Tuesday, February 18, 2014

ኢትዮጽያ ያለችበትን ችግር በዓለም ዙርያ ለማሳወቅ የተጠቀመበት ትልቅ አጋጣሚ ነው።


ሃይስኩል የጨረሰው በጣና ዓይቅ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ዕስትሬት A በማምጣት ያጠናቀቀው እና በአዲሰ አበባ ዩኒቨርስቲ ኢንጀነሪንግ ፋክልቲ 5 ዓመት የአርቴክቸር ኢንጅነሪንግ ተማሪ እያለ ልዩ የሆነው እልሙን ለሟሟላት የአብራሪነት ፈተናውን በመፈተን በሙሉ ነጥብ በማለፉ ምክንያት ነው ፓይለት መሆኑን ያረጋገጠው።
ዓስተዋይ እና ብሩህ ዓይምሮ ያለው፣ለሰሆች ባለው ዓክበሮት እና እርህራሄ የሚታወቀው ሃይለመድህን አበራ ሲሆን በትምህርት ደረጃቸው ከፍተኛ ነጥብ ባስመዘገቡ እና ተደላድለው በሚኖሩባት በባህር ዳር ከተማ በአከባቢው ሰው ትልቅ ከቤሬታ ባላቸው ቤተሰቦች ታቅፎ ያደገው  ነው።

ዛሬ ዓገራቸውን ሊጠቅሙ የሚችሉ ምሁራን በተለያዩ ችገሮች በመወጠራቸው ፣ አላግባብ በሚደርስባቸው ችግር እና ጫና ምክንያት መፍትሄ ባለማግኘታቸው እንዲሁም ህሊናን በሚነካ መንገድ ባለመገዛታቸው የሚደርስባቸው ከባድ የሆነ ችግር ብሎም ሂወታቸውን ለማዳን በሚያደርጉት ጥረት ዓገራቸው በከባድ ችግር ውስጥ እንደምትገኝ የሚያሳይ ድርጊቶች በየጊዜው ሲከሰቱ እናያለን።

የተለያዩ የዓለም መገናኛዎች ብዙሃን እንደዘገቡት ፌብራሪ 17/2014 ዓ/ም ሊነጋጋ ዓካባቢ የኢትዮጽያ ዓየር መንገድ የበረራ ቁጥሩ ET7 02 አይሮፕላን በረዳት ፓይለቱ አማካኝነት በመጠለፉ ሮም ውስጥ ያርፋል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው ይሄው በረራ ባልተጠበቀው መንገድ ጄኔቫ ለማረፍ ተገዷል ።የኢትዮጽያ መንግስት ከተለያዩ ነገሮች ጋር ሲያገናኘው የነበረው የዓይሮፕላን ጠለፉ  ከሽብርተኛነት ጋር እንደደመደሙት ተመልክተናል። የዚው ዓይሮፕላን ጠላፊ የሆነው ሃይለመድህን አበራ ከዚህ በፊት እንደተገለፀው በስነምግባር ታንፆ ጥሩ በሆነ አስተዳደግ ያደገ ጎልማሳ ነው።

ይህንን ድርጊት ሊያድርግ የቻለው የራሱ የሆነ በቂ ምክንያት ያለው ሲሆን እንደዚህ ዓይነት እርምጃ ሲወስድ ዛሬ በጣም በከፋ ችግር ምትገኘው ኢትዮጽያ በዓለም መንግስት ምንም ዓይነት ትኩረት ባለመግኘቷ ምክንያ ምን ዓልባት ዓገራችን ያለችበት ትልቅ ችግር በዚህ አጋጣሚ ለዓለም ለማሳወቅ እና ምንም ዓይነት ከአሸባሪሆች ጋር ንኪኪ ያለው ሰው እንዳልሆነ እና በተሳፋሪሆችም ላይ ምንም አይነት ችግር ሳይደርስባቸው በሰላም ማሳረፉ የኢትዮጽያ መንግስት እንደሚለው አሽባሪ አንዳልሆነ ያስገነዝበናል።

በርግጥ የኢትዮጽያ መንግስት ተጨባጭ ሆኖ ባልተገኘ ሁኔታ ለህዝቦቻችን የተምታታ መግለጫ በመስጠት ስልጣናቸውን መከታ በማድረግ በዓገራችን ላይ እያደረሱ ያለውን ከባድ ችግሮች ለመሸፋፈን የሚያቀነባብሩት ሚና እንድሆነ የሚያሳይ ግራ የተጋባ መግለጫዎች በመስጠት ላይ ይገኛሉ። ሃይለመድህን አበራ የተለያዩ አገሮች ቪዛ ያለው በመሆንኑ ያለምንም ችግር የፈለገው ዓግር ውስጥ ጥገኝነት መጠይቅ የሚችል አቅም ያለው መሆኑን ሁላችንም መገንዘብ እንችላለን ።

ዓገራችን የምትገኝበትን ከባድ ስቃይ፣መከራ፣ችግር፣ መታፈን፣ መገደል ፣ መታስር ፣ መሬታችን እየተሸነሸነ ለባእድ ሲሳይ ሲሆን ለወገኖቻችን ግን መንከራተት እና መሰቃየት እንዲሁም ተከባብረው እና ተሳስበው በፍቅር የሚኖሩትን ህዝቦቿን በከባድ የዘር ወጥመድ ማነቆ ውስጥ ለማስገባት የሚጥሩትን በዓለም ዙርያ በታሪኳ እና የቱሪስቶችን እይታ በመሳብ የምትታወቀውን ኢትዮጽያ ድምጥማጧን ለማጥፋት ቀን ከሌት የሚደክሙት ወገኖቻችን ላይ ኢሰባዊ ድርጊት እየፈጸሙ ዓገሪቷ ላይ በማን አለብኝነት እንዳሻቸው የሚኖሩትን በጭካኔአቸው እና በመጥፎ ምግባራቸው የመጀመርያ ደረጃ በመያዝ ዓገሪቷን እየጨቆነ የሚያስተዳድረውን ይሄንን ክፉ መንግስት ለዓለም ለማሳወቅ በሚችለው ዓቅም የትኛውም በሰው እና በቁሳዊ ነገሮች ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት ሳያደርስ ኢትዮጽያ ያለችበትን ችግር በዓለም ዙርያ ለማሳወቅ የተጠቀመበት ትልቅ አጋጣሚ ነው ማለት ይቻላል።
ከራሄል ኤፍሬም

No comments:

Post a Comment