Monday, August 4, 2014

ኃይለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ ሌሎች የአፍሪካ መሪዎች አሜሪካ ከመግባታቸው በፊት የኢቦላ ቫይረስ እንደሚመረመሩ ተገለጸ

 ሰሜን አሜሪካ ከነገ ጀምሮ በሚደረገው ትልቅ ስብሰባ ላይ የሚሳተፉ ኃይለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ የአፍሪካ መሪዎች ስብሰባው ውስጥ ከመግባታቸው አስቀድሞ ከኢቦላ ቫይረስ ነፃ መሆናቸውን ምርመራ እንደሚያደርጉ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ አስታወቁ።

Ethiopian Prime Minister Hailemariam Desalegn speaks during an interview with Reuters inside his office in the capital Addis Ababa
ከ729 ሰዎች በላይን የገደለውና በርካቶችን በቫይረሱ ተጠቂ ያደረገው ኢቦላ በአሁኑ ወቅት የታማሚዎች ቁጥር ከ 1 ሺህ 200 በላይ እንደሚሆንና ቫይረሱም ከአገራቱ አልፎ በስፋት በመሰራጨት የአህጉሪቷ ብሎም የዓለም ስጋት ሊሆን እንደሚችል ባለሙያዎች የሰጡትን አስተያየት በመጥቀስ ሲኤን ኤን መዘገቡ አይዘነጋም።
በጊኒ፣ በሴራሊዮን እና ላይቤሪያ በርካቶችን እየፈጀ ያለውና የአፍሪካም ትልቁ ስጋት እንደሆነ የሚነገርለት ይኸው በሽታ ወደ ስሜን አሜሪካ እንዳይሰራጭ መንግስታቸው በሰፊው እየሰራ እንደሚገኝ ያስታወቁት ባራክ ኦባማ ይህ ለ3 ቀናት በዋሽንግተን ዲሲ የሚደረገው በዚህ ትልቅ ስብሰባ ላይ ከ50 በላይ የአፍሪካ መሪዎች የሚገኙ ሲሆን ሁሉም የኢቦላ ምርመራ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።

ይህ ሰሚት (ስብሰባ) ነገ ኦገስት 4 ተከፍቶ ኦገስት 6 ቀን 2014 ዓ.ም ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሲዲሲ የተባለው የአሜሪካ የጤና ተቋም ባለፈው ሰኞ በሰጠው መግለጫ፣ በአገሪቱ ይህ ነው የሚባል የኢቦላ ወረርሽኝ ስጋት እንደሌለ አረጋግጧል፡፡ ይህም ሆኖ ግን በሽታው አደገኛ በመሆኑ መጠንቀቅ ይበጃል ብሏል ተቋሙ፡፡ በሽታው ከተከሰተባቸው የአፍሪካ አገራት የሚመጡ መንገደኞችን ወደ አሜሪካ አለማስገባት ሁነኛ መከላከያ መላ ነው ይላሉ- የሲዲሲ ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት ዶ/ር ማርቲ ሴትሮን፡፡ በቅርቡ ከእነዚያ አገራት የመጡና የኢቦላ ምልክቶች የተሰሟቸው ሰዎችም፣ ዛሬ ነገ ሳይሉ በአፋጣኝ ወደ ህክምና መሄድ እንደሚኖርባቸው ዶክተሩ መክረዋል፡፡ በአገራቱ የሚኖሩ ዜጎችም፣ የበሽታውን መተላለፊያ መንገዶች ጠንቅቀው በመረዳት ራሳቸውን እንዲጠብቁ ተናግረዋል፡፡
  • 532
     
    EmailShare
(ዘ-ሐበሻ)

No comments:

Post a Comment