Monday, March 31, 2014

Telecom and Internet Surveillance in Ethiopia – Human Rights Watch report


The 137 page report details the technologies the Ethiopian government has acquired from several countries and uses to facilitate surveillance of perceived political opponents inside the country and among the diaspora. The government’s surveillance practices violate the rights to freedom of expression, association, and access to information. The government’s monopoly over all mobile and Internet services through its sole, state-owned telecom operator, Ethio Telecom, facilitates abuse of surveillance powers.
Summary
One day they arrested me and they showed me everything. They showed me a list of all my phone calls and they played a conversation I had with my brother. They arrested me because we talked about politics on the phone. Itwas the first phone I ever owned, and I thought I could finally talk freely.
— Former member of an Oromo opposition party, now a refugee in Kenya, May 2013
Since 2010, Ethiopia’s information technology capabilities have grown by leaps and bounds. Although Ethiopia still lags well behind many other countries in Africa, mobile phone coverage is increasing and access to email and social media have opened up opportunities for young Ethiopians—especially those living in urban areas—to communicate with each other and share viewpoints and ideas. The Ethiopian government should consider the spread of Internet and other
communications technology an important opportunity. Encouraging the growth of the telecommunications sector is crucial for the country to modernize and achieve its ambitious economic growth targets.
Instead, the ruling Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF), a coalition of ethnically-based political parties in power for more than 20 years, continues to severely restrict the rights to freedom of expression, association, and peaceful assembly. It has used repressive laws to decimate civil society organizations and independent media and target individuals with politically-motivated prosecutions. The ethnic Oromo population has been particularly affected, with the ruling party using the fear of the ongoing but limited insurgency by the Oromo Liberation Front (OLF) in the Oromia region to justify widespread repression of the ethnic Oromo population. Associations with other banned groups, including Ginbot 7, are also used to justify repression.  …… ( Read the Report )

Monday, March 24, 2014

ከሰው ለሰው ድራማ የሚገኘው ገቢ ለማንም እንዳይከፈል በፍርድ ቤት እግድ ተጣለበት

mar 24,2014

ተጻፈ በ ታምሩ ጽጌ
በየሳምንቱ ረቡዕ ማታና በድጋሚ ቅዳሜ ላለፉት 127 ሳምንታት በመተላለፍ ላይ ካለው ‹‹ሰው ለሰው›› ድራማ የሚገኘው ማንኛውም ዓይነት ገቢ ለማንም እንደይከፈል፣ መጋቢት 2 ቀን 2006 ዓ.ም. በፍርድ ቤት ዕግድ ተጣለበት፡፡
ክፍያው እንዳይፈጸም በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የግልግል ዳኞች ክልከላ የተጣለባቸው፣ አቶ መስፍን ጌታቸው (በአሁኑ ጊዜ የድራማው ፕሮዲዩሰርና ዳይሬክተር) አቶ ሰለሞን ዓለሙ (ስክሪፕት ጸሐፊ ተዋናይ)፣ አቶ ነብዩ ተካልኝ (የኢትዮ ኢንተር ኤጁኬት ፕሮሞሽን ባለቤት)፣ የአቶ ዳንኤል ኃይሌና የአቶ ሰለሞን ዓለሙ ስፓርክ ፊልም ፕሮዳክሽን የሚባለው ድርጅት ናቸው፡፡
የግልግል ዳኞቹ የዕግድ ትዕዛዙን ያስተላለፉበት ምክንያት፣ የሰው ለሰው ድራማ ፕሮዲዩሰርና በድራማው ‹‹ናርዶስ›› የምትባለውን ገጸ ባህሪ ወክላ የምትተውንና በፋይናንስና አድሚኒስትሬሽን ኃላፊነት ትሠራ ከነበረችው ወ/ሮ ብሥራት ገመቹ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ክስ በመመሥረቱ መሆኑን የዕግድ ትዕዛዙ ያስረዳል፡፡
ወ/ሮ ብሥራት ገመቹ፣ አቶ ነብዩ ተካልኝ፣ አቶ መስፍን ጌታቸው፣ አቶ ሰለሞን ዓለሙና አቶ ዳንኤል ኃይሌ ታኅሣሥ 22 ቀን 2003 ዓ.ም. በሰነዶችና ማረጋገጫና ምዝገባ ጽሕፈት ቤት ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ለማዘጋጀት ተስማምተው የሽርክና ውል መፈራረማቸውን የክስ ማመልከቻው ያስረዳል፡፡
ቀድሞ ‹‹የመጨረሻው ሰሞን›› የሚል ስያሜ ሰጥተውት የነበረውን ድራማ ‹‹ሰው ለሰው›› በማለት ሰይመው ለመሥራት ሲስማሙ፣ ወ/ሮ ብሥራትና ሦስቱ ተከሳሾች የትርፍ ክፍፍላቸውን በመቶኛ እንደየተሳትፏቸው ለመከፋፈል ተስማምተው መፈራረማቸው በሰነዶቹ ላይ ተጠቅሷል፡፡
ኢትዮ ኢንተር ኤጁኬት ፕሮሞሽን በተባለው የአቶ ነብዩ ተካልኝ የንግድ ድርጅት ፈቃድ፣ ከኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ጋር ውል ተፈራርመው ‹‹ሰው ለሰው›› ድራማን በመሥራት ላይ እያሉ፣ ንግድ ፈቃዳቸውን ሲያድሱ የአቶ ሰለሞን ዓለሙ ድርጅት መሆኑ በተጠቀሰው ስፓርክ ፊልም ፕሮዳክሽን በሚል ድርጅት ስም በማደስ፣ ከሳሽ ወ/ሮ ብሥራት የትርፍ ተካፋይ የማትሆንበት አሠራር መጀመሩን ክሱ ይገልጻል፡፡ 22 ማዞሪያ አካባቢ በሚገኘው ቡና ባንክ ቅርንጫፍ አቶ ሰለሞን ዓለሙና አቶ መስፍን ጌታቸው በጋራ ሒሳብ ሲያንቀሳቅሱ እንደነበርም የክሱ አቤቱታ ይጠቁማል፡፡
ለድራማው ቀረፃ ቤቷንና መኪናዋን በማቅረብ ተባብራ ስትሠራ የነበረችው ከሳሽ ወ/ሮ ብሥራት ድራማው ከተጀመረ ጀምሮ በፕሮዲዩሰርነት፣ በፋይናንስ አድሚኒስትሬሽን በወር አምስት ሺሕ ብር ተከፍሏትና ‹‹ናርዶስ›› የተባለችውን ገጸ ባሕሪ ወክላ ትሠራ እንደነበርም ለፍርድ ቤት ያቀረበችው ሰነድ ያብራራል፡፡
በመሆኑም በኃላፊነትም ሆነ በተዋናይነት እንዲሁም ከትርፍ ሊከፈላት የሚገባው ክፍያ ሳይፈጸምላት፣ ለጊዜው በግልጽ መግለጽ በማትፈልገው ምክንያት ከአንዱ ተከሳሽ ጋር አለመግባባት በመፈጠሩ፣ ከድራማው 54ኛ ክፍል ጀምሮ ‹‹ናርዶስ››ን ሆና ትተውንበት የነበረውን ገጸ ባህሪ መነጠቋን፣ ከ90ኛው ክፍል ጀምሮ ደግሞ ከፕሮዲዩሰርነቷ መሰረዟን በክሷ ለፍርድ ቤቱ አስረድታለች፡፡ ከድራማው 26ኛ ክፍል ጀምሮም የገቢ ክፍፍል እንዳልተፈጸመላት አክላለች፡፡
አቶ መስፍንና አቶ ሰለሞን ከተለያዩ ስፖንሰሮችና ከኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት መጠኑን ያላወቀችው ክፍያ እያሰባሰቡ ለግል ጥቅማቸው እያዋሉት መሆኑን፣ አቶ ዳንኤል የተባሉት ተከሳሽም የጥቅም ተጋሪ መሆናቸውን አስረድታ፣ 100 ሺሕ ብር በካሽ አዋጥታ ካቋቋመችው የድራማ መድረክ በዕውቀትና በዓይነት ከሰጠችው አገልግሎት በላይ ሞራል የሚነካ (ለኢትዮጵያ ሕዝብ ክብር ሲባል የማይገለጽ) ተግባር እንደተፈጸመባት በክሷ ዘርዝራ አቅርባለች፡፡
ከሳሽ ወ/ሮ ብሥራት ከቴሌቪዥን፣ ከማስታወቂያና ከስፖንሰሮች ከተሰበሰበውና የአገር ውስጥ ገቢ ተቀንሶ የሚደርሳት 16.25 በመቶ ድርሻዋ በወራት ተባዝቶ ከነወለዱ እንዲከፈላት፣ በፋይናንስና አድሚኒስትሬሽን ለሠራችበት በወር የሚከፈላትን አምስት ሺሕ ብር በ35 ወራት ተባዝቶ እንዲከፈላት፣ ‹‹ናርዶስ›› የምትባለውን ገጸ ባህሪ ወክላ ለተወነችበት 56 ክፍሎች በ500 ብር ታስቦ በድምሩ 163 ሺሕ ብር እንዲከፈላት ዳኝነት ጠይቃለች፡፡
የከሳሽን አቤቱታ ዝርዝር ማብራሪያ የተመለከተው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ንፋስ ስልክ ላፍቶ ምድብ ሁለተኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት በሰጠው ብይን፣ ከሳሽና ተጠሪዎች እያንዳንዳቸው አንድ ዳኛ እንዲመርጡ፣ የግራ ቀኙን ተከራካሪ የሚሰበስብ ዳኛ በጋራ እንዲመርጡና በሽምግልና ዳኝነት እንዲታይ የተወሰነ ቢሆንም፣ በአንድ ወር ውስጥ መምረጥ ባለመቻላቸው በፍርድ ቤቱ ሬጅስትራር በኩል የግልግል ዳኛ እንዲሾም አዞ ነበር፡፡
የግልግል ዳኞች በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለውን አቤቱታ በመመርመር ላይ ቢሆኑም፣ ከሳሽ ወ/ሮ ብሥራት የግልግል ዳኝነቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ከድራማው የሚገኘው ገቢ እንዲታገድላት ለግልግል ዳኞቹ ማመልከቻ በማቅረብዋ፣ የግልግል ዳኞቹ በፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 154 መሠረት ክርክሩ እልባት እስከሚያገኝ፣ ለተጠቀሱት ተከሳሾችም ሆነ ለሦስተኛ ወገን ምንም ዓይነት ክፍያ እንዳይፈጸም የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥንን ድርጅት ታዟል፡፡

Sunday, March 23, 2014

ለማኝዋ ስትሞት አራት ሚሊየን ዶላር ተገኘባት

ክንፉ አሰፋ

አንዲት የተጎሳቆለች ወይዘሮ በሪያድ ጎዳናዎች ላይ ምጽዋት ትጠይቃለች። አላፊ አግዳሚው እቺን ወይዘሮ አይቶ አያልፋትም። ሰደቃ እየወረወረላት ያልፋል። በተለይ በበዓል ወራት ገቢዋ በእጥፍ ይጨምራል።አይሻ ትባላለች። ነዋሪነትዋ ሪያድ ሳውዲ አረቢያ ነው። ላለፉት 50 አመታት በልመና ስራ ስትተዳደር ቆይታ በተወለደች በ100 አመትዋ በያዝነው

ሳምንት እሁድ እለት ከዚህ አለም በሞት ተለይታለች። አማሟቷም ድነገት ነበር ይላል አረብ ኒውስ።
ጉድና ጅራት ከወደኋላ ነው እንዲሉ የአይሻ ህልፈት አለምን ያስደመመ ጉድ ይዞ መጣ። ለሃምሳ አመታት በልመና የተሰማራችው ወይዘሮ ሚሊየነር ኖራለች። የወርቅ ጌጣጌጦች እና የጥሬ ገንዘብ ሃብትዋ አራት ሚሊየን ዶላር ሲሆን በጂዳ ከተማ የአራት ትላልቅ ህንጻዎች ባለቤትም ነበረች።
የአይሻን ንብረት የሚወርስ ዘመድ የለም። አብሮ አደግ ነኝ የሚል አህመድ አል ሰይድ የሚባል ሰው ግን የውርስ መብት አለኝ ብሏል። በእርግጥ አይሻ ሌላ ዘመድ የላትም። እህትና እናትዋ ለማኞች ነበሩ። ወላጆችም በልመና ይተዳደሩ የነበሩ መሆናቸውን የጠቀሰው የአረብ ኒውስ፣ አይሻ ንብረታቸውን በከፊል ከነሱ በውርስ እንዳገኙም ዘግቧል። አሁን ሁለቱም ሞተዋል።
አህመድ አል ሰይድ ንብረቱን “አይሻ ለኔ አውርሳኝ ሞታለች እኔም ተቀብዬ ለድሆች እንዳከፋፍል ይፈቀድልኝ” ብሎ ነበር። ከመንግስት ያገኘው ምላሽም ግን የለም።

ልመናውን እንድትተው ቢወተውታትም አሻፈረኝ ማለቷን ለመገናኘ ብዙሃን ገልጿል።
ሌላው የሚገርመው ነገር አይሻ ህንጻዋ የሚኖሩትን ሰዎች የቤት ኪራይ አታስከፍላቸውም ነበር።
አይሻ ሚሊየነር ነበረች። አንድ ቀን ጥሩ ምግብ ሳትበላ፣ ጥሩ መኝታ ላይ ሳትተኛ፣ ጥሩ ቤት ውስጥ ሳትኖር፣ ጥሩ ልብስ ሳትለብስ ኖራ ለዘላለሙ አሸለበች። ግን ይህ ለምን ሆነ የሚለው ጥያቄ ምላሽ አላገኘም።
አልፎ አልፎ የዚህ አይነት ክስተቶችን በአለም ላይ እናያለን። በሺዎች የሚቆጠሩ የኔብጤዎች ያሉባት ኢትዮጵያም በዚህ ስራ ከፍተኛ ሃብት እና ንብረት ያፈሩ ለማኞች አጋጥመውኛል።
እርግጥ የልመና ገንዘብ ስላልተለፋበት ይጣፍጥ ይሆናል። ልመናም እንደ አደንዛዥ እጽ ሱስ ያስይዝ ይሆን?

Wednesday, March 19, 2014

ሴቶች ለዓገራቸው ነጻነት የሚያደርጉትን ተሳተፎ በመደገፍ ኢትዮጵያ ዓገራችንን ካለችበት ስቃይ እንታደጋት....!!!

ራሄል ኤፍሬም
ቀደም ካለው ከሴቶች ተሳትፎ በመነሳት አውን እስካለንበት ጊዜ እንስቶች በፖለቲካው ያላቸውን ትልቅ ሚና ላነሳ ወዳለው።
በሁሉም የማህበራዊ ህይወት ዘርፎች ውስጥ የኢትዮጵያ ሴቶች የሚጫወቱት ጉልህ እና ወሳኝ ሚና ያላቸው ቢሆንም ሃገሪቱ ባላት ባህል፣ ታሪክ፣ እና ፖለቲካዊ ስርአት ምክንያት በሁለንተናዊ ማህበረሰብ እድገት ያደረጉት አስተዋጽኦ ተገቢውን ትኩረትና እውቅና አላገኘም። በዚህ ማህበረሰብ ውስጥ ያሉ አግላይ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ እና ማህበረሰባዊ ህግና ደንቦች ምክንያት ሴቶች የልፋታቸውን ውጤት ሳያገኙ ቆይተዋል። እንደሚታወቀው ሴቶች የዓለማችን ግማሽ አካል እንደመሆናቸው መጠን ተገቢውን ስፍራ ሳይሰጣቸው ነገር ግን በዘልማድ በማህበርሰቡ ውስጥ ሴቶች በዓገር፣ በእናት፣በሚስት ይመሰላሉ። እንዲሁም አንዳንድ ጊዜ ከታዋቂ ወንድ በስተጀርባ ጠንካራ ሴት እንዳለች ቢነገርም በማህበረሰብ ውስጥ ያላቸውን ተገቢ ቦታ እና እውቅና አልተስጣቸውም። ቀደም ባሉ ጊዜያት ሴትልጅ ከቤት ስትወጣ ነውር በሆነበት ወቅት አጠቃላይ የቤት ውስጥ ስራ ሃላፊነት በተለይም ለወንዶች ምግብ አዘጋጅቶ የመጠበቅ ግዴታ የሷ ሲሆን፣ከማጀት ስራዋ በተጓዳኝ ዓገር ተረካቢ ዜጋን የመንከባከብ እና የማሳደግ ጫናው የዚችው የምስኪኗ ሴት ሓላፊነት ነበር ።
በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ብዙ ታሪክ የሰሩ ጀግኖች እናቶች ቢኖሩም ባለው ማህበረሰባዊ አፈና ምክንያት በሴቶች ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ዙሪያ ጉልህ ሚና ሳይጫወት ቀርተዋል። እነዚ ቆራጥ እና ጀግና ታሪካዊ ሴቶች በወቅቱ የነበረውን ዋላቀር  አስተሳሰብ በመቋቋም በድፍረት እና በጀግንነት ከወንዶች በስተጀርባ በመሆን ላገራቸው ነጻነት ያላቸውን ተሳትፎ በቆራጥነት አሳይተዋል። ከጊዜ ወደ ጊዜም የሴቶች እንቅስቃሴ እየተሻሻለ የመጣበት ወቅት ላይ እንገኛለን። የግል ጥቅሙን በማራመድ ላይ በሚገኘው በዚህ አረመኔ መንግስት ምክንያት ዓገራቸውን ትተው በስደት ላይ የሚገኙ እና የትውልድ ዓገራቸው ላይ እንደ ሁለተኛ ዜጋ  በመቆጠር በስቃይ ላይ የሚገኙ  ቆራጥ ሴት የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፣ ጋዜጠኞች፣ የፖለቲካ ፓረቲ አመራሮች ቁጥር እየጨመረ ይገኛል። ይህም የሆነበት ምክንያት በአገራቸው የፖሊቲካ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበረስባዊ ሁኔታ በጉልህ መብቶቻቸውን ለመተግበር እና ስለ መብቶቻቸው ተሟጋች እንዲሆኑ ስለማይፈቅድ ከውጭ በመሆን ባገራቸው ለውጥ ለማምጣት እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ። ዛሬ በግለሰብም ሆነ በድርጅት ደረጃ  የሴቶች ተሳትፎ እድገት እንዲጨምር ትልቁን የህይወት መሰዋትነትን ከፍለው ያለፉ እንዲሁም እየከፈሉም ያሉ ጀግና እንስቶች ለኛም ሆነ ለዓለም ትልቅ ምሳሌወቻችን ናቸው ።

በኢትዬጽያ ውስጥ የፖለቲካና ሲቪክ መብቶች ከሆኑት ውስጥ የመናገር፣ የመጻፍ፣ እና በአጠቃላይ ሃሳብን በነጻነት የመግለጸ መብት በሌለበትና በተገደበበት ሁኔታ ገዢው መንግስት መስማት የሚፈልገውን ብቻ መናገር እና መጻፍ ግዴታ በሆነበት ቦታ ላይ መስዋእትነት የሚከፍሉ ሴቶች ቁጥር ከፍተኛ ነው። ለዓገራቸው፣ ለወገኖቻቸው እና ለነጻነታቸው በመቆም አምባገነናዊ ስርአትን በመታገል የበኩላቸውን አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ ይገኛሉ ። ለህዝብ ደህንነትና መብት ደንታቢስ የሆነው  በስልጣን ላይ የሚገኘው  ይህ ክፉ መንግስት ሴቶች እህቶቻችን እና ወገኖቻችን በነጻነት በመናገራችው፣በመጻፋቸው ፣በዴሞክራሲያዊ መንገድ በመቃወማቸው እና የሚፈልጉትን ፓርቲ በመምረጣችው ብቻ አሸባሪ በማለት እስር ቤት በማጎር ይገኛል።
 ከነዚህ ጉልህ ሚና ከሚጨወቱ ሴቶች እህቶቻችን መካከል በሰብአዊ መብት ተሟጋችነት እና በጋዜጠኝነት እንዲሁም በግለሰብም ሆነ በድርጅት ደረጃ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙትን እንስቶች እንዳሉ እና ከነዚህም መካከል እንደ ነብርቱካን ሜዴቅሳ እና እንደ  ሪዖት አለሙ ወ.ዘ.ተ ያሉ ለኛ ትልቅ ምሳሌ የሚሆኑን ጀግና ሴቶች ናቸው ።
የጀግኖቻችንን ምሳሌ በመከተል የአለም አቀፍ ሴቶች ቀን ማርች  8  በተከበረ ማግስት በአዲስ አበባ በተደረገ የሩጫ ውድ ድር  ከተሳተፉ ሴቶች መካከል አጋጣሚውን በመጠቀም በፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ እና በማህበራዊ ኑሮ የ ሚደርስባቸውን አፈና እና ጭቆና በማሰማት መብታቸውን ለማስከበር ጠንካራ ቋም እንዳላቸው ያሳዩበት አጋጣሚ ነበር። ይህም ክስተት ሴቶች እህቶቻችን ልክ እንደ ቀድሞው አሁንም የወገኖቻችንን ድምጽ ማፈን እና ማሰቃየት የለት ልማዱ ያደረገውን የወያኔ መንግስት የሚያደርስባቸውን ከባድ ጫና ወደጎን በማድረድ ድምጻቸውን ከማሰማት እና ችግሮቻቸውን ከማሳወቅ ወደዋላ ሳይሉ  ከፊታቸው የተደቀነ መሳሪያና የሚደርስባቸውን እስር ሳያስፈራቸው አምባገነናዊ ስርዓቱ እያደረሰባቸው ያለውን ጭቆና በተቃውሞ ገልጸዋል።

ሴቶች ለዓገረቸው በፖለቲካው ዘርፍ ከፍተኛ ሚና በሚጫወቱበት በዚህ ወቅት አበረታች እና ተስፋ የሚጣልባቸው አዲስ ጀግና እና ለመብታቸው ተሟጋች ትውልዶች እየመጡ እንዳሉ በተግባር እያየን ነው።  ከጎናቸው በመቆም የህቶቻችን ድምጽ እንዲሰማ አስተዋጽዖ በማድረግ ያሉበትን ስቃይ እና መከራ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ በማሰማት በወያኔ መንግስት ላይ ውግዘትና ውርደት ማድረስ ተገቢ ነው። ዓገራችን ካለችበት ከባድ ችግር ለማውጣት አንዱ እና ዋንኛው የሴቶች ተሳትፎ እንደመሆኑ መጠን ያላቸውን የመስራት ትልቅ ችሎታ ግምት ውስጥ በማስገባት ለዓገራቸው ነጻነት የሚያደርጉትን ተሳተፎ በመደገፍ ዓገራችን ካለችበት ስቃይ እንታደጋት።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር ..!!

Monday, March 10, 2014

በግለስብ ስልኮች እየደወሉ አላግባብ የሚሳደቡ የወያኔ ጉጅሌሆች...!!



በኖርዌይ ተስፋ የቆረጡ የውያኔ ካድሬዎች አማራን ህዝብን ሲስድቡ


አንድ አገዛዝ ወይም ፓርቲ ጥንካሬው ከሚፈተንባችው አንዱ መለኪያ የካድሬዎች ወይም ደጋፊዎች ቀጥር ብዛት ብቻ ሳይሆን የመቀስቀስና የማሳመን አቅማችው ሲጎለብት ነው ሆኖም ግን የኛው (ካባ ማስልጠኛ ) መግባቱን የሚያጠራጥር አንድ የወያኔ ካድሬ ስልኬን ሲያጨናንቀው ስንብቶል ፣ የተገናኘንበትም አጋጣሚም የህዝብን ድምጸ ለማስማት ላይ ታች ለሚለው ኢሳት የህዝብ ድጋር ለማሳደግና ጥቂት የምጣኔ እርዳታ ለማድረግ በትሮንድሀይም ባዘጋጀነው የኢሳት ምሽት ታዳሚዎቻችን በተገቢው መንገድ ለማስተናግድ ሁለት አባላት ስልክ ቁጥር በበራሪ ወረቀት ላይ ስፍሮ በማግኘቱ አጀሬ ካድሬ አፈፍ አድርጎ የስልክ ጥሪውን ማዠጎድጎድ ጀመረ፣፣
የሚስደንቀው ነገር ግን ካነሳልኝ የመከራከሪያ ነጥቦች አንዱም ሚዛን የማያነሳ መሆኑ አልፎ ህጸናትን እንኳን  የማሳመን አቅም የሌለው ነጥቦች በመደጋገም ብዙ ግዜዬን ስላባከነብኝ ስልኩን አለማንሳት ወስንኩ ግን አጀሬ ካድሬ መች በዚህ ይፈታና ስልኩን ቀጥር አይነት በአይነት በመቀያየር ፋታ ቢከለከለኝም ከአቋሜ ፈንክች አላልኩም ይህንንም ዘግይቶ ሲረዳ የጭቃ ጅራፉን ( ዘር ማንቋሽሹን ) ጀመረ በዚህ ዴሞክራሲና  እኩልነት ሞልቶ የተረፈባት አገር ውስጥ ለአመታት እንደኖረ እየነገረኝ ይህን አይነት ስብእናን ይሚነካ ስድብ ያዘንብብኝ ጀመረ  ስድቡንም በሁለት ከፍሎት አማራ እና WANT TO BE አማራ በማለት ፈርጆ  ከአለቆቹ የተማረውን ጸያፍ ስድብ ያለ ምንም እፍረት አዠጎደጎደው ሆኖም የሱን ያህል የዘቀጠ አስተሳስብ ስለሌለኝ የሱን ዘር በመስደብ አጸፋውን አልመለስኩም ይህም ስው አማኑኤል ስይፈ  ይባላል የእስታቫንገር ነዋሪ ሲሆን ስላምና እኩልነት የምትሹ የአገሬ ህዝብ ሁሉ ይህን ስው አምርረን ልንቃወመው ይገባል ፣፣
የድምጸ መረጃ እነሆ

Sunday, March 9, 2014

ትግሉን በእስራት እና በግድያ ማስቆም አይቻልም

ነፃነት እንፈልጋለን ያሉ ሴት እህቶች በአደባባይ ተቃውሞ ካሰሙ በኋላ 6ቱ ወዲያው ታሰሩ (የተቃውሞውን ቪድዮ ይዘናል)



ሰማያዊ ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ እና የድርጅት ጉዳይ ሃላፊው ከሴቶቹ ጋር በቁጥጥር ስር ውለዋል
የሰማያዊ ፓርቲ ወጣት ቡድን እንደዘገበው ዛሬ በተካሄደው የሴቶች 5ሺሜትር ሩጫ ላይ የሰማያዊ ፓርቲ የሰቶች ጉዳይ ባመቻቸው እድል የፓርቲው ሴቶች የሮጡ ሲሆን በሩጫውም ላይ የተለያዩ መፈክሮች ማለትም ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ትፈታ፤ አቡበከር ይፈታ፣ እስክንድር ይፈታ፣ አንዷአለም ይፈታ፣ ነፃነት እንፈልጋለን እና ሌሎች ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጥያቄዎች አሰምተዋል::
ከመነሻው የጀመረው የተቋውሞ ድምጽ እስከ ማብቂያው የቀጠለ ሲሆን ሩጫቸውን ጨርሰው ሊገቡ ሲሉ በፖሊሶች ተቆርጠው በአሁኑ ሰዐት ታስረው ይገኛሉ። በሩጫው ወቅት ተቋውሞ ሲያሰሙ የሚያሳይ ቪድዮ እና ፎቶ እንደደረሰን ምንለቅ መሆኑን በትህትና እንገልጻለን::
የሰማያዊ ፓርቲ የሴቶች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሴት አባላት እና ከእናርሱ ጋር የነበሩ ሴቶች በዛሬው እለት በተካሄደው ሩጫ ላይ ተሳትፈው ሃሳባቸውን በመግለጽ ላይ አንዳሉ በሩጫው መጨረሻ ላይ በፖሊስ ታፍሰው ወዳልታወቀ ቦታ ተወስደዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በአከባቢው የነበሩት የሰማያዊ ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ብርሃኑ እና የድርጅት ጉዳይ ሃላፊው አቶ ጌታነህ ሴቶቹ መታሰራቸው ምንም አግባብነት እና ህጋዊ መሰረት የለውም በማለታቸው ከሴቶቹ ጋር በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
የእስረኞች ስም ዝርዝር
1 ንግስት ወንድይፍራ(የህዝብ ግንኙነት ኮሚቴ)
2 ወይንሸት ሞላ (የምክርቤት አባል)
3 ወይኒ ንጉሴ(አባል)
4. እመቤት ግርማ(አባል)
5. ሜሮን አለማየሁ (አባል)
6. ምኞት መኮንን(አባል)
ለጊዜው የሴቶች ጉዳይ እና የህግ ጉዳይ ኮሚቴ የሆኑት ኢየሩስ ተስፋው እና ኤልሳ ወሰኔ ያሉበትን ልናውቅ አልቻልንም፡፡
ከነዚህ ሴቶች በተጨማሪም በቦታው የነበሩት የፓርቲው ህዝብ ግንኙነት አቶ ብርሀኑ ተ/ያሬድ ፤ የድርጅት ጉዳይ ሀላፊው አቶ ጌታነህ ባልቻ እና የህዝብ ግንኑነት ኮሚቴ አቶ አቤል ኤፍሬም ናቸው፡፡
እንዲሁም የሰማያዊ ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ አባል አቶ አቤል ኤፍሬም በአካባቢው ስለነበሩ ብቻ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ያሉበትን ለማጣራት የሰማያዊ ወጣት ክንፍ አባላት በእንቅስቃሴ ላይ መሆናችንን እያስታወቅን የደረስንበትን ይፋ የምናደርግ መሆኑን እናስታውቃለን፡
ትግሉን በእስራት እና በግድያ ማስቆም አይቻልም::

Monday, March 3, 2014

(ሰበር ዜና)

 አንድ ሰው ከተገደለ በኋላ ሹፌሮች ባደረጉት አድማ ከአዲስ አበባ ጅቡቲ የሚወስደው መንገድ ከተዘጋ 3 ቀን ሆነው


(ዘ-ሐበሻ) ከአዲስ አበባ ጅቡቲ የሚወስደው መንገድ ከተዘጋ 3 ቀን እንደሞላው በአካባቢው የከባድ ሹፌር አሽከርካሪዎች ለዘ-ሐበሻ ገለጹ። እነዚህ ሹፌሮች እንዳስታወቁት ይህ መንገድ የተዘጋው የከባድ መኪና ሹፌሮች ባደረጉት አድማ የተነሳ ነው።
ለዘ-ሐበሻ መረጃ ያቀበሉት ሹፌሮች እንደገለጹት ለከባድ መኪና አሽከርካሪዎቹ የሥራ ማቆም አድማ ምክንያት የሆነው አንድ ሹፌር ባልታወቁ ሰዎች ተገድሎ መንገድ ላይ በመገኘቱ የተነሳ ነው። በገዋኔ አካባቢ ይህ መንገድ እንደተዘጋ የገለጹት ሾፌሮቹ መንገዱ በመዘጋቱ የተነሳ የቆሙት መኪኖች ብዛት በኪሎ ሜትር እንደሚቆጠር አስታውቀዋል።
የስራ ማቆም አድማ ያደረጉት እነዚሁ ሹፌሮች ጥያቄያቸው የደህነንት ዋስትና እንደሆነ የገለጹት ምንጮቹ በአሁኑ ወቅት በፖሊስ ተከበው እንደሚገኙ የደረሰን መረጃ አመልክቷል።