለመጎብኘት ከአዲስ አበባ (ከማዕከል) የድርጅት ጉዳይ ኃላፊው አቶ ብርሃኑ ተክለያሬድና የድርጅት ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ አባል የሆነው ዮናስ ከድር ለጉብኝት በሄዱበት ወቅት ሲያስተባብሩ የነበሩት አባላት ከማዕከል የሄዱት የፓርቲው አመራሮች ሲመለሱ ለእስር መዳረጋቸውን ከአካባቢው የደረሰን መረጃ ይጠቁማል፡፡

በመሆኑም አቶ ከሳሁን አየለ የተባለው የሰማያዊ ፓርቲ አርባምንጭ አስተባባሪ ከአዲስ አበባ የመጡትን የፓርቲው አመራሮች ጋር በመሆን የዞኑን አደረጃጀትና በእስር ላይ ያሉትን የፓርቲው አስተባባሪዎች አስጎብኝቷል በሚል መታሰራቸው ታውቋል፡፡ በተመሳሳይ ሻምበል ካሳ የታሰሩትን ጠይቀሃል በሚል ለእስር መዳረጋቸውንና ነፃነት የተባለው የፓርቲው አስተባባሪ ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር እንዳይሰራና በታሰሩት ላይ እንዲመሰክር በማስፈራሪያ መለቀቁ ታውቋል፡፡
በዞኑ የሚገኙ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች እስራትና መከባ እየደረሰባቸው ሲሆን በአሁኑ ወቅትም ሉሉ መሰለ፣ በፈቃዱ አበበ፣ ካሳሁን አየለ፣ ሻምበል ካሰና ኢ/ር ጌታሁን የተባሉት የፓርቲው አስተባባሪዎችና አባላት በእስር ላይ እንደሚገኙ ለመረዳት ተችሏል።

Thursday, August 14, 2014

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የአፍ ወለምታ ።

ከፍተኛ ቁጣን የቀሰቀሰው የዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የአፍ ወለምታ ስለሙስሊም ታሳሪዎች – የጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ ልዩ ትንታ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ቴዎድሮስ ስለሙስሊም ታሳሪዎች ምን አሉ ? ድንበር የለሹ የህወሃት ፕሮፖጋንዳ ሲፈተሸ የዶ.ር ቴዎድሮስን ንግግር አስመልክቶ ሳዲቅ አህመድ ልዩ ዝግጅት አሰናድቷል

ሳዲቅ እዉነታዎችን በመፈተሽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ንግግር የ አፍ ወለምታ ሳይሆን ሚኒስቴሩ ሆን ብለዉ የፈጠሩት ብዥታ በመሆኑ ኦፊሴላዊ መግለጫ ሊሰጡ ይገባል ሲል ይደመድማልና ፕሮግራሙን እንከታተለዉ።