Saturday, June 28, 2014

በአ.አ ዩኒቨርሲቲ 52 ተማሪዎች ክስ ተመሰረተባቸው ።

በአ.አ ዩኒቨርሲቲ 52 ተማሪዎች በ”ዲሲፕሊን” ሰበብ ፖለቲካዊ ክስ ተመሰረተባቸው (ዝርዝራቸውን ይዘናል)

  • 1466
     
    EmailShare
 በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመብት ጥያቄ አንስተው በሃገራዊ ጉዳይ ነቃ ያለ ተሳትፎ የሚያደርጉ 52 ተማሪዎች ላይ የዲሲፕሊን ክስ መመስረቱ ተሰማ። የዲሲፕሊን ክስ የተመሰረተባቸውን ተማሪዎች ስም ዝርዝር የያዘውን ወረቀት በማህበራዊ ድረገጾች ላይ የለቀቁት የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ክሱ የተመሰረተባቸው ሰኔ 21 ቀን 2006 ዓ.ም ከጠዋቱ በ2 ሰዓት በተማሪዎች ጽ/ቤት እንዲገኙ ት ዕዛዝ ተሰጥቷል።
ምናልባትም እነዚህ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ትኩረት አድርገው የሚንቀሳቀሱት ተማሪዎች ላይ በዲሲፕሊን ሰበብ ፖለቲካዊ እርምጃ ሊወሰድባቸው እንደሚችል የቅርብ ምንጮች  ያስታወቁ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው ይህን እርምጃ ከወሰደ ሌላ የተማሪዎች አመጽ እንዲነሳ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ታዛቢዎች ይናገራሉ።
በዲሲፕሊንክ ክስ ሰበብ የፖለቲካ እርምጃ ሊወሰድባቸው የተዘጋጁት ተማሪዎች ስምዝርዝር የሚከተለው ነው፦
students 1

students 2

Friday, June 27, 2014

የህወሓት ባለስልጣናት የመቀሌውን ሰላማዊ ሰልፍ ለማስቆም ሽርጉድ በማለት ላይ ናቸው።

ህወሓቶች የመቐለን ሰለማዊ ሰልፍ ለመከልከል ወስነዋል። 

(አብርሃ ደስታ)

  • 68
     
    Share
mekeleትናንት ሐሙስ ማታ (ከምሽቱ 4:30) አንድ የህወሓት ባለስልጣን ደውሎ እንደነገረኝ ከሆነ ህወሓቶች የመቐለን ሰለማዊ ሰልፍ ለመከልከል ወስነዋል። ትናንት ማታ አስቸኳይ ስብሰባ የተጠራው “ሰልፉ በመቐለ እንዳይካሄድ፣ እንዳታዋርዱን፣ የህዝቡን ስሜት መረዳት እንዴት ያቅታችኋል? ነገሮች ሳይበላሹ ሰልፉ በሆነ ምክንያት እንዲቀር አድርጉ! ተብሎ ተደውሎልናል” ብሎ ነገረኝ። ማን ለማን ነው የሚደውልለት? አልነገረኝም። ግን ከአዲስ አበባዎቹ ይሆናል ብለን እንገምት።

ህወሓት ሰልፉን ለመከልከል ወስኖ ከሆነ በጣም የሚያሳፍር ተግባር ነው። ከመጠን በላይ ፈርቷል ማለት ነው። የመቐለ ህዝብ ሰልፍ የማድረግ መብቱ ተነፈገ ማለት ነው። ድሮምውም ኮ የህዝብ ስሜት የሚያጤኑ የደህንነት ሰዎች በዝተዋል። ህዝቡ እንደሚሰለፍ ስለተረዱ ይሆናል። መረጃው ትክክል ከሆነ በቃ የትግራይ ህዝብ ሰለማዊ ሰልፍ የማድረግ መብት የለውም ማለት ነው።
ግን ሰልፉን መከልከላቸው በደብዳቤ እስኪያሳውቁን ድረስ ሰልፉ እንደሚካሄድ ነው ታሳቢ የምናደርገው። ዉሳኔው ትክክል ስለመሆኑ የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ያስፈልገናል። እውነት ግን ሰልፉ አይደረግም ብለው ደብዳቤ ሊሰጡን? አላምንም። ደብዳቤ ካልሰጡን ደግሞ ሰልፉ ይደረጋል። ስለዚህ እናያለን።

Monday, June 16, 2014

(ሰበር ዜና)

 ከ1000 በላይ የሚሆኑ ዜጎች ቤታችን ፈረሰ በሚል ኢሰመኩ ደጃፍ ተቃውሞ ወጡ

  • 1237
    Share
(ዘ-ሐበሻ) በአሁኑ ሰዓት በአዲስ አበባ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን መስሪያ ቤት ደጃፍ ከ1000 በላይ የሚሆኑ ዜጎች ቤታችን ፈረሰ፣ የምንሄደበት አጣን በሚል ለተቃውሞ መውጣታቸውን የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች በፎቶ ግራፍ አስደግፈው ዘገቡ።
ከ1000 በላይ የሚሆኑት እነዚሁ ተሰላፊዎች መንግስት አንድ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ለመጠየቅ በኢሰመኮ ደጃፍ ላይ በመስፈር መፍትሄ ካላገኘን አንነቃነቅም እንዳሉ ነው። አካባቢውን ፌደራል ፖሊስ ከቦታል ሕዝቡ ግን ካለምንም ፍራቻ ተቀምጦ መብቱን እየጠየቅ እንደሚገኝ የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች አስታውቀዋል።
ፎቶዎችን ተመልከቱ፤ ተጨማሪ መረጃዎች እንደደረሱን እንመለሳለን። ዘ-ሐበሻ የትኩስ መረጃ ምንጭ።

Thursday, June 12, 2014

የቀድሞው የጋምቤላ ርእሰ መስተዳድር ኦኬሎ ኦኳይ በሽብር ወንጀል ተከሰሱ



  • 25
     
የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ርእሰ መስተዳድር የነበሩት ኦኬሎ ኦኳይ በሽብር ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው።
news
ተከሳሾቹ የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ርእሰ መስተዳድር የነበሩት ኢኬሎ ኦኳይ ፣ ዴቪድ ኡጁሉ፣ ኡቻን ኦፔይ ፣ ኡማን ኝክየው ፣ ኡጁሉ ቻም ፣ አታካ ኡዋር እና ኡባንግ ኡመድ ናቸው።
የፌደራል አቃቤ ህግ ሁሉንም ግለሰቦች ራሱን የጋምቤላ ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ /ጋህነን/ እና እህት ድርጅት ነው በሚሉት የጋምቤላ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ጋህነን/ በተሰኙ የሽብር ቡድን ድርጅቶች ከአመራር ሰጪነት እስከ አባልነት ተሳትፎ አላቸው በሚል ነው በሽብር ወንጀል ክስ የመሰረተባቸው።

1ኛው ተከሳሽ ኦኬሎ ኦኳይ በ1996 ዓ.ም የጋምቤላ ርእሰ መስተዳድር ነበሩ።
ክሱ በወቅቱ በክልሉ የሚገኙ የአኙዋክና የኑዌር ብሄረሰብ አባላት መካከል ግጭት ይቀሰቀሳል፣ በግጭቱም ከ 400 በላይ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል ፤ እኚህው ርእሰ መስተዳደሩ ሃላፊነታቸውን ተጠቅመው ግጭቱ በቁጥጥር ስር ሊያውሉ ሲገባ እንዳባባሱት ይጠቅሳል።
በዚህ ብቻ አላበቁም ግጭቱን አስመልክቶ ለተለያዩ የውጭ ሃገር መገናኛ ብዙሃን የተዛባ መግለጫ መስጠታቸውና የሚሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እልቂቱን አባብሶት እንደነበርም ተጠቅሷል።
ኋላም ድርጊታቸው እንደሚያስጠይቃቸው በመረዳት የግል አጃቢያቸውና ሾፌራቸውን እንደያዙ ጥር 1996 ሃገር ከድተው መውጣታቸውን ፣ ሃገር ቤት ሆነው እልቂቱን ያባባሰ መግለጫቸውን መቀመጫቸውን ውጭ ሃገር ላደረጉ መገናኛ ብዙሃን መስጠት መቀጠላቸውን ክሱ አመልክቷል።
ወደ ኖርዌይም በማቅናት ጥገኝነት ካገኙና ሃገር ከድተው ከወጡ ከሶስት አመታት በኋላ ራሱን የጋምቤላ ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ/ጋህነን/ የተባለውን የሽብር ቡድን ለመቀላቀል በመወሰን በወቅቱ የዚህ ሽብር ቡድን መስራችና ሊቀመንበር ከሆነው ፒተር ካጋ ጋር በመገናኘት የውጭ ግንኙነት ሃላፊ በመሆን ተሹመው የሽብር ቡድኑን ተልእኮ ማስፈጸም አንድ ብለው መጀመራቸውን ክሱ አትቷል።

በአውሮፓና በአሜሪካ እየተዘዋወሩ የሽብር ቡድኑን አባላት በመመልመል ፣ ከአባላቱ በወር እስከ 50 ዶላር ሰብስበዋል የሚለው በክሱ የተጠቀሰ ሌላ ጭብጥ ሲሆን ፥ ታህሳስ 2000 ዓ.ም ላይ ከድርጅቱ የሽብር አመራሮች ጋር ያደረጉት ቴሌ ኮንፈርንስም በክሱ ላይ ተጠቅሷል።
በዚሁ ዓመት ጥር ወር ላይ ጋህነን ለሁለት ሲከፈል ኦኬሎ ኦኳይ አንዱን ክንፍ መስራቹ ፒተር ካጋ ደግሞ ሁለተኛውን መያዛቸው በክሱ ተመልክቷል።
የሊቀመንበርነትን በትረ ስልጣን እንደጨበጡ ኤርትራ በመሄድ በሽብር እቅዳቸው ላይ ለ45 ቀናት ያህል ውይይት አደረጉ፤ጀርመን ሳውዲ አረቢያ እና ስዊድን በመሳሰሉ ሃገራትም በማቅናት የሽብር ቡድኑን ለማጠናከር መከሩ ይላል ክሱ።
አሜርካም ተጉዘው በወቅቱ ከጋምቤላ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ጋዴን/ ሊቀመንበር ጆንሰን ኡጁሉ የሊቀመንበርነቱን ሃላፊነት ተረክበው ጋህነን እና ጋዴንን መርተዋል የሚለውም ተጠቅሷል።
በዚህ ሃላፊነታቸው ኡጋንዳ መጡ 860 አዳዲስ አባላትን መልምለው ወታደራዊና ፖለቲካዊ ስልጠና እንዲያገኙ ካደረጉ በኋላ ፤ አባላቱ ከደቡብ ሱዳን አማጽያን ጋር እንዲቀላቀሉ ማስደረጋቸውም ተዘርዝሯል።
ሁለተኛው ተከሳሽ ዴቪድ ኡጁሉ የደቡብ ሱዳን ዜግነት ያለው የ36 አመት ጐልማሳ ሲሆን ፥ በሽብር ቡድኑ የደቡብ ሱዳን ሃላፊ ነው።

ከመስከረም 2005 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ጊዜያት አሜሪካ ሃገር ሚኒሶታ ከተማ ለሽብር ስራው ማከናወኛ በተለያዩ ባንኮች የሚላክለትን ገንዘብ ሲቀበል ቆይቷል ፣ የመለመላቸው አባላቱ የደቡብ ሱዳን አማጺያንን እንዲቀላቀሉ አስተባብሯል የሚለው በክሱ ላይ ተጠቅሷል።
ከእርሱ ሌላ ኦኬሎ ኢኳይን ጨምሮ ሰባቱም ተከሳሾች ከሌሎች ተመሳሳይ የሽብር ድርጅቶች ያገኟቸውን ልዩ ልዩ የሽብር ስልጠና ተጠቅመው ፥ አንድ አስከፊ ድርጊት ሊፈጽሙ ዝጅግት በማድረግ ላይ እያሉ ነው በደቡብ ሱዳን የጸጥታ ሃይሎች የተያዙት።
በጋምቤላ ክልል ወርቅ በሚቆፈርባቸው የዲማ እና ጆር የተሰኙ ወረዳዎች ላይ በማቅናት ፤ በወርቅ ቁፋሮ ላይ የተሰማሩ በርካታ ወጣቶችን በማፈን የደቡብ ሱዳን አማጺ መሪ ዴቭድ ያውያው ስልጠና በሚሰጥበት ቦታ በማምጣት፣ ሰልጥነው የሽብር ቡድኑን እንዲቀላቀሉ የማድረግ አላማ እንደነበራቸው በክሱ ላይ ተመልክቷል።።
ይህንን ምክራቸውን ጠንስሰው ወደ ኢትዮዽያ መጥተው ተግባራዊ ለማድረግ ሲዘጋጁ ድንገት የኢትዮዽያ መንግስት ከደቡብ ሱIዳን ጋር ባለው የጋራ የጸጥታ ስራ ቅንጅት በቁጥጥር ስር ውለዋል ፤ ዛሬ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤተ 4ኛ የወንጀል ችሎት ቀርበውም ክሱ ተነቦላቸዋል።
የአማርኛ ቋንቋ ለማይናገሩት በአስተርጓሚ እንዲረዱት የተደረገ ሲሆን ፥ መንግስት ጠበቃ ያቁምልን በማለታቸውም ችሎቱን አቤቱታቸውን ተቀብሏል።
የተጠቀሰባቸው የህግ አንቀጽ ዋስትና የሚከለክል በመሆኑ ፥ ከሚመደብላቸወ ጠበቀ ጋር ተመካክረው የክስ መቃወሚያ እንዲያቀርቡ ችሎቱ ሰኔ 24 2006ን ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።

Wednesday, June 11, 2014

አቶ በላይነህ ዳምጠው የባለቤታቸው ቤተሰቦች ቤት ውስጥ በጥይት ተመትተው ሕይወታቸው ማለፉ ታወቀ ፡፡

   

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሠራተኛ በጥይት ተመትተው ሕይወታቸው አለፈ 
ተጻፈ በ ታምሩ ጽጌ (ሪፖርተር )

-በመግደል የተጠረጠረው ግለሰብ አልተያዘም
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሠራተኛ ናቸው የተባሉት አቶ በላይነህ ዳምጠው፣ ሰኔ 1 ቀን 2006 ዓ.ም. ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ሲሆን ቤላ አካባቢ በሚገኘው የባለቤታቸው ቤተሰቦች ቤት ውስጥ በአንድ ግለሰብ በጥይት ተመትተው ሕይወታቸው ማለፉ ታወቀ፡፡
ባለትዳርና የአንድ ልጅ አባት መሆናቸው የተነገረው አቶ በላይነህ፣ ከሰኔ 1 ቀን 1992 ዓ.ም. ጀምሮ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተለያዩ ኃላፊነቶች ላይ ይሠሩ እንደነበር፣ ሕይወታቸው ባለፈበት ዕለትም ቀን በሥራ ገበታቸው ላይ እንደነበሩ የምክር ቤቱ ሠራተኞች ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

አቶ በላይነህ ሰኔ 1 ቀን 2006 ዓ.ም. ሥራ ውለው ቤላ አካባቢ ወደሚገኘው የባለቤታቸው ቤተሰቦች ቤት መሄዳቸውን የገለጹት የሥራ ባልደረቦቻቸው፣ ምክንያቱን በማያውቁትና ባላሰቡት ሁኔታ ሰኔ 2 ቀን 2006 ዓ.ም. ጠዋት ወደ ሥራ ሲገቡ የሥራ ባልደረባቸው መሞታቸውን መስማታቸውን አስረድተዋል፡፡

ግለሰቡ የተገደሉት በጥይት ተመትተው መሆኑንና ለመሞታቸውም ምክንያት የሆነችው አንዲት የፖሊስ ባልደረባ መሆኗን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡ የፖሊስ ባልደረባዋ፣ የሟች ባለቤት ቤተሰቦች ግቢ ውስጥ ተከራይታ እንደምትኖር የገለጹት ምንጮች፣ በዕለቱ እሷ ዘንድ የመጣ አንድ ተጠርጣሪ ግለሰብ ባልታወቀ ምክንያት እሷን እያባረረ ሟች ወደነበሩበት ክፍል ሲገባ፣ መጀመሪያ የሟችን ባለቤት ያገኛል፡፡ እሷን ሁለት እጆቿን በጥይት መትቶ ከጣላት በኋላ ወደ ውስጥ ሲዘልቅና ሟች ሲወጡ በመገናኘታቸው በተደጋጋሚ በጥይት ደብድቦ ሕይወታቸው እንዲያልፍ እንዳደረጋቸው አስረድተዋል፡፡
ተጠርጣሪው በአካባቢው የነበሩትን ነዋሪዎች በማስፈራራት የያዘውን ተሽከርካሪ አስነስቶ ከነመሣሪያው መጥፋቱንም የአካባቢው እማኞች ገልጸዋል፡፡
የ44 ዓመት ጐልማሳ የነበሩት የአቶ በላይነህ የቀብር ሥርዓትም ሰኔ 3 ቀን 2006 ዓ.ም. በፈረንሳይ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን መፈጸሙ ታውቋል፡፡ የሟች ባለቤት በዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታል የሕክምና ዕርዳታ እንደተደረገላቸውና ለደረሰው አደጋ ምክንያት ናት የተባለችው የፖሊስ ባልደረባ በቁጥጥር ሥር ውላ በምርመራ ላይ መሆኗም ታውቋል፡፡ ተጠርጣሪ ገዳይም ለጊዜው ማምለጡ ተጠቁሟል፡፡ ጉዳዩ በምርመራ ላይ በመሆኑ ፖሊስ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥቧል፡