ቀደም ካለው ከሴቶች ተሳትፎ በመነሳት አውን እስካለንበት ጊዜ እንስቶች በፖለቲካው ያላቸውን ትልቅ ሚና ላነሳ ወዳለው።
በሁሉም የማህበራዊ ህይወት ዘርፎች ውስጥ የኢትዮጵያ ሴቶች የሚጫወቱት ጉልህ እና ወሳኝ ሚና ያላቸው ቢሆንም ሃገሪቱ ባላት ባህል፣ ታሪክ፣ እና ፖለቲካዊ ስርአት ምክንያት በሁለንተናዊ ማህበረሰብ እድገት ያደረጉት አስተዋጽኦ ተገቢውን ትኩረትና እውቅና አላገኘም። በዚህ ማህበረሰብ ውስጥ ያሉ አግላይ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ እና ማህበረሰባዊ ህግና ደንቦች ምክንያት ሴቶች የልፋታቸውን ውጤት ሳያገኙ ቆይተዋል። እንደሚታወቀው ሴቶች የዓለማችን ግማሽ አካል እንደመሆናቸው መጠን ተገቢውን ስፍራ ሳይሰጣቸው ነገር ግን በዘልማድ በማህበርሰቡ ውስጥ ሴቶች በዓገር፣ በእናት፣በሚስት ይመሰላሉ። እንዲሁም አንዳንድ ጊዜ ከታዋቂ ወንድ በስተጀርባ ጠንካራ ሴት እንዳለች ቢነገርም በማህበረሰብ ውስጥ ያላቸውን ተገቢ ቦታ እና እውቅና አልተስጣቸውም። ቀደም ባሉ ጊዜያት ሴትልጅ ከቤት ስትወጣ ነውር በሆነበት ወቅት አጠቃላይ የቤት ውስጥ ስራ ሃላፊነት በተለይም ለወንዶች ምግብ አዘጋጅቶ የመጠበቅ ግዴታ የሷ ሲሆን፣ከማጀት ስራዋ በተጓዳኝ ዓገር ተረካቢ ዜጋን የመንከባከብ እና የማሳደግ ጫናው የዚችው የምስኪኗ ሴት ሓላፊነት ነበር ።
በኢትዬጽያ ውስጥ የፖለቲካና ሲቪክ መብቶች ከሆኑት ውስጥ የመናገር፣ የመጻፍ፣ እና በአጠቃላይ ሃሳብን በነጻነት የመግለጸ መብት በሌለበትና በተገደበበት ሁኔታ ገዢው መንግስት መስማት የሚፈልገውን ብቻ መናገር እና መጻፍ ግዴታ በሆነበት ቦታ ላይ መስዋእትነት የሚከፍሉ ሴቶች ቁጥር ከፍተኛ ነው። ለዓገራቸው፣ ለወገኖቻቸው እና ለነጻነታቸው በመቆም አምባገነናዊ ስርአትን በመታገል የበኩላቸውን አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ ይገኛሉ ። ለህዝብ ደህንነትና መብት ደንታቢስ የሆነው በስልጣን ላይ የሚገኘው ይህ ክፉ መንግስት ሴቶች እህቶቻችን እና ወገኖቻችን በነጻነት በመናገራችው፣በመጻፋቸው ፣በዴሞክራሲያዊ መንገድ በመቃወማቸው እና የሚፈልጉትን ፓርቲ በመምረጣችው ብቻ አሸባሪ በማለት እስር ቤት በማጎር ይገኛል።
ከነዚህ ጉልህ ሚና ከሚጨወቱ ሴቶች እህቶቻችን መካከል በሰብአዊ መብት ተሟጋችነት እና በጋዜጠኝነት እንዲሁም በግለሰብም ሆነ በድርጅት ደረጃ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙትን እንስቶች እንዳሉ እና ከነዚህም መካከል እንደ ነብርቱካን ሜዴቅሳ እና እንደ ሪዖት አለሙ ወ.ዘ.ተ ያሉ ለኛ ትልቅ ምሳሌ የሚሆኑን ጀግና ሴቶች ናቸው ።
የጀግኖቻችንን ምሳሌ በመከተል የአለም አቀፍ ሴቶች ቀን ማርች 8 በተከበረ ማግስት በአዲስ አበባ በተደረገ የሩጫ ውድ ድር ከተሳተፉ ሴቶች መካከል አጋጣሚውን በመጠቀም በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ እና በማህበራዊ ኑሮ የ ሚደርስባቸውን አፈና እና ጭቆና በማሰማት መብታቸውን ለማስከበር ጠንካራ ቋም እንዳላቸው ያሳዩበት አጋጣሚ ነበር። ይህም ክስተት ሴቶች እህቶቻችን ልክ እንደ ቀድሞው አሁንም የወገኖቻችንን ድምጽ ማፈን እና ማሰቃየት የለት ልማዱ ያደረገውን የወያኔ መንግስት የሚያደርስባቸውን ከባድ ጫና ወደጎን በማድረድ ድምጻቸውን ከማሰማት እና ችግሮቻቸውን ከማሳወቅ ወደዋላ ሳይሉ ከፊታቸው የተደቀነ መሳሪያና የሚደርስባቸውን እስር ሳያስፈራቸው አምባገነናዊ ስርዓቱ እያደረሰባቸው ያለውን ጭቆና በተቃውሞ ገልጸዋል።
ሴቶች ለዓገረቸው በፖለቲካው ዘርፍ ከፍተኛ ሚና በሚጫወቱበት በዚህ ወቅት አበረታች እና ተስፋ የሚጣልባቸው አዲስ ጀግና እና ለመብታቸው ተሟጋች ትውልዶች እየመጡ እንዳሉ በተግባር እያየን ነው። ከጎናቸው በመቆም የህቶቻችን ድምጽ እንዲሰማ አስተዋጽዖ በማድረግ ያሉበትን ስቃይ እና መከራ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ በማሰማት በወያኔ መንግስት ላይ ውግዘትና ውርደት ማድረስ ተገቢ ነው። ዓገራችን ካለችበት ከባድ ችግር ለማውጣት አንዱ እና ዋንኛው የሴቶች ተሳትፎ እንደመሆኑ መጠን ያላቸውን የመስራት ትልቅ ችሎታ ግምት ውስጥ በማስገባት ለዓገራቸው ነጻነት የሚያደርጉትን ተሳተፎ በመደገፍ ዓገራችን ካለችበት ስቃይ እንታደጋት።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር ..!!
No comments:
Post a Comment