Tuesday, February 25, 2014

የስዊስ አቃቢ ህግ የረዳት ሃይለመድህን አበራን ሰብአዊ መብቶች ያከብራል ሲሉ ቃል አቀባዩዋ ተናገሩዊ።




ኢህአዴግ ክፉ መንግስት ነው...!!ወደ ድሬዳዋ እንኳን መጣችሁልን እንጂ አብረናችሁ እንታገላለን፤ ለነጻነታችን ለመታገል ሞትን አንፈራም››

ድሬዎች ለሰማያዊ ፓርቲ፡ “ኢሕአዴግ ክፉ መንግስት ነው፤ አብረናችሁ እንታገላለን”


*‹‹ወደ ድሬዳዋ መጥታችሁ ስላነጋገራችሁን ደስ ብሎናል›› የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪዎች፤
ዘገባ በጌታቸው ሽፈራው
ድሬዳዋ፡- ሰማያዊ ፓርቲ (ሰማያዊ) በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮችና በፓርቲው የትግል አቅጣጫ ዙሪያ ከድሬዳዋ ከተማ ነዋሪዎች ጋር የካቲት 16 ቀን 2006 ዓ.ም በከተማዋ ተገኝቶ ባደረገው ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ተወያየ፡፡
በስብሰባው ላይ ፓርቲው እስካሁን ያደረጋቸውን ህዝባዊ ትግሎችና ያስገኛቸውን ዋና ዋና ውጤቶች በድርጅት ጉዳይ ኃላፊው አቶ ጌታነህ ባልቻ በኩል ለነዋሪዎች ገለጻ አድርጓል፡፡ በተጨማሪም በፓርቲው ሀገራዊ አላማና የፖለቲካ ፕሮግራም ዙሪያ ለከተማዋ ነዋሪዎቹ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡



‹‹ወደ ድሬዳዋ ከተማ መጥታችሁ ስላነጋገራችሁን ደስ ብሎናል›› ያሉት የከተማዋ ነዋሪዎች፣ ‹‹ምርጫ ሲደርስ ብቻ ወደ እኛ የመምጣቱን የቆየ ልምድ ሰብራችሁ ከአሁኑ ራሳችሁን ስላስተዋወቃችሁንና የትግል አጋራችሁ እንድንሆን ስለፈቀዳችሁ እናመሰግናለን›› ብለዋል፡፡ በስብሰባው ላይ የተገኙ አንድ አስተያየት ሰጭ በድሬዳዋ ከተማ ስላለው ወቅታዊና የፖለቲካ ሁኔታ አንስተው፣ በኢህአዴግ አገዛዝ የድሬዳዋ ነዋሪዎች እየደረሰባቸው ያለውን በደል አጋልጠዋል፡፡

‹‹ኢህአዴግ የማይገባበት ነገር የለም፤ ወዳጅ መስሎ በመሐላችን እየገባ ያጣላናል፡፡ ኢህአዴግ ክፉ መንግስት ነው፡፡ እንኳን መጣችሁልን እንጂ አብረናችሁ እንታገላለን፤ ለነጻነታችን ለመታገል ሞትን አንፈራም›› ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
በድሬዳዋው ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ከህዝቡ በርካታ ጥያቄና አስተያየቶች የተሰነዘሩ ሲሆን በፓርቲው ከፍተኛ አመራሮችም ምላሽ ተሰጥቷቸዋል፡፡ የድሬዳዋ ነዋሪዎች መሬትን፣ ብሄር ብሄረሰብን፣ ሰንደቅ አላማን፣ የታሰሩ ጋዜጠኞችንና ፖለቲከኞችን፣ ምርጫ-2007ን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የውህደት አጀንዳን እና ሌሎች በርካታ አንኳር ጉዳዮችን አንስተዋል፡፡

የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በተለይ የብሄር ብሄረሰቦችን መብት በተመለከተ ‹‹በኢትዮጵያ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እንዳሉ እንገነዘባለን፡፡ ነገር ግን ፓርቲያችን በግለሰብ ነጻነትና መብት ያምናል፡፡ ምክንያቱም የግለሰብ መብት ከተከበረ የቡድን መብትም አብሮ እንደሚከበር እናውቃለን፡፡ እስኪ ለአብነት የግለሰብ መብት ተከብሮ የቡድን መብት የማይከበርበት ሁኔታ ካለ እናንሳ…የለም፡፡ ስለዚህ ትኩረታችን በግለሰብ መብት መከበር ከሆነ የቡድን የሚባሉ መብቶችም አብረው መከበራቸው እሙን ነው›› በማለት አስረድተዋል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ‹ሞደሬት ሊብራሊዝም› አይዶሎጅን እንደሚያራምድ የተናገሩት ሊቀመንበሩ፣ የመሬትና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ከዚህ መነሻነት የተቃኙ እንደሚሆኑ ጠቅሰዋል፡፡ ኢ/ር ይልቃል ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር ያላቸውን ግንኙነት በተመለከተም ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ‹‹ሰማያዊ አብሮ በመስራትና በትብብር ያምናል፡፡ ነገር ግን ሁሌም ምርጫ ሲደርስ እንደሚደረገው በሩጫ ወደ ውህደት ለመግባት አንፈልግም፡፡ ካለፉት የሌሎች ተሞክሮዎች ብዙ ተምረናል፡፡›› ብለዋል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ድሬዳዋ በነበረው ቆይታ በዚያው የከፈተውን ቢሮና የአካባቢውን መዋቅር የማስተዋወቅና የማጠናከር ስራም ሰርቷል፡፡ ፓርቲው በሌሎች ከተሞችም ተመሳሳይ ስራ መስራቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሏል፡፡

Sunday, February 23, 2014

ከባዶ ጭንቅላት ባዶ እግር ይሻላል!!

ከ15 ሺህ ህዝብ በላይ የተሳተፈበት ሰላማዊ ሰልፍ በባህር-ዳር [ፎቶ]

February 23, 2014
የተለያዩ መፈክር ያነገቡ ሰልፈኞች በባህር ዳር የአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት አካባቢ በመገኘት ሰልፉን ሲጠባበቁ ነበር በአሁኑ ሰዓት ከ15 ሺህ የሚበልጥ ህዝብ ሰልፉን ተቀላቅሏል:: የአንድነት ፓርቲ ፕሬዝዳንት ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው፣ የመኢአድ ፕሬዝዳንት አቶ አበባው መሃሪ እንዲሁም የትብብር ለዴሞክራሲ ሰብሳቢ አቶ ግርማ በቀለ እንዲሁም የአንድነት ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አንጋፋው ፖለቲከኛ ዶ/ር ኃይሉ አርአያን ጨምሮ ሰልፉን በቀዳሚነት እየመሩ ይገኛሉ::
በአማራ ክልል የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የብአዴን ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አለምነው መኮንን በአማራ ህዝብ ላይ የሰነዘሩትን ዘለፋ በመቃወም ነው የባህር ዳር ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ ሰላማዊ ሰልፍ ያደረገው።
ድል የህዝብ ነው!! ኢትዮጵያዊ አንድነታችን ከልዩነታችን በላይ ነው!!  ከባዶ ጭንቅላት ባዶ እግር ይሻላል!!  ብአዴን የአማራውን ሕዝብ አፍኖ መግዛት ያቁም!! የኢሀደግ አምባገነን አገዛዝ ሰልችቶናል!! የሚሉ መፈክሮችን እያሰሙ ይገኛሉ።




 
   
             

Friday, February 21, 2014

የብአዴኑ ባለስልጣን የተናገሩትን በመቃወም በባዶ እግራቸው በከተማዋ በመዘዋወር ለህዝቡ ግንዛቤ እየፈጠሩ ነው።

በባህርዳር የአንድነትና የመኢአድ ደጋፊዎች ጫማቸውን በማውለቅ ተቃውሟቸውን ገለጹ፤ ለእሁዱ ሰልፍ ቅሰቀሳው ቀጥሏል



ብአዴን እና አመራሮቹን በመቃወም እሁድ የካቲት 16 በባህር ዳር ከተማ በአንድነትና በመኢአድ ለተጠራውን የተቃውሞ ሰልፍ የአንድነት ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴና የብሔራዊ ምክር ቤት አባላት ለመቀስቀስ ዛሬ ወደ ባህር ዳር ማቅናታቸውን የአንድነት የዜና ምንጮች ለዘ-ሐበሻ በላኩት መረጃ ላይ አስታውቀዋል። እንደ አንድነት የዜና ምንጮች ገለጻ እሁድ ለሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ቅስቀሳው በሰፊው የቀጠለ ሲሆን በኢሕአዴግ በኩል የሚፈጸምባቸው ትንኮሳም በዛው ልክ በሰፊው ቀጥሏል ብለዋል።

“በረዳት አንስፔክተር ክንፈ ሀይሌ ጉልላት የሚመራ የፖሊስ ሀይል በተለምዶ ከአባይ ማዶ በሚባለው አካባቢ የመኪና ላይ ቅስቀሳ እናዳይደረግ ማይክራፎን መበስበር ጭምር ሙከራ ማድረጉን” የገለጹት የአንድነት የዜና ምንጮች የከተማዋ ነዋሪዎች ግን የፖሊሶቹንና የትራፊኮቹን ህገወጥ ድርጊት በማስቆም ተባብረዋል ብለዋል። አካባቢው “ተከብረሽ የኖርሽው በአባቶቻችን ደም እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይውደም” በሚለው ዜማ መድመቁን የገለጹት እነዚሁ የዜና ዘጋቢዎች ፖሊሶቹ ከህጉ ይልቅ ለአለቆቻቸው ታማኝነታቸውን እያረጋገጡ መሆናቸው ትዝብት ውስጥ ጥሏቸዋል ብለዋል። ህዝቡ የመኢአድ እና የአንድነት ደጋፊ የሆኑት ቀስቃሾቹ ሊነኩ አይገባም በማለት ተቃውሞውን ሲያሰማ ረዳት ኢንስፔክተሩ ተጨማሪ ሀይል እንዲመደብላቸው ትዕዛዝ ቢያስተላልፉም በህዝቡ ጫና የቅስቀሳ ቡድኑ ስራውን ቀጥሏል፤ ይህም የሚያኮራ ተግባር ነው ተብሏል።
ዘገባዎቹ እንደጠቆሙት በባህር ዳር የአንድነትና የመኢአድ አባላት ጫማ በማውለቅ በብአዴን ላይ ተቃውሟቸውን በመግለፅ ቅስቀሳቸውን የቀጠሉ ሲሆን፤ ይሄም በቅርቡ አቶ አለምነው መኮንን የአማራውን ሕዝብ ለመሳደብ የተጠቀሙበትን ቃል ለማስታወስና ምላሽ ለመስጠት እንደሆነ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ። በዛሬው እለት 14/06/2006 ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ የአንድነትና የመኢአድ አባላት በሞንታርቦ በመቀስቀስ ላይ ሲሆኑ በራሪ ወረቀት የሚያድሉ አባላት በፍፁም ቁርጠኝነት የብአዴኑ ባለስልጣን የተናገሩትን በመቃወም በባዶ እግራቸው በከተማዋ በመዘዋወር ለህዝቡ ግንዛቤ እየፈጠሩና በራሪ ወረቀቶችን እያደሉ ሲሆን የከተማው ነዋሪ በቁጭት አጋርነቱን እየገለፀ ይገኛል፡፡
በባህርዳር አቶ አለምነው መኮንን አማራውን ከተሳደቡ ወዲህ ብአዴን ከፍተኛ የሆነ ደጋፊ እንዳጣ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።

Thursday, February 20, 2014

ዛሬ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን .....!!

“ድምፁ የእኔ ነው ስድቡ ግን የእኔ አይደለም” አቶ አለምነው መኮንን
አንድነት እና መኢአድ የተሳዳቢው ባለስልጣን አቶ አለምነው መኮንን እንጀራ እናት የሆነችውን ብአዴንን ለመቃውም እሁድ በባህር ዳር ሰልፍ መጥራታቸው እንደተስማ፤
እኒያ የአማራ ህዝብ ምንትስ ነው… ቅብርጥስ ነው… ብለው በሞቅታ ውስጥ ያለ ሰው እንኳ የማይሞክረውን የስድብ ውርጂብኝ “በመረጣቸው” ህዝብ ላይ ያወረዱት ሰውዬ፤ ዛሬ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቀርበው። “ድምፁ የእኔ ነው ስድቡ ግን የእኔ አይደለም… ይህ የተደረገው በኮምፒውተር ቆርጦ ቀጥል ቴክኖሎጂ ነው…” ብለው መግለጫ ሰጥተዋል መባሉን ስሰማ ሮጬ ወደ ኢቲቪ ድረ ገጥ ሄጄ ያሉትን ለመስማት ሞከርኩ።
“ድምጹ የእኔ ነው…” የሚለው ከንግግራቸው ውስጥ ተቆርጦ ውጥቷል። “ተሳደበ ይሉኛል… እንዴት እሳደባለሁ… መራጮቼን… ወላጆቼን… ዘመዶቼን… ወገኖቼን… ምን በወጣኝ እና ምን ቆርጦኝ እሳደባለሁ…???” ብለው እኛኑ ሲጠይቁ የሚያሳየው ንግግራቸውን ግን ሰማሁት።
እንግዲያስ አቶ አለምነህ፤
አንደኛ የብዙሃኑም ጥያቄ ይሄው ነው… ይሄ ህዝብ ቅጥ ባጣ ድህነት እንዲኖር የተፈረደበት አንሶ ምን በድሎ ምን አጥፍቶ ይብጠለጠላል… ምን በወጣውስ ይሰደባል…???
ሁለትኛ አዩት አይደል መቁረጫ እና መቀጠያ ቴክኖሎጂው ያለው ኢቲቪ ቤት ነው…! በአደባባይ ተናግረው ዞር ከማለትዎ “ድምጹ የእኔ ነው” የሚለው የእምነት ቃልዎ ተስረዘልዎ!
ሶሰት… አራት…አምስት…. መቶ፤  ይሄንን ለሁሉም ኢህአዴጎች ንገሩልኝ፤
ወይ ልቦና ግዙ! ንስሃም ግቡ እና ተንበርከካችሁ ይሄን ህዝብ ይቅርታ ጠይቁ፤ ወይ ደግሞ “ማስተዳደሩን” ርግፍ አድርጋችሁ ትታችሁ ማደሪያችሁን ፈልጉ!

እኛ እንግዛ እነሱ ያልቅሱ......

መከላኪያ የህዝብ ወይስ የህወሓት?



ህወሓት ደርግን ማሸነፍ ማለት የኢትዮጵያ ህዝብን ማሸነፍ ማለት ነው ብሎ ስለሚያስብ ተግባሩ ሁሉ የንቀት፣ የማንቋሸሽና የማዋራድ ስራ እየፈፀመ ይገኛል። ሌላውን ትተን ጥቂት የሻዕቢያ ተላላኪ የሆኑትን የህወሓት መሪዎች የግንጠላ አጀንዳቸውን ይዘው በረሃ የሸፈቱበት ቀን ልክ የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም የትግራይ ህዝብ “ደደቢት ሂዳችሁ ታገሉሉኝ” ብሎ ወክሎ የላካቸው ይመስል “እኛ ታግለን ነፃ ስላወጣንህ እንደፈለግን እናደርጋሃለን” በማለት ዓይን አዉጣ በሆነ መንገድ ሰሞኑን “የካቲት 11 የትግራይ ህዝብ ዳግም ልደት ነው” እየተባለ በመከላኪያ ሰራዊት ታጅቦ በመከበር ላይ ስለሚገኘው የህወሓት አስቂኝ፣ አስገራሚና አሳዛኝ ድራማ የሚከተሉትን ጥቂት ነጥቦችን በአጭሩ እንመልከት።


የህወሓት ድራማ ቁጥር 1.
የህወሓት መሪዎች እናስተዳድራለን የሚሉት 90 ሚሊዮን የኢ/ያ ህዝብ ነው እየገዙ ያሉት። ከፍተኛ ባለስልጣናቱን ጨምሮ ካድሬዎቻቸው፣ አባላቶቻቸውና ደጋፊዎቻቸው በቀጥታም ሆነ በስውር እየጋጡ ያሉት የኢትዮጵያ ህዝብ ሀብት ነው። የገጠሩን ትተን በሀሪትዋ ዋና ዋና ከተሞች ቁልፍ ቦታዎችን በመያዝ 90 ከመቶ የትግራይ ባለሀብቶች የቢዝነስ እንቅስቃሴያቸውን የሚያካሂዱትና ባለቤት የሆኑት በሌሎች ክልሎች ነው። በአጠቃላይ የሀገሪትዋ ሀብት በተለያየ መልኩ የተቆጣጠሩት የህወሓት መሪዎች፣ ካድሬዎችና አጃቢዎቻቸው ናቸው። በመሆኑም በመሬት ላይ ያለው ህዝቡ የሚያውቀው ሐቅ ይህ ሆኖ ሳለ እነሱ የሚሉን ግን “የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ነን” ነው። ልብ በሉ!! ስልጣን ላይ ያሉት እነሱ። ሀገሪቱን የተቆጣጠሩት እነሱ። ሀገሪትዋን እየዘረፉ ያሉት እነሱ። ነገር ግን ነፃ እናወጣለን የሚሉት ህዝብ አንድ ክልል ነው። ታዲያ!! ቆም ብሎ ላሰበውና ላስተዋለው ሰው ይህ መንግስት ከኛ አብራክ የወጣ ኢትዮጵያዊ መንግስት ነው ለማለት ያስችላልን?።

የህወሓት ድራማ ቁጥር 2.
የትግራይ ህዝብ ኢትዮጵያን ከነ ባንዴራዋ ከፈጠሩት የታሪክ አስኳል አንዱ መሆኑን ዋቢ የሚያስፈልገው አይደለም። ቢያንስ አንድ ሶስተኛው የትግራይ ህዝብ በመላ ሀገሪቱ ከሌላው ወገኑ ጋር ተሳስሮ፣ ሀብት አፍርቶ፣ ተጋብቶና ተሰባጥሮ በነፃነት ይኖራል። በኢትዮጵያ የትግራይ ተወላጅ የሌለበት መንደር የለም ቢባል ማጋነን አይሆንም። ሲኖርም እንደ መጤ ወይም እንደ ስደተኛ አይደለም ራሱም ሆነ ሌላው ሰው የሚያስበው “ሀገሬ!! መብቴ!! ነው” በማለት በልበ ሙሉነትና በመተማመን ይኖራል። በሌላ አነጋገር ህዝቡ ለዘመናት በጋራ የኖሮው በመልካም ጉርብትና ብቻ ሳይሆን በራሱ ፈቃደኝነት በፍቅር፣ በወንድማማችነት፣ በመከባበርና በመተማመን ላይ የተመሰረተ ባንድ እናት ሀገር ጥላ ስር ተቃቅፎ ባህሪያዊ ዝምድናን በመመስረት ነው። ዛሬ 90 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ እሴት አለን የምንለውም ይኸው ነው።

ታዲያ!! ይህ ከሆነ ሐቁ የትግራይ ህዝብ ነፃ የሚወጣው ከማን ነው? ነፃ የሚያወጣውስ ማን ነው? እውነት ለራሱ ነፃ ያልወጣና የሻዕቢያ ሎሌ የሆነውን ዘራፊና ከሃዲ ድርጅት የትግራይ ነፃ አውጪ ነኝ ማለቱ ለታላቁ ህዝብ ውርደትና ሀፍረት አይሆንም ወይ? ለመሆኑ ባድመን ጨምሮ የትግራይን መሬትና ህዝብ የተደፈረው በሀይለ ስላሴ ግዜ ነውን? በሀይለ ስላሴ ስርዓት በትግራይ ምድር ሰው እንደ አራዊት በአደባባይ ተደብድቦስ ያውቃልን? ሀገርን እያፈረሱ ነፃ አውጪ ነኝ ማለቱስ የትግራይ ህዝብ ፍላጎትና ጥቅም መጠበቅ ማለት ነውን? በኢትዮጵያ ደረጃ ትክክለኛ ዲሞክራሲያዊ ስርዓትና ፍትሕ ሳይረገጋጥ በትግራይ ብቻ ትክክለኛ ለውጥ ሊረጋገጥ ይችላል ወይ? ህወሓት የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪና መድህን ቢሆን ኖሮ ህዝቡን ከሻዕቢያ ወረራ ያዳነው ማን ነው? እናንተ የትግራይ ነፃ አውጪ ነን ትላላችሁ ነገር ግን ሌሎች ከሰማንያ በላይ ብሄር ብሄረሰቦችስ ማን ነፃ ያውጣቸው?
አዎ!! ይህ ዓይነቱ ድራማና ጥያቄ ላለፉት ሶስት ዓሰርተ ዓመታት እንቆቁልሽ ሆኖ የቆየና ገና በሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ዘንድ በሆድ ውስጥ ታምቆ አንድ ቀን ሊፈነዳ የተቃረበ እሳተ ጎመራ መሆኑን አልጠራጠረም። ከላይ ለተጠቀሱት ጥያቄዎች ህወሓቶች መልስ ይሰጡኛል ብዬም አልጠብቅም። “ከኛ በላይ ወንድ የለም። ተልባ ቢንጫጫ በአንድ መውቀጫ። እኛ እንብላ እነሱ ይጩኹ። እኛ እንግዛ እነሱ ያልቅሱ። ያበጠው ይፈንዳ!! ብለው በንፁኃን ደም የሰከሩ፣ በፍቅረ ንዋይ ዓይናቸው የታወሩ፣ በቂም በቀል አእምሮዋቸው የደነዘዙና በጠባብነት ሻማ የተሸበቡ ካድሬዎችና መሪዎች ዛሬ ዊስኪ እየተራጩና ጮማ እየቆረጡ የልደት በዓላቸውን ቢያከብሩ ብዙም አዲስ ነገር አይደለም።


የህወሓት ድራማ ቁጥር 3.
የህወሓት መሪዎች ህዝቡን ለማታለል ከሚሰሩት ድራማ አንዱ በሀገሪትዋ ላይ ሕገ መንግስት፣ መድብለ ፓርቲ ስርዓት፣ ነፃ የመከላኪያ ኃይልና ፍትሕ መኖሩን ለማስረዳት ይሞክራሉ። እነዚህ መሰረታዊ መርሆዎች ለኢትዮጵያ ህዝብ ሳይሆን የአንድ ድርጅት ሞኖፓላዊ ስልጣን ለመጠበቅና ለማገልግል ሲባል ሌላ ቀርቶ ሰሞኑን የህወሓት መሪዎች ልደት ለማከበር እንዴት እንደሚጠቀሙበት ከሚከተሉት ጭብጦች መረዳት ይቻላል።
 ሕገ መንግስት አለ ይሉናል። ነገር ግን በሕገ መንግስቱ የሰፈሩ መብቶች ሌላ ዜጋ እንዳይጠቀምባቸው በተግባር ተገድበዋል። ሕገ መንግስቱ በነፃ መደራጀት ይፈቅዳል በነፃ መንቀሳቀስ ግን በሽብርተኝነት አዋጅ ተገድበዋል። ሕገ መንግስቱ የመናገርና የመፃፍ ነፃነት ይፈቅዳል ነገር ግን በህዝብ ሀብት የሚተዳደሩ የብዙሓን መገናኛ አውታሮች በአንድ ድርጅት በሞኖፓል ተይዟል። የፃፈ ወይም የተናገረ ዜጋ ሁሉ ሰፈሩ ቃሊቲ ወህኒ ቤት ሆኗል። ሕገ መንግስቱ ምርጫ ይፈቅዳል ነገር ግን የምርጫው መወዳደሪያ ሜዳ ተዘግቷል። በአጠቃላይ አንድ ድርጅት ራሱ ሕግ አውጪ፣ ራሱ ሕግ ፈፃሚ፣ ራሱ ገዳይ፣ ራሱ ከሳሽ፣ ራሱ ዳኛ የሆነበት ስርዓት ነው ያለው።

 በሀሪቱ መድብለ ፓርቲ ስርዓት አለ ይሉናል። ነገር ግን አውራ ፓርቲ ወይም ልማታዊ መንግስት በሚል ፓሊሲ ትርጉም ያለው ተቀናቃኝ የፓለቲካ ድርጅት እንዳይበቅል በሩ ተዘግቷል። በሕገ መንግስቱ ላይ አንድ ፓርቲ ከሌሎቹ ፓርቲዎች የበለጠ መብት እንዲኖረው ወይም በአውራ ፓርቲነት የሚፈርጅ አንቀፅ የለም። ነገር ግን ህወሓት ከሌሎቹ የተለየ መብት ያለው የበኩር ልጅ በመሆን የሀገሪትዋን ገንዘባዊ፣ ተቋማዊ፣ ማተሪያላዊና ሰብኣዊ ሀብት በቀጥታም ሆነ በተለያየ መልክ በመጠቀም በዓሉን ሲያከብር እናያለን። ሌላው ሀገር በቀል ኢትዮጵያዊ ድርጅት ያልተሰጠው መብት ለህወሓት ግን ከደደቢት በረሃ በመምጣቱና የመከላኪያ ሰራዊት ከጎኑ ስላሰለፈ ብቻ ሀገርንና ህዝብን እንደፈለገ እንዲንድ፣ እንዲዘርፍ፣ እንዲገድልና እንዲያፍን መብት ተሰጥቶታል።
 መከላኪያ ሰራዊት ከፓለቲካ ነፃ ነው፣ የሕገ መንግስት ዘብ ነው፣ የህዝብ ሰራዊት ነው፣ የልማት ሰራዊት ነው፣ ወዘተ ይሉናል። ነገር ግን በተግባር ሲታይ የአንድ ድርጅት ህወሓት ጠበቃና አጃቢ እንጂ የህዝብ ወገንና መድህን ሲሆን አላየንም። ለምሳሌ ሰሞኑን እንዳየነው ሁሉ የመከላኪያ ሰራዊት ሳምንት በሚል ሽፋኝ እየተካሄደ ያለው ሰልፍና ኤግዚቪሽን ሆን ተብሎ ከህወሓት ልደት ጋር የተያያዘ እንዲሆን ተደርጓል።
“አትረፍ ያለው በሬ ቆዳውን ለከበሮ ይውላል እንዲሉ” የትግራይ ህዝብ ላለፉት አርባ ዓመታት ያሳለፈውን መከራና ስቃይ እንዳይበቃው ዛሬም ከጀርባው አልወረዱም። እንደ ህዝብ መከበር ሲገባው በአንፃሩ ህወሓት ከሕግ በላይ በመሆን አማራጭ መንገዶችን በመዝጋት የአንድ ድርጅት አገልጋይ ሆኖ እንዲኖር ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል።
ስለዚህ ኢትዮጵያውያን በተለይም የትግራይ ወንድሞችና እህቶች በሙሉ!! ድርጅትና ግለ መሪዎች አላፊ ናቸው።ህዝብና ሀገር ግን ነባሪ መሆናቸውን አምነን ህዝባችንን ከጅብ ምንጋጋ እንዲላቀቅ እጅ ለእጅ ተያይዘን መነሳት አለብን እላለሁ። ዋስትናችን፣ መድህናችንና ጋሻችን አንድ ድርጅት ሳይሆን ታላቁ የኢትዮጵያ ህዝብ መሆኑን አማራጭ የሌለው የህልውና ጥያቄ ነው። ስለዚህ አንድ ድርጅት ወይም ግለሰቦች መምረጥ እንችላለን ነገር ግን አንዲት እናት ሀገር ነው ያለችን ሌላ አማራጭ የለንም።
ከበላይ ገሰሰ
Addera5021@yahoo.com

Wednesday, February 19, 2014

“ከሃገሬ የወጣሁበት ቀን በረዘመ ቁጥር፣ ሀገሬ ላይ በጣም ክህደት የፈፀምኩ ያህል ይሰማኛል” – ታማኝ በየነ (ቃለ ምልልስ ከተመስገን ደሳለኝ ጋር)



የዚህ ዕትም እንግዳችን ታዋቂው አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ ነው። ረዥም ጊዜያት በኪነ-ጥበብ ሙያ ላይ የቆየው ታማኝ፣ የደርግ መውደቅን ተከትሎ ኢሕአዴግ የአራት ኪሎውን ቤተ-መንግስት ከተቆጣጠረበት ዕለት (ግንቦት 20/1983 ዓ.ም) ጀምሮ በድፍረት የስርዓቱን አምባገነንነት፣ ፋፋይነት፣ በብሔራዊ ጥቅም ላይዝ ያለውን ቸልተኝነት… ጠቅሶ ተችቷል። ይህንንም ተከትሎ በደረሰበት ከባድ ጫና፣ እስርና ግርፋት ሀገሩን ለቆ ለመውጣት ተገድዷል። በስደት በሚኖርባት አሜሪካም ያለውን የተከፋፈለ የተቃውሞ ፖለቲካ አስተባብሮ ከመምራቱም በላይ በየጊዜው የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ የሚጠይቁና መሰል ሀገራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ የሚዘጋጁ የተቃውሞ ሰልፎችን አስተባብሮ መርቷል። በዚህም በመላው ዓለም በሚገኙ በርካታ ኢትዮጵያውያን ከበሬታን አትርፏል። አክትቪስት ታማኝ በየነ፣ ከተመስገን ደሳለኝ ጋር ያደረገው ቃለ-መጠይቅ እንደሚከተለው ተዘጋጅቷል።
Read Full Story in PDF/ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

Tuesday, February 18, 2014

ኢትዮጽያ ያለችበትን ችግር በዓለም ዙርያ ለማሳወቅ የተጠቀመበት ትልቅ አጋጣሚ ነው።


ሃይስኩል የጨረሰው በጣና ዓይቅ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ዕስትሬት A በማምጣት ያጠናቀቀው እና በአዲሰ አበባ ዩኒቨርስቲ ኢንጀነሪንግ ፋክልቲ 5 ዓመት የአርቴክቸር ኢንጅነሪንግ ተማሪ እያለ ልዩ የሆነው እልሙን ለሟሟላት የአብራሪነት ፈተናውን በመፈተን በሙሉ ነጥብ በማለፉ ምክንያት ነው ፓይለት መሆኑን ያረጋገጠው።
ዓስተዋይ እና ብሩህ ዓይምሮ ያለው፣ለሰሆች ባለው ዓክበሮት እና እርህራሄ የሚታወቀው ሃይለመድህን አበራ ሲሆን በትምህርት ደረጃቸው ከፍተኛ ነጥብ ባስመዘገቡ እና ተደላድለው በሚኖሩባት በባህር ዳር ከተማ በአከባቢው ሰው ትልቅ ከቤሬታ ባላቸው ቤተሰቦች ታቅፎ ያደገው  ነው።

ዛሬ ዓገራቸውን ሊጠቅሙ የሚችሉ ምሁራን በተለያዩ ችገሮች በመወጠራቸው ፣ አላግባብ በሚደርስባቸው ችግር እና ጫና ምክንያት መፍትሄ ባለማግኘታቸው እንዲሁም ህሊናን በሚነካ መንገድ ባለመገዛታቸው የሚደርስባቸው ከባድ የሆነ ችግር ብሎም ሂወታቸውን ለማዳን በሚያደርጉት ጥረት ዓገራቸው በከባድ ችግር ውስጥ እንደምትገኝ የሚያሳይ ድርጊቶች በየጊዜው ሲከሰቱ እናያለን።

የተለያዩ የዓለም መገናኛዎች ብዙሃን እንደዘገቡት ፌብራሪ 17/2014 ዓ/ም ሊነጋጋ ዓካባቢ የኢትዮጽያ ዓየር መንገድ የበረራ ቁጥሩ ET7 02 አይሮፕላን በረዳት ፓይለቱ አማካኝነት በመጠለፉ ሮም ውስጥ ያርፋል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው ይሄው በረራ ባልተጠበቀው መንገድ ጄኔቫ ለማረፍ ተገዷል ።የኢትዮጽያ መንግስት ከተለያዩ ነገሮች ጋር ሲያገናኘው የነበረው የዓይሮፕላን ጠለፉ  ከሽብርተኛነት ጋር እንደደመደሙት ተመልክተናል። የዚው ዓይሮፕላን ጠላፊ የሆነው ሃይለመድህን አበራ ከዚህ በፊት እንደተገለፀው በስነምግባር ታንፆ ጥሩ በሆነ አስተዳደግ ያደገ ጎልማሳ ነው።

ይህንን ድርጊት ሊያድርግ የቻለው የራሱ የሆነ በቂ ምክንያት ያለው ሲሆን እንደዚህ ዓይነት እርምጃ ሲወስድ ዛሬ በጣም በከፋ ችግር ምትገኘው ኢትዮጽያ በዓለም መንግስት ምንም ዓይነት ትኩረት ባለመግኘቷ ምክንያ ምን ዓልባት ዓገራችን ያለችበት ትልቅ ችግር በዚህ አጋጣሚ ለዓለም ለማሳወቅ እና ምንም ዓይነት ከአሸባሪሆች ጋር ንኪኪ ያለው ሰው እንዳልሆነ እና በተሳፋሪሆችም ላይ ምንም አይነት ችግር ሳይደርስባቸው በሰላም ማሳረፉ የኢትዮጽያ መንግስት እንደሚለው አሽባሪ አንዳልሆነ ያስገነዝበናል።

በርግጥ የኢትዮጽያ መንግስት ተጨባጭ ሆኖ ባልተገኘ ሁኔታ ለህዝቦቻችን የተምታታ መግለጫ በመስጠት ስልጣናቸውን መከታ በማድረግ በዓገራችን ላይ እያደረሱ ያለውን ከባድ ችግሮች ለመሸፋፈን የሚያቀነባብሩት ሚና እንድሆነ የሚያሳይ ግራ የተጋባ መግለጫዎች በመስጠት ላይ ይገኛሉ። ሃይለመድህን አበራ የተለያዩ አገሮች ቪዛ ያለው በመሆንኑ ያለምንም ችግር የፈለገው ዓግር ውስጥ ጥገኝነት መጠይቅ የሚችል አቅም ያለው መሆኑን ሁላችንም መገንዘብ እንችላለን ።

ዓገራችን የምትገኝበትን ከባድ ስቃይ፣መከራ፣ችግር፣ መታፈን፣ መገደል ፣ መታስር ፣ መሬታችን እየተሸነሸነ ለባእድ ሲሳይ ሲሆን ለወገኖቻችን ግን መንከራተት እና መሰቃየት እንዲሁም ተከባብረው እና ተሳስበው በፍቅር የሚኖሩትን ህዝቦቿን በከባድ የዘር ወጥመድ ማነቆ ውስጥ ለማስገባት የሚጥሩትን በዓለም ዙርያ በታሪኳ እና የቱሪስቶችን እይታ በመሳብ የምትታወቀውን ኢትዮጽያ ድምጥማጧን ለማጥፋት ቀን ከሌት የሚደክሙት ወገኖቻችን ላይ ኢሰባዊ ድርጊት እየፈጸሙ ዓገሪቷ ላይ በማን አለብኝነት እንዳሻቸው የሚኖሩትን በጭካኔአቸው እና በመጥፎ ምግባራቸው የመጀመርያ ደረጃ በመያዝ ዓገሪቷን እየጨቆነ የሚያስተዳድረውን ይሄንን ክፉ መንግስት ለዓለም ለማሳወቅ በሚችለው ዓቅም የትኛውም በሰው እና በቁሳዊ ነገሮች ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት ሳያደርስ ኢትዮጽያ ያለችበትን ችግር በዓለም ዙርያ ለማሳወቅ የተጠቀመበት ትልቅ አጋጣሚ ነው ማለት ይቻላል።
ከራሄል ኤፍሬም

Saturday, February 15, 2014

ሴቶች በፖሊቲካው ያላቸው ትልቅ ሚና...!!!

ገራችን በታሪክ ዘመኗ የብዙ ታላላቅ ሰዎችና የጀግኖች እናት እንደሆነች ታሪክ አበክሮ ይዘክራል ።                                             ከነዚህ ታላላቅና  ጀግኖች ቶቻችን በስተ ጀርባ ጠንካራነታችው፣ብልህነታቸው ከምንም በላይ ገር ወዳድነታቸው ሁሌም ልናስታውሳቸው የሚገባን ጠንካራ እናቶች እንደነበሩ ታሪክ አስቀምጦልናልየታሪካችን አመጣጥና የጀግኖቻችንን ዋነኛው ምክንያት አገራችን ከመውደድ እንዴውም ላገራችን ካላቸው ትልቅ አክብሮትና ፍቅር የመጣ መሆኑን ሁላችንም ልብ ልንን ይገባል።
                     ለቀባሪው አረዱት አይሁንብኝና !!
               ሰለ ውብ ታሪካችን ትንሽ አወጋችዋለው!!
  የታሪካችን አመጣጥ እጅግ  ማራኪ መላውን  ዓለም ያስደመመ  ሲሆን ፣ባለን ባህል እጅግ የምንኮራ ከባእድ የወረስነው ሳይሆን  ከራሳችንን የመነጨ ቱባ ባህል ያለን ድንግል መሬታችን  ከኛ  አልፎ  ለሌላው  ጥጋብ  ሊሆን የሚችል አንጡራ ሃብት ያለን ከዚህም በላይ ተሳስበው እና ተከባብረው የሚኖሩ  ሃይማኖቶችየተለያዩ  ቋንቋ ተናጋሪ ብሄር ቤረሰቦች ያሉባት  ታላቅ ገር ናት
ኢትዩጽያ ያከበራትን እጅግ የምታከብር ስትሆን ለተነኮሳት እና ሊከፋፍላት አስቦ ለመጣ ግን አዋርዶ የመመለስ አቅም ያላቸውና ለሃገራቸው ከወንድ የማይተናነሱ ብልህ ሴቶች እንዳሏት የሞሶሎኒ ውርደት አብይ ምሳሌን ነው
 ስለ ራችን ሴት ጀግኖች ሲነሳ ዛሬ በሙሉ ልብ ጀግንነታቸውን፣አገር ወዳድነታቸውን ፣ብልህ ነታቸውን ከምንም በላይ አይበገሬ ነታቸው መናገር እንድንችል ታሪክ አስቀምጦልናል  አገር ማለት ህዝብ ነው የሚለውን መርሆ ይዘው በመነሳት ሃገራቸውን እና ዝባቸውን አክብረውና ከጠላት ጠብቀው ለትውልድ ካስተላለፉ ከጀግኖች አባቶቻችን በተዳኝ ልጅን ከመንከባከብ እና ከማጀት ስራው  ጎን ለጎን ጀግና እንስቶች እንዳሉ ታሪክ ካስቀመጠልን ላገራቸው ያላቸውን ፍቅር በጀግንነት ካሳዩት መካከል ንደ ምሳሌ ጣይቱን ልንወስድ አንችላለ




    የዓገራችንን ጀግና አናቶች ታሪክ በመከተል ዛሬ እኛም ባለንበት ዘመን አገር ማለት ህዝብ መሆኑን የሚያምኑ ህዝብ ከሌለ አገር እንደሌለ ተገንዝበው ወገኖቻቸውን ሲዋረዱ፣ሲጨቆኑ ፣ሲራቡ ሰብአዊ  መብታቸው ሲገፈፍ፣የመናገር መብታቸው ሲገደብ፣ በየቦታው እሬሳቸው  የአሞራ ሲሳይ ሲሆን፣ድምጻቸው ሲታፈን ፣ነፃነታቸው ሲነጠቅ ማየት ያላስቻላቸውና የወገኖቻቸው መንገላታት የእግር እሳት የሆነባቸው የህዝባችን ህመም ያመናል፣ስቃያቸው ስቃያችን ነው ፣እውነት መታፈን የለባትም 
ብለው የወገኖቻቸውን ድምጽ በማስማታቸው እና ለእውነት ወግነው በመቆማቸው ብቻ ኢሰባዊ ድርጊትና ከፍተኛ ስቃይ እንዲሁም የሴት ልጅ  እርግዝና አመቺ በሆነበት ቦታ ላይ እንን እጅግ ፈታኝ  በሆነበት ሁኔታ ለነፃነታቸው በመቆማቸው ብቻ ጊዜ ዓቸውን  አስከፊ  በሆነው ስር ቤት  ውስጥ በአሰቃቂ ሁኔታ ሲወጡት ታይቷል። 
ኢትዮጽያ ላይ እንደ ወረርሽ  በመነሳት በህዝቦች እና በሃይማኖቶች መካከል የቆየ አብሮ የመኖር ,የመተሳሰብ እና የመቻቻል ድንቅ የሆነ የአኗኗር ዘይቤአችንን  ለማጥፋት  ሆን  ብሎ የተነሳው አምባገነኑ የህወሃት መንግስት የንጹሃንን ደም በማን አለብኝነት አፍስሷል ። 
የህወሃት ቡድን ብቻ የሚወክሉት  ፍጹም የኢትዮጵያዊነት ገፅታ በሌላቸው እንደመዥገር በኢትዮጵያዊያን አካል ላይ ተጣብቀው ደም በመምጠጥ የሀገሪቱን ግብአተ መሬት ለማስፈጸም  እና ለብዙ ወገኖቻችን እንደቅጠል መርገፍ ፣መንከራተት ፣ መዋረድና መበታተን ፣ በአሰቃቂ  ሁኔታ መሞት  በተለይም ለሴት ህቶቻችን ከዓገራቸው እርቀው ንዲሰቃዩና ለእይታ በሚከብድ ሁኔታ እንዲደፈሩ ፣ እንዲንገላቱ ፣እንዲሁም  ለተለያዩ ችግርና ስቃይ እንዲዳረጉ ሌት ተቀን የሚሰሩ  የወሮበላ ቡድን የሆነው የህወሃት  ለዚ ድርጊቱ ተጠያቂ ነውይህ ፈርጀ ብዙውን ኢትዮጵያዊ ደለከጉያው ለወጡት የትግራይን  ህዝብ  እንኳን  የማይወክል ጠባብ  እና ጎሰኛ  ቡድን ነው።

ባለቤቱን ካናቁ አጥሩን አይነቀንቁም ነው እና
ከቀድሞ ታሪካችን ምሳሌ በመውሰድ በዚዘመን ጀግና እንስቶች  እንዳሉንና አገራችን በባንዳ ስትታፈን አናይም ብለው መብታቸውን በመጠየቃቸው ብቻ ዛሬ  ቤተሰቦቻቸውን በትነው ክፉ ና ደጉን መለየት ያልቻሉ ልጆቻቸውን በዚህ  አፋኝ መንግስት ምክንያት ለማየትና ለማቀፍ ያልታደሉ በእስር የሚገኙ ለመብታቸው እና ለሃገራቸው ከቆሙት ኢትዮጽያዊያን መካከል በዋነኝነት ሊጠቀሱ የሚገባ ሴት ጀግና ኢትዮጽያዊያን ዛሬ በእስር ቤት እየተሰቃዩ ይገኛሉ።

በኛም ዘመን ጀግና ጣይቱ፣ጀግና ዘውዲቱ...ወ.ዘ.ተ እንዳሉን በማወቅ እኛም ከነሱ ምሳሌ በመውስድ ላገራችን በመቆም የመናገር መብታችንን በመጠቀም የወገኖቻችንን አይን እና ጆሮ  የሆነውን ኢሳትን በመርዳት እኛም እንደ ሴት ጀግኖች ወገኖቻችን ለሃገራችን በመቆም ሃገራችንን እና ህዝቧዋ ትከሻ ላይ ተቀምጦ አልወርድ ካላት ከዚህ  ክፉ መንግስት ለማላቀቅ የሴትነት ብልሃታችንን  እንደ ጥንት እንስት ጀግኖቻችን በመጠቀም ለሃገራችን ነፃነት ነገ ዛሬ ሳንል መነሳት ይኖርብናል።
ራሄል ኤፍሬም