Saturday, August 2, 2014

በዋሽንግተን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሊኢ ህ አ ዴ ግ ባለስልጣናት አንመችም አሉ..


non_pulsating_econ_caption

ይቺ አባባል ራሷ ቀላል ተመቸችኝ እንዴ፤ ትላንት በዋሽንግተን ዲሲ በአንዱ ምግብ ቤት ደረታቸውን ነፍተው ሊበሉ ሊጠጡ ተከስተው የነበሩት የንግድ ሚኒስትሩ አቶ ከበደ ጫኔ አንዳች ጫን ያለ ነገር ገጥሟቸው፤ ሳይበሉ ሳይጠጡ ጎንበስ ብለው እንደወጡ ተሰማ፤
ባለስልጣኑ የገጠማቸው ነገር ሳይወዱ በግዳቸው ልክ ልካቸውን መስማት ሲሆን፤ ይህንን ያደረጉ የዲሲ ወጣቶች የ ኢ ህ አ ዴ ግ ባለስልጣናት በተገኙበት ቦታ ሁሉ፤ በህዝብ ምግብ ቤትም ይሁን በህዝብ መጽዳጃ ቦታ እየጠበቁ ልክ ልካቸውን መንገር እና የሁላችንም ሃላፊነት ነው ሲሉ ይናገራሉ።
ይህንን ማድረግ ፋይዳው ምንድነው… ሲል እሳት የላሰው የኢሳት ጋዜጠኛ መሳይ ከበደ በጠየቃቸው ጊዜም፤ ”እነርሱ በኢትዮጵያ ላሉ ወንድሞቻችን አልመች እንዳሉ ሁሉ እኛም እንርሱን ምቾት መንሳት ዋናው አላማችን ነው” ሲሉ መልሰውለታል።
የኢ ህ አ ዴ ግ ባለስልጣናት ባለፈው ጊዜ በአቶ መልስ ላይ የደረሰውን ነገር ረስተውታል መሰለኝ ሰኞ በአሜሪካ ዋሽንግተን ለአንዳች ስብሰባ ልዑካን ልከዋል አሉ። ዘንድሮ ደግሞ ማን ደንግጦ ሊሞት ይሆን እያልን እየተጨነቅን ባለበት በዚህ ሰዓት የዲሲ ወጣቶች ለባልስልጣኖቹ ኮረኮንች መንገድ ሆነው አልመች ብለዋቸዋል። (ባለስልጣኖቹም ምን አለኝ ኮብል ስቶኔ… እያሉ መስሪያ ቤታቸውን እና መሳሪያ ታጣቂዎቻቸውን እየናፈቁ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው)
በዚህ አጋጣሚ ሰኞ በዋሽንግተን እና አካባቢዋ ይሚገኙ ኢትዮጵያውያን ባለስልጣኖቹ ላይ የተቃውሞ ቁጣቸውን ለማሰማት ተቀጣጥረዋል። ባለስልጣኖቻችን እንግዲህ ቆፍጠን ነው! ብለን እንምከር ወይስ ይቻሉት…! ?

No comments:

Post a Comment