Friday, May 30, 2014
Thursday, May 22, 2014
በኖርዌ ዓገር በታላቋ ስታቫንገር ከተማ ምን ሊከናወን እንደሆነ ማወቅ ይፈልጋሉ ??
ከታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጫን የታቀደውን ልዩ ዝግጅት ይመልከቱ..!!
https://www.youtube.com/watch?v=d_OxYYabjUY&feature=youtu.be

Tuesday, May 20, 2014
Democratic change in Ethiopia support organization in Norway proudly announce to all Ethiopians and supports that our radio station soon be on air.
Democratic change
in Ethiopia support organization in Norway strongly believe in the
existence of free media which is one of the building blocks of
democratic system unfortunately the ruling party in Ethiopia crackdown
all free media institutions and surpassed freedom of expression for over
two decades.
Our organization relentlessly condemn this inhuman regime ever since our establishment and one of our primary goal is to work with any legitimate organization with the agenda of change the current regime to embark our country to a democratic and peaceful state , on anther hand to help and facilitate the struggle for freedom implying vital instruments , as a result we are proud to announce the establishment of our new radio service via internet in order to reduce the absence of free media in Ethiopia and we aim to intensify our struggles to build democratic system in Ethiopia under which freedom and justice are guaranteed .
Our radio station starts its first broadcast system test on 24th of May 2014 from 1pm till 3pm through our internet radio services dceson.listen2myradio.com/ to all of our esteemed audiences here in Norway and all over the world.
Our services are accessible everywhere the internet is available. We work alongside with all freedom loving citizens and organizations to get our voice heard as well as to reach out our supporters and members about organizational, local and international activities.
Victory to the people of Ethiopia.

Tuesday, May 13, 2014
የሃይለመድህን አበራን ወደ ኢትዮጵያ ለማስመለስ......
/ር ሼክስፒር ፈይሳ የሃይለመድህን አበራን ጉዳይ ለመከታተል ወደ ጄኔቫ አመራ
May 13, 2014
13 may 2014 (EMF ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራን ጉዳይ ለመከታተል ኢትዮጵያዊው የህግ ባለሞያ ዶ/ር ሼክስፒር ፈይሳ ባለፈው ሳምንት ወደ ጄኔቭ-ስዊዘርላንድ ተጉዟል።
ሼክስፒር ፈይሳ የረዳት ፓይለቱን ጉዳይ ከሚኖርበት ከሲያትል ከተማ በቅርብ ሲከታተል ቆይቶ ነው ወደ ጄኔቭ ያመራው። ጄኔቭ እንደደረሰም የሃይለመድህን አበራን ጠበቃና ጉዳዩን ከሚከታተሉ አካላት ጋር በስፋት ተወያይቷል። በተለይ ከረዳት ፓይለቱ ጠበቃ ጋር ረጅም ሰዓታት በመውሰድ በበርካታ የህግና የቴክኒክ ጉዳዮች ላይ በጥልቅ ተነጋግሯል።
ረዳት ፓይለቱ ሙሉ በሙሉ ጤነኛ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል።
ኢትዮጵያዊ የህግና እንዳስፈለጊነቱ የህክምና ባለሞያዎች ጋር እንዲገናኝም ዶ/ር ሼክስፒር ምክር ሰጥቷል።
የረዳት ፓይለቱ ጠበቃ የስዊስ መንግስት ሃይለመድህን አበራን ለኢትዮጵያ አሳልፎ እንደማይሰጥና ግዚያዊ የስደት ፈቃድ እንዲሰጠው ውሳኔ መተላለፉን ያረጋገጠ ሲሆን – ጉዳዩ በቅርብ ጊዜ በሚሰየመው ግልጽ ችሎት እልባት እንደሚያገኝ አመላክቷል።
የሃይለመድህን አበራን ወደ ኢትዮጵያ ለማስመለስ በአቶ አስመላሽ ወልደ-ስላሴ የተመራ ከፍተኛ የኢህአዴግ ቡድን ጄኔቭ፣ ከርሞ ጥያቄው በስዊዘርላንድ መንግስት ውድቅ መደረጉ ይታወሳል።
ቡድኑ የስዊስ ፌዴሬሽን የህግ አካላትን ለማሳመን ካቀረበው ምክንያት ዋነኛው፣ ረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ የአእምሮ በሽተኛ መሆኑን እና ይህንንም የራሱ ቤተሰብ አባላት እንዳረጋገጡላቸው ገልጸዋል። የስዊዝ መንግስት ግን ጥያቄውን ውድቅ አድርጎታል። ለዚህም የሰጠው ዋነኛ ምክንያት፤ የሞት ፍርድን ተግባራዊ ለሚያደርግ መንግስት ማንንም አሳልፌ አልሰጥም የሚል ሲሆን ይህ ባይሆንም፣ በስዊዘርላንድ እና በኢትዮጵያ መሃል ተጠርጣሪ እስረኛን የማስመለስ ውል የለም ብለዋል።
ረዳት ፓይለቱ ለግዜው ሰው ማግኘት እንደማይፈልግ የተነገረ ሲሆን: ወንድሙ ዶ/ር እንዳላማው አበራ እና በጀርመን የምትኖር እህቱ ሃይማኖት አበራ ጄኔቭ ድረስ በመሄድ ሃይለመድህን አበራን ከሚገኝበት እስር ቤት ጎብኝተውታል።
ወጣት ሃይለመድህን አበራ ባለፈው የካቲት 10፣ 2006 ዓ.ም. የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነውን ቦይንግ 767 አግቶ ጄኔቭ ስዊዘርላንድ ላይ በማሳረፍ እዚያው የፖለቲካ ጥገኝነት መጠየቁ ይታወሳል። የአለም ዜና ርዕስ ሁሉ ትኩረት ስቦ የነበረው ይህ ልዩ ክስተት የኢትዮጵያን የሰብአዊ መብት ሁኔታና የአስተዳደር በደል አደባባይ በማውጣቱ የገዢው ፓርቲ አባላትን እጅግ እንዳበሳጨ ይነገራል።
አንዳንድ መገናኘ ብዙሃን እንደገለጹት የአጎቱ ድንገተኛ ህልፈት ርዳት ፓይለቱን አስቆጥቶት ነበር። የሃይለመድህን አበራ አጎት፤ ዶ/ር እምሩ ሥዩም ህይወት በድንገት ማለፍ ለብዙዎች ያልተፈታ እንቆቅልሽ ነው። ዶ/ር እምሩ ሥዩም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር ነበሩ።
በአለም ዙሪያ ያሉ ኢትዮጵያውያን ወጣቱ ፓይለት ሃይለመድህን አበራን መደገፋቸውን እንደቀጠሉ ሲሆን በረዳት ፓይለቱ ስም የተከፈቱ ድረ-ገጾች እና የፌስቡክ መድረኮች ላይ አሁንም ሰፊ ዘመቻ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
ዶ/ር ሼክስፒር ፈይሳ በረዳቱ ጉዳይ ላይ ማንኛውንም ትብብር ለማድረግ ቃል የገባ ሲሆን የስዊስ ጠበቆችም በዚህ ከክፍያ ነጸ የሆነ ትብብሩ አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

ተስፋለም ሆይ! ስላንተ ምን ልናገር? ስለልጅነትህ?!
ሚያዚያ 18 ቀን 2006 ዓ.ም ንጋት ላይ ትንሿ ስልኬ አንጫረረጭ፡፡ ከእንቅልፌ ብንን ብዬ ስልኬን ተመለከትኩት፡፡ የደወለው ወዳጄከዚህ ቀደም በዚህ ሰዓት ደውሎልኝ አያውቅም ነበር፡፡ ስልኩን ሳላነሳው ‹‹ምን አንዳች ነገር ተፈጥሮ ይሆን?›› ብዬ ማሰላለሌን ተያያዝኩት፡፡ ከ20 ደቂቃ በኋላ ስልኩ በድጋሚ ተደወለ፣ አነሳሁት፡፡ ከደዋዩ ወዳጄጋርም ሰላምታ ተለዋወጥን፡፡ ‹‹ጓደኞችህ ታሰሩ አይደል?›› አለኝ፡፡ ‹‹እነማን?›› በማለት በችኮላ መለስኩለት፡፡ ‹‹ተስፋለም፣ በፍቃዱ ኃይሉ፣ ዞን ዘጠኞች…›› ደንግጬ መረጃው እንደለሌለኝ ነገርኩት፡፡ …ተስፋለም ከመታሰሩ ሁለት ቀናት በፊት ደውሎ ከሥራ ጋር የተገናኘ መረጃ ጠይቆኝ ነበር፡፡
ያለ ወትሮ ስልክ ሲደወል በተቻለ አቅም እረጋ ብሎ ማሰላለሰልን ከተሞክሮ ተምሬያለሁ፡፡ የቀድሞ የአውራምባ ታይምስ ማኔጂንግ ኤዲተር ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደን ከኢትዮጵያ መሰደድ ንጋትላይ ‹‹አለቃችሁ ተሰደደ አይደል?›› ብሎ የነገረኝ፣ እስከአሁን ድረስ በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ መታሰሩ በጣም የገረመኝ፣ የማከብረው እና የምወደው የልጅነት ጓደኛዬ እና ወንድሜ ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ነበር፡፡ እንደአንድ ነጻ እና ጎበዝ ጋዜጠኛ ለመረጃ ያለውን ቅርበት ተመልከቱ!
የሌሎቹም የጋዜጠኛ አስማማው ኃይለጊዮርጊስ፣ የጋዜጠኛ እና ጦማሪ በፍቃዱ ኃይሉ (በፍቄ)፣ የጦማሪያኑ የማህሌት ፋንታሁን፣ የአጥናፍ ብርሃኔ፣ የዘላለም ክብረት፣ የናትናኤል ፈለቀ፣ የአቤል ዋበላና የኤዶም ካሳዬ መሰል እስርም እጅግ አሳዝኖኛል፡፡ ዋይ! ሀገሬ!
ከተስፋለም ወልደየስ ጋር ትውውቃችን ከለጋ አፍላ ዕድሜያችን ይጀምራል፡፡ ወላጆቹ ጦላይ ወታደራዊ ካምፕን ለቅቀው አዲስ አበባ መኖር ከጀመሩ በኋላ ማለት ነው፡፡ ዛሬ በሕይወት የሌሉት የተስፍሽ ወላጅ እናት ወ/ሮ አበበች አክስት ከወላጅ አባቴ ጋር በጣም የቅርብቤተሰባዊ ትስስር አላቸው፡፡ ወ/ሮ አበበች እና አክስታቸው ለረዥም ዓመታት ልደታ መኮንኖች ክበብ አቅራቢያ አንድ ግቢ ውስጥ ኖረዋል፡፡
ዛሬ በሕይወት የሌሉት ወላጅ አባቱ እና እናቱ እንዲሁም አሁን ላይ በቅርቡ ያለችው እህቱ ራሄል ተስፋለምን ‹‹አቡሽ/አቡሼ›› በማለት ነበር ፍቅራቸውን በመግለጽ የሚጠሩት፡፡ እኔም እስከቅርብ ዓመታት ድረስ ‹‹አቡሽ›› ነበር የምለው፡፡
ከተስፋለም ጋር አብሮ በመሆን በነበሩን አጋጣሚዎች ሁሉ በጣም ደስ የሚል ጨዋታ፣ እያወጉ ረዥም ወክ የማድረግ ተደጋጋሚ ልምድናእውቀት የመካፈልየቁም ነገር ጊዜያቶችን በልጅነታችን በደንብ አጣጥመን አሳልፈናል፡፡ …እነዚህ መቼም አይደገሙ! ትዝታ ሆነው አልፈዋል፡፡ ተስፋለም አዲስ ነገር ለማወቅ እና አዲስ ነገርን ለመንካት ያለውን ጉጉት እና ትጋት ወደር የለውም፡፡ አከባቢያዊ፣ ሀገራዊ እና ዓለማቀፋዊ መረጃዎችን ከአቅሙ በላይ ለማወቅ ይታትር ነበር፡፡ ለዕውቀት እና ለመረጃ የነበረውም የተንቀለቀ ስሜት እና ጥማትየላቀ ነው፡፡ ለዚህ ይሆን፣በብዙዎች ዘንድ በኢትዮጵያ የፕሬስ ታሪክ ትልቅ ተምሳሌት ከነበረችው የ‹‹አዲስ ነገር›› ጋዜጣ መስራቾች መካከል አንዱ የሆነው?
ተስፋለምን ልጅነት ካወኩት ጊዜ አንስቶ የንባብ ቀበኛ ነው፡፡ ገበያ ላይ ያሉ መጽሐፍትን፣ ጋዜጦችንና መጽሄቶችን ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ከሰዎች ይዋሳል፣ ያነብባል፣ ይገዛል፣ አደራጅቶ በጥንቃቄ ያስቀምጣል፡፡ ለምሳሌ፣ ሆሊውድ ጋዜጣ እና ኢንፎቴይንመንት መጽሄትለአንባቢያን ቀርበው ህትመታቸው እስከተቋረጠባቸውጊዜያት ድረስ ያሉትን ቅጾች በተስፋለም ቤት አሁንም ድረስ በክብር ተቀምጠው ያገኟቸዋል፡፡ የሬዲዮ እና የቴሌቭዥን ፕሮግራሞችንበሚያስገርምመልኩ በአንክሮ ይከታተላል፡፡ ፊልሞችንም እንደዚሁ፡፡ የተመለከታቸውን ፊልሞች መቼ እንደተመለከታቸውጠቅሶ ከነዕርሶቻቸው ማስቀመጥም ልምዱ ነበር፡፡ ዛሬ ላይ ምን እንዳደረጋቸው ባላውቅም በርካታ ግጥሞችንም ይጽፍ ነበር፡፡ ግለ-ሀሳቡንም ይጽፋል፡፡
ተስፋለም፣ የጋዜጠኝነት ሙያን መማር ጥልቅ ፍላጎቱ መሆኑንለወላጆቹ ተናግሮ ካሳመነ በኋላ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ጋር በሚገኘው በቀድሞ የማስሚዲያ ማሰልጠኛ ኤጀንሲ የጋዜጠኝነትትምህርትን ለመመዝገብ የሄደው ከእኔ ጋር ነበር፡፡ …ከዚህ መደበኛ ትምህርት ባሻገር በሂደት ሙያውን በራሱ ጥረት ለማሻሻል ጥረቱ ትልቅ ነበር፡፡ በዚህ ወቅት የፍሪላንስ ሥራን በጎን በመጀመሩ ምክንያት እና በትምህርት ጥናት የተነሳ አምሽቶ ከእኩለ ሌሊት በኋላወደቤት መግባትን ልምድ አድርጎም ነበር፡፡በዚህ ወቅት በመኖሪያ ቤቶቹ ግቢ ውስጥ በጣም አምሽቶ የሚገባው ተስፋለም ነው፡፡ ተስፋለም ‹‹ለእውነተኛ ጋዜጠኝነት የተፈጠረ›› ብል አፌን ሞልቼ ነው፡፡ ሙሉ ሕይወቱን ለጋዜጠኝት ሙያ ስለመስጠቱም ሆነ ስለጥንቃቄውእመሰክራለሁ፡፡
አሁን ላይ ቀን እና ዓመተምህረቱን ዘንግቼዋለሁ፡፡ ወላጅ አባቱ ለረዥም ወራት እያመማቸው እና እየተሸላቸው ከቆዩበኋላአመሻሽ ላይ ሕይወታቸው አለፈ፡፡ በቦታውም ነበርኩ፡፡ ተስፋለም ግን ከነፍሱ ለሚወደው ሙያ ሌሊቱን ሙሉ ሲሰራ አድሮ ንጋት ላይ ወደቤቱ ሊገባ የአጥሩንበር ሲከፍት መኖሪያ ቤታቸው በሰዎች ተከብቧል፡፡ ድንጋጤው ፊቱ ላይ በግልጽ ያስታውቅበት ነበር፡፡ ማንምም ሳያናግር ወደቤቱ ዘለቀ፡፡ በጥልቅ የሚወዳቸው እና የሚሳሱለትየወላጅ አባቱ ሞት እውነት መሆኑን ተረዳ፡፡ ፊቱ ተቀያየረ፣ ግራ ተጋባ፣ አይኖቹ በዕንባ ተሞሉ፣ የአባቱን መሪር ሀዘን …
ከደቡብ ዩኒቨርሲቲ በደን ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ ከተመረኩኝ በኋላ አንድ ቀን አመሻሽ ላይ ከተስፋለም ጋር ከልደታ ተነስተን ወደቦሌ መስመር ወክ በማድረግ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይበተመስጦ እያወጋን ነበር፡፡ አስታውሳለሁ፣ ወሎ ሰፈር ጋር አንድ ጥያቄ ጠየኩት፡፡ ‹‹በተማርኩት ትምህርት ደስተኛ ብሆንም ነፍሴ ግን አልረካችም›› አልኩት፡፡ ‹‹ኤልያስ ውስጥህን በእርጋታ አዳምጠው›› በማለት ተስፋለም መለሰልኝ፡፡ እውነቱን ለመናገር ውስጥን ማዳመጥ ምን ማለት እንደሆነ እስከዚያች ቅጽበት ድረስ አላውቅም ነበር፡፡ ዛሬ ከነፍሴ በምወደው የጋዜጠኝነት ሙያ ላይ እንድገኝ ‹‹…ውስጥህን አዳምጠው›› የሚለው የተስፋለም ወንድማዊ ምክር እጅጉን እንደጠቀመኝ ዛሬ ላይ ተነፈስኩት፡፡ ተስፍሽ አስተዋይ የሆነ የትንሽ ትልቅ ነበር፡፡
ተስፍሽ፣ ድንገተኛ እስርህ አመመኝ፣ ቁጭት ፈጠረብኝ፡፡ ዛሬም ድረስ ውስጤን እያንገበገበው ይገኛል፡፡ ሆኖም እሰሩ የዜጎችን ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ ሕገ-መንግስታዊም ሆነ ዓለማቀፋዊ መብት እንዲከበር ለምወደው ሙያ ይበልጥ በጽኑ እንድቆም ጤናማ እልህ አቀጣጥሎብኛል፡፡ የእናንተ እስርም በነጻው ፕሬስ ውስጥ የሚገኙ በርካታ ጋዜጠኞችን ልብ በሃዘን ነክቷል፣ ንዴታዊ ስሜት ውስጥም ከትቷል፡፡ በጋዜጠኝነት ለመስራት ‹‹ሙያው አስጠላን›› ያሉኝም አሉ - መፍትሄ ባይሆንም፡፡
በአዲስ አበባ አራዳ ፍርድ ቤት የጓደኞችህን እና የአንተን ሁለት እጅችህ በብረት ካቴና ተጠፍንገው ስመለከት ደግሞ በመንግሥታችን እጅጉን አዘንኩ፡፡ ጠረጼዛ ላይ ያሉ ጋዜጦችን፣ መጽሄቶችንና መጽሐፍቶችን እንኳን ከልጅነትህ ጀምሮ ማዝረክረክ የማትወደው ልጅ ከነፍስህ የምትወዳትን እምዬ ኢትዮጵያን ከሙያ አጋሮችህ ጋርበሽብር እና በአመጽ ለማተራምስ ተንቀሳቅሰሃል ብዬ ለሰከንድ እኩሌታ እንኳን በጭራሽ አላስብም፡፡ለምትወደው ሙያህ ዘወትር ሚዛናዊ ዘገባን ለማቅረብ መታተርህ መንግሥት ላይ ስጋት ፈጥሮ ይሆን እንዴ? …በእናንተ ላይ የሚቀርበውን ክስ ለማወቅ በጣም የጓጓሁትምለዚሁ ነው፡፡
አይደለም ከልጅነቴ ጀምሮ በደንብ የማውቀውን ተስፋለምን ቀርቶ ሌሎች የታሰሩት የሙያ አጋሮቻችንእንኳን በሚወዷት ሀገር ላይ ሽብር እና አመጽ ለማካሄድ የማሴርዓላማ እና ዕቅድ አላቸው ብዬ ለማሰብ ፍጹም እቸገራለሁ፣ይህ የግሌ እምነት ነው፡፡
…ተስፋለምን ለረዥም ዓመታት ከማውቀው አኳያ ብዙ ማለት ብችልምለዛሬ የልጅነት ሕይወቱን ብቻ ጠቅሼ ለማለፍ ወደድኩ፡፡ተስፍሽ፣ ንጽሕናህ እና ሙያዊ ጥንቃቄህ ነጻ ያወጣሃል!!! ነገር ግን፣ በጊዜው የኢሕአዴግ መንግሥት የፍትሕ ሥርዓት ላይ እምነት ካጣሁ ቆየሁ፡፡
እንደመውጫ
ስለተስፋለም በሥራው ላይ ስለላው ባህሪ እና ትጋት በቅርበት የሚያውቁት ጓደኞቹ፣ ባልደረቦቹና ወዳጆቹ በማኅበራዊ ድረ-ገጽ እና በሕትመት ሚዲያዎች ላይ ሃሳባቸውን መግለጻቸው ይታወቃል፣ አሁንም እየገለጹ ነው፡፡
ከእነዚህም መካከል ሁለትጓደኞቹለእሱ ከጻፉለት ጽሑፎች ውስጥመርጬ በድጋሚ በዚህ ጽሑፌላይ ባሰፍርለት ልቤ ወደደ፡፡ የቀድሞ አዲስ ነገር ጋዜጣ ባልደረባው ጋዜጠኛ ማስረሻ ማሞ በፌስ ቡክ ገጹ እንዲህ ብሎ ነበር፡-
‹‹ …ተስፋለም የግል ፖለቲካ አመለካከቱ ከጋዜጠኝነቱ ጋር እንዳይጋጭበት የሚጠነቀቅ ወጣት ነው፡፡ ከጋዜጠኝነት ከፍ ያለ ክብር እና ዋጋ ይሰጣል፡፡ አንዳንዴ እቀናበታለሁ፡፡ ስለሚዛናዊነቱ እቀናበታለሁ፡፡ ስለሚዛናዊነቱ፣ ስለተገቢነትና ስለእውነተኛ ዘገባ አብዝቶ ይጨነቃል፡፡ ማንኛውም ዓይነት ዘገባ ከትክክለኛው ወንዝ ተቀድቶ እንዲፈስ ይመኛል፣ ያደርጋል፣ ይጓዛል፡፡ መጀመሪያ ለሙያው ታማኝ መሆንን ያስቀድማል፡፡ ከተስፋለም ጋር ሳወራ ከታናሽ ወንድሜ ጋር የማወራ ነው የሚመስለኝ፡፡ ኢሕአዴግ እንደተስፋለም መሥመራቸውን ጠብቀው ለሚሰሩ ሰዎች የማይመለስ ይሆናል ብዬአስቤ አላውቅም፡፡ አሁንም መታሰሩን ማመን እውነት እውነት አልመስልህ ብሎኛል! የሚሰማኝ እልህ፣ ቁጭት፣ ተስፋቢስነትና ቁጣ ነው፡፡ እኔ እስከማውቀው ድረስ ተስፋለም የማንም ወገን አይደለም፡፡ ብቻውን በራሱ የቆመ ጋዜጠኛ ነው፡፡››
ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ ደግሞ ባለፈው ሳምንት ለንባብ በበቃው ‹‹ፋክት› መጽሔት ላይ ‹‹ትንሹ ተስፋለም›› በሚል ርዕስ ከጻፈችው የቀነጨብኩትን ደግሞ እንዲህ አስቀመጥኩት፡-
‹‹በአነጋገሩ ቀጥተኛና በጠባዩ ገራገር ነው፡፡ ‹ጥርስ ያሳብራል› በሚባሉ ስብሰባዎች፣ በኃይለ ቃል በተሞሉ የኢዲቶሪያል ውይይቶችና ግምገማዎች ሳይቀር ስሜቱን ውጦ በተረጋጋ መንፈስና በለዘብታ ቃል መመላለስ ጸጋው ነው፡፡ በኤዲቶሪያል ጠረጼዛዎች እና ዴስኮች ዙሪያ በሐሳብ ለመግባባት ከሚደረጉ ግብግቦች ውጭና ባሻገር ቂም እና በቃል አያውቅም፡፡ በደሙ ውስጥ ከሚዘዋወረውና ራሱን ከሰጠለት የጋዜጠኝነት ሙያውና የጋዜጠኝነት መርህ የተነሳ ሌላ ዓለም፣ ሌላ ኑሮ ያለም አይመስለው፡፡ ለእርሱ ኑሮው፣ ለእርሱ ዓለሙ፣ ተጨባጭ መረጃን ከወገናዊነት በጻዳ መልኩ ለሕዝብ ማድረስ ነው፡፡…››
…ከቀናቶች በኋላም ለተወሰኑ ወራት በዕንቁ መጽሄት ላይ አብረን በመሰራት ስለማውቀው ጋዜጠኛ እና ጦማሪ በፍቃዱ ኃይሉ (በፍቄ) ብዕሬን አንስቼ እጽፋለሁ፡፡
በእስር ላይ የሚገኙትን፣ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት በፖሊስ እንደተፈጸመባቸው በፍርድ /ቤት የተናሩትን ጋዜጠኞችን እና ጦማሪያን እግዚአብሄር ጽናት፣ ብርታትና ጥንካሬ ይስጣቸው፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!

Friday, May 2, 2014
ሰበር ዜና- የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ (ኢጋመ) ፕሬዝደንት ጋዜጠኛ በትረ ያቆብ ተሰደደ
ሰበር ዜና-
ከሳምንት
በፊት የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ ፕሬዝዳንትና ምክትል ፕሬዝዳንት በአፍሪካ ህብረት ጋባዥነት የኢትዮጵያን ችግርና
አፈና በተለይ በሚዲያው ላይ ያለውን ጫና እና ጋዜጠኞች ላይ የሚደርሰውን አፈና ለመግለጽ ወደ አንጎላ አቅንተው
ነበር፡፡ በጉዳዩ ላይ ሰፊ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ለአፍካ ህብረትም የመፍትሄ ሀሳብ ማቅረቡና ለሰብአዊ መብት
ኮሚሽነሩም መልስ መስጠቱ ይታወቃል፡፡
ጋዜጠኛ በትረ ያቆብ ስብሰባው ከተጠናቀቀ በኋላ ወደ አገሩ ለመመለስ
በሚዘጋጅበት ወቅት የዓለም አቀፍ የጋዜጠኛ ማህበራትን ጨምሮ ሌሎች የዓለም አቀፍ ተቋማት ሳይቀሩ እሱን ለማሰር
የተደረገው ዝግጅት በተጨባጭ ማስረጃ ስላቀረቡለት መሰደዱን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ የዞን ዘጠኝ
ጦማሪዎች በታሰሩበት ወቅት ፖሊስ የበትረ ያቆብን ቤት በመፈተሸ ያገኘውን ወረቀት ሁሉ እንደወሰደም ምንጮቻችን
ጨምረው ገልጸዋል፡፡
ጋዜጠኛ በትረ ያቆብ አንጎላ በተደረገው የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ኮሚሽነሩን በግል
እንዳገኛቸውና ኮሚሽነሩም በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ በመግለጽ እንዲሚያገኙት ቃል ገብተውለት እንደነበር
ተገልጿል፡፡ በተጨማም ከበርካታ የአፍሪካ ህብረት ባለስልጣናት ጋር ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታና በሚዲያው ላይ
ስለሚደረገው ጫና የተወያዩ ሲሆን አብዛኛዎቹ በተለያዩ መንገዶች እገዛ ለማድረግ ቃል ገብተውለት እንደነበር ከታማኝ
ምንጮች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ በስብሰባው ወቅት ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክን ወቅታዊ ሁኔታ
የሚገልጹ ጽሁፎች ለተሰብሰብሳቢዎቹ ተበትነዋል፡፡
የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ መቋቋም ያስፈራቸው ሌሎች
የጋዜጠኞች ማህበራት በትረ ያቆብን ለሂውማን ራይትስ ዎች፣ ለሲፒጄ፣ ለአርቲክል 19ና ሌሎች የጋዜጠኞች ማህበራት
ይሰራል፣ ይሰልላል፣ የእነዚህ ድርጅቶች ተላላኪ ነው፣ ሪፖርት ይጽፋል በሚል በመግለጫቸውና ‹‹የጋዜጠኞች ክብ
ጠረጴዛ›› በተባለው ፕሮግራም ይከሱት እንደነበር ጋዜጠኛ በትረ ያቆብ አገር ውስጥ በነበረበት ወቅት ለነገረ
ኢትዮጵያ ገልጻል፡፡
ነገረ ኢትዮጵያ /
ከሳምንት በፊት የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ ፕሬዝዳንትና ምክትል ፕሬዝዳንት በአፍሪካ ህብረት ጋባዥነት የኢትዮጵያን ችግርና አፈና በተለይ በሚዲያው ላይ ያለውን ጫና እና ጋዜጠኞች ላይ የሚደርሰውን አፈና ለመግለጽ ወደ አንጎላ አቅንተው ነበር፡፡ በጉዳዩ ላይ ሰፊ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ለአፍካ ህብረትም የመፍትሄ ሀሳብ ማቅረቡና ለሰብአዊ መብት ኮሚሽነሩም መልስ መስጠቱ ይታወቃል፡፡
ጋዜጠኛ በትረ ያቆብ ስብሰባው ከተጠናቀቀ በኋላ ወደ አገሩ ለመመለስ በሚዘጋጅበት ወቅት የዓለም አቀፍ የጋዜጠኛ ማህበራትን ጨምሮ ሌሎች የዓለም አቀፍ ተቋማት ሳይቀሩ እሱን ለማሰር የተደረገው ዝግጅት በተጨባጭ ማስረጃ ስላቀረቡለት መሰደዱን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች በታሰሩበት ወቅት ፖሊስ የበትረ ያቆብን ቤት በመፈተሸ ያገኘውን ወረቀት ሁሉ እንደወሰደም ምንጮቻችን ጨምረው ገልጸዋል፡፡
ጋዜጠኛ በትረ ያቆብ አንጎላ በተደረገው የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ኮሚሽነሩን በግል እንዳገኛቸውና ኮሚሽነሩም በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ በመግለጽ እንዲሚያገኙት ቃል ገብተውለት እንደነበር ተገልጿል፡፡ በተጨማም ከበርካታ የአፍሪካ ህብረት ባለስልጣናት ጋር ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታና በሚዲያው ላይ ስለሚደረገው ጫና የተወያዩ ሲሆን አብዛኛዎቹ በተለያዩ መንገዶች እገዛ ለማድረግ ቃል ገብተውለት እንደነበር ከታማኝ ምንጮች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ በስብሰባው ወቅት ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክን ወቅታዊ ሁኔታ የሚገልጹ ጽሁፎች ለተሰብሰብሳቢዎቹ ተበትነዋል፡፡
የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ መቋቋም ያስፈራቸው ሌሎች የጋዜጠኞች ማህበራት በትረ ያቆብን ለሂውማን ራይትስ ዎች፣ ለሲፒጄ፣ ለአርቲክል 19ና ሌሎች የጋዜጠኞች ማህበራት ይሰራል፣ ይሰልላል፣ የእነዚህ ድርጅቶች ተላላኪ ነው፣ ሪፖርት ይጽፋል በሚል በመግለጫቸውና ‹‹የጋዜጠኞች ክብ ጠረጴዛ›› በተባለው ፕሮግራም ይከሱት እንደነበር ጋዜጠኛ በትረ ያቆብ አገር ውስጥ በነበረበት ወቅት ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጻል፡፡
ነገረ ኢትዮጵያ /
Subscribe to:
Posts (Atom)