OCT 30, 14 • BY GPF •
የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ለ 90 ቀናት በተከታታይ በወታደራዊ፣ ፖለቲካዊ እና የመረጃ እና ደህንነት ትምህርቶች ያሰለጠናቸውን ታጋዮች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የተለያዩ የተቃዋሚ ድርጅቶች ተወካዮች በተገኙበት በደመቀ ሁኔታ አስመርቀ።
ህዝባዊ ሃይሉ ከዚህ በፊት 4 ተከታታይ ዙሮችን ያስመረቀ ሲሆን የዛሬው ለአምስተኛ ጊዜ ነው። በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የህዝባዊ ሃይሉ ዋና አዛዥ ኮማንደር አሰፋ ማሩ ‘’ህዝባዊ ሃይላችን በኢትዮጵያ ውስጥ የተንሰራፋውን ዘረኛና አፋኝ የወያኔ ስርዓት ከህዝብ እና ከሃገራችን ጫንቃ ላይ አስወግዶ በምትኩ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመገንባት ከተመሰረተ ጀምሮ ባለፉት ጊዚያት በርካታ ስራወችን በመስራት አስተማማኝ ድርጅታዊ አቋም ላይ ይገኛል’’ ብለዋል።
ኮማንደሩ አያያዘውም ‘’ይህን የአምስተኛ ዙር ምርቃት ከቀደምቶቹ የሚለየው የኢትዮጲያ ህዝብ አርበኞች ግንባር፣ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ እና የግንቦት 7 የፍትህ፣ የነጻነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ ተዋህደው ባንድ ድርጅት ጥላ ስር ትግላቸውን አስተባብረው ለመታገል የሚያደርጉትን የውህደት ሂደት የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ ያደረሱበት ወቅት ላይ መደረጉነው’ ብለዋል። በተጨማሪም ‘’ይህ የህዝባዊ ሃይላችን ስልጠና በግንቦት ሰባት ስም ከሚደረጉት ስልጠናወች የመጨረሻው ይሆናል ብለዋል።
በመጨረሻም ለተመራቂወች ባስተላለፉት መልዕክት ‘’ስልጠና ለአንድ ታጋይ የትግሉ የመጀመሪያ ምዕራፍ ሲሆን በስልጠና ላይ ያገኛችሁትን ትምህርት በተግባር ለቆምንለት ዓላማ እና ተልዕኮ በቁርጠኝነት እንደምታውሉት ሙሉ እምነቴን እገልጻለሁ‘’ ካሉ በኋላ ለስልጠናው መሳካት የተለያዩ ድጋፎችን ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
No comments:
Post a Comment