ዓገራችን በታሪክ ዘመኗ የብዙ ታላላቅ ሰዎችና የጀግኖች እናት እንደሆነች ታሪክ አበክሮ ይዘክራል ። ከነዚህ ታላላቅና ጀግኖች አባቶቻችን በስተ ጀርባ ጠንካራነታችው፣ብልህነታቸው ከምንም በላይ በዓገር ወዳድነታቸው ሁሌም ልናስታውሳቸው የሚገባን ጠንካራ እናቶች እንደነበሩ ታሪክ አስቀምጦልናል ።የታሪካችን አመጣጥና የጀግኖቻችንን ዋነኛው ምክንያት አገራችን ከመውደድ እንዴውም ላገራችን ካላቸው ትልቅ አክብሮትና ፍቅር የመጣ መሆኑን ሁላችንም ልብ ልንን ይገባል።
ለቀባሪው አረዱት አይሁንብኝና !!
ሰለ ውብ ታሪካችን ትንሽ አወጋችዋለው!!
የታሪካችን አመጣጥ እጅግ ማራኪ መላውን ዓለም ያስደመመ ሲሆን ፣ባለን ባህል እጅግ የምንኮራ ከባእድ የወረስነው ሳይሆን ከራሳችንን የመነጨ ቱባ ባህል ያለን ድንግል መሬታችን ከኛ አልፎ ለሌላው ጥጋብ ሊሆን የሚችል አንጡራ ሃብት ያለን ከዚህም በላይ ተሳስበው እና ተከባብረው የሚኖሩ ሃይማኖቶች፣የተለያዩ ቋንቋ ተናጋሪ ብሄር ቤረሰቦች ያሉባት ታላቅ ዓገር ናት ።
ኢትዩጽያ ያከበራትን እጅግ የምታከብር ስትሆን ለተነኮሳት እና ሊከፋፍላት አስቦ ለመጣ ግን አዋርዶ የመመለስ አቅም ያላቸውና ለሃገራቸው ከወንድ የማይተናነሱ ብልህ ሴቶች እንዳሏት የሞሶሎኒ ውርደት አብይ ምሳሌአችን ነው።
ስለ አገራችን ሴት ጀግኖች ሲነሳ ዛሬ በሙሉ ልብ ጀግንነታቸውን፣አገር ወዳድነታቸውን ፣ብልህ ነታቸውን ከምንም በላይ አይበገሬ ነታቸው መናገር እንድንችል ታሪክ አስቀምጦልናል ። አገር ማለት ህዝብ ነው የሚለውን መርሆ ይዘው በመነሳት ሃገራቸውን እና ህዝባቸውን አክብረውና ከጠላት ጠብቀው ለትውልድ ካስተላለፉ ከጀግኖች አባቶቻችን በተጓዳኝ ልጅን ከመንከባከብ እና ከማጀት ስራው ጎን ለጎን ጀግና እንስቶች እንዳሉ ታሪክ ካስቀመጠልን ላገራቸው ያላቸውን ፍቅር በጀግንነት ካሳዩት መካከል እንደ ምሳሌ ጣይቱን ልንወስድ አንችላለን።

የዓገራችንን ጀግና አናቶች ታሪክ በመከተል ዛሬ እኛም ባለንበት ዘመን አገር ማለት ህዝብ መሆኑን የሚያምኑ ህዝብ ከሌለ አገር እንደሌለ ተገንዝበው ወገኖቻቸውን ሲዋረዱ፣ሲጨቆኑ ፣ሲራቡ ፣ሰብአዊ መብታቸው ሲገፈፍ፣የመናገር መብታቸው ሲገደብ፣ በየቦታው እሬሳቸው የአሞራ ሲሳይ ሲሆን፣ድምጻቸው ሲታፈን ፣ነፃነታቸው ሲነጠቅ ማየት ያላስቻላቸውና የወገኖቻቸው መንገላታት የእግር እሳት የሆነባቸው የህዝባችን ህመም ያመናል፣ስቃያቸው ስቃያችን ነው ፣እውነት መታፈን የለባትም
ብለው የወገኖቻቸውን ድምጽ በማስማታቸው እና ለእውነት ወግነው በመቆማቸው ብቻ ኢሰባዊ ድርጊትና ከፍተኛ ስቃይ እንዲሁም የሴት ልጅ እርግዝና አመቺ በሆነበት ቦታ ላይ
እንኳን እጅግ ፈታኝ በሆነበት ሁኔታ ለነፃነታቸው በመቆማቸው ብቻ ጊዜ ዓቸውን አስከፊ በሆነው እስር ቤት ውስጥ በአሰቃቂ ሁኔታ ሲወጡት ታይቷል።
ኢትዮጽያ ላይ እንደ ወረርሽኝ በመነሳት በህዝቦች እና በሃይማኖቶች መካከል የቆየ አብሮ የመኖር ,የመተሳሰብ እና የመቻቻል ድንቅ የሆነ የአኗኗር ዘይቤአችንን ለማጥፋት ሆን ብሎ የተነሳው አምባገነኑ የህወሃት መንግስት የንጹሃንን ደም በማን አለብኝነት አፍስሷል ።
የህወሃት ቡድን ብቻ የሚወክሉት ፍጹም የኢትዮጵያዊነት ገፅታ በሌላቸው እንደመዥገር በኢትዮጵያዊያን አካል ላይ ተጣብቀው ደም በመምጠጥ የሀገሪቱን ግብአተ መሬት ለማስፈጸም እና ለብዙ ወገኖቻችን እንደቅጠል መርገፍ ፣መንከራተት ፣ መዋረድና ፣ መበታተን ፣ በአሰቃቂ ሁኔታ መሞት በተለይም ለሴት ህቶቻችን ከዓገራቸው እርቀው እንዲሰቃዩና ለእይታ በሚከብድ ሁኔታ እንዲደፈሩ ፣ እንዲንገላቱ ፣እንዲሁም ለተለያዩ ችግርና ስቃይ እንዲዳረጉ ሌት ተቀን የሚሰሩ የወሮበላ ቡድን የሆነው የህወሃት ስብስብ ለዚ ድርጊቱ ተጠያቂ ነው።ይህ ስብስብ ፡ ፈርጀ ብዙውን ኢትዮጵያዊ አይደለም ከጉያው ለወጡት የትግራይን ህዝብ እንኳን የማይወክል ጠባብ እና ጎሰኛ ቡድን ነው።

ባለቤቱን ካናቁ አጥሩን አይነቀንቁም ነው እና
ከቀድሞ
ታሪካችን ምሳሌ በመውሰድ በዚዘመን ጀግና እንስቶች እንዳሉንና አገራችን
በባንዳ ስትታፈን አናይም ብለው መብታቸውን በመጠየቃቸው ብቻ ዛሬ
ቤተሰቦቻቸውን በትነው ክፉ እና ደጉን መለየት ያልቻሉ ልጆቻቸውን በዚህ አፋኝ መንግስት ምክንያት ለማየትና ለማቀፍ ያልታደሉ በእስር የሚገኙ ለመብታቸው
እና ለሃገራቸው ከቆሙት ኢትዮጽያዊያን መካከል በዋነኝነት ሊጠቀሱ የሚገባ ሴት ጀግና ኢትዮጽያዊያን ዛሬ በእስር ቤት እየተሰቃዩ
ይገኛሉ።
ራሄል ኤፍሬም
No comments:
Post a Comment