Monday, November 17, 2014

የአዲስ አበባ ፓርቲ ብቻ ሆኖ ለዉጥ ማምጣት አይቻልም።

የሚሊየነሞች ድምጽ – በትግራይ እና በኦሮሚያ ክልሎች አንድነት መዋቅሩን እያጠናከረ ነው

በቅርቡ የአንድነት ፓርቲ በመቀሌ ከተማ ጽ/ቤቱን መክፈቱ ተዘግቧል። በተመሳስይ ሁኔታ በኦሮሚያ የምስራቅ ሸዋ ዞን ፣ በአዳማም በአዲስ መልኩ የዞኑ ጽ/ቤት ተከፍቷል። የምስራቅ ሸዋ ዞን በዉስጡ 11 ወረዳዎች ያሉት ሲሆን የዞኑ ወረዳዎችን በሙሉ ለለዉጥ፣ ለአንድነት ለማስቀሳቀስ ሥራ ተጀምሯል።

የአዲስ አበባ ፓርቲ ብቻ ሆኖ ለዉጥ ማምጣት አይቻልም። በአገራችን ለዉጥ እንዲመጣ የለዉጥ ባለቤት የሆነውን መላው የኢትዮጵያን ሕዝብ ማደራጀትና ማንቀሳቀስ ያስፈልጋል። የአንድነት ፓርቲ እያደረገ ያለው ይሄንን ነው።
አንድነት ፓርቲ ከሚያደርገው እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ፣ የፍኖት ጋዜጣ ከአዲስ አበባ ዉጭ በአዳማ/ናዝሬትም ስትሸጥ ነበር። “የድሮው ተካ አዳራሽ የአሁኑ ሕብረት ባንክ አጠገብ ስንደርስ ሰዎች እጅብ ብለው አየን ጠጋ ስንል ምን ቢሆን ጥሩ ነው…ሰዉ ሁሉ የማንበብ ጥማት ይዞት ከርሞ ኖሮ ጋዜቶጦችን ያገላብጣል ይገዛል ፡፡ብዙዎቹ ስለ አሮሞ በዋና ገጧ ይዛ የወጣችውን የእኛዋን ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣን ገዝተው ሲሄዱ አይተን በጣም ተደሰትን!” ሲሉ የአዳማ/ናዝሬት አንድነቶች ግልጸዋል።

No comments:

Post a Comment