Friday, June 27, 2014

የህወሓት ባለስልጣናት የመቀሌውን ሰላማዊ ሰልፍ ለማስቆም ሽርጉድ በማለት ላይ ናቸው።

ህወሓቶች የመቐለን ሰለማዊ ሰልፍ ለመከልከል ወስነዋል። 

(አብርሃ ደስታ)

  • 68
     
    Share
mekeleትናንት ሐሙስ ማታ (ከምሽቱ 4:30) አንድ የህወሓት ባለስልጣን ደውሎ እንደነገረኝ ከሆነ ህወሓቶች የመቐለን ሰለማዊ ሰልፍ ለመከልከል ወስነዋል። ትናንት ማታ አስቸኳይ ስብሰባ የተጠራው “ሰልፉ በመቐለ እንዳይካሄድ፣ እንዳታዋርዱን፣ የህዝቡን ስሜት መረዳት እንዴት ያቅታችኋል? ነገሮች ሳይበላሹ ሰልፉ በሆነ ምክንያት እንዲቀር አድርጉ! ተብሎ ተደውሎልናል” ብሎ ነገረኝ። ማን ለማን ነው የሚደውልለት? አልነገረኝም። ግን ከአዲስ አበባዎቹ ይሆናል ብለን እንገምት።

ህወሓት ሰልፉን ለመከልከል ወስኖ ከሆነ በጣም የሚያሳፍር ተግባር ነው። ከመጠን በላይ ፈርቷል ማለት ነው። የመቐለ ህዝብ ሰልፍ የማድረግ መብቱ ተነፈገ ማለት ነው። ድሮምውም ኮ የህዝብ ስሜት የሚያጤኑ የደህንነት ሰዎች በዝተዋል። ህዝቡ እንደሚሰለፍ ስለተረዱ ይሆናል። መረጃው ትክክል ከሆነ በቃ የትግራይ ህዝብ ሰለማዊ ሰልፍ የማድረግ መብት የለውም ማለት ነው።
ግን ሰልፉን መከልከላቸው በደብዳቤ እስኪያሳውቁን ድረስ ሰልፉ እንደሚካሄድ ነው ታሳቢ የምናደርገው። ዉሳኔው ትክክል ስለመሆኑ የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ያስፈልገናል። እውነት ግን ሰልፉ አይደረግም ብለው ደብዳቤ ሊሰጡን? አላምንም። ደብዳቤ ካልሰጡን ደግሞ ሰልፉ ይደረጋል። ስለዚህ እናያለን።

No comments:

Post a Comment