Wednesday, December 10, 2014

ፖሊስ እስረኞቹን ነጥሎ ለማጥቃት እየጣረ ነው


‹‹አብረውን የታሰሩት ካልተፈቱ ብቻችን አንወጣም፡፡›› ሴት እስረኞች
ፖሊስ በሰላማዊ ሰልፉ ወቅት ታፍሰው የታሰሩትን አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎችን ነጣጥሎ ለማጥቃት ጥረት እያደረገ መሆኑን የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት አቶ ዮናታን ተስፋዬ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ በሰልፉ ወቅት ከታሰሩት መካከል በዛሬው ዕለት አብዛኛዎቹ ሴት ታሳሪዎችና የተወሰኑ ወንዶች ብቻ የመታወቂያ ዋስ አምጥተው እንዲወጡ የተነገራቸው ቢሆንም ታሳሪዎቹ ‹‹አብረውን የታሰሩት ካልተፈቱ በስተቀር ብቻችን አንወጣም፡፡›› እንዳሉ ተሰምቷል፡፡

በጉዳዩ ያነጋገርናቸው አቶ ዮናታን ተስፋዬ ‹‹ፖሊስ በተመሳሳይ ወንጀል ያዝኳቸው ያላቸውን ሰላማዊ ታጋዮች አንዱን በመታወቂያ ዋስ ውጣ ብሎ ሌላውን አስሮ በማቆየት ልዩነት የፈጠረው በዚህ አጋጣሚ ያሰጉኛል የሚላቸውን አመራሮችና ግለሰቦች ለማጥቃት ቀዳዳ እየፈለገ እንደሆነ ያሳያል›› ሲሉ ገልጾልናል፡፡
ለአዳሩ ሰልፍ ቅስቀሳ ላይ እያሉ በተመሳሳይ ጉዳይ ታስረው ከነበሩትን የሰማያዊ ፓርቲ አባላት መካከል አንዳንዶቹን በመፍታት ስጋት ይፈጥሩብኛል ብሎ የሚያስባቸውን በተለይም የፓርቲውን አመራሮች አሁንም ድረስ አስሮ እንደሚገኝ በመግለጽ ስልቱ የተለመደ ነው ያሉት አቶ ዮናታን አሁን በአንድ በኩል እየደረሰበት ያለውን ጫና ለማርገብ የተወሰኑትን በመፍታት አመራሮቹን ለማጥቃት የተደረገ ስልት ነው ብለዋል፡፡
ገዥው ፓርቲ በሰልፉ ላይ በተገኙት አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች ላይ በፈጸመው ጭካኔ ከደረሰበት ጫና በተጨማሪ ሰላማዊ ሰልፉ ላይ ከተያዙበት ጊዜ ጀምሮ በሚፈጸምባቸው በደል አዲስ አበባ ፖሊስ (ሶስተኛ) የሚገኙት እስረኞች ዛሬ ታህሳስ 1/2007 ዓ.ም የርሃብ አድማ መጀመራቸውና ፖፖላሬ የሚገኙትም እስር ቤት ሆነው ትግላቸውን እንደሚያጠናክሩ መግለጻቸው ስርዓቱን ጫና ውስጥ እንደከተተው የገለጹት የህዝብ ግንኙነቱ ፖሊስ በህገ ወጥ መንገድ የያዛቸውንና ጭካኔ የፈጸመባቸውን ሁሉንም እስረኞች ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታና መነጣጠል ሊፈታ ይገባል ብለዋል፡፡
ከነገረ  ኢትዮጲያ

በፍቃዱ አበበ ወደ ቂሊንጦ ተዛወረ፡፡



በ‹‹ሽብርተኝነት›› ተከሶ ለሶስት ወር ያህል ማዕከላዊ እስር ቤት የቆየው የሰማያዊ ፓርቲ የአርባ ምንጭ ሰብሰቢ አቶ በፍቃዱ አበበ ወደ ቂሊንጦ መዛወሩ ተነገረ፡፡ በዛሬው ዕለት የፓርቲው አባላት ወደ ማዕከላዊ በማቅናት በጠየቁበት ወቅት ፖሊስ በፍቃዱ አበበ ወደ ቂሊንጦ እንደተዛወረ ገልጸውላቸዋል፡፡
በሌላ በኩል ከሰላማዊ ሰልፉ በፊት ታፍና የታሰረችው ወይንሸት ንጉሴ የምትገኝበት ቤላ 18 ተብሎ የሚጠራ እስር ቤት ‹‹ሰማያዊ ናችሁ›› ተብለው ተጨማሪ ሴቶች መታሰራቸውንም ለማወቅ ተችሏል፡፡

Tuesday, December 9, 2014

ዴሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጲያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ አቋም መግለጫ ፡፡

 DCESON    DCESON


ዴሞክራሲያዊ ውጥ በኢትዮጲያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ  ከተቋቋመበት አላማዎች አንዱና ዋነኛው በሃገራችን  በኢትዮጲያ ያለውን ኢፍትሃዊ የአንድ ዘር የበላይነት የሰፈነበትን አምባገነን  ስርሃት በማውገዝ እንዲሁም በመታገል ዴሞክራሲያዊ ኢትዮጲያን ማለትም  የዜጎችን እኩልነት የተረጋገጠባት፣  የህዝብ የስልጣን ባለቤትነት የተረጋገጠባት ፣ የዜጎች ሰብአዊ መብት የተከበረባት ፣  የህግ የበላይነት የሰፈነባት፣ እንዲሁም  ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በኩል አይን የሚታይባት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጲያን ለመገንባት የሚደረገውን ህዝባዊ ትግል መደገፍና ብሎም በአጋርነት ሞቆም ነው፡፡

ስለሆነም ባሳለፍነው ሳምንት ማለትም ህዳር 27/28 የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የሃገሪቱ ህገ- መንግስት በሚፈቅደው መሰረት  ለሃያ አራት ሰአት የሚቆይ ሰላማዊ ሰልፍ ጠርተው እንደነበረ ይታወሳል፡፡ ሆኖም በማን አለብኝ ሃገሪቱን እንዳሻው የሚያደርግ ህውሃት(ኢህአዴግ)አሁን በህብረተሰቡ ዘንድ የተፈጠረውን የለውጥ ስሜት እንዲሁም ለዚህ ክስተት ምክኒያት ናቸው ያላቸውን የ9ኑ ፖርቲዎች ትብብር ከመቼውም በላይ ስላሰጋው ከላይ  በተጠቀሰው ቀን የአደባባይ የ24 ሰአት ሰልፍ እንዳይካሄድ የትብብሩን አምራሮችና አባላትን በማዋከብ ስራ በዝቶበት ሰንብቷል፡፡

በመጨረሻም በሰልፉ ላይ የተገኙ የ9ኙ ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮችና አባሎችን እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ፍርሃት ባሸበረው ህውሃት (ኢህአዴግ)በጭካኔ ተደብድበዋል፣ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፣ ተግዘው ታስረዋል፡፡ ሙስሊሙ ማህበረሰብ  በሰላማዊ ሰልፉ ላይ በመገኝታቸው ብቻ ከጎዳና ታፍሰው የአገዛዙ አረመኔዊ እርምጃ ሰለባ ሆነዋል፡፡ እስካሁንም በዚሁ ዘረኛና አረመኔያዊ አገዛዝ ቁጥራቸው ከ300 የሚበልጡ  ሰላማዊ ታጋዮች በእስር ቤት ታፍነውከፍተኛ ድብደባ ደርሶባቸዋል ፡፡
ዴሞክራሲያዊ ውጥ በኢትዮጲያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ  አምባገነኑ ህውሃት(ኢህአዴግ) በሰላማዊ ታጋዮች እንዲሁም በሰላማዊ መንገድ ድምጻቸውን ሊያሰሙ በወጡ ዜጎች ላይ የወሰደውን አረመኔያዊ እርምጃ በጥብቅ እያወገዘ የ9ኙ ፖርቲዎች ትብብር እያደረገ ያለውን እልህ አስጨራሽ ትግል በንቃት የሚከታተልና ከጎናችሁ መቆሙን እየገለጸ ለተጀመረው የነጻነት ትግል አጋርነቱን ይገልጻል፡፡
ድል ለኢትዮጲያ ህዝብ!!!!!
ዴሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጲያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ !!

በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የተካሄደውን ድብደባና እስራት እናወግዛለን


ህዳር 27፣ 2007

 ቅዳሜ ህዳር 27 ቀን 2007 ዓ. ም (ዲሴምበር 6፣ 2014) በዘጠኝ ተቃዋሚ ድርጅቶች አስተባባሪነት በአዲስ አበባ ተጠርቶ በነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የህወሀት/ ኢህአዴግ አገዛዝ የጸጥታ ሰራዊት ህዝቡን በዱላ በመደብደብና ብዙዎችን ወደ  እስር በመወርወር ሰላማዊ ሰልፉን በትኗል። 
የዚህ ግፍ ሰለባ ከሆኑት ውስጥም የትብብሩ ሰባሳቢ ኢንጅነር ይልቃል  እነደሚገኙበት ታውቋል። ይህን ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት ሽንጎው አጥብቆ ያወግዛል። በግፍ የታሰሩት ሁሉ ባስቸኳይ እንዲፈቱም ይጠይቃል።  –-[ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]—