Tuesday, June 30, 2015

ግብረሰዶም እና መፅሃፍ ቅዱስ (ከTeaching of EOTC የፌስቡክ ገፅ የተወሰደ)

“ጥበበኞች ነን ሲሉ ደንቆሮ ሆኑ” ሮሜ. 1÷22
በዚህ ዘመን ግብረ ሰዶማዊነት እንደ ጥሩ ነገር እየታየ በመምጣቱ ጠዋትና ማታ በተለያዩ ማስ ሚዲያዎች፣ ድረ ገጾች፣ ፊልሞች፣ ጋዜጦች እና መጽሔቶች ይቀነቀናል፤ ይሰበካልም፡፡ አንዳንዶችም ከሰው ልጅ ሥልጣኔ ጋር አብሮ የመጣ አድርገው ሲመለከቱት እና ሲያናፍሱት እናስተውላለን፡፡
በሰለጠነው ዓለም በወንድና በወንድ መካከል ያለው የግብረ ሰዶማዊ ግንኙነት (Gays) በሴትና በሴት መካከል ያለው የግብረ ሰዶማዊ ግንኙነት (Lesbians) እንደ ጥሩ ነገር እየታየ መምጣቱ ብቻ ሳይሆን ሕጋዊነት እያገኘ መጥቷል፡፡ በርካታ ሀገሮች የወንድ ለወንድ እና የሴት ለሴት ጋብቻን ከፈቀዱ ሰንብተዋል፤ በሒደት ላይ ያሉም ብዙ ናቸው፡፡ በአሜሪካና በአውሮፓ የሚገኙ አንዳንድ የእምነት ተቋማትም/ፕሮቴስታንት እና ካቶሊክ ድርጅቶች/ ከመሪዎቻቸው ጀምሮ በዚህ ግብረ ሰዶማዊ ግብር ስለቆሸሹ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ግብረ ሰዶማዊነትን ደግፈው ሲሰብኲ እንዲሁም ወንድ ለወንድ ሲያጋቡ ታዝበናል፡፡ ይህ አስደንጋጭ እና አሳፋሪ ክስተት ብዙዎቻችንን ሊያስደነግጠን ቢችልም መጽሐፍ ቅዱስ ግብረ ሰዶማዊነት ዛሬ የተጀመረ ክፉ ግብር ሳይሆን ጥንትም የነበረ ብዙዎችን ያረከሰ ነውር እና አስጸያፊ ተግባር መሆኑን ይመሰክራል፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ፡- የመጽሐፍ ቅዱስ የመጀመሪያ መጽሐፍ በሆነው በኦሪት ዘፍጥረት መጽሐፍ ስለ ግብረ ሰዶማዊነት ይናገራል፡፡ የሰዶምና የገሞራ ሰዎች ግብረ ሰዶማውያን ነበሩ፡፡ ሰዶምና ገሞራ በዮርዳኖስ ሸለቆ የተቆረቆሩ ከተሞች ነበሩ፡፡ በእነዚህ ሁለት ከተሞች ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ግብረ ሰዶማውያን ማለትም ወንድ ከወንድ፣ ሴት ከሴት ጋር ዝሙት የሚያደርጒ ይህ ኃጢአትም በእነርሱ ይበዛ ስለነበር ስያሜው የቦታውን ስም በመያዝ ግብረ ሰዶም ተባለ፡፡ በዘመናት ሁሉ ይህን ኃጢአት የሚሠሩ መጠሪያ ሆኖ አገለገለ፡፡ ዛሬም በግብር የሚመስሉአቸው ሰዎች ግብረ ሰዶማዊ ወይም ሰዶማውያን እየተባሉ ይጠሩበታል፡፡ የሰዶምና የገሞራ ሰዎች ወንድ ከወንድ፣ ሴት ከሴት ጋር የሚፈጽሙት ዝሙት አጸያፊ ስለነበር እግዚአብሔር ሊያጠፋቸው ወሰነ፡፡ (ዘፍ. 18÷20፣ ዘፍ.19÷5-9)፡፡ ሁለት መላእክትን ወደ ሰዶም ላከ፡፡ ሁለቱ መላእ ክት የእግዚአብሔር ሰው እና ከሰዶማዊነት ግብር ንጹሕ የነበረውን ሎጥን ከከተማው እንዲወጡ ካደረጉ በኋላ እግዚአብሔር ሰዶምንና ገሞራን በእሳትና በዲን አጠፋ፡፡ (ዘፍ.19÷10-26) ሰዶምና ገሞራ አሁን በጨው ባሕር እንደተሸፈኑ የሥነ ምድር ተመራማሪዎች ይናገራሉ፡፡
በመጽሐፍ ቅዱስ ሰዶምና ገሞራ የክፋት ሁሉ የፍርድም ምሳሌ በመሆን ተጠቅሰዋል፡፡ (ኢሳ. 1÷9-10፣ ኢሳ. 3÷9፣ ኤር. 23÷14፣ ሰ.ኤ.4÷6፡፣ ሕዝ. 16፡46፣ ማቴ.10÷15፣ ራእ. 11÷8)
ሰዶማዊነት ነውር ነው፡-
መጽሐፍ ቅዱስ ግብረ ሰዶማዊነት ነውር እና አጸያፊ እንደሆነ ይመሰክራል፡፡ ነውር የሆነበትም ምክንያት ይህ ነው፡፡
ሀ. እግዚአብሔር የመሠረተውን የጋብቻ ሥርዓት ማለትም አንድ ወንድ ለአንዲት ሴት የሚለውን ሕግ የሚያፈርስ በመሆኑ፤
ለ. በሁለት ተቃራኒ ጾታ ማለትም በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል የሚደረገውን ተፈጥሮአዊ የግብረ ሥጋ ግንኙነት/መሳሳብ/ የሚያቆሽሽ አዲስ ልምድ ስለሆነ፤
ሐ. የሰው ልጅ ዘሩን የመተካት ከፊጣሪ የተሰጠውን መብቱን የሚገፋ (የሚያሳጣ) ተግባር በመሆኑ፤
መ. ሰዶማዊነት በአንድ ወንድ ወይም በአንዲት ሴት ብቻ የሚቆም ግብር ስላልሆነ፤ ወንዱ ብዙ ወንዶችን ሴቷ ብዙ ሴቶችን ሲለምዱ ለተለያዩ በሸታዎች ስለሚያጋልጥ፤
ሠ. ሰዎች ስለ ፍቅር ትክክለኛ ሥእል እንዳይኖራቸው እና በስሜት የሚነዱ ራስ ወዳዶች እና ሓላፊነት የማይሰማቸው ዜጎችን ስለሚፈጥር፤
ረ. የተለያዩ አካላዊ፣ ሥነ ልቡናዊ እና መንፈሳዊ ክስተቶችን ስለሚያስከትል በእግዚአብሔር የተናቀ እንዲሁም የተጠላ ግብር ነው፡፡ከተፈጥሮ ሥርዓትና ሕግ ውጪ በመሆኑ በኅብረተሰቡም ዘንድ ተቀባይነት የሌለው ማኅበራዊ መገለልን የሚያስከትል ክፉ ተግባር ነው፡፡ይህ ክፉ ግብር ወንድ ከወንድ ሴት ከሴት ጋር ብቻ ሳይሆን ከእንስሳትም ጋር ግንኙነትእንዲፈጽሙ በር የሚከፍት ነውረኛ ሕይወት ነው፡፡
“ማናቸውም ሰው ከሴት ጋር እንደሚተኛ ከወንድ ጋር ቢተኛ ሁለቱ ጸያፍ ነገር አድርገዋል፤ ፈጽመው ይገደሉ፤ ደማቸው በላያቸው ነው፡፡” (ዘሌ. 30÷13)
“የሰዶም ሰዎች ግን ክፉዎችና በእግዚአብሔር ፊት እጅግ ኃጢአተኞች ነበሩ፡፡” (ዘፍ. 13÷13)
“እንዲሁም እንደ እነርሱ ዝሙትን ያደረጒና ሌላን ሥጋ የተከተሉ ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸው የነበሩ ከተማዎችም በዘላለም እሳት እየተቀጡ ምሳሌ ሆነዋል፡፡” (ይሁዳ. ቁ. 7)
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም በሮሜና በቆሮንቶስ መልእክቱ ግብረ ሰዶማዊነትን “እስነዋሪ”፣ “ለባሕርይ የማይገባ”፣ እንዲሁም “ከተፈጥሮ ሕግና ሥርዓት ውጪ” እንደሆነ አጽንኦት ሰጥቶ ያስተምራል፡፡ በዚህ ሰዶማዊ ግብር ኃጢአት የሠሩት ወንዶች ብቻ ሳይሆኑ ሴቶችም እንደሆኑ ይናገራል፡፡
“ . . . ስለዚህ እርስ በርሳቸው ሥጋቸውን ሊያዋርድ እግዚአብሔር በልባቸው ፍትወት ወደ ርኲስነት አሳልፎ ሰጣቸው . . ሴቶቻቸውም ለባሕርያቸው የሚገባውን ሥራ ለባሕርያቸው በማይገባው ለወጡ፤ እንዲሁም ወንዶች ደግሞ ለባሕርያቸው የሚገባውን ሴቶች መገናኘት ትተው እርስ በርሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ፤ ወንዶችም በወንዶች ነውር አድርገው በስሕተታቸው የሚገባውን ብድራት በራሳቸው ተቀበሉ፡፡” (ሮሜ. 1÷24-27)
“. . . ወይስ ዓመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንዳይወርሱ አታውቁምን አትሳቱ ሴሰኞች ቢሆኑ ወይም ጣኦትን የሚያመልኲ ወይም አመንዝሮች ወይም ቀላጮች ወይም ከወንድ ጋር ዝሙት የሚያደርጒ . . . የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም፡፡” (ቆሮ. 6÷9-10)
ወጣቶች “ቀላጭ” ማለት ወንዳገረድ ለጾታው የማይገባ ዝሙትን ለመፈጸም እንደ ሴት ሆኖና ከወንድ ዘርን የሚቀበል ማለት ነው፡፡ እንደዚሁም ሴት ከወንዳ ወንድ ሴት ጋር ዝሙት ስትፈጽም ‹‹ቀላጭ›› ትባላለች፡፡
ማጠቃለያ፡-
ወንድሞችና እህቶች ግብረ ሰዶማዊነት በእግዚአብሔር የተጠላ ክፉ ግብር መሆኑን ተገንዝባችሁ ራሳችሁን ከዚህ ክፉ ተግባር ጠብቁ፡፡ ብዙ ንጹሐን ሰዎች በእነዚህ ክፉ ሰዎች እንዳይበላሹና ሰዶማውያን እንዳይሆኑ እውነታውን ማስተማር ግንዛቤ መፍጠር የሁላችሁም ሓላፊነት መሆኑን አንዘንጋ፡፡እንዲሁም በዚህ ህይወት ያሉትን ሰዎች በተቻለን መጠን መክረን ከዚህ ህይወት እንዲወጡ መፀለይ ያስፈልገናል እንዲሁም እዚህ ህይወት ውስጥ ያሉትን ሰዎች እግዚአብሔር መሀሪ እና ይቅር ባይ ፍቅር መሆኑን አምነው በንስሀ እንዲመለሱ ጥረት እናድርግ ፡፡እግዚአብሔር አምላካችን አገራችንን ቤተክርስቲያናችንን አለማችንን ከዚህ ክፉ መንፈስ ይጠብቅልን ከአለማችን ይህንን ክፉ መንፈስ ያጥፋልን አሜን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፡-
1.ግብረ ሰዶማዊነት እና የሴቶች ክህነት/ብፁ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የቀድሞ ፓትርያሪክ እንደፃፉት ትርጉም ታደለ ፋንታ/ዲ/ን/
2. አባ ሳሙኤል ሰዶማውያንና የኃጢአት ደሞዝ (1998) ዓ.ም አዲስ አበባ፡፡እና ሁለተኛ እትም
3.የተለያዩ ድህረ ገፆች

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!!!

Saturday, May 16, 2015

በስቶክሆልም በሊቢያ ሕይወታቸውን ያጡ ኢትዮጵያውያን በደመቀ ሁኔታ ታስበው ዋሉ




ንኤል ሐረር ለዘ-ሐበሻ ከስዊድን እንደዘገበው:- 
ትላንት ሐሙስ ግንቦት 6/2007 በምስራቅ አፍሪካ እና አውሮፓ አህጉረ ስብከት የመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ እስቶኮልም ሆተርየት ባዘጋጀው የ21ኛው ክፍለ ዘመን ድንቅ የእግዚአብሔር ምስክሮች ለሆኑት 30 (ሰላሳ ) የኦርቶዶክስ ልጆች መታሰቢያ ፕሮግራም በዕለቱ ከተገኙ የግብፅ የሶርያ ብጹአን አባቶች ጋር በደማቅ ሁኔታ ታሥቦ ውሏል፡፡ 

በዕለቱ የኤርትራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ካህንና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ካህናት ተገኝተዋል። እንዲሁም በስቶኮልም ባሉ አብያተ ክርስቲያናት ስንበት ት/ቤት ተማሪዎች የህብረት መዝሙረና በወቅቱ የነበረውን የሰማዕታቱን ጽናት የሚያሳይ ትዕይንት ፤የአበባ ማስቀመጥ እና የጧፍ ማብራት ፕሮግራሞ ተካሂዷል። 

Sunday, March 1, 2015

ሰበር ዜና: የወያኔ ሰላይ ከሆላንድ ተባረረ!

ሂሩት መለሰ – ከሮተርዳም
ሮተርዳም፣ ጥቅምት 28 ቀን 2015 – በስደት ስሙ አለማየሁ ስንታየው በመባል የሚታወቀው የህወሃት ሰላይ ከኔዘርላንድስ ተባረረ። አለማየሁ ስንታየሁ ቋሚ ነዋሪ ከነበረበት ከኔዘርላንድስ እንዲባረር የተደረገው በዚያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በከፈቱበት የስለላ ክስ መሆኑም ታውቋል።
የሮተርዳም ከተማ ፍርድ ቤት በአለማየሁ ላይ የተመሰረተውን የስለላ ክስና ማስራጃ ለረጅም ጊዜ ሲመረምር ከቆየ በኋላ የግለሰቡ የመኖርያ ፈቃድ እና ቤት እንዲነጠቅ፣ የሆላንድን ምድርም በአስቸኳይ ለቆ እንዲወጣ ውሳኔ አስተላልፏል። ከሆላንድ የምመራ ቡድን እንደተረዳነው ከሆነ – የግለሰቡ ቤት ሲፈተሽ ወያኔ የሰጠው እውነተኛ መታወቂያ እና በርካታ የስለላ ሰነዶች ተገኝተውበታል። በእርዳታ ስም የተቋቋመለት ድርጅትም ተፈትሾ ማስረጃዎች እንደተገኙ ለማወቅ ተችሏል።

ይህ ሰው ትክክለኛ ስሙ ዘለቀ ፎላ ይባላል። በደርግ ጊዜ የኢትዮጵያ ሰራዊት አባል ሆኖ ለረጅም አመታት አገልግሏል። ወያኔ ስልጣን ሲቆጣጠር ለፖለቲካ ተሃድሶ አዋሳ ደቡብ ጦር ቅጥር ግቢ ተላከ። በተሃድሶ በነበረበት ጊዜ ቁጥራቸው ብዙ የሆኑ የሰራዊቱ አባላትን ለወያኔ በማጋለጥ ታማኝነቱን ሲያሳይ እንደነበር የዚህ ዜና ዘጋቢ እማኝ ነው። የበርካታ ኢትዮጵያውያን ደም በእጁ ያለው አለማየሁ ከተሃድሶው ከወጣ በኋላ እስራኤል ገደቡ (የፓልቶክ ስሙ ኢዛና) ከተባለ ወታደር ጋር በመሆን የሰላም ተጓዥ ነኝ ብሎ በመገናኛ ብዙሃን ሲታይ ነበር። አለማየሁ እና ኢዛና በየሃገሩ እየዞሩ ስለ አዲሱ ስርዓት መልካምነት ሲሰብኩ ከረሙ። ከዚያም አስመራ ድረስ ተልከው የሻእቢያውን መሪ ኢሳያስ አፈወርቂን በወታደሩ ስም ይቅርታ ጠይቀዋል።

አለማየሁ እና ኢዛና ለወያኔ በሰሩት ውለታ ሆላንድ ገብተው እንዲቀሩ ተደረገ። ይህም የተደረገበት ምክንያት በአውሮፓ የሚኖሩ ኢዮጵያውያንን ተቃዋሚ በመምሰልና በረቀቀ መንገድ እንዲያበጣብጡና እንዲሰልሉ ነው።
በሆላንድ ሃገር የፖለቲካ ጥገኝነት ጠይቆ ለወያኔ ቡድን የስለላ ስራ መስራት ወንጀል ነው። አለማየሁ የሆላንድ ዜግነት ቢኖረው ኖሮ ቅጣቱ የከፋ ይሆን እንደነበር ጉዳዩን እየተከታተሉ ያሉ የህግ ባለሙያዎች ተናግረዋል።


የአለማየሁ መባረር በተሰማ ግዜ በሮተርዳም ያሉ የህወሃት ደጋፊዎች የአቤቱታ ደብዳቤ በመጻፍ ፊርማ ማሰባሰብ ቢጀምሩም ሊሳካላቸው አልቻለም። የአቤቱታ ደብዳቤው ግለሰቡ እዚህ የተወለዱ ሁለት ለጆቹን እየመጣ እንዲጎበኝ ይፈቀድለት የሚል ነበር።
አለማየሁ ስንታየሁ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከሆላንድ ተባረረ። ኢዛና ግን አሁን የተቃዋሚ ጭንብሉን አውልቆ በግልጽ ወያኔ መሆኑን መናገር ጀምሯል።


ኢዛና የሆላንድ ዜግነት ቢኖረውም በሆላንድ ሃገር ስራ ሰርቶ አያውቅም። የቀንና ማታ ስራው በፓልቶክ ላይ ነው። ባለፈው ወር ኢትዮጵያ የተጓዙ ዲያስፖራ ኢንቨስተሮችን እየመራ በቴሌቭዥን መግለጫ ሲሰጥ አይተነዋል። ይህ ትርኢት የወያኔ ኢንቨስተሮች በጨበጣ እንደሚንቀሳቀሱም ያሳየናል።

Thursday, February 26, 2015

ከአንድነት ሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ማህበርና ከሰማያዊ ሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ማህበር የተሰጠ የጋራ መግለጫ


  • 203
     
    Share
ANAASO Blueእንደሚታወቀው የኢህአዴግ አገዛዝ ከጊዜ ወደ ጊዜ ጸረ ዲሞክራሲ አካሄዱ እየባሰበት የመጣና መሠረታዊ መብቶችን ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ ማፈኑን አጠናክሮ ቀጥሎበታል፡፡ በቅርቡ በአንድነትና በመኢአድ ፓርቲ ላይ አገዛዙ በሚያዝዛቸው የተቋማት ኃላፊዎች ቀጭን ትዕዛዝ የፓርቲዎቹ ሕልውና ለጥቂት ግለሰቦች ተላልፎ ተሰጥቷል፡፡ ይህ ዓይነቱ ህገ-ወጥ ድርጊት መቼዉም ቢሆን ተቀባይነት አይኖረውም! ለአገራችን የሠላማዊ የስልጣን ሽግግር ከባድ መሠናክል ሊሆን እንደሚችል ሁሉም ይገነዘባል ብለን እናምናለን፡፡ የኢህአዴግ የምርጫ ቦርድ እንዲህ ዓይነቱን ክፉ ስራ ሲወስን የአገራችንን የረጅም ሠላም አይተው ሣይሆን በአገዛዙ ቁንጮ ሰዎች በመታዘዝ በተቋም ስም የሚሠሩት የማደናገር የድንቁርና ተግባራቸዉ አንድ አካል ነው ብለን እናምናለን፡፡ ማህበራችን ይህን ድርጊት እጅጉን ያወግዛል። በመሆኑም ድርጊቱን በጋራ እንቃወማለን።
በምርጫ ቦርድ ስም የተወሰነው ህገ-ወጥ ውሣኔ ምክንያት መላ የአንድነትና የመኢአድ አባላት የፖለቲካ እንቅስቃሴአቸው ተገድቧል፡፡ ይሁን እንጂ ለአገራቸው ካላቸው ፅኑ ፍቅር አኳያ ትግሉን ለማስቀጠል ከሠማያዊ ፓርቲ ጋር አብሮ ለመሥራት የአባልነት ፎርም በመሙላት ትግሉን ቀጥለዋል፡፡ ይህ ዓይነቱ የአባላት ቆራጥ ውሣኔ ሊበረታታና ሞራል ሊሰጠው የሚገባ ነው ብለን እናምናለን! እኛም በሰሜን አሜሪካ የምንገኝ የሁለቱ የድጋፍ ማህበራት ሙሉ በሙሉ ድጋፋችንን እንደምንሰጥ እናረጋግጣለን፡፡
ስለሆነም በሰሜን አሜሪካ የምንገኝ የአንድነትና የሠማያዊ የድጋፍ ማህበራት በጋራ በኮሜቴ ደረጃ ተዋቅረን በዋና ዋና ጉዳዬች ላይ ማለትም በፋይናንስ፤ በእስረኞች ጉዳይ እና በዲኘሎማሲው ዙሪያ ሙሉ በሙሉ በትብብር አብረን እየሠራን የሰማያዊ ፓርቲንና ሌሎች በሃገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ሃይሎችን በጋራ ድጋፍ ለመስጠት ውሣኔ አሣልፈናል፡፡ በቀጣይም በጋራ የኮሚቴ ውይይቶችን እያደረግን ለሰማያዊ ፓርቲ የሚያስፈልጉ የሞራልና የማቴሪያል ርዳታ እንደምንሰጥ እናረጋግጣለን፡፡
የሰማያዊና የአንድነት ሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ማህበራት
የካቲት 19 2007 ዓ/ም
- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/39330#sthash.Jbph1yVo.dpuf

ESAT

http://ethsat.com/video/esat-daily-news-amsterdam-february-26-2015-ethiopia/#