Friday, January 31, 2014

በጎንደር ክ/ሃገር ሳንጃ ወረዳ የልዩ ሃይል አዛዥ ሻለቃ ቀለሙ ክብረት መገደላቸው ተሰማ


(ዘ-ሐበሻ) በጎንደር ክ/ሃገር ሳንጃ ወረዳና አካባቢው ሕዝብን ሲያሰቃይ ነበሩ የተባለት የልዩ ሃይል አዛዥ ሻለቃ ቀለሙ ክብረት መገደሉ ተሰማ። የአርበኞች ግንባር ለግድያው ሃላፊነቱን ወስዶ “ግለሰቡ የተገደለው በጥር 21-2006 ዓ.ም ከቀኑ 12 ሰዓት ላይ በኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰርጎ ገቦች ማሰሮ ደንብ የተባለ ቦታ በጥይት ተደብድቦ ቆስሎ ወዲያውኑ ወደ ጎንደር ቸቸላ ሆስፒታል ቢወሰድም በማግስቱ ማለትም በጥር 22-2006 ዓ,ም ህይወቱ አልፏል።” ብሏል።


እንደ አርበኞች ግንባር ገለጻ ከሆነ “ይህ ግለሰብ በወረዳው የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን የአርበኞች ደጋፊ ናችሁ በሚል ሲያሰቃይ የነበረ ሲሆን፣ ብዙ ንፁሃን ግለሰቦችን በድርጅቱ ደጋፊነት ስም እየፈረጀ እንደገደለ፣ እንዳሰረና እንዲሰደዱ ሲያደርግ የነበረ መሆኑ ይታወቃል ። ይህን ተከትሎ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ግለሰቡ ከድርጊቱ ታቅቦ ሰላማዊ ኑሮውን እንዲኖር ካልሆነ ግን አስፈላጊው እርምጃ እንደሚወሰድበት የፅሁፍ መልዕክት የደረሰው ቢሆንም ሊታረም ባለመቻሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰርጎ ገቦች እርምጃ እንዲወስዱበት ተደርጓል።” ብሏል።


“በጎንደር አካባቢ ምንም አይነት ወታደራዊ እርምጃ በኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሠራዊት ሲወሰድ የአካባቢውን ሕዝብ ማንገላታቱ የተለመደ ቢሆንም ሻለቃ ቀለሙ ክብረት ከሞተበት ከትናንት ጀምሮ ግን በህዝቡ ከፍተኛ ስቃይ እያደረሰበትና ገዳዮቹን ታውቃላችሁ እናንተ ናችሁ እየደበቃችሁና ቀለብ እየሰፈራችሁ የምታስጨርሱን በሚል ብዙ ሰዎች እንደታሰሩ ታውቋል።” የሚለው የአርበኞች ግንባር ዜና “የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ወታደራዊ መምሪያ በበኩሉ ወደፊትም ቢሆን ወያኔና ተላላኪዎቹን ከዚህም በከፋ ሁኔታ አይቀጡ ቅጣት እንደሚቀጣ አስታውቆ ሕዝቡም ከመሬቱና ከንብረቱ እየተፈናቀለ መኖሩ ያበቃ ዘንድ ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት ጎን በመሰለፍ ይህን አፋኝ ስርዓት ለመገርሰስ የበኩሉን አስተዋፅዖ ማበርከት እንዳለበት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን” ብሏል።

በዚህ ዜና ዙሪያ የመንግስትን ምላሽ ለማካተት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

Thursday, January 30, 2014

በጎንደር የሰላማዊ ሰልፍ ቅስቀሳ ላይ የነበሩ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች እና ደጋፊዎች ታሰሩ


(ዘ-ሐበሻ) የፊታችን እሁድ በጎንደር ከተማ የሚደረገውን ሰላማዊ ሰልፍ በማስመልከት ሕዝቡ በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ወጥቶ ለሱዳን በሚሰጠው መሪት ዙሪያ ድርጊቱን እንዲቃወም በቅስቀሳ ላይ የነበሩ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች እና ደጋፊዎች በጎንደር ከተማ መታሰራቸው ተሰማ።
ዘ-ሐበሻ ከሰማያዊ ፓርቲ አካባቢ የደረሳት መረጃ እንደሚያመለክተው ዛሬ የታሰሩት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች እና ደጋፊዎች በጎንደር ሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያ ይገኛሉ።
ፖሊስ የሰልፉን ቀስቃሶች ካሜራ እና ላፕቶፖችን ጨምሮ ሌሎች ቁሳቁሶችን መውሰዱን የጠቆመው ከሰማያዊ ፓርቲ የተገኘው መረጃ ፖሊስ ዛሬ በቅስቀሳ ላይ የነበሩትን “እሁድ የሚደረገው ሰልፍ ሕጋዊ ፈቃድ ስለሌለው መቀስቀስ አትችሉም” ያላቸው ሲሆን አስተባባሪዎችም “በሕገመንግስቱ መሠረት ሰልፍ ለማድረግ ማስፈቀድ የለብንም። ቀድመን ማሳወቅ እንጂ። ይህን ደግሞ አድርገናል” ቢሉም ፖሊስ ማስተዋወቅ አትችሉም በሚለው አቋሙ ጸንቶ መደብደብ መጀምሩም ተሰምቷል።
የሰማያዊ ፓርቲ የጎንደር ሰልፍ አስተባባሪዎች እና ደጋፊዎች ከድብደባው በኋላ ወደ ሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደው መታሰራቸውንና ይህ መረጃ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ አለመፈታታቸውም ታውቋል።

ከ40ዎቹ ዝርዝር ውስጥ ኢትዮጵያ 25ኛ ላይ ትገኛለች፡፡

የ2014 የዓለም የመፈንቅለ መንግሥት ትንበያ

ኢትዮጵያ 25ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች
coup map
በያዝነው የአውሮጳውያን ዓመት ሊከሰቱ የሚችሉ የመፈንቅለ መንግሥት አደጋዎች ይፋ ሆኑ፡፡ በርካታዎቹ በአፍሪካ አገራት ሲሆኑ አደጋው ካንዣበበባቸው አገራት መካከል ኢትዮጵያ 25ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡
በአሜሪካ የፖለቲካ ሳይንቲስት የሆኑት ጄይ ዑልፌልደር የተለያዩ የሒሳብ ስሌቶችን በመጠቀም የ2014ዓም የመፈንቅለ መንግሥት ትንበያቸውን ሰጥተዋል፡፡ እንደ እርሳቸው ትንበያ ከሆነ 40 አገራት ቀይ የአደጋ ምልክት በርቶባቸዋል፡፡ ስለ ጉዳዩ ሲናገሩ መፈንቅለ መንግሥት እንዲሆን የሚመኙት ነገር ባይሆንም የመከሰቱ ጉዳይ ግን መነገር ያለበት ነው ይላሉ ምሁሩ፡፡
በተለያዩ የአሜሪካ አንጋፋ ጋዜጦች ላይ የተዘገበው ይኸው ጥናት እንደሚያመለክተው በዓለማችን ላይ 40 አገራት ከፍተኛ የመፈንቅለ መንግሥት አደጋ ያነጣጠረባቸው መሆናቸውን በጥናቱ ተገልጾዋል፡፡ አብዛኛዎቹም ከአፍሪካ መሆናቸው አሁንም አህጉሪቱ ለበለጠ ቀውስ የተጋለጠች መሆኗን የሚያሳይ ነው፡፡
forecast-dot-2014በቀዳሚነት የመፈንቅለ መንግሥት የሚያሰጋቸው አገራት ጊኒ፣ ማዳጋስካር፣ ማሊ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ኒጀር፣ ጊኒ ቢሳው እና ሱዳን፣ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፑብሊክና ደቡብ ሱዳን ናቸው፡፡ ከአውሮጳ ምንም አገር በዝርዝሩ ውስጥ ያልገባ ሲሆን ዩክሬይን አደጋው ጥላ ካጠላባቸው በቀዳሚነት የምትጠቀስ ሆናለች፡፡ ከወደ አሜሪካ ዩኳዶርና ሃይቲ ቀዩ የአደጋ ምልክት የታየባቸው ሲሆን ከእስያ ታላንድ፣ አፍጋኒስታን እና ፓኪስታንን ጨምሮ ስድስት አገራት የመፈንቅለ መንግሥት የቀይ ምልክት አደጋ ካለባቸው 40 አገራት ውስጥ ይገኛሉ፡፡
ከ40ዎቹ ዝርዝር ውስጥ ኢትዮጵያ 25ኛ ላይ ትገኛለች፡፡ በየጊዜው የሚወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ህወሃት/ኢህአዴግ ሥልጣኑን ለራሱ ታማኞች ብቻ በመከፋፈል እንዲያም ሲል በቤተሰብ ደረጃ በማውረድ እየሸነሸነው በመሆኑ ሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የበይ ተመልካች ሆኗል፡፡ ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ድርጅት ሰሞኑን ያወጣውን መረጃ ጠቅሶ አዲስ አድማስ ሲዘግብ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳሩ መጥበቡን እና የነጻው ሚዲያ ህልውና አደጋ ላይ መውደቁን ገልጾ ነበር፡፡
አፋኝ ሕጎችን በማውጣትና ማንኛውንም ዓይነት የግለሰብ መብት በመንፈግ በአንጻሩ ሊኖር የማይችል የቡድን መብት አስከብራለሁ የሚለው ህወሃት/ኢህአዴግ በተመሳሳይ የሚወጡ መረጃዎችን በማጣጣል ዋጋ ቢስ ሲያደርግ መቆየቱን የተለያዩ የሲቪክ ማኅበራትና የፖለቲካ ፓርቲዎች በየጊዜው የሚያነሱት ነጥብ ነው፡፡ በተቀረው ደግሞ “ልማት፣ ህዳሴ፣ ውዳሴ፣ … ” በማለት የለውጥ ሃሳብ ከመጣ የተጀመሩ የልማት ሥራዎች ይስተጓጎላሉ በሚል በሕዝቡ ዘንድ ማደናገሪያ በመፍጠር በአገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱትን የፖለቲካ ፓርቲዎች “ጸረ ልማት” በማለት እንደሚወነጅላቸው ያማርራሉ፡፡ በምርጫ ማጭበርበርና ማንኛውንም ፖለቲካዊ ሆነ ማኅበራዊ እንዲሁም ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴ በሙሉ ቁጥጥር ሥር ማዋል ኢህአዴግ በሥልጣን ለመቆየት የሚጠቀምባቸው ዓይነተኛ መንገዶቹ እንደሆኑ በስፋት ይጠቀሳል፡፡
ይህንን የመፈንቅለ መንግሥት ትንበያ የቀመሩት ምሁር ስሌታቸውን ለማቀናበር የተለያዩ መረጃዎችን መጠቀማቸውን ገልጸዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል የአገራቱ ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ፣ በቅኝ ግዛት የመያዝ ሁኔታ፣ የአገራቱ ዕድሜ፣ ከነጻነት በኋላ የኖሩበት ዓመታት፣ የፖለቲካ መረጋጋት፣ የእርስበርስ ግጭት፣ የነጻ ምርጫ ሁኔታ፣ የኢኮኖሚ ዕድገት፣ በየቀጣናው ያለ የመፈንቅለ መንግሥት እንቅስቃሴ፣ ወዘተ የተወሰኑት ናቸው፡፡ ይህንን አያይዘውም የመፈንቅለ መንግሥት ትንበያ ማድረግ የግድ መፈንቅለ መንግሥት ይሆናል ማለት እንዳይደለ ነገር ግን አደጋውን ተመልክቶ አስፈላጊ እርምጃዎች በመውሰድ እንዳይሆን መከላከል ዓይነተኛ አማራጭ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ (ካርታዎቹ የተወሰዱት ከጄይ ዑልፌልደር ብሎግ ነው)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ የዛሬ ዓመት የአሜሪካንን የደኅንነት ምክርቤት ጠቅሶ ባወጣው ዜና በ2030 እኤአ ከሚከሽፉ መንግሥታት (failed states) መካከል ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗን ዘግቦ ነበር፡፡ ዜናውን ከዚህ በታች በድጋሚ አትመነዋል፡፡

“በ2030 ከሚከሽፉ መንግሥታት አንዷ ኢትዮጵያ ነች”

ዘገባው የ15 አገራትን ዝርዝር አውጥቷል
የአሜሪካ የብሔራዊ የደኅንነት ምክርቤት እንደ አውሮጳውያን አቆጣጠር በ2030 የሚከሽፉ 15 መንግሥታትን (failed states) ዝርዝር አውጥቷል፡፡ “በግጭት መብዛትና በአካባቢ ጥበቃ ቀውስ ምክንያት” ይከሽፋሉ ተብለው ከተተነበዩት የአፍሪካ፣ የእስያና የመካከለኛው ምስራቅ አገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ ነች፡፡
እጅግ የነጠረ፣ ያልተዛባና የተጠና ዘገባ ለአሜሪካ የስለላ ተቋማት፣ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ አውጪዎችና ለዓለምዓቀፍ ግንኙነት ተመራማሪዎች በማውጣት የታወቀው የአሜሪካ ብሔራዊ የደኅንነት ምክርቤት ከተቋቋመ በርካታ ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ ምክርቤቱ በሚያወጣቸው ዘገባዎች የአሜሪካ መንግሥትም ሆነ የተለያዩ መ/ቤቶች ተጽዕኖ እንደማያደርጉበት የሚናገር ሲሆን፤ ዘገባዎቹንም ከአድልዎ እና ከአሜሪካ መንግሥት አቋም ነጻ በመሆን እንደሚያዘጋጃቸው ይናገራል፡፡
NICየም/ቤቱ ዘገባ በተለይ ምርጫ ከተካሄደ በኋላ ለመጪው ፕሬዚዳንት የወደፊቱን የዓለማችን መልክ ምን እንደሚመስል የመካከለኛና የረጅም ጊዜ ስትራቴጂካዊ አስተሳሰቦች እና ዓለምአቀፋዊ ዝንባሌዎች ላይ አቅጣጫ የሚጠቁም ትንበያ ያደርጋል፡፡ ለፕሬዚዳንቱ ዓለምአቀፋዊ የደኅንነት ዘገባ ያቀርባል፤ ለብሔራዊ የጸጥታ ምክርቤት እና ለአገር ውስጥ ደኅንነት መ/ቤት ምክር ያቀብላል፤ በአጠቃላይ የአሜሪካን የስለላና የደኅንነት ማኅበረሰብ ሊከተል በሚገባው ጉዳይ ላይ አቅጣጫ የሚያስይዝ ሃሳብ ያቀርባል፡፡
በዚሁም መሠረት ባለፈው የታህሳስ ወር “በ2030 የዓለም አቅጣጫ፡ አማራጭ አገራት” በሚል ርዕስ አንድ ዳጎስ ያለ ጥናት አቅርቧል፡፡ ይኸው 160ገጽ ያለው ዘገባ የዛሬ 17ዓመት የዓለማችን ገጽታ ምን እንደሚመስል ከየአገራቱ በተወሰደ ጥናትና እዚያው በሚገኙ ተመራማሪዎች የሰበሰበውን ያካተተ ነው፡፡ ዓለማችን የምታዘነብልባቸው ቀዳሚ ሁኔታዎች አንዱ ሰዎች በራሳቸው አነሳሽነት ድህነትን ለመቀነስ፣ በትምህርት ለማደግ፣ በቴክኖሎጂና በህክምና ለመራቀቅ እንዲሁም በገቢም የመካከለኛው መደብ ላይ ለመድረስ የሚያደርጉት ጥረት በከፍተኛ ሁኔታ ከተጠቀሱት አንዱ አቅጣጫ ጠቋሚ ነው፡፡
ሌሎቹ ዓለምን አንድ አድርጎ በመዳፉ ሥር የሚገዛ ኃይል የማይነሳ መሆኑ ከሚታዩት ከፍተኛ ዝንባሌዎች ተጠቃሽ ሲሆን አሜሪካ ምንም እንኳ “የዓለም ፖሊስ” የመሆኗ ሁኔታ የሚቀንስ ቢሆንም የዓለምን አቅጣጫ መቆጣጠሯ ይቀራል ማለት እንዳልሆነ ይጠቁማል፡፡ የዓለም የሕዝብ ቁጥር ከመጨመሩ አኳያ “እያረጁ” የሚሄዱ አገራት የኢኮኖሚ ዕድገታቸው እንደሚያሽቆለቁልና ከገጠር ወደከተማ ፍልሰት እንደሚጨምር፤ 60በመቶ የሚሆነው የዓለማችን ሕዝብ በከተሞች አካባቢ ኑሮውን እንደሚያደርግ ይተነብያል፡፡ በዚህም ምክንያት የውሃ፣ የምግብና የኃይል (ኤነርጂ) ፍላጎት ከሕዝብ ቁጥር መጨመር ጋር ተያይዞ በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያድግ ይናገራል፡፡ የቴክኖሎጂ ምጥቀትና የማኅበራዊ ሚዲያ አገልግሎትም የዓለማችንን አቅጣጫ እንደሚቀይር ያስረዳል፡፡
የቻይና እና የአሜሪካ ግንኙነት በስፋት እንደሚቀጥልና በበርካታ ፈርጆች ትብብርና ስምምነት እየፈጸሙ ሰፋ ያለ ዓለምአቀፋዊ ኅብረት እንደሚያደርጉ የሚናገረው ይህ ሪፖርት በየአገራቱ እየሰፋ የመጣው በድሃና በሃብታም መካከል ያለው ክፍተት የማኅበራዊ ቀውስ እንደሚያስከትል ይጠቁማል፡፡ ይህም ቀውስ በአንዳንድ አገራት ውስጥ እየሰፋ በመምጣት ለተባባሰ ግጭትና ክስረት እንደሚያጋልጥ የኑሮ ልዩነቱም የማኅበራዊ ቀውሱን ወደ ከፍተኛ ደረጃ እንደሚያደርሰው ይተነትናል፡፡ የሃይማኖት ሚና እንደሚጨምር የጠቆመው ዘገባ ይህንኑ ተከትሎ መካረርና ግጭት እንዲሁም አሸባሪነት ለመስፋፋት ሃይማኖት ምክንያት እየሆነ እንደሚሄድ ይናገራል፡፡
በዘገባው ከተነገረው በተጻጻሪ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ከተጠናቀቀ ወዲህ እስካሁን በ44 አገራት ጉዳይ በቀጥታና በተዘዋዋሪ መንገድ ጣልቃ በመግባት ጦርነት ያካሄደችው አሜሪካ የዓለም ኃያል ሆና እንደምትቀጥል በመናገር ሪፖርቱን የሚያጣጥሉ ጥቂቶች አይደሉም፡፡ እንደማስረጃም አድርገው አሜሪካ በተለያዩ አገራት ያላትን 737 የወታደራዊ ተቋማት ይጠቅሳሉ፡፡ ስለሆነም ዘገባው የአሜሪካ የበላይነት የመቀነሱን ጉዳይ አንስቶ የተናገረውን አይቀበሉም፡፡
እኤአ በ2030 የሚክሽፉት 15ቱ መንግሥታት (ፎቶ: ጂአይ)
ዘገባው የዓለማችንን የወደፊት ሁኔታ ሲተነብይ በዋንኛነት ከጠቀሳቸው ጉዳዮች አንዱ በ2030 የሚከሽፉ መንግሥታትን ዝርዝር ሰጥቷል፡፡ “በግጭት መብዛትና በአካባቢ ጥበቃ ቀውስ ምክንያት” የሚከሽፉ መንግሥታት ተብለው ከተጠቀሱት 15 አገራት መካከል ኢትዮጵያ እንዷ ስትሆን አፍጋኒስታን፣ ፓኪስታን፣ ባንግላዴሽ፣ ቻድ፣ ኒጀር፣ ማሊ፣ ኬኒያ፣ ቡሩንዲ፣ ሩዋንዳ፣ ሶማሊያ፣ ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ፣ ማላዊ፣ ሃይቲና የመን የተቀሩት ናቸው፡፡
ይሁንና ይኸው ም/ቤት እኤአ በ2015 ፓኪስታን የምትከሽፍ አገር ትሆናለች በማለት ትንቢት ሰጥቶ ይኸው እስካሁን አለች በማለት ዘገባውን የሚያጣጥሉ ክፍሎች ኢትዮጵያም ሆነ ሌሎቹ አገራት ለመክሸፋቸው በቂ ማስረጃ የለም በማለት የዘገባውን ጥቆማ ይቃረናሉ፡፡ በሌላ በኩል እንዲህ ያለው የመክሸፍ ሁኔታ ሊዋጥለት የማይችለው ኢህአዴግ “ህዳሴ፣ ውዳሴ” ከማለት ይልቅ ይህንን ጉዳይ አጥብቆ ሊያስብበት እንደሚገባና የሥርዓት መበስበስ አመላካች የሆነውን “የመንግሥት ሌቦች” መበራከት መፍትሔ ሊያበጅለት እንደሚገባ ደጋፊዎቹና አመራሩ በየጊዜው የሚያነሱት ነጥብ ነው፡፡
በዚሁ የኢትዮጵያ እንደ አገር የመክሸፍ ጉዳይ ላይ ያነጋገርናቸው አሁን ካላቸው ተግባር አኳያ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ በአውሮጳ የሚገኙ የፖለቲካና ዓለምአቀፋዊ ግንኙነት ተመራማሪ “ችግሩ የኢህአዴግ ብቻ ሳይሆን የተቃዋሚውም ነው” ይላሉ፡፡ “በአገር ውስጥ ያለው ተቃዋሚ ከውስጥ የሥልጣን ሽኩቻና ከስብሰባ/ውይይት ጋጋታ ባለፈ መልኩ ሕዝብን የሥልጣን ባለቤት ሊያደርግ የሚችል የተቀናጀና ውጤታማ ተግባር ሊፈጽሙ ይገባቸዋል” የሚሉት ምሁር በውጭ ያለውም “ከጊዜያዊና ጥቃቅን የራስ ክብር የመፈለግ አካሄድ በመላቀቅ ተጨባጭ ለውጥ የሚያመጣ ጡንቻውን በወያኔ ላይ ማሳረፍ ይጠበቅበታል” ብለዋል፡፡ “የደኅንነት ተቋሙ ባወጣው ዘገባ ላይ በግልጽ እንደተነበየው የማኅበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ የመጨመሩ ያህል በውጭ ያለው ኢትዮጵያዊ ይህንኑ ለውጥ ማምጣት የሚችል የዘመኑ ቴክኖሎጂ ለአሉባልታና ተራ የፖለቲካ ወሬ ከመጠቀም ይልቅ አገር ለማዳን ተግባር ሊጠቀምበት ይገባል” በማለት አስተያየታቸውን ደምድመዋል፡፡
የደኅንነት ምክርቤቱ ያወጣው ሙሉ ዘገባ እዚህ ላይ ይገኛል፡፡

Wednesday, January 29, 2014

በአፍሪካ መዲናዋ አዲስ አበባ ከጥቂት ወራት በፊት..........

የሞ ኢብራሂም ፋውንዴሽንና የአፍሪካ አምባገነን መሪዎች –
 ዘንድሮስ ተሸላሚ ያገኝ ይሆን ወይ?

በአፍሪካ መዲናዋ አዲስ አበባ ከጥቂት ወራት በፊት የሞ ኢብራሂም ፋውንዴሽን ኮንፈረንስ አዘጋጅቶ የነበረ ሲሆን ኮንፈረንሱ አፍሪካ ውስጥ ስላለው የመልካም አስተዳደርና ዲሞክራሲ በተመለከተ እንዲሁም አህጉሪቷ ወደፊት ስለሚኖሩዋት እድሎችና ስላጋጠሙዋት ችግሮች ከተለያዩ ሃገራት ከመጡ ፖለቲከኞ፤ ታዋቂ ግለሰቦችንና ጋዜጠኖችን ጨምሮ የተካሄደ ነበር።
ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ/ Read Full Story in PDF

በድሬዳዋ ክልል የኦሮሞ ኮንግረስ/ መድረክን በመወከል ተወዳድረው ነበር፡፡

“በዝዋይ የታሰሩት ባለቤቴ እዛው እስር ቤት መሞታቸውን ሕዝብ ይወቅልኝ” – ወ/ሮ ፈሪሃ አብድርሃማን


በዳዊት ሰለሞን


(ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ እንደዘገበው) አቶ አህመድ ነጃሽ ሐሰን በ2002 ዓ.ም በተደረገ አገር አቀፍ ምርጫ በድሬዳዋ ክልል የኦሮሞ ኮንግረስ/ መድረክን በመወከል ተወዳድረው ነበር፡፡የፖለቲካ ተሳትፏቸውን እንዲያቋርጡ በተለያዩ መንገዶች ሲነገራቸው ቢቆዩም በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞ ማሰማትና መደራጀት ህገ መንግስታዊ መብት መሆኑን በመጥቀስ ሲከራከሩ መቆየታቸውን ባለቤታቸው ወ/ሮ ፈሪሃ አብድርሃማን የሱፍ ለፍኖተ ነጻነት አስታውሰዋል፡፡

በ2003 የመንግስት የጸጥታ ሰዎች አቶ አህመድን በኦነግ አባልነት ተጠርጥረሃል በማለት ያስሯቸዋል፡፡የ57 አመቱ አህመድ ከታሰሩ በኋላ ለአራት ወራት ያህል በህይወት ይኖሩ ወይም ይሙቱ ለቤተሰብ ሳይታወቅ ከቆዩ በኋላ ፍርድ ቤት ቀርበው በኦነግ አባልነት ተከሰው ይፈረድባቸዋል፡፡ፍርዳቸውን ተከትሎም ለምርመራ ከቆዩበት ማዕከላዊ ወደ ዝዋይ ወህኒ ቤት እንዲዘዋወሩ ይደረጋሉ፡፡
ከአቶ አህመድ ነጃሽ ያገኟትን አንድ ልጅ ለብቻቸው የማሰደግ ዱብ ዕዳ የወደቀባቸው ወይዘሮ ፈሪሃ ገቢያቸው በመቋረጡ ስራ ፍለጋ ወደ አረብ አገር ያቀናሉ፡፡በአረብ አገር ያለሙትን ማግኘት ባለመቻላቸው ወደ አገር ቤት ይመለሳሉ፡፡ካልተሳካው ስራ ፍለጋ መልስ ወይዘሮዋ ባለቤታቸውን ለመጠየቅ ወደ ዝዋይ ሲያመሩ የማረሚያ ቤቱ ሃላፊዎች ባለቤታቸው ወደ ቃሊቲ መዘዋወራቸውን ይነግሯቸዋል፡፡

ከዝዋይ በቀጥታ ወደ ቃሊቲ በማምራትም ይጠይቃሉ፣ቃሊቲዎች እንዲህ አይነት እስረኛ ወደ እነርሱ አለመምጣቱን በመጥቀስ ያሰናብቷቸዋል፡፡ከብዙ የዝዋይና ቃሊቲ ምልልስ በኋላ አቶ አህመድ በጠና ታመው ምኒሊክ ሆስፒታል እንደገቡ ይነገራቸዋል፡፡ምኒልክ ሆስፒታል ለጥየቃ ባመሩበት ወቅት መጥፎውን ዜና ይሰማሉ፡፡አቶ አህመዲን ይህችን አለም ከተሰናበቱ ረዘም ያሉ ወራቶች ተቆጥረዋል የሚል፡፡
አስከሬን የለ፣ የት እንደተቀበሩና የሞታቸው መንስኤ ምን እንደነበር የሚያስረዳ የለ፣ ሁሉ ነገር ድፍንፍን ያለባቸው ወይዘሮዋ ለፍኖተ ነጻነት በሰጡት ቃል‹‹የመንግስት ሰዎች ምንም አይነት ቀና ምላሽ እንደማይሰጡኝ አውቃለሁ ነገር ግን በታሰሩበት ወቅት ፍጹም ጤነኛ የነበሩት ባለቤቴ መሞታቸውን ህዝቡ ይወቅልኝ ብለዋል፡ ፡የኦሮሞ ኮንግረስ በኋላም የኦፌኮ ፕሬዘዳንት የሆኑት ፕሮፌሰር መራራ ጉዲና የአቶ አህመድን ሞት ከባለቤታቸው እንደሰሙ በመጥቀስ ነገር ግን ምንም ማድረግ አለመቻሉን አውስተዋል፡፡

Tuesday, January 28, 2014

We call on the Ethiopian government to release Eskinder Nega and all journalists convicted.......

2014 Golden Pen of Freedom awarded to jailed Ethiopian journalist


Eskinder Nega, an Ethiopian publisher, journalist and blogger who is serving an 18-year jail sentence under anti-terror legislation, has been awarded the 2014 Golden Pen of Freedom, the annual press freedom prize of the World Association of Newspapers and News Publishers (WAN-IFRA).

Mr Nega was arrested on September 14, 2011 after publishing an article criticising his government’s use of the 2009 Anti-Terror Proclamation to jail and silence critics, including Ethiopian actor and activist Debebe Eshetu. He was sentenced on 23 January 2012 and denounced as belonging to a terrorist organisation.
In making the award, the WAN-IFRA Board sent a message to the Ethiopian government that misusing anti-terror legislation to jail journalists and those critical of his government is unwarranted and against international protocols, including the Vienna Declaration on Terrorism, Media and the Law.
“This award recognises the courage of Eskinder Nega to speak out despite the risks that saw him jailed under his country’s draconian and overly broad anti-terror laws,” said WAN-IFRA President Tomas Brunegård, speaking on behalf of the Board.

“We call on the Ethiopian government to release Eskinder Nega and all journalists convicted under the sedition provisions, including Solomon Kebede, Wubset Taye, Reyot Alemu, and Yusuf Getachew”, said Mr Brunegård, who recently visited Ethiopia as part of an international mission that found that the country’s publishers and journalists practice journalism in a climate of fear.

The Golden Pen of Freedom is an annual award made by WAN-IFRA since 1961 to recognise the outstanding action, in writing or deed, of an individual, a group or an institution in the cause of press freedom. More on the Golden Pen can be found at http://www.wan-ifra.org/node/31099
The award will be presented on 9 June during the opening ceremonies of the World Newspaper Congress, World Editors Forum and World Advertising Forum, the global summit meetings of the world’s press, to be held in Torino, Italy.
In an opinion piece published in the New York Times, Mr Nega said of his imprisonment: “I’ve never conspired to overthrow the government; all I did was report on the Arab Spring and suggest that something similar might happen in Ethiopia if the authoritarian regime didn’t reform… I also dared to question the government’s ludicrous claim that jailed journalists were terrorists.”

WAN-IFRA has been vocal in their opposition to Ethiopia’s misuse of anti-terror legislation, writing to late Prime Minister H.E. Meles Zenawi in 2012 requesting the immediate release of Mr Nega and most recently demanding his release, along with four other imprisoned journalists, in a joint international press freedom mission to Ethiopia, conducted with the International Press Institute. The full report from the international press freedom mission can be found at http://www.wan-ifra.org/node/97172
Mr Nega opened his first newspaper, Ethiopis, in 1993, which was soon shut down by authorities due to its critical reporting. He then, along with his wife Serkalem Fasil, managed Serkalem Publishing House, responsible for newspapers such as Asqual, Satenaw and Menelik, all of which are currently banned in Ethiopia. He has also had his journalist’s licence revoked since 2005, but continued to publish articles despite the ban.
Mr Nega is no stranger to being imprisoned due to his writings. He was detained at least seven times under Prime Minister Meles Zenawi. This included a 17-month jail sentence, along with his wife, on treason charges for their critical reporting on the Meles government’s violent response to peaceful protests that followed the disputed 2005 elections.
WAN-IFRA, based in Paris, France, and Darmstadt, Germany, with subsidiaries in Singapore and India, is the global organisation of the world’s newspapers and news publishers. It represents more than 18,000 publications, 15,000 online sites and over 3,000 companies in more than 120 countries. Its core mission is to defend and promote press freedom, quality journalism and editorial integrity and the development of prosperous businesses.


ለራሱ ምስል የተጠነቀቀው የሱዳን መንግስት ቀድሪያንና ሞርጋን ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ አስሮአት.......

በ6 የሱዳን ወጣቶች የተደፈረችው ኢትዮጵያዊት በእስር ላይ እንደምትገኝ ታወቀ


ወጣቷ በአሁኑ ጊዜ ነፍሰጡር ስትሆ
ጥር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቀድሪያ እንድሪስ የተባለች ኢትዮጵያዊት ወጣት በ6 የሱዳን ወጣቶች እጅግ አሰቃቂ በሆነ መንገድ ስትደፈር የሚያሳይ  ቪዲዮ ኢሳት  የደረሰው ሲሆን ፣ ካርቱም የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ የዲያስፖራ ክፍል ሃላፊ የሆኑት አቶ አረጋ ልጂቷ መደፈሩዋን አምነው ተጨማሪ መረጃ ለመስጠት ግን ከፍተኛ ባለስልጣኖች መፍቀድ አለባቸው በሚል ዝርዝር ጥያቄዎችን ለመመለስ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።
ጥቅምት ወር አካባቢ ቤት ለመከራየት በአካባቢው የነበሩትን ወጣቶች የጠየቀችው ኢትዮጵያዊት፣ ወጣቶችም ” እኛ የሚከራይ ቤት እናሳይሻለን” ብለው በመውሰድ በአሰቃቂ ሁኔታ እየደፈሩ በእርቃኑ ላይ የተለያዩ አስጸያፊ ስራዎችን እየሰሩ በቪዲዮ እየቀረጹ ተጫውተውባታል።
ለራሱ ምስል የተጠነቀቀው የሱዳን መንግስት ቀድሪያንና ሞርጋን ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ አስሮአት እንደሚገኝ ኢሳት ከኢምባሲው የውስጥ ምንጮች መረጃ የደረሰው ሲሆን፣ የኢምባሲው የዲያስፖራ ሃላፊ ግን ልጅቱ በጥሩ ሁኔታ ላይ ትገኛለች ብሎአል። የሱዳን ፍርድ ቤት ድርጊቱ ሲፈጸም በወቅቱ ለምን ሪፖርት አላደረግሽም በሚል ወጣቷንም ተጠያቂ ለማድረግና የአገሪቱን መንግስት ከተጠያቂነት ለማውጣት እንቅስቃሴ መጀመሩን የውስጥ ምንጮች የገለጹ ሲሆን፣ ወጣቷ በበኩሏ ” መረጃውን የምታወጪው ከሆነ  እንገድልሻለን ስለተባለች በፍርሃት በወቅቱ ሪፖርት ለማድረግ እንዳልቻለች ገልጻለች።” በአሁኑ ጊዜ ወጣቷ ከማንኛውም ሰው ጋር እንዳትገናኝ በመደረጓ ኢሳት ለማነጋገር ሳይችል ቀርቷል። ወጣቷን በእስር ቤት ለማነጋገር የሚፈልጉ ሰዎች ልዩ ወረቀት ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ማምጣት የሚኖርባቸው ሲሆን፣ አንዳንድ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅት ወጣቷን ለመጠየቅ ፈልጎ በወረቀት ክልከላ ምክንያት ሳይችል ቀርቷል።
በወንጀል ከሚፈለጉት ወረበሎች መካከል የተወሰኑት የታሰሩ ቢሆንም ሌሎች ደፋሪዎች ግን እስካሁን አለመታሰራቸው ታውቋል። በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጉዳዩን እየተከታተልኩት ነው ቢልም  እስካሁን በእስር ላይ የምትገኘዋን ወጣት ለማስፈታት አልቻለም።
ወጣቷ በአሁኑ ጊዜ ነፍሰጡር ስትሆን፣ የእርግዝናዋ ምክንያት ከመደፈሩዋ ጋር የተያያዘ ይሁን አይሁን የታወቀ ነገር የለም

Monday, January 27, 2014

አቤ በእስር ቤት በነበረው መልካም ባህርይ.......

“ ሰው ጥሩ” ( አርአያ ተስፋማሪያም)

January 27, 2014

አሜሪካ መኖር ከጀመረ 16 አመት አለፈው። ለፍቅር ሲል ከፍተኛ መስዋእትነት የከፈለ ታዋቂ አርቲስት ነው። እጅግ ለሚያፈቅራት ልጅ አቀንቅኖላታል። ይህ ድምፃዊ፥ አበበ ተካ ነው። “ሰው ጥሩ..” የሚለው የግጥም ድርሰት በህልሙ ነበር የታየው። ፍቅረኛው እታገኝ ሙላው ትባላለች።
አቤ በህልሙ “ፍቅረኛውን ጥቅጥቅ ባለ ጫካ ውስጥ እየሮጠ ሲከተላት..ሲሮጥ…ሳይደርስበት ይቀራል። ከዛም ደክሞት ለምለም ሳር በሆነ ሜዳ ቁጭ ብሎ…”ሰው ጥሩ..” እያለ ያዜማል፤”. ህልሙን ለገጣሚ ሙልጌታ ተስፋዬ (ነፍሰ ሄር) ይነግረዋል። ዘፈኑም ተሰራ። “ምንድነው ቀለበት፣.. እንዳንቺ አላየሁም በዝች ምድር ላይ፣.. አገሯ ወዲያ ማዶ፣..በይ ካልረሳሽኝ-ንገሪኝ..” ዜማዎች ለፍቅረኛው እታገኝ የተደረሱ ናቸው። አበበ ተካ በ1989ዓ.ም “ምርጥ የአመቱ ድምፃዊ” ተብሎ የገንዘብና ወርቅ ሽልማት አግኝቷል።
ብዙ ጊዜ መድረክ ላይ ሲዘፍን እንባው ይፈስ ነበር። ምክንያቱ ደግሞ በመለየት ስቃይ ውስጥ አሻግሮ የእርሱ አይነት እጣ (የመለያየት) የደረሰባቸውን እያሰበ ጭምር ነበር።…አበበ በ1990ዓ.ም ለንደን ይጓዛል። በዛው የጣሊያን ፓስፖርት አሰርቶ ፍቅረኛውን ለማግኘት ወደ አሜሪካ ይበራል። እንዳቀደው ግን አልሆነም። ፓስፖርቱ ተመሳስሎ የተዘጋጀ ስለነበረ በአሜሪካ ፖሊስ ተይዞ እስር ቤት ተላከ። 5 አመት ተፈረደበት። ጎንደር ይኖሩ የነበሩት አባቱ አቶ ተካ የልጃቸውን መታሰር እንደሰሙ (በደም ግፊት) ደንግጠው ሕይወታቸው አለፈ። እስር ቤት እንዳለ መርዶ መጣበት።..
አቤ በእስር ቤት በነበረው መልካም ባህርይ 1አመት ከ8 ወር ከታሰረ በኋላ እንዲለቀቅ ተደረገ። በብዙ ፈተና ያለፈበትን ፍቅረኛውን የማግኘት ህልም እውን ሆነ። አበበ አሁን ድረስ ፈጣሪን ያመሰግናል። ከፍቅረኛው እታገኝ ሙላው ጋር ጎጆ ቀልሰው ሶስት ልጆች አፍርተዋል። ልጆቹ ትእግስት አበበ፣ ብርሃን አበበ፣ አዲስኪዳን አበበ ይባላሉ። አበበ እጅግ ሲበዛ ትሁትና ሰው አክባሪ ሲሆን በዲሲ የሚኖሩ ሃበሾች ትልቅ ከበሬታ ይሰጡታል። ስለእርሱ ሲናገሩ፥ « አበበ የትዳርና ፍቅር ተምሳሌት ነው። ጨዋና ቤተሰቡን አክባሪ ሰው ነው። ብዙ ቦታ ልታይ- ልታይ አይልም። ከስራው መልስ ከቤተሰቡ ጋር ነው የሚያሳልፈው። ስለ ሃገሩ ኢትዮጲያ በየመድረኩ ያዜማል።» በማለት ምስክርነት ይሰጣሉ። በየሳምንቱ ቅዳሜ በ”ዱከም” መዝናኛ የሚዘፍነው አበበ ሲናገር፥ « የሰው ልጅ በተለይ በስደት አገር ያለው ሃበሻ ወገኔ..ከሚወደው አገሩ፣ከቤተሰቡ፣ ከፍቅረኛው…እንዲገናኝ ሁሌም ፈጣሪን እለምናለሁ።
የተለያየ ሰው ናፍቆቱን ሳይወጣ ክፉ አይንካው!! ተነጣጥሎ መኖር ከባድ ስቃይ ነው። የናፍቆትና ብቸኝነት ስቃይን የደረሰበት ያውቀዋል። » ይላል። ከኳስ የቡና ክለብ አድናቂና ደጋፊ የሆነው ድምፃዊ አበበ ሁለተኛ አልበም ሊያወጣ ነው። በአንድ ሰው አገናኝነት ገጣሚና ደራሲ Fasil Tekalign የላካቸውን ጨምሮ የግጥምና ዜማ ስራዎች ቅድመ ዝግጅት እየተደረገባቸው ነው። በእውነተኛ ታሪክ ዙሪያ የተመሰረቱ እንዲሁም አገርና ህዝብን የተመለከቱ ዜማዎች ይገኙበታል።..የሰው ልጅ ህልሙ ሲሰምር እንዴት ያስደስታል!!
( አበበና ፍቅረኛው እታገኝ (ከፎቶ ማህደር) ..እንዲሁም በቅርብ ተገናኝተን..)

Friday, January 24, 2014

“የታሰርከው ሰርቀህ ወይም ሌላ ወንጀል ሰርተህ ሳይሆን፤ እውነትን ስለተናገርክ ነው::

ከቃሊቲና ቂሊንጦ እስር ቤቶች በላይ የሚያንጸባርቁ ከዋክብት (ዳዊት ከበደ ወየሳ፣ አትላንታ)

January 23, 2014ዳዊት ከበደ ወየሳ (አትላንታ)
(ይህ ጽሁፍ የርዕዮት አለሙ የልደት በአል በአዲስ አበባ በተከበረበት ወቅት; ከውጭ አገር ንግግር እንዳደርግ በተጋበዝኩበት ወቅት… የስራ ባልደረቦቼን እስክንድር, ውብሸት እና ርዕዮትን በማሰብ የተዘጋጀ ነው)
ይህ ሳምንት የታላቁ ማርቲን ሉተር ኪንግ የልደት በአል በመላ አሜሪካ የሚከበርበት ነው:: በአሜሪካ ከክርስቶስ ልደት ቀጥሎ ስራ እና ትምህርት ቤት ተዘግቶ ልደቱ የሚከበርለት አንድ ሰው ቢኖር ማርቲን ሉተር ኪንግ ብቻ መሆኑን ልብ ይበሉ:: የማርቲን ሉተር ኪንግ የልደት በአል በሚከበርበት ወቅት በህይወት ዘመኑ ለጥቁር ህዝብ ነጻነት ያደረገው አስተዋፅኦ ይታወሳል:: በህይወት በነበረበት ወቅት ለሰው ልጅ እኩልነት ተሟግቷል; የነጻነት ቀንዲልን ለኩሷል:: ሆኖም እኩልነት እና ነጻነትን ሳያጣጥም በበርሚንግሃም እስር ቤት ተጥሎ ፍዳውን እንዲቆጥር ተፈርዶበት ነበር:: በመጨረሻም የሰውን ልጅ ክብር እና ነጻነት በማይደግፉ ሰዎች ህይወቱ ማለፉ ይታወቃል – መልካም ስራዎቹ ግን አላለፉም::Reeyot Alemu, the 31 year-2012 Courage in Journalism Award winner.
ዛሬም በአገራችን ስለፍትህ, ስለነጻነት የሰበኩና የደሰኮሩ; የጻፉና የመሰከሩ… ለሃቅ ቆመው፣ ግፍ የተሰራባቸው፣ ከአገር የተሰደዱና የወጡ፤ በግፍ ሰንሰለት ለጨለማ እስር የተዳረጉ ወገኖቻችን ብዙ ናቸው:: እስክንድር፣ ውብሸት፣ ርእዮት፣ አንዷለም እና ሌሎች ኢትዮጵያውያን ራሳቸውን በሰብአዊነት መሰረት ላይ ስላነጹ እና ሃሳባቸውን በነጻነት ስለገለጹ መጨረሻቸው እስር እና እንግልት ሆኗል::
እንደ እውነቱ ከሆነ ሃሳብን በነጻነት መግለጽ… ብሎም የህዝብ ልሳን ሆኖ ለህዝብ የቤዛነት ዋጋ መክፈል የሚያስከብር እንጂ የሚያሳስር አልነበረም:: በመሆኑም ለነጻ ፕሬስ መክፈል የሚገባቸውን ዋጋ ከመጠን አሳልፈው የከፈሉት፤ ርዕዮት አለሙ፣ እስክንድር ነጋ እና ውብሸት ታዬ… ሶስቱም ከአገራቸው አልፈው በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና አግኝተዋል:: በአለም አቀፍ ደረጃም በልዩ ልዩ አለም አቀፍ የጋዜጠኞች ማህበራትና ተቅውውማት ለሽልማት ታጭተው አሸናፊ ሆነዋል::
የ’ነዚህ የስራ ባልደረቦቼ ብዕር… ህዝብን ሳይሆን የተወሰኑ ወገኖችን አሸብሮ ሊሆን ይችላል:: እነርዕዮት አለሙ በዚህ አይነት ሰበብ አስባብ በቃሊቲ እና በቂሊንጦ እስር ቤት ታግተው፤ ነጻነታቸውን አጥተውና ህክምና ተነፍገው ይታሰሩ እንጂ፤  ለእውነት የቆሙ ወገኖች ግን ለመልካም ስራቸው ሽልማትን አልነፈጓቸውም::
ማርቲን ሉተር ኪንግ በበርሚንግሃም እስር ቤት ታስሮ ቢማቅቅም የአሜሪካም ሆነ የአለም አቀፉ ማህበረሰብ አልዘነጋውም:: ቆይቶም ቢሆን የአለም አቀፉ ኖቤል ተሸላሚ እስከመሆን ደርሷል:: ዛሬ በእስር ላይ የሚገኙት የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞች የኖቤል ተሸላሚ ባይሆኑም አለም ግን አልረሳቸውም:: ከታሰሩበት የጨለማ ወህኒ ቤት ጀርባ፤ ከብረት ፍርግርግ እና ከግድግዳዎቹ ባሻገር በመቶዎች፣ በሺዎች እና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች እነዚህን ጋዜጠኞች በመልካም ስራቸው ያስታውሷቸዋል; ይዘክሯቸዋል:: ስለሆነም የጻድቃን ሞት፤ የሰማዕትነት ጽድቅ ተደርጎ እንደሚቆጠረው ሁሉ… የነ እስክንድር፣ ውብሸትና ርዕዮት እስር፤ ከቶውኑ ዋጋ ቢስ እና ፍሬ አልባ ሊሆን አይችልም::
ኢትዮጵያ ውስጥ በነበርኩበት ወቅት በፕሬስ ጉዳይ ተደጋጋሚ የሆነ እስር ደርሶብኛል:: በ’ነዚህ የእስር እና እንግልት ጊዜያት ግን… ከጨለማው እስር ቤት ማዶ ለምን እንደታሰርኩ የሚረዱ ሺዎች በመኖራቸው ሁልጊዜ እጽናና ነበር:: በተደጋጋሚ እስር ቤት እየመጣ የሚጠይቀኝ እና የዋስ መብቴን አስጠብቆ ከእስር እንድወጣ ያደርገኝ የነበረው ወላጅ አባቴ፤ “የታሰርከው ሰርቀህ ወይም ሌላ ወንጀል ሰርተህ ሳይሆን፤ እውነትን ስለተናገርክ ነው:: ስለዚህ አንገትህን ቀና ልታደርግ እንጂ ልትሸማቀቅ አይገባህም::” የሚል አጽናኝ ቃል ሁሌ ይነግረኝ ነበር:: ዛሬ አባቴ በህይወት የለም:: ቃሉ እና ምክሩ ግን አብሮኝ አለ:: በእስር ላይ ለሚገኙ የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞች፤ “አንገታችሁን ቀና አድርጉ!” የሚለውን መልዕክት አጋራቸዋለሁ::
ዛሬ በጋዜጠኞቻችን ላይ የተለያዩ ክሶች ተመስርቶባቸው መታሰራቸው ሳያንስ; ከታሰሩም በኋላ በሃሰት ሊወነጅሏቸው የሚሹ ብዙ ግራ ዘመም ሰዎች መኖራቸውን ታዝበናል:: በአሜሪካ ከፍተኛ የአየር ሽፋን አግኝቶ ዲሞክራቶችን በመሳደብ የሚታወቀው ራሽ ሊምቦ የተባለ ጋዜጠኛ በቅርቡ ኔልሰን ማንዴላ በሞት ሲለዩ… “ብታምኑም ባታምኑም ኔልሰን ማንዴላ አሸባሪ ነበሩ::” ብሎ ሰፊ ሙግት ፈጥሮ ነበር:: ይህ አባባሉ ለኛ እና ለሌሎች አፍሪቃውያን ሊገርመን ይችል ይሆናል:: ነገር ግን የራሳቸው አመዛዛኝ ህሊና ያልፈጠረባቸውና ይህን ሰው በጭፍን የሚከተሉት ሰዎች “አዎ ማንዴላ አሸባሪ ነበሩ” ብለው ቢሉ ሊገርመን አይገባም::
ዛሬም ባገራችን በተመሳሳይ መልኩ የነርዕዮት አለሙን መልካም ስም ጥላሸት ለመቀባት እላይ ታች የሚሉ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ… እኛ ግን እንላለን:: “ወንጀል አልሰራችሁምና አንገታችሁን ቀና አድርጉ!” ስማችሁ ከቃሊቲና ከቂሊንጦ እስር ቤቶች በላይ፤ በጠራው ሰማይ ላይ ያንጸባርቃል፤ ቃለ ሃቃቹህ በአየር ናኝቶ… ኢትዮጵያዊያን ባሉበት ሁሉ በመላው አለም ላይ ተሰራጭቷል::
የማርቲን ሉተር ኪንግ ልደት ሲከበር መልካም ስራዎቹ እንደሚወደሱ ሁሉ፤ ዛሬም ሆነ ወደፊት የነርእዮት አለሙ ልደት ሲከበር መልካም ስራዎቻቸው በተደጋጋሚ ይነሳሉ ይዘከራሉ:: ዛሬ ማንዴላን አሸባሪ ብለው የሚከሱ ሰዎች እንደመኖራቸው መጠን; በተመሳሳይ መልኩ ለነርእዮት አለሙ ተመሳሳይ ስም የሰጡና ያሰጡ… ለመስጠት እና ለማሰጠት የሚጥሩ ሰዎች አሉ:: እኛ ግን የተለኮሱ ሻማዎች ይዘን ልደት ስናከብር; የብርሃናችን  ጮራ፤ ሌሎች የፈጠሩትን የጨለማ ድባብ ሰንጥቆ… አንዳች ብርሃን እንደሚፈነጥቅላቸው በማመን ነው:: ዛሬ የርዕዮት አለሙን የልደት ቀን ስናከብር፤ ያለፍትህ የታሰሩትን ፍትህ የሚፈልጉትን፤ ነጻነት የተጠሙትን ነፍሶች በማሰብ ጭምር ነው::
መልካም ልደት – ርዕዮት!

Thursday, January 23, 2014

“ፍትህ የምትዋረድበትን ወይም ፍትህ የምትታይበትን” ታሪካዊ ቀን እንዲመለከት ከቤተሰቦቻቸው እና ከወዳጆቻቸው ጥሪ ቀርቧል።

እነ አንዷለም አራጌ ነገ ሰበር ሰሚ ችሎት ይቀርባሉ፤ ሕዝብ ችሎቱን እንዲከታተል ጥሪ ቀረበ


በዘ-ሐበሻ አንባቢዎች ዘንድ የ2005 ዓ.ም የዓመቱ ምርጥ ሰው የሚለውን ስያሜ ያገኘው የሕሊና እስረኛው አንዷዓለም አራጌ፣ ናትናኤል መኮንንና ክንፈ ሚካኤል ደበበ ነገ ጥር 16 ቀን 2006 (ጃንዋሪ 24 ቀን 2014) በሰበር ሰሚ ችሎት እንደሚቀርቡ ከቤተሰቦቻቸው አካባቢ የተገኘው መረጃ አመለከተ። እነዚህን የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ የሚፈልጉ ወገኖች 6 ኪሎ የሚገኘው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድቤት እንዲገኙ ጥሪ ቀርቧል።

በአንካሳው የኢትዮጵያ የሽብር ሕግ ከግንቦት 7 ጋር በማያያዝ ሽብር ለመፈጸም በማቀድ በሚል እድሜ ልክ እስራት የተፈረደበት ወጣቱ ፖለቲከኛ አንዷአለም አራጌ በ እስር ቤት በመሆንም በጽናት በመታገል የሰላማዊ ትግል አርማ ሆኗል በሚል በብዙዎች ዘንድ ይወደሳል። ወጣቱ ፖለቲከኛ አንዷዓለም አራጌ የተላለፈበትን ዕድሜ ልክ እስራት ፍርድ፤ እንዲሁም ናትናኤል መኮንን እና ክንፈሚካኤል ደበበ የተላለፈባቸውን ቅጣት ለታሪክ ለመተው ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ወደ ሰበር ሰሚ ችሎት እንዲታይ የወሰዱት ሲሆን ነገ ሰበር ሰሚ ችሎቱ የሚሰጠው ውሳኔም በቤተሰቦቻቸው ዘንድ በትልቅ ተስፋ እንደሚጠበቅ ጨምሮ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
ነገ በስድስት ኪሎ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ላይ ሲሰየም እነ አንዷለም አራጌም አብረው የሚቀርቡ ሲሆን የሚታገሉለትና መስዋዕትነት እየከፈሉለት የሚገኘው ሕዝብ በችሎቱ በመገኘት ይህን “ፍትህ የምትዋረድበትን ወይም ፍትህ የምትታይበትን” ታሪካዊ ቀን እንዲመለከት ከቤተሰቦቻቸው እና ከወዳጆቻቸው ጥሪ ቀርቧል። ይህን ተከትሎም በፌስቡክና በተለያዩ የማህበራዊ ድረገጾች “እነ አንዷለም ፍትህ ያግኙ፤ ይፈቱ” የሚለው ቅስቀሳ ቀጥሏል።

Tuesday, January 21, 2014

ለጨጓራ መላጥ (አልሰር) በሽታ መፍትሄው ምንድን ነው

Health

ዘ-ሐበሻዎች በጋዜጣችሁ እንዲሁም በድረገጻችሁ የምታቀርቧቸው ጤና ነክ ዘገባዎች በጣም በፍቅር ነው የማነባቸው። ዛሬ ወደ እናንተ እንድጽፍ ያስገደደኝ አንድ ጉዳይ ገጥሞኛል። ‹ለጨጓራ መላጥ /አልሰር/ በሽታ መፍትሄው ምንድን ነው? ምላሻችሁን እጠብቃለሁ።

ሰለሞን
የዶ/ር ዓብይ ዓይናለም ምላሽ፦ ሰለሞን በቅድሚያ ለላክልን ደብዳቤ በጣም እናመሰግናለን፡፡ ወደ ጥያቄህ ስንመለስ ከሶስት ወር በፊት አንድ ክሊኒክ ሄደህ የጨጓራ መላጥ /አልሰር/ መታመምህ እንደተነገረህ ገልፀኻል፡፡ የመድሃኒቱን ስም ባትጠቅሰውም በሐኪም የታዘዘ መድሃኒት ተጠቅመህ ምንም አይነት መፍትሄ እንዳላገኘህ ተረድተናል፡፡


አንባቢያችን እንደገለፅከው የሆድ ውስጥ መቃጠል፣ ማቅለሽለሽና ትውከትን የመሳሰሉ ህመም ነክ ምልክቶች ተስተውለዋል፡፡ በእርግጥ አንተ የገለፅካቸውን ጨምሮ የሆድ መነፋት፣ በትንሽ ምግብ የሆድ መሙላት ስሜት፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣ ደም የተቀላቀለበት ትውከት፣ የአይነምድር መጥቆርና ደም የቀላቀለ አይነምድር መውጣት ለጨጓራ መላጥ /አልሰር/ በሽታ መኖር ጠቋሚ ምልክቶች ናቸው፡፡ በእርግጥ እነዚህ ህመም ነክ ምልክቶች ለጨጓራ መላጥ በሽታ ብቻ ምልክት ላይሆኑ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ ቀለል ባለ የጨጓራ መታወክ ለሐሞት ቀረጢት ችግሮችና ለሌሎች መሰል በሽታዎች መከሰትም ጠቋሚ ምልክት ሆነው ሊያገለግሉ እንደሚችሉ መገንዘብ ይገባል፡፡ ለጨጓራ መላጥ በሽታ የሚጋለጡ የተለያዩ ጉዳዮች አሉ፡፡ ለአብነት ሄሊኮባክተር ፓይሎሪ የሚባል ባክቴሪያ በሚያመጣው ኢንፌክሽን የተነሳ የአሲድ ምርት መዛባትና የግድግዳው ስስ ሽፋንን በማሳጣት ለቁስለት ያጋልጠዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ለስቃይ ማስታገሻ ተብለው በሐኪም የሚታዘዙ እንደ አስፕሪን የመሰሉ መድሃኒቶች የጨጓራ ቁስለትን የሚያስከትሉ ሲሆን በዘር፣ በሲጋራ በማጨስና አልኮል በመጠጣት ለጨጓራ መላጥ /አልሰር/ ችግር የመጋለጥ እድል ይኖራል፡፡

የባህር ዳሩ ሰለሞን የአንተ ጤና ችግር በትክክል የጨጓራ መላጥ /አልሰር/ መሆኑን በትንፋሽ፣ በደምና በሰገራ የሄሊኮባክተር ፓይሎሪ ምርመራን በማካሄድ በተጨማሪም የኢንዶስኮፒ ምርመራ አድርገህ የህመምህን ምንነት ለማረጋገጥ ተገቢውን ትኩረት ብትሰጥ ጠቃሚ ነው ብለን እንገነዘባለን፡፡ ምክንያቱም የችግሩ ምንነት በግልፅ ካልታወቀ ትክክለኛና ውጤታማ መፍትሄ ለመስጠት አዳጋች ነው የሚያደርገው፡፡ ውድ የባህርዳሩ አንባቢያችን የጨጓራ መላጥ /አልሰር/ ችግር በወቅቱ ታክሞ መዳን ካልተቻለና ከዘገየ የመድማት፣ የጨጓራ ግድግዳ መበሳትና የአንጀት መጥበብ በተጨማሪም ምግብ ያለማሳለፍ ችግሮች ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡

በግልፅ መገንዘብ እንደሚቻለው የጨጓራ መላጥ /አልሰር/ ማለት በጨጓራ የውስጠኛው ግድግዳ ሽፋን ላይ የሚፈጥረው መላጥ ሲሆን አብዛኛው ጊዜ የመላጥ ችግር የሚስተዋልባቸው አካባቢዎች የጨጓራ ግድግዳና የመጀመሪያው ትንሹ አንጀት በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ፡፡ የጨጓራ መላጥ በሽታ ሁለት አይነት ነው፡፡ የመጀመሪያው ጋስትሪክ አልሰር ሲሆን ሁለተናው ዲዎድናል አልሰር በመባል ይታወቃል፡፡ አንባቢያችን ሰለሞን ይህ በሽታ አንተን ጨምሮ በዓለም ላይ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ያጠቃል፡፡ በሀገራችንም በጥልቀት የተጠኑ ጥናቶች ባይኖሩም በጤና ተቋማት የተገኙ መረጃዎችን መሰረት አድርገው የተጠኑ ጥናቶች እንደሚያመላክቱት በሀገራችን የችግሩ ስፋት ከጊዜ ወደ ጊዜ አድማሱን እያሰፋ መሄዱን ነው የሚያረጋግጡት፡፡ በሽታው ሳይባባስና ስር ወደ ሰደደ ችግርነት ሳይለወጥ በወቅቱ ተገቢውን ህክምና ከተደረገ ሙሉ በሙሉ መዳን የሚችል ነው፡፡ የጨጓራ በሽታ ህክምና እንደ መንስኤውና እንዳስከተለው የጉዳት አይነት ይለያያል፡፡ ጠቅለል ተብለው ሲታይ የህክምና መፍትሄዎች /የህክምና ዘዴዎች/ የሚከተሉት በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

- ኤች.ፓይሎሪን የማጥፋት ህክምና ይካሄዳል
- የአሲድ መቀነሻ መድሃኒቶች ይሰጣሉ
- የጨጓራ መላጥ ህመምን ያስከተሉት ሌሎች ህመሞች ተብለው የተወሰዱ መድሃኒቶች ከሆኑ እነዚህን በማስቆም ለውጥ ማምጣት ይቻላል፡፡
- ሲጋራ ማጨስን አልኮል መጠጣት ማቆም
- የህመሙን ስሜት የሚቀሰቅሱ ምግቦችን አለመመገብ
- በህመሙ ሳቢያ የተከሰቱ ጉዳዮችን በአግባቡ ማከም ከተቻለ የጨጓራ አልሰርን/መላጥን በተገቢው መንገድ አክሞ ማዳን ይቻላል፡፡
ጠያቂያችን ሰለሞን መድሃኒት ተጠቅመህ እንዳልተሻለህ መግለፅህ ይታወሳል፡፡ በእኛ እምነት ከሁሉም አስቀድመህ የተሻለ ህክምና ወደ ሚሰጥበት የጤና ተቋም በመሄድ ተገቢውን ህክምና ብታደርግና የበሽታውን ትክክለኛነትና መንስኤውን ብታረጋግጥ ጠቃሚ ይሆናል፡፡ በተማሪም በሐኪም የሚታዘዝልህን መድሃኒቶች በተገቢው ጊዜና መጠን መጠቀም መቻልህን መዘንጋት የለብህም፡፡ ከዚህ በተረፈ ለጤና ችግሩ መባባስ ምክንያት ከሆኑ ጉዳዮች ራስህን በማራቅ ከችግሩ ሙሉ በሙሉ መላቀቅ የምትችል መሆኑን እንመክርሃለን፡፡

Thursday, January 16, 2014

አሁን በቃኝ ማለት ሰራዊት በትኖ እንደሚፈረጥጥ መሪ የመሆን ያህል ነው።

ፕ/ር በየነ “የአካኪ ዘራፍ ትግል አክሳሪ ነው፤ የስሜት ፖለቲካ ያብቃ” አሉ

“ከኤርትራ ጋር መስማማት አግባብ ነው፤ ግን ፍርሃቻ አለኝ”
beyene petros
“የአካኪ ዘራፍ ፖለቲካና ከስሜት ያልጸዳ የፖለቲካ ትግል መሪውንም ሆነ አምኖ የሚመራውን ህዝብ ለድል” እንደማያበቃ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ገለጹ። ከኤርትራ ጋር ስምምነት ቢደረግ መልካም መሆኑን፣ ነገር ግን ስምምነቱ የመሪዎችና የፖለቲከኞች ሳይሆን የህዝብን ስሜት የጠበቀ ሊሆን እንደሚገባውም ጠቁመዋል።
ከጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ጋር በተለይ ቃለ ምልልስ ያደረጉት ፕ/ር በየነ “አሁን ያለው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሁኔታ ከመቼውም ጊዜ በላይ አስተዋይነት የሚፈልግ፣ ዘመናዊ የትግል ስልት የሚጠይቅ ነው” በማለት ተናግረዋል። በቃለ ምልልሳቸው ደጋግመው  “አሁን በተያዘው የአካኪ ዘራፍ መንገድ የትም አይደረስም” በማለት ምክንያታቸውን ዘርዝረዋል።
ትንንሽ ጠርዝ በመያዝ የትም የማይደርስ ትግል ከየአቅጣጫው እንደሚፈለፈል ፕ/ር በየነ አመልክተዋል። በዚሁ የተነሳ ስትራቴጂካልና ታክቲካል ጉዳይ የመለየት አቅም አናሳ በመሆኑ የፖለቲካው መንደር የርስ በርስ ንትርክና ውግዘት ሊሆን እንደቻለ ገልጸዋል። ለዚህም ተጠያቂዎችና ቅድሚያ ተወቃሾች ህዝብና አገር የምትፈልጋቸው የዘመናዊ ለውጥ መሪዎች መሆን ሲገባቸው የዳር ተመልካች የሆኑት የአገሪቱ ልሂቃን እንደሆኑም በግልጽ ተናግረዋል።
“ችግሩ በአገር ውስጥ ባሉት ልሂቃን ላይ ጎልቶ ቢታይም፣ በውጪው ዓለም ባሉት ምሁራኖችም ላይ ተመሳሳይ ችግር አለ” የሚሉት ፕ/ር በየነ “እነዚሁ ክፍሎች ትግሉን ከመቀላቀል ይልቅ እኛን በመውቀስ አገራዊ ሃላፊነታቸውን የተወጡ መስለው ይታያሉ” ሲሉ ስሜታቸውን ገልጸዋል።
“የፖለቲካው መስመር ክፍተትን አይወድም” በማለት የሰከነ አመለካከት ላላቸውና ከስሜት ፖለቲካ ነጻ ለሆኑት ዜጎች መልዕክት ያስተላለፉት ዶ/ር በየነ፣ ሰዓትና በጀት በመመደብ የተለየ አመለካከት ያላቸውን ክፍሎች ሰድቦ የማሰደብ ተግባር ሲከናወን ማየታቸው በጅጉ እንደሚያሳዝናቸው ተናግረዋል። በጦር መሳሪያና በሃብት ብዛት መፎካከር ባይቻልም፣ በሰብአዊ ብቃት ኢህአዴግን መፎካከር እንደሚቻል የጠቆሙት ዶክተሩ የተቃዋሚው ሰፈር በተቃራኒው የተፈረካከሰ፣ እርስበርስ ለመባላት ቅድሚያ የሚሰጥ፣ የትግል ስልቱም ሆነ አቅሙ ስትራቴጂካዊና ታክቲካል ጉዳዮችን መለየት በማያስችል ደረጃ የተዋቀረ መሆኑ ትግሉን ፍሬ አልባ እንዳደረገው ተናግረዋል።
beyene_petros“ለአውራነት/ኮርማነት የታሰበ በሬ ተመልሶ ላሚቱን ጠባ” በሚል በሃድያ የሚነገር ተረት በማስታወስ ሃሳባቸውን ያጠናከሩት ዶ/ር በየነ፣ የዚህ ሁሉ ችግር መንስዔው የልሂቃኑ ዝምታ እንደሆነ አመልክተዋል። አገራቸውን ወደ ተሻለ መንገድ ለማሸጋገር የሚችሉ ሁሉ ዝምታቸውንና ዳር ቆመው የሚመለከቱትን የአገራቸውን ውድቀት እንዲታደጉ ጥሪ አቅርበዋል። ዶ/ር ነጋሶ የወሰዱትን ርምጃ በማንተራስ ስለ ፖለቲካ ጡረታም ተጠይቀው መልስ ሰጥተዋል።
“እናንተ አርጅተሃል ካላችሁ እንጂ እኔ አላረጀሁም። ጤነኛ ነኝ። የነጋሶን ያህል እድሜም የለኝም” በማለት መልሳቸውን ይጀምራሉ። በማያያዝም “ልተውስ ብል እንዴት ብዬ?” ሲሉ ይጠይቃሉ። “ልሂቃኑ ዳር ቆመው ተመልካች ሆነዋል። በዚህ ላይ የምመራቸውና ውህደት የፈጠሩት የደቡብ ህብረትና የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራት ፓርቲ አደራውን ከኔ አላወረዱም። አሁን በቃኝ ማለት ሰራዊት በትኖ እንደሚፈረጥጥ መሪ የመሆን ያህል ነው።”
ኸርማን ኮህን በቅርቡ ይፋ ያደረጉትን የእርቅ ሃሳብ አስመልከቶ ማብራሪያ ሰጡት ዶ/ር በየነ “በአልጀርሱ ስምምነት መሰረት የሚደረግ ስምምነት ከቶውንም ቢሆን ተቀባይነት የለውም። ከኤርትራ ጋር እርቅ መልካም ቢሆንም በፖለቲከኞችና በውስን ሃይሎች ፍላጎት ተከናውኖ ሰዶ ማሳደድ እንዳይሆን እፈራለሁ” ብለዋል። ከዚሁ ጋር በማያያዝ አሜሪካ በኢህአዴግና በወያኔ የፖለቲካ እምነት ደስተኛ እንዳልሆነች ተናግረዋል። ድጋፍ የምትሰጠው ከፍቅር ብዛት እንዳልሆነ በማመልከት የተቃዋሚው ክፍል ይህንኑ ቀዳዳ ሊጠቀምበት ይገባል ብለዋል። “ታዲያ” አሉ ፕ/ር በየነ “ታዲያ በማንጓጠጥና በዘለፋ ሳይሆን በሰከነ መንፈስና ስሜትን በገደለ አስተዋይነት” ሊሆን ይገባል። በመጪው ምርጫ የ1997 ምርጫ ዓይነት ሁኔታ እንዲፈጠር ዘመቻ መጀመሩንና የድጋፍ ፍንጭ መታየቱን የገለጹት ዶ/ር በየነ ስለ ሃይል አማራጭና ኢህአዴግ፣ በተለይም ህወሃት ውስጥ አለ ስለሚባለው የመፈረካከስ ችግር ተጠይቀው “ጦርነት የሁለት የጎበዝ አለቆች ጸብና ድብድብ ነው። ከአሁን በኋላ እኔ ላገሬ ጦርነት አልመኝም” በማለት ከምክንያታቸው ጋር አስቀምጠዋል። ህወሃትና ኢህአዴግ ውስጥ አለ ስለተባለ የመፈረካከስ ችግር “የዋህነት አይጠቅምም፣ በስሜትና በአካኪ ዘራፍ ፖለቲካ የሚመጣ ለውጥ ይኖራል ብዬ አላስብም” ብለዋል። ስለ ስጋታቸውም ተናግረዋል።
“ወያኔ የሚባለውና ተዘጋጅቶ አገሪቱን የተቆጣጠረ ሃይል ለሰበሰበው ሃብትና ንብረት ሲል ፖለቲካውን በበላይነት ለመምራት ከቀን ወደ ቀን የሚፈጽመው ጥፋት ህዝብ እያማረረ መጨረሻው አገሪቱን ወደ ጥፋት እንዳይወስድ ነው። የከፋቸው በጨመሩ ቁጥር ችግሩ መከሰቱ አይቀርምና በጥበብ ታግሎ ካሰቡት ለመድረስ እነሱ ከሚያስቡት በተለየ በልጦ ማሰብና መታግል አስፈላጊ ነው። ለዚህም የልሂቃኑ ዳር ቆሞ መመልከት መቆም አለበት” ብለዋል። በማያያዝም ዲያስፖራው አገር ውስጥ ለሚታገሉ ድርጅቶች ልዩነት ሳያደርግ ድጋፍ ሊሰጥ እንደሚገባ አሳስበዋል። ድጋፉም ሆነ እገዛው ሰክኖ ለማሰብ እንደሚመነጭም ገልጸዋል። ዶ/ር በየነ ጴጥሮስ በተለይ ከጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ያደረጉትን ሙሉ ቃለ ምልልስ በቀጣይ ይዘን እንቀርባለን።

Wednesday, January 15, 2014

የሚገርመው እንዴት የአንድ ሰው መኖሪያ ቤት የቀድሞ የአድዋ ወይም ባድመ፣…የውጊያ ስፍራ ሊመስል እንደቻለ ግልፅ አይደለም፡፡

ይድረስ ለጠ/ሚ/ር ኃይለማርያም፡ ማስረሻ ላይ የተፈፀመው በእርስዎ የበኩር ልጅ ዮሐና ላይ ቢፈፀም ምን ይሰማዎታል?



                                        ይድረስ ለአቶኃይለማርያም ደሳለኝ እና ለኢህአዴግ አመራሮች!
ብስራት ወልደሚካኤል
afrosonb@gmail.com,
addismediab@gmail.com

በቅድሚያ የከበረ ሰላምታዬ በያላችሁበት ይድረሳችሁ፤ ምንም እንኳ እናንተ ብዙውን ሰላም እየነሳችሁ ብታስቸግሩም፡፡ ዛሬ ግን እስኪ በእናንተ እና በቤተሰባችሁ ላይ እንዳይፈፀም የምትፈልጉትን በሌላው ላይ ስላደረጋችሁት ከብዙው አንዲት እውነት ብቻ አንስቼ ልጠይቃችሁ ወደድሁ፡፡ የጥያቄው መልስ ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለህሊናችሁ፣ እናንተ በምትመሩት አስከፊ፣ አፋኝ እና ጨቋኝ ስርዓት ሰለባ ለሆኑ እንዲሁም አሁንም በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የተለመደውን እኩይ ተግባር ለምትፈፅሙባቸውና ለቤተሰቦቻችሁ ይሆን ዘንድም አበክሬ እጠይቃለሁ፡፡

ክቡር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ እርስዎ ተወልደው ባደጉበት የደቡብ ክልል ወላይታ ዞን ቦለሶ ሶሬ ወረዳ መዲና በሆነችው አረካ ከተማን መቼም የሚረሷት አይመስለኝም፡፡ እርስዎ አሁን የደረሱበት የይምሰልም ይሁን ተግባር የጠቅላይሚኒስትርነት በትረ ስልጣን ከመጨበጦ በፊት እዛው አረካ ከተማ አካባቢ እንደ አብዛኛው የሀገራችን ህዝብ በግብርና እርሻ ሙያ ዕየተዳደሩ ነው እንበል፡፡ ታዲያ በዚህ ሙያ ሳሉ ልክ አሁን እንዳሉት ባለትዳር እና የ3 ልጆች አባት ሆነው፤ እርስዎ በሚመሩት ኢህአዴግም ይሁን 24 ሰዓት በምትኮንኑት ደርግ ስርዓት አርዓያ “ሞዴል” አርሶ አደር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ተብለው የትውልደ ቀዬዎትን ወክለው በደቡብ ክልል መንግስት ቢሸለሙ ምን ይሰማዎታል? ያው ደስታ እንደሚሉኝ አልጠራጠርም፡፡

አለበለዚያም ገበሬ ሆኜ አላውቅም ካሉም፤ ያኔ አርባምንጭ የውሃ ቴክኖሎጂ ተቋም (የአሁኑ አርባምንጭ ዩኒቨርስቲ) ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በተመረቁበት ሲቪል ምህንድስና(Civil Engineering) አሊያም ከፊንላንድ በተመረቁበት የአካባቢ ንፅህና ምህንድስና(Sanitory Enegineering) እስተማሩና እያስተዳደሩ ሞዴል መምህር ተብለው በወቅቱ ገዥ ስርዓት ቁንጮዎች ቢሸለሙ ምን ይሰማዎታል? አሁንም ያው ደስታ ነው እንጂ ሀዘን ሊሉኝ አይችሉም፡፡ ምክንያቱም ማንም ሰው በሙያው ጥሮ ግሮ ላበረከተው አስተዋፅዖ እና ለሌሎች መልካም አርዓያ በመሆኑ የሚጠላ አይኖርምና፡፡ ይሄንን ምሳሌ ለራስዎ መቀበል ካልቻሉም ከቤተሰብዎ እጅግ መልካም ነው ብለው አብልጠው የሚወዱት ወንድምዎ ካሉም በእርስዎ ምትክ እርሳቸውን ተክተው እርስዎን በታዛቢነት ያስቀምጡ፤ ስሜቶንም ያሰላሱ፣ ይግለፁ፡፡

በሙያዎ ለብዙ ዓመታት ሰርተው ለሌሎች አርዓያ ተብለው ሽልማት፣ እውቅና እና ሙገሳ ከተሽጎደጎደልዎ 3 ወር ሳይሞላ፤ ከትዳር አጋርዎ ወ/ሮ ሮማን ተስፋዬ እና የበኩር ልጅዎን ተማሪ ዮሐና ኃይለማርያምን ጨምረው ከሌሎች ልጆቾ ጋር አምላኬ በሰላም አሳድረኝ ብለው ተቃቅፈው ተኝተው በሸለሞት አካል አሸባሪ ተብለው ሌሊት በቤትዎና በቤተሰብዎ ላይ በ 16 “የፀረ-ሽብር” ግብረ ኃይል የጥይት እሩመታ ሲሰሙስ ምን ይሰማዎታል? አሁን ልክ እንደቅድሙ ደስታ ሊሉኝ አይችሉም፡፡ በዚህ ብቻ ሳያበቃ እርስዎን በቤተሰብዎ ፊት በሸለሞት አካል በ 16 ግብረ ኃይል ሽፍታ ነው ተብለው በክብር አርፈው ከተኙበት ቤት በሚተኮሱ የጥይት ናዳዎች በቤተሰብዎ ፊት ህይወትዎ እስከወዲያኛው ቢያልፍ እና እንደው ግማሽ ነብስ የለም እንጂ በከፊል ድርጊቱን ቢታዘቡት ምን ይላሉ; ከእርስዎ በተጨማሪ ለፍተው ጥረው ግረው ያቆሟት ቤት፣ ያፈሯቸው ላሞች ፣በጎችና በሬዎች በማያውቁት ነገር የጥይት ናዳ ሲያርፍባቸውስ; ከላይ በተጠቀሱት ሳያበቃ ግብረ ኃይሉ አሁን የሰው ህክምና ሳይንስ የምታጠናው የበኩር ልጅዎ ተማሪ ዮሐና ሌሊቱን ገና በ8 ዓመቷ ከእቅፎ ተኝታ እርስዎ ሲገደሉ እርሷ የምትፅፍበት፣ አሊያም በትርፍ ጊዜዋ ከብቶች የምታግድበት ወይንም እንደሌሎች ህፃናት ከአቻዎቿ ጋር ለመጫወት የምትጠቀምበት የቀኝ እጇ ሙሉ ለሙሉ በጥይት ቢቆረጥስ ምን ይሰማዎታል? በዚህም ደስታ እንደማይሉኝ ግልፅ ነው፡፡
 ልክ በውጊያ አውድማ እንዳለ ወታደር ከወላጆቿ እቅፍ ሳለች ቀኝ እጇ የተቆረጠችው ልጅ ስታድግስ ምን ይሰማት ይሆን? ፍርዱን ህሊና ላለው ሁሉ ልተወው፡፡
ልክ እንደ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በሌሎች የኢህአዴግ አመራሮች እና አባላት ላይ ተመሳሳይ ድርጊት ቢፈፀም ምን ይሰማችኋል; እናንተም ደስታ እንደማትሉኝ አልጠራጠርም፡፡ ይህንን ሁሉ የጠቀስኩት በማንም የሰው ሰብኣዊ የሰው ልጅ ላይ እንዲህ ዓይነት ዘግናኝ ድርጊት እንዲፈፀም ፈልጌ ይደለም፤ ይሄንንም አቶ ኃይለማርያምም ሆኑ ሌሎች ግብር አበሮእዎ በቅን ልቦና እንድትረዱልኝ እሻለሁ፡፡
ክቡርነትዎ፤ ከላይ ብእርስዎ የጠቀስኩት ምሳሌ በሌላ ኢትዮጵያዊ ላይ በእናንተ ስርዓት አመራር የተፈፀመ እውነተኛ ድርጊት መሆኑንን ከዚህ እንደሚከተለው በአጭሩ ልነግሮት እወዳለሁ፡፡

ጥቅምት 15 ቀን 2006 ዓ.ም. በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ አረቦር ቀበሌ ልዩ ቦታው ደቀፉቀር በሚባል ስፍራ ከሌሊቱ 12 ሰዓት ከነ መላው ቤተሰቦቻቸው አምላኬ በሰላም አሳድረኝ ብለው የተኙ፤በእነ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ስርዓት ሞዴል አርሶ አድር ተብለው የተሸለሙ ታታሪ ገበሬ አቶ ማስረሻ ጥላሁን በ 16 የፀረ ሽብር ግብረኃይል በተተኮሱ የጥይት ናዳዎች እዛው እቤታቸው ህይወታቸው አልፏል፡፡ የሚያሳዝነው ለግድያ የተላከው ግብረ ኃይል አቶ ማስረሻን ከገደሉ በኋላም በመኖሪያ ቤታቸው ላይ ተከታታይ የጥይት ናዳ በማውረድ ቤታቸውን የጥይት ጌጥ ሲያደርጉት ጥረው ግረው ያፈሯቸው ከብቶችንም ከመግደል እና ከማቁሰል አልቦዘኑም ነበር፡፡

የሚገርመው እንዴት የአንድ ሰው መኖሪያ ቤት የቀድሞ የአድዋ ወይም ባድመ፣…የውጊያ ስፍራ ሊመስል እንደቻለ ግልፅ አይደለም፡፡
ከላይ ከተጠቀሰው በተጨማሪ እጅግ የሚዘገንነው እና የሚያሳዝነው በተመሳሳይ ሰዓት የአቶ ማስረሻ ጥላሁን የ 8 ዓመት ልጅ ስለእናት ማስረሻ እዛው በሞት ከተነጠቀው ወላጅ አባቷ እና በፀረ ሽብር ግብረኃይል ከተሸበሩ ምስኪን ቤተሰቦቿ እቅፍ ሆና ሲነጋ ጥቅምት 16 ቀን 2006 ዓ.ም. ከአቻዎቿ ጋር ትምህርት ቤት ስለመሄድ እና ስለመጫወት ስታልም ብዙ ስራዎችን የምትሰራበት ቀኝ እጇ በግብረ ኃይሉ ጥይት ሙሉ ለሙሉ ተቆርጧል፡፡
አቶ ኃይለማርያም በእርስዎ እና በግብር አበርዎ የሚመራው ኢህአዴግ ሞዴል አርሶ አደር ያላችኋቸውን አቶ ማስረሻ ጥላሁንን በ 16 “የፀረ ሽብር” ግብረ ኃይል ለማስገደል በወረዳውና በዞኑ አመራሮች ሽፍታ ነው የሚል ለባለቤታቸውና በህይወት ለተረፉ ልጆቻቸው መልስ ተሰጥቶ ፍትህ እንጦርጦስ ገብቷል፤ ቀድሞም ቢሆን ኢትዮጵያ ውስጥ ኢህአዴግ እስካለ ፍትህ እና ርትዕ ከማግኘት ሰማይ ቤት ደርሶ መመለስ የቀለለ ይመስል ሰው ተስፋ ቢቆርጥም፤ ለወጉም ቢሆን ፍርድ ቤት መኳተኑ አልቀረም፡፡ ነገር ግን እሮጣ ያልጠገበች፣ክፉና ደጉን የማታውቅና ቂም በቀል የሌለባት፣ ዓለማችንንም ይሁን ሀገራችንን ኸረ እንደውም አካባቢዋን በቅጡ ለይታ የማታውቅ የ 8 ዓመቷ ህፃን ስለእናት ማስረሻ ጥላሁንን ምን ብላችሁ ይን እጇ እንዲቆረጥ የተደረገው? ነው ወይስ ይህቺን ህፃንም ሽፍታ ነች ልትሉን ነው? ኸ…ረ…ረ..የፍትህ ያለህ፣…የህፃን ልጅ ያለህ፣…ቢያንስ ሰብዓዊነት እንኳ እንዴት ይሳናችኋል?

እስኪ አቶ ኃይለማርያም ስለእናት ማስረሻ ላይ የተፈፀመው በእርስዎ የበኩር ልጅ ዮሐና ኃይለማርያም ላይ ቢፈፀም ምን ይሰማዎታል? ስለ እናንተ ልጆች እንደምታስቡ ሁሉ ስለሌሎች ህፃናት ያላችሁ አስተሳሰብና አመለካከት ወይም ግንዛቤ የት ድረስ ነው? ዛሬ በዚህ ግፈኛ ስርዓት ቀኝ እጇ የተቆረጠው ስለእናት ማስረሻ ነገ እንደማንኛውም ልጅ አራሷን፣ ቤተሰቧን፣ ሀገሯን ብሎም የዓለምን ማኀበረሰብ ልታገለግል ምትችል፣ ብዙ ተስፋ የሰነቀች ነች፡፡
አሁን ግን ገና የ !ኛ ክፍል ትምህርቷን በጀመረች አንድ ወር ከአስር ቀን የመመህሮቿን የፊደል አጣጣል ትዕዛዝ የምትቀበልበት ቀኝ እጇ ገና ከጅምሩ ተቆርጧል፡፡ በዚህም ምክንያት ሰኞ ማክሰኞ እያለች ትምህርቷን መከታተል ሲገባት ፍትህ አጥታ ከምትኖርበት ዳባት ወረዳ፣ ሰሜን ጎንደር ዞን ከዚያም የአማራ ክልል ፍትህ ፅፈት ቤት እስከ ህፃናት ጉዳይ በጥይት ናዳዎች ከተረፉ ቤተሰቦቿ ጋር ፍትህን ፍለጋ እየተንከራተተች ትገኛለች፡፡
በአንፃሩ ደግሞ የአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ልጅ ዮሐና ኃይለማርያም በተደላደለ ሰላም፣ ጤናና እና ሁኔታ የህክምና ትምህርት ትከታተላለች፣ የብአዴኑ ሊቀመንበር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን ልጆችም የተሻለ ትምህርት ቤት ከዚሁ ደህ ህዝብ በሚገኝ ገንዘብ ይማራሉ፣ የአቶ በረከት ስምዖንን ፣ የዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል፣ የአቶ ሙክታር ከድር፣ የነ ሀሰን ሽፋ፣ የነ ጌታቸው አሰፋ ፣ የነ አያሌው ጎበዜ፣ የነ ገዱ አንዳርጋቸው፣ የነ ግዛቱ አብዩ እና የሌሎች የኢህአዴግ ሹማምንት ልጆች በህዝብ ሃብት ተንደላቀው በተመቻቸ ሁኔታ ይማራሉ፡፡ የዳባት ወረዳ ነዋሪዋ ህፃን ስለ እናት ማስረሻ ደግሞ ለትምህርት ባልተመቻቸ ሁኑታ እንኳ የጀመረችውን ትምህርት እንዳትማር ቀወላጅ አባቷን በግፍ ከማጣቷ በተጨማሪ ቀኝ እጇን ተቆርጣ ፍትህን ፍለጋ ትኳትናለች፡፡
ታዲያ ክቡር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ እና ሌሎች የኢህአዴግ ሹማምንት ሆይ፤ የምትመሩት ስርዓት በህፃናት ስም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ረብጣ ዶላሮችን እንደሚያገኝ የምትዘነጉት አይመስለኝም፡፡ ይሁን እንጂ በህፃናቱ ስም የሚመጣው እርዳታ ቢያንስ በአግባቡ ጥቅም ላይ መዋል ባይችል እንኳ ለምን አንዲትን ህፃን በፀረ-ሽብር ግብረኃይል በጥይት ለማስመታት ዋለ? በዚህች ህፃን ልጅ እና ወላጅ አባቷን ጨምሮ በቤተሰቦቿ ላይ የተፈፀመው ግፍ የት ድረስ ያስኬዳችኋል? ይህችን ደብዳቤ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ አቶ ኃለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ ይህቺ ደብዳቤ ደረሳችሁ ሌሎች የኢህአዴግ አመራሮች ፤ ስለ ህፃናት ልጆቻችሁ፣ ስለ እናቶቻችሁ ፣ ስለሚስቶቻችሁ እና ስለራሳችሁ ብላችሁ የዚህቺን ህፃን እና ቤተሰቦች ጊዜ ሳትሰጡ ፍትህን ፍለጋ እየደከሙ ነውና ፍትህን ይሻሉ፡፡
እነ አቶ ኃለማርም ደሳለኝ የእውነት ከልብ አዝናችሁና እና ተሰነምቷችሁ ፍትህን መስጠት ከቻላችሁ የድርጊቱ ፈፃሚዎች ብዙ በምታወሩበት ኢቴቪና በሌሎች መድረኮች ሌሎች አመራሮችም ሆኑ ህዝብ እንዲማሩበት ጭምሩ ተገቢው ፍርድ በግልፅ በአደባባይ ሊሰጥ ይገባል፡፡ እዚህ ላይ የሴቶች እና ህፃነት ጉዳይ ቢሮዎች፣ አቃቤ ህግ፣ ጠበቆች ፣የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችና ሌሎች የሚመለከታችሁ አካላት የድርሻችሁን ትወጡ ዘንድ ተግባሩ የት አለ? ስል መልሳችሁን በአክብሮት እጠይቃለሁ፡፡
ታህሣሥ 2006 ዓ.ም. ተፃፈ
አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ

አርሶ አደሩን እንደፈለገ ብናደርገው በኢህአዴግ ላይ አይነሳም ሲሉ አቶ በረከት ተናገሩ


ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ አማካሪ የሆኑት አቶ በረከት ስምኦን ለመንግስት ሚኒስትሮችና ለከፍተኛ የኢህአዴግ አመራሮች በተዘጋጀው የምርጫ ውይይትና ግምገማ ላይ ባቀረቡት ንግግር ላይ እንደገለጹት አርሶ አደሩ እስካሁን በተሰረላት ስራ በመርካቱ ” መንግስት ሰላማዊ ሰልፍ ውጣ ቢለው ይወጣል፣ መንግስት ተኛ ቢለው ይተኛል፣ ግፍ ብንፈጽም አርሶአደሩ ይህን መንግስት ምንም አይለውም፣ ይሸከመዋል” ብለዋል።

30 በመቶ የሚሆነውን ወጪ የምንሸፍነው በውጭ እርዳታ በመሆኑ፣ ከውጭ ተጽእኖ ለመላቀቅ ወጪያችንን የሚሸፍን ገቢ ማግኘት አለብን ያሉት አቶ በረከት፣ “በ1997 ምርጫ ወቅት የውጭ ሃይሎች ጥፋት ያጠፉትን መሪዎችን ወደ ፍርድ ቤት የምትወስዱዋቸው ከሆነ እርዳታ እናቆማለን ባሉት መሰረት እርዳታ አቁመውብን ነበር” ሲሉ ለራሳቸው ባለስልጣኖች ተናግረዋል።

አቶ በረከት  ”በ1884ቱ ድርቅ ጊዜ የአሜሪካ የእርዳታ ድርጅት ሃላፊው የመሬት ፖሊሲያችሁን ካልቀየራችሁ እርዳታ አንሰጥም” ብለዋቸው እንደነበር ተናግረዋል።ኢህአዴግ ከዋናዎቹ አመራሮች ጀምሮ በተዋረድ ለሌሎች አመራሮችም ምርጫውን ስለሚያሸንፉበት ሁኔታ ስልጠና እየሰጠ ነው። ኢህአዴግ የገጠሩን ድምጽ ሙሉ በሙሉ እንደሚያገኝ አቶ በረከትና ኢህአዴግ ሙሉ በሙሉ ተማምነዋል። ይሁን እንጅ የኢህአዴግ ካድሬዎች  በየገጠሩ በመዞር ያልተደራጀውን አርሶአደር በአንድ ለአምስት በማደራጀት፣ በመሬት እጥረት የተከፋውን ወጣት የወል መሬት እየሸነሸኑ በመስጠት ላይ መሰማራታቸውን የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።

በአገራችን እየከሰመ ያለው ሃሳብን በነፃ የመግልፅ እና መረጃ የማግኘት መብት በገዥው መንግስት መልካም ፍቃድ ላይ የተመሠረት ወደመሆን ደረጃ ተሸጋግሯል፡፡

የመረጃ ነፃነት ? …. (ይድነቃቸው ከበደ )

January 14, 2014
‹‹ ሕዝቡ እኔ ማን እንደሆንሁ ይላል ? ›› በማለት እየሱስ ክርስቶስ መረጃ ይጠይቃል ፤ ደቀመዛምርቶችም ስለሱ የተባለውን አንድም ሳያስቀሩ ይነግሩታል፡፡ እሱም መልሱ እንዲህ ይላቸዋል ‹‹ እናንተስ እኔ ማን እንደሆንሁ ትላላችሁ ? ››አላቸው ፡፡ እነሱም መለሱለት፡፡ ሙሉ ታሪኩ ሉቃስ 9ቁ 18 ላይ ይገኛል ፡፡Yidnekachew Kebede
መረጃ አይናቅም አይደነቅም ማለት እንዲህ ነው፡፡ በመሰረቱ ክርስቶስ ሰዎች ስለሱ ምን እንዳሉ ብቻ ሳይሆን ምን እያሰብ እንደነበር የሚያውቅ አምላክ ነው፡፡ ግን መጠየቅ እና መመለስ አሳብን መግለፅ የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ባህሪ ነው፡፡ ለዚህም ነው ክርስቶ እንደሰው በምድር በተመላለሰበት ወቅት መረጃ ይጠይቅ የነበረው እሱም ስለራሱ መረጃ ይሰጥ የነበረው፡፡ እርግጥ ነው ክርስቶስ ይህን ሲጠይቅ የራሱ ምክንያት አለው፡፡
በመሆኑም ሃሳብ መግለፅ ተፍጥራዊ መብት ነው ወደሚለው ዓለም አቀፍ ስምምነት በመደረሱ የመናገር ሃሳብን የመግለፅ ነፃነት የዲሞክራሲ ዋና የድም ስር ነው የተባለው፡፡ ስለዚህም ተሰባስቦ መቃወም እንዲሁም መደገፍ ፣ አንድ ሰው የሚመስለውን ሃሳብ በፈለገው መንገድ መግለፅ፣ የመምረጥና የመመረጥ፣ መንግስትን የመተቸት፣ በራስ ፍቃድ የመናገረ እና ያለመናገር ፣ በዓልንና አይማኖትን መከተልና ማስፋፋት እንዲሁም ህግ ለሁሉም የሚሰራ ስለመሆኑ መረጋገጥ እና የመሳሰሉት ሁሉ ተግባራዊ የሚሆነው ተአቅቦ ያልተደረገበት የመናገርና የመረጃ መብት ልውውጥ ተግባሪዊ ሲሆን ብቻ ነው፡፡
ለመደርደሪያነት የዚህን ያኸል ከተባለ ወደ ዋናው ጉዳይ አስፈቅደን ሳይሆን ፈቅደን እንገባለን፡፡ ያነሳነው አሳብ ‹‹ መረጃ ›› እንደመሆኑ መጠን ያለማንም ጣልቃ ገብነት ተፍጥሯዊ መብታችን በፈለግነውና በፈቀድነው መንገድ እንገልፃለን፡፡ እኛ ስል ለመረጃ ነፃነት የቆምነው ሁላችንም ማለቴ ነው፡፡
ሰው በመናገሩ አና በመፃፉ ብቻ ለእስር እና ለስደት የሚዳረግበት አገር በዋነኝነት ከሚጠቀሱት ውስጥ ኢትዮጵያ አንዶ ናት፡፡ ነገር ግን ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት የአመለካከት እና ሐሳብን በነፃ የመያዝና በማንኛውም የማሰራጫ ዘዴ በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ የመግለፅ ነፃነት አለው፡፡የሚለው በኢትዮጵያ ህገመንግስቱ አንቀፅ 29 ተፅፎ ይገኛል፡፡ በእርግጥ ይህ መብት ገደብ ሊጣልበት እንደሚችል በህገ መንግስቱ ላይ ተገልፆ የተቀመጠ ሲሆን ገደብ ግን መሠረታዊ የሆነውን መረጃን የመስጠት እና የማግኘት እንዲሁም አስተሳሰብ ላይ ወይም አመለካከት ላይ ውጤት እንደማይኖረው በህገመንግስቱ ተገልፆ ይገኛል፡፡
ይሁን እንጂ አሳብን በነፃ ማሰብና ማንሸራሸር በአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ እጅግ አዳጋች ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ አልፎ ተርፎ በአስተሳሰብ ወይም በአመለካከት ላይ ተፅኖ እስከመፍጠር ተደርሶኦል ፡፡ ነገር ግን እንዲህ አይነቱ ሁኔታ ለህግም ሆነ ለሞራል ተቃራኒ እንደመሆኑ መጠን የፈጀውን ፈጅቶ ወደነበረበት መመለሱ የማይቀር ሃቅ ነው፡፡ ነፃ አሳብ የሚንሸራሸርባቸው ነፃ ጋዜጦችና መፅሔቶች ምን ያህል አሉ ? ያሉት ጋዜጦች እና መፅሔቶች እየደረሰባቸው ያለው ማስፈራሪያና ዛቻ ደረጃው ምን ያኸል ደርሶአል የሚለውን መመልከት ተገቢ ነው፡፡ ለዚህም ማሳያ የሚሆነው በቅርቡ በወጣው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ አክራሪነትና ፅፈኝነት የሚያበረታቱና የሚያሰራጩ በማለት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለህዝቡ ተገቢውን መረጃ እያስተላለፉ ያሉ የእትመት ውጤቶችን ከገቢያ ለማውጣትና ፈርጆ ለመክሰስ እየተደረገ ያለው ዝግጅት ሌላው ማሳያ ነው፡፡ጋዜጠኞችን በማሰቃየት፣በማሰር እና እንዲሰደዱ በማደረግ ኢትዮጵያ በዓለም ላይ በሁለተኝነት ደረጃ ላይ ትገኛለች ፡፡መንግስትን ተችቶ የፃፈና ፁሁፉ የወጣበት ጋዜጣ ወይም መፅሔት ጨምሮ ሁሉም ለእስር የሚዳረግበት ወይም አደገኛ ዛቻና መስጠንቀቂያ የሚሰጥበት ደረጃ ላይ ተደርሷል፡፡
በዲሞክራሳዊ ሥርዓተ ዜጎች የሚኖሩት ግልፅ በሆነ የሃሳብ ልውውጥ ነው፡፡ የትኛውም አይነት ሃሳብ ከማንም ሊመጣ ይችላል ቁም ነገሩ መሆን ያለበት የሚመጣው ሃሳብ የሚመከተው በምንድነው የሚለው ነው፡፡ ለነፃ ንግግር ችግር የተሻለው መንገድ የበለጠ ነፃ ንግግር ነው፤ በመናገር መብት ላይ የሚደረግ ማናቸውም ተፅእኖ ሲውል ሲያድር በእያንዳንዱ ግለሰብ የመናገር መብት ላይ ስጋት ሊያስከትል ይችላል፡፡ለዚህም ነው ወደነበረበት መመለሱ የማይቀር ነው ለማለት የሚያስደፍረው፡፡ምክንያቱ ደግሞ ማንም ሰው በስጋት ውስጥ መኖርን ስለማይፈልግ ነው፡፡
በመሆኑም በአገራችን እየከሰመ ያለው ሃሳብን በነፃ የመግልፅ እና መረጃ የማግኘት መብት በገዥው መንግስት መልካም ፍቃድ ላይ የተመሠረት ወደመሆን ደረጃ ተሸጋግሯል፡፡ለዚህም እንደማሳያ ከሰሞኑ የህዝብ ሳይሆን የገዥው መንግስት አንደበት በሆነው በኢቲቪ በተላለፈው የዘጋቢ ፊልም ግለሰቦችም ሆነ በአገር ውስጥ ያሉ የተቃዋሚ ፓርቲዎች በተለይ ሰማያዊ እና አንድነት ፓርቲ ለኢሳት መረጃ ከመስጠት እንዲቆጠቡ ምክር መሰል ማስጠንቀቂያ ተላልፏል፡፡
ለዚህም እንደምክንያት የቀረበው ኢሳት የተባለው የመገናኛ ብዙሃን በሽብርተኛ ድርጅት የሚደገፍ ነው የሚል ምክንያት ነው፡፡ ኢቲቪ በኢህአዴግ እንደሚደገፍ ሁሉ ኢሳት በማንም ሊደገፍ ይችላል፤ ቁም ነገር ሆኖ መታየት ያለበት ኢቲቪ ሆነም ኢሳት የሚያስተላልፉት መልዕክት ምንድነው ፡፡ በተጨማሪ መልዕክቱ ለህግም ሆነ ለሞራል ምን ያኸል ተቃራኒ ነው የሚለውን ነው፡፡ በተጨማሪ ኢቲቪ እንዲሁም ኢሳት በህግ መደመጥ እንዲሁም መሰማት የተከለከሉ የመገናኛ ብዙሃን ናቸው ወይ ተብሎ መጠየቅና መልስ ሊሰጥባቸው የሚገባ አሳቦች ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ ወደ መልሱ ስናመራ ኢቲቪ እንዲሁም ኢሳት በህግ የተከለኩ አይደሉም ዋንኛው እና አስፈላጊው ነገር ይሄ ነው ሌላው የህጉ ደጋፊ ሃሳብ ነው፡፡
በመሆኑም ከዚህ በኋላ የህግ ጉዳይ ሳይሆን የፍላጎት ምርጫ ነው የሚሆነው፡፡ የፈለጉትን መስማት እና ማዳመጥ እንዲሁም በፈለጉት የመገናኛ ብዙሃን መንገድ ሃሳብን መግለፅ እና መረጃን ማግኘት ግለሰብ ከሆነ እንደግለሰቡ፣ ተቋም እንደተቋም እንዲሁም ፓርቲ እንደ ፓርቲ የመምረጥ የራስ መብት ነው፡፡ ይህ ደግሞ አንዱ የዲሞክራሲ መገለጫ ነው፡፡ በዚህም መሠረት ከኢቲቪ ኢሳት ከአዲስ ዘመን አዲስ አድማስ የዝወትር ፍላጎታቸው ለሆነ እንዲሁም በተመሳሳይ ከኢሳት ኢቲቪ ከአዲስ አድማስ አዲስ ዘመን ለመረጡ ምርጫቸውን ማክበረ ነው፡፡
ሌላው እና አሳሳቢ ሊሆን የሚገባው ሰው የመረጠውን መስማትና ማዳመጥ እንዲሁም ማንበብ መብቱ እንደጠጠበቀ ሆኖ ግለሰበ ወይም ተቋም ሃሳቡን እንዴት የመግለፅ መብት እና ግዴታ አለበት የሚለው ነው፡፡ ይህን በተመለከተ ተቋም ወይም ግለሰብ ሃሳብን ወይም መረጃን በማንኛውም መንገድ የመገልፅ ሙሉ መበት በህግ የተጠበቀ ነው ፡፡እንዲኹም የዚህ መብት ተቃራኒ የሆኑ ማናቸውም ነገሮች ተቀባይነት እንደሌላቸው በህገመንግስቱ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት በኢሳት ሆነ በማናቸውም የመገናኛ ብዙሃን ሃሳብን መግለፅ እና መረጃን መስጠጥ በራሱ ወንጀል ወይም ጥፋት አይደለም ይህ የሆነው ደግሞ መብት ከመሆኑ አንፃር ነው፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞ መታየት ያለበት ሃሳብን በመግለፅ እና መረጃን በመስጠት ዙሪያ ግዴታ ሊያመጣ የሚችለው ምንድነው የሚለው ነው፡፡ ግለሰቡ ወይንም ተቋሙ በግልፅ በህግ የተከለከለ መረጃ ወይም ሃሳብ የገለፀ እንደሆነ ግዴታው ተጠያቂነትን ስለሚያመጣ በህጉ መሠረት ተጠያቂ ይሆናል፡፡ ይህ የህግ ተጠያቂነት አዱላዊነት የሌለበት ለሁሉም በሁሉም ቦታ እኩል የሚሰራ ነው፡፡ ይህም ማለት በህግ የሚያስጠይቅ ንግግር በኢሳትም ሆነ በኢቲቪ እንዲሁም በቢቢሲ ያደረግ በህግ ከመጠየቅ ንግግር ያደረገበት የብዙሃን መገኛኛ ሊታደገው አይችልም እንደማለት ነው፡፡
በመሆኑም በኢሳት ሃሳብን መግለፅ እንዲሁም መረጃ መስጠት አልፈልግም ማለት መብት ነው፡፡ ነገር ግን በኢሳት አሳባችሁን አትግለፁ መረጃም አትስጡ ማለት ከፍላጎት የመነጨ ሃሳብ ብቻ ሳይሆን የለየለት የእብሪት ተግባር ነው፡፡ እንዲህ አይነቱ አሰፋሪ ምኞት እና ተግባር የሕግና የዲሞክራሲያዊ መብት ካለማወቅ የሚመነጭ አስተሳሰብ ብቻ ሳይሆን ተምሮ ያለመለወጥ ልክፍትም ጭምር ነው! በተለይ በመንግስት ደረጃ ሲታሰብ እጅግ በጣም ያሳፍራል፡፡

Friday, January 10, 2014

በሰላማዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች በተለይም ሰማያዊ ፓርቲ በኢሳት የመገናኛ ብዙሃን እንዳንጠቀም የማስጠንቀቂያ ዛቻ ተላልፎልናል፡፡

የምንናገርበትን የመገናኛ ብዙሃን ማንም እንዲመርጥልን ወይም እንዲወስንልን አንፈቅድም!

January 10, 2014
ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ
ጥር 1 ቀን 2006 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የብሔራዊ ደህንነት መረጃ እና የፀረ ሽብር ግብረ ኃይል የጋራ ኃይል አድርጎ ራሱን የሚጠራ አካል የዜጎችንና የተቋማትን ሕገ-መንግስታዊና ዲሞክራሲያዊ መብት በመጣስ ጥፋተኝነታቸው በፍርድ ቤት ሳይወሰን ወንጀለኛ ሲያደርጋቸውና ስማቸውን ሲያጎድፍ ማየት እየተለመደ የመጣ ተደጋጋሚ ጉዳይ ሆኗል፡፡ ይህ ከላይ ከተጠቀሱት ሁለት ተቋማት ተውጣጥቶም ይሁን ተቀናጅቶ የሚሰራ አካል በተደጋጋሚ ጊዜ በሽብር ወንጀል ጠርጥሬአቸዋለሁ የሚላቸውን ሁሉ በመክሰስ ወደ እስር ቤት እንዲወርዱ እያደረገ ጉዳያቸው የፍርድ ቤት ውሳኔ ሳያገኝ እንደፈለገ በሚቆጣጠረው ወይም በሚያዘው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ድርጅት አማካኝነት የፈለገውን ዓይነት ፍረጃና ሥም ማጥፋት ሲያካሒድባቸው ቆይቷል፡፡
ይህ ራሱን ከሕግ በላይ የሰቀለ አካል ያለምንም ገደብ ከሚሰራቸው ተግባራት እንዲታቀብ በሕግ የሚያስቆመው በመጥፋቱ እስካሁን የፈፀማቸውን የማንአለብኝነት ተግባራት እንደጥፋት ሳይሆን እንደ መልካም ሥራ ቆጥሯቸው በተመሳሳይ የሥም ማጥፋትና የፍረጃ ተግባሩ እንዲገፋበት አድርጎታል፡፡ በዚሁም መሰረት ታህሳስ 25 ቀን 2006 ዓ.ም ምሽት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ባስተላለፈው የዘጋቢ ፊልም ፕሮፓጋንዳ አሸባሪ ያላቸውን ድርጅቶችና ግለሰቦች አድርሰውታል ያለውን ጥፋት በዝርዝር አቅርቧል፡፡ ፓርቲያችንን በዚሁ ዘገባ ከተጠቀሱት “አሸባሪ” ድርጅቶች ጋር በማገናኘት ስም ለማጉደፍና ለማስፈራራት የተደረገውን መፍጨርጨር አይተናል፣ ሰምተናል፣ ተገርመናል በመጨረሻም አዝነናል፡፡
በዘጋቢ ፊልሙ የቀረቡ ፓርቲያችንን የማይመለከቱ ጉዳዮችን ትተን ከፓርቲያችን ጋር በማገናኘት የተጠቀሰው “ኢሳት” የተባለ የመገናኛ ብዙሃን በኢትዮጵያ መንግስት በሽብርተኝነት ከተፈረጀ ድርጅት የገንዘብ ድጋፍ እንደተደረገለትና በሰላማዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች በተለይም ሰማያዊ ፓርቲ በዚህ የመገናኛ ብዙሃን እንዳንጠቀም የማስጠንቀቂያ ዛቻ ተላልፎልናል፡፡ ይህ አስፈራሪ አካል ራሱን ሕግ አውጭና ሕግ ተርጓሚ በማድረግ የፈለገውን አካል ለመፈረጅ፣ ለመክሰስና ለመፍረድ ሥልጣኑን ከየት እንዳገኘ የማይታወቅ ሲሆን የዚህች ሐገር ዜጎችም ሃሳባችንን የምንገልፅበትንና የማንገልፅበትን የመገናኛ ብዙሃን እየመረጠልንና እየወሰነልን ይገኛል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ እንዲህ ዓይነቱን የእብሪት መልዕክት ከተራ ርካሽ ፕሮፓጋንዳነት የማያልፍ የሕግና የዲሞክራሲያዊ መብት ገደብን ካለማወቅ የሚመነጭ አስተሳሰብ ነው ብሎ ያምናል፡፡
የገዥው ቡድን ሰዎች ሀሳብን በሃሳብ ማሸነፍ እንደማይችሉ ስለሚያውቁት የቀራቸው አማራጭ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ሃሳባቸውን የሚያሰራጩባቸውን መንገዶች መዝጋት ብቻ መሆኑን ፓርቲያችን ይገነዘባል፡፡ ነገር ግን ማንም አካል በሕግም ሆነ በሞራል ተጠያቂ የሚሆነው የሚያስተላልፈው መልዕክት ይዘት የሌሎችን ዲሞክራሲያዊና ሞራላዊ መብት የሚጋፋ መሆን አለመሆኑ እንጂ ገዥው ቡድን በጠላው ወይም በወደደው የመገናኛ ብዙሃን መልዕክቱን ማስተላለፍ አይደለም፡፡ መልዕክትን የገዥው ቡድን ሰዎች በጠሉት የመገናኛ ብዙሃን ማስተላለፍ በራሱ ወንጀለኛ ወይም ሽብርተኛ ለማድረግ የሚያበቃ ምንም ዓይነት የሕግ መሰረት የለም፡፡ ማንም መልዕክት የሚያስተላልፍ አካል የሚያሰራጨው ሃሳብ የሌሎችን ዲሞክራሲያዊና ሞራላዊ መብት የሚጋፋ ከሆነ መልዕክቱ የተላለፈበት መገናኛ ብዙሃን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንም ይሁን ሌላ ህጋዊ የተባለ የመገናኛ ብዙሃን መሆኑ ብቻ መልዕክት አስተላላፊውን አካል ከተጠያቂነት ሊያድን እንደማይችልም ለማንም የተሰወረ ይሆናል የሚል እምነት የለንም፡፡
በመሆኑም ሰማያዊ ፓርቲ መልዕክቱን የሚያስተላልፍበትን መገናኛ ብዙሃን ማንም አካል እንዲመርጥለት ወይም እንዲወስንለት የማይፈልግ መሆኑን ግልፅ እያደረገ በሕገ መንግስቱ የተረጋገጠውን ማንም ሰው በመረጠው መንገድ ሃሳቡን የማስተላለፍ መብቱን በመጠቀም በኢሳትም ሆነ እድሉን ካገኘ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን አቋሙንና እምነቱን ማስተላለፍ የሚቀጥል መሆኑን ማረጋገጥ ይወዳል፡፡ በዚሁ አጋጣሚም የፓርቲያችንን መልካም ስም በሃሰት ለማጉደፍ የተሰነዘሩ ቃላትን በቀላሉ የማንመለከታቸው መሆኑን ሕግ ባለበት ሐገር ራስን ከሕግ በላይ በማስቀመጥ ማንንም አካል መፈረጅና ስም ማጉደፍ በሕግ የሚያስጠይቅ መሆኑን የዘጋቢ ፊልሙ ባለቤቶች እንዲያውቁትና ወደፊትም ተመሳሳይ ድርጊት ከመፈፀም እንዲቆጠቡ እናሳስባለን፡፡
ጥር 1 ቀን 2006 ዓ.ም
አዲስ አበባ

ዶክተር እሙን አብዱ፤ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ሴቶች አርዓያ የሆነች ኒይሮ-ሰርጀን

January 9, 2014ሳዲቅ አህመድ

ወጣቷ ኢትዮጵያዊት ዶክተር ድንቅ የቀዶ-ጥገና ስራዎችን እንደምታከናዉን በአሜሪካ የመገናኛ ብዙሗን ተዘግቧል። እርሷ የሙያ ግዴታዋን ትወጣ እንጂ ያደረገቻቸዉ የቀዶ ጥገናዎች አስደናቂ ናቸዉ ብላ አትገምትም፤ ግን ቤተሰቦቿ እዉነታዉን ያረጋግጣሉ። ኒይሮ-ሰርጀኗ ዶክተር እሙን አብዱ ባለፈዉ አመት መገባደጃ ላይ ያደረገችዉ የቀዶ ጥገና ሁሉንም ያስደነቀ ነበር።

Dr. Emun Abdu says. "He had a 4.5 centimeter aneurysm."
ዶ/ር እሙን አብዱ
ነፍሰጡር ባለቤቱ ለወሊድ የተቃረበችዉ ኬኔት ዊሊያም የሐያ አምስት አመት ወጣት ነዉ። የአሪዞና ግዛት ነዋሪ የሆነዉ ኬኔት በገጠመዉ ሐይለኛ የጭንቅላት ህመም ሳቢያ የመዳን ተስፋዉ ሐምሳ በመቶ ነዉ ተብሎ ነበር። የሚወለደዉን ህጻን ድምጽ የመስማትም ህጻኑንን የማየትም እድል እንዳልነበረዉ ተነግሯል። ይህ አሜሪካዊ ወጣት እድሉ ሆኖ የዶክተር እሙን አብዱ ታካሚ ይሆናል፤ እሙንም ቀዶ ጥገናዉን በተገቢዉ መልኩ ታከናዉናለች። ቀዶ ጥገናዉ በፈጣሪ እርዳታ የተሳካ ይሆንና ኬኔት ዊሊያም የሚወለደዉን ልጅ ድምጽ መስማት ብቻ ሳይሆን ለማቀፍም በቅቷል።
ምን ያህል ኢትዮጵያዉያን ኒይሮ-ሰርጀኖች እንዳሉ መረጃዉ ለግዜዉ ባይኖረንም፤ እሙን አብዱ ካሉት ጥቂት ኒይሮ-ሰርጀኖች አንዷ ናት። እሙን ለብዙ ኢትዮጵያዉያን ሴቶች ሁሉንም ማድረግ እንደሚቻል”እሙን” መሆኑንን በተምሳሊትነት የምታሳይ የሰሜን አሜሪካ ኢትዮጵያዉያን-አሜሪካዉያን ማህበረሰብ አባል ናት። ምን አልባትም እናት-አገራችን ዉስጥ በኒይሮ-ሰርጀን የቀዶ ጥገና እጦት አደጋ ላይ ለሚወድቁ ኢትዮጵያዉያን ወገኖቿ ደራሽ ትሆን ይሆናል።

THE PRICE OF FREEDOM AND JUSTICE: የዜጎች ደም እንዲሁ በከንቱ ፈሶ መቅረት የለበትም።

THE PRICE OF FREEDOM AND JUSTICE: የዜጎች ደም እንዲሁ በከንቱ ፈሶ መቅረት የለበትም።: የግንቦት 7 ወቅታዊ መልዕክት፡ “ከተገኙት አስከሬኖች ግድያው የቅርብ መሆኑን ማረጋገጥ ይቻላል” አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ፈረንሳይ ለጋሲዮን በሚገኘው የክብርዘበኛ ጦር ካምፕ ውስጥ ማንነታቸው ያልታወቁ የ6 ዜ...

Thursday, January 9, 2014

የዜጎች ደም እንዲሁ በከንቱ ፈሶ መቅረት የለበትም።

የግንቦት 7 ወቅታዊ መልዕክት፡ “ከተገኙት አስከሬኖች ግድያው የቅርብ መሆኑን ማረጋገጥ ይቻላል”



አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ፈረንሳይ ለጋሲዮን በሚገኘው የክብርዘበኛ ጦር ካምፕ ውስጥ ማንነታቸው ያልታወቁ የ6 ዜጎች አስከሬን ለመንገድ ሥራ በተሠማሩ ቆፋሪዎች አማካኝነት መገኘቱ የሰሞኑ አሳዛኝ ዜና ነው።

አንድ አይነት ቀለም ባላቸው ብርድ ልብሶች ተጠቅልለው ከተገኙ 6 አስከሬኖች የመጀመሪያዎቹ 
 ሁለት ሰለባዎች ታስረውበት የነበረው የእጅ ሰንሰለታቸው እንኳ እንዳልወለቀና ከተቀሩት የአንዱ እጆች ደግሞ የፍጥኝ ወደ ኋላ እንደታሰሩ መገኘታችው ግድያው በቅርብ እንደተፈፀም አንዱ አስረጂ ነው።በእንዲህ አይነት ጭካኔ የተገደሉ ዜጎች አስከሬን መገኘት በመንግሥት ተብየው አካል ካለመገለጹም በላይ ግቢውን በማስተዳደር ላይ የሚገኘው 3ኛ ክፈለ ጦርም ሆነ በግብር ከፋይ ገንዘብ የሚተዳደሩ መገናኛ ብዙሃን እስከዛሬ አንድም ቃል መተንፈስ አለመፈለጋቸው ጉዳዩን እጅግ የሚያሳዝን ብቻ ሳይሆን የሚያስገርምም አድርጎታል። ይባስ ተብሎም በመንገድ ሥራ ቁፋሮው የበለጠ አስከሬን ሊወጣ ይችላል በሚል ስጋት አካባቢው በፖሊስ እንዲታጠር ከተደረገ በኋላ ሥራውም እንዲቋረጥ ተደርጓል።

በፖለቲካ መስመር ልዩነት ምክንያት ደርግ ያለ ርህራሄ የጨፈጨፋቸውን ከመቃብር እያወጣ ዘመድ አዝማድ በማላቀስ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ሲዳክር የኖረ አገዛዝ በእንዲህ አይነት አሳዛኝ ሁኔታና አጋጣሚ የተገኘውን የጅምላ አስከሬን አይቶ አንዳላየ ለማለፍ መሞከሩ ለምን ይሆን?
አብዛኛው የአዲስ አበባ ነዋሪ እንደሚያስታውሰው የክብር ዘበኛ ጦር ካምፕ በመባል የሚታወቀው የጃን ሜዳ 3ኛ ክፍለ ጦር ግቢ ድህረ ምርጫ 97 ወያኔ ለጅምላ እስር ቤትነት ከተጠቀመባቸው የማጎሪያ ቦታዎች አንዱ ነበር። ከዚያን ጊዜ በፊትና በኋላም ቢሆን ካምፑ በወያኔ ጠላትነት ተፈረጀ በጸጥታ ሠራተኞች ከታገቱ በኋላ አድራሻቸው እስከዛሬ ተሰውሮ ላሉ በርካቶች በምስጢር እስርቤትነት በማገልገል ላይ ከሚገኙ ወታደራዊ ካምፖች አንዱ እንደሆ ይታወቃል።
ዘመድ አዝማዶቻቸው ይመለሳሉ ብለው ሲጠብቋቸው ሳይመለሱ እንደወጡ የሚቀሩ በርካታ ዜጎች አሉ። በእንዲህ ሁኔታ ወጥተው ከቀሩ መካከል ከሰሞኑ የስድስቱ መቃብር በአጋጣሚ ተገኝቷል። የተገነዙበት ብርድ ልብስ ይነትብና ምንም ዓይነት ብልሽት ሳይደርስበት መገኝቱ ግዲያው በህወሃት ዘመነ መንግስት ስለመፈፀሙ ጥሩ ማስረጃ ነው። ለህወሃት ሰው መግደል ሥራ እንጂ ወንጀል አይደለም። በህወሃት ነፍሰ ገዳይ ይሞገሳል ይሾማል እንጂ አይወቀሰም አይጠየቅም። የስድስቱ ስዎች አስከሬን ሲገኝ መንግስትነኝ የሚለው ህወሃት አይቶ እንዳላየ መሆን ብቻ ሳይሆን ሌሎች አካላትም የሥፍራውን ሚስጢር እንዳያዩ ከልክሏል።በቁጥጥሩ ሥር ያሉ መገናኛ ብዙሃንም ዜናውን እንዳይናገሩ ታግደዋል። ህወሃት ከሚሰራቸው አስገራሚ ወንጀሎች መካከል አንዱይሄው ነው። ይሄ ግድያ በሌላ አካል ተፈፅሞ ቢሆን ኑሮ በረከት ስምዖንና እና ሺመልስ ከማል እየተፈራረቁ ያደነቁሩን ነበር።ይሄ የራሳቸው የእጅ ሥራነውና አይነገርም። የሄንንም የሚናገር እንደ ኢሳት ያለ ነፃ ሚዲያ ካለም ይታፈናል። አሸባሪም እየተባለ ይፈረጃል።
ግንቦት ሰባት የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ እነዚህ ዜጎች በህወሃት ተግድለው እንደተጣሉ ያምናል። ውሎ አድሮ እውነቱ እስከሚወጣ ድረስ ግን ዜጎች በሙሉ ይሄን ግድ በተመለከተ መረጃ የመሰብሰብና የማሰረጫት ሥራችውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ እናሳስባለን። ይሄን ወንጀል የፈፀሙ አካላት መጠየቅ አለባቸው። የዜጎች ደም እንዲሁ በከንቱ ፈሶ መቅረት የለበትም።

ለኢትዮጵያ ህዝብ መብትና ጥቅም እንታገላለን የሚሉ የፖለቲካና የስቪክ ድርጅቶች እንዲሁም ለሰው ልጆች የሰብአዊ መብት የሚሟገቱ ሁሉ የተገኘው አስከሬን በአስቸኳይ ተመርምሮ ማንነታቸው ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲገለጽ፤ ተጨማሪ አስከሬን ሊገኝ ይችላል በሚልስጋት የመንገድ ቁፋሮውን ከሰዎች እይታውጪ ለማካሄድ እንዲቋረጥ የተደረገው ሥራ ለህዝብ እይታ ግልጽ በሆነመንገድ በአስቸኳይ እንዲጀመር የመጠየቅ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ግንቦት 7 ያሳስባል::
በዚህአጋጣሚ ወያኔ ሥልጣን ከተቆጣጠረበት ጊዜጀምሮ በሱማሌ፣ በጋምቤላ፣ በአዋሳ፣ በጎንደር፣ በአዲስ አበባና ሌሎች የአገራችን ክፍሎች በጠራራ ጸሃይ ካስጨፈጨፋቸው በተጨማሪ በፖለቲካ እምነታቸው ምክንያት ታግተው በየእሥርቤቱ የተወረወሩትንና ከታገቱበት ዕለት ጀምሮ እስከ ዛሬ የደረሱበት ያልታወቁ ወገኖቻችንን ዝርዝር በአስቸኳይ ያሳውቅ ብለን አንመክረውም።እኛ ግን ህወሃት የደበቀውን ወንጀል ሁሉ ህዝብ እንዲያውቀው ለማድረግ ያለምንም ማቅማማት ጠንክረን እየሰራን ነው። መንግስት ነኝ ብሎ በሥልጣን ላይ የሚወጣ ማንኛውም አካል የህዝብ አገልጋይ እንጂ ነፍሰገዳይ እንዳይሆን የጀመርነው ትግል ተጠናክሮ ይቀጥላል።
እንግዲህ ህወሃት በህዝባችንና በአገራችን ላይ የሚፈጽመውን ሰቆቃ ለማስቆም ግንቦት 7 የጀመረውን የነጻነት ትግል አጠናክሮ እንደሚቀጥል እያስታወቅን እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ እንዲህ በየቦታው ተገድሎ ከመጣል ራሱን ለመታደግ ሲል የነፃነቱ ትግል አካል እንዲሆን ጥሪያችንን አሁንም ደግመን እናቀርባለን::
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!

Wednesday, January 8, 2014

የኢትዮጵያ ትምህርት አደረጃጀት ጋጋታ ለዉድቀት ወይስ ለጥራት!

January 8, 2014
Baile Derseh
ምህርት ሚኒስተር በ1ኛና በ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ላይ የመማር ማስተማሩን ሂደት በጥራት ለማከናወን ይረዳል በሚል ስበብ በየግዜዉ የሚፈበረኩ የአደረጃጀት ኩልኩሌ /ጋጋታ/ በማምጣት መምህራንን፤ተማሪንና ወላጅን ከማስጨነቅ አልፎ የትምህርቱን ጥራት ከመቸዉም በላይ እየዘቀጠ እንዲሄድ አድርጓል። ለዚህ መረጃ ይሆን ዘንድ ዓለም ባንክ በዲሴበር 7/2012 በ221 ገጽ በዘጠኝ ምዕራፍ በሰጡት መግለጫ አንኳር ነገሮችን አንስተዋል። እነዚህም አንኳር ጉዳዮችን በሰፊዉ በማተት የችግሩን አሳሳቢነት በማጉላት መንግስት በአስቸኳይ ርምት መዉሰድ እንዳለበት በአንክሮ ያስጠነቀቀ ሲሆን ችግሩንም በአፈጣኝ መግታት ካልተቻለ በአገርና በህዝብ ላይ ለያመጣ የሚችለዉን ችግር በግምገማዉ አስቀምጧል።
ኢህአደግ በየግዜዉ አዳዲስ የአደረጃጀት ጋጋታ በማምጣት ከመምህራንና ከተማሪዎች ጋር ግብግብ ሲፈጥር ይታያል እነዚህም አዳዲስ የትምህርት አደረጃጀቶች፡-የትምህርት ጥራትፓኬጅ፤ ኮማንድ ፖስት፤አንድ ለአምስት፤BPR/መሰረታዊ የስራ ሂደት፤የመምህራን ዉጤት ተኮር፤የልማት ሰራዊት፤ታህድሶ ፤የለዉጥ ሰራዊት፤ተማሪን ያማከለ የማስተማር ሂደት፤ሪፎርሜሽን/Reformation/…,የመሳሰሉትን የአደረጃጀት ኩልኩሌ/ጋጋታ/በማምጣት በትምህርቱ፤ በመምህራንና በተማሪዎች ዘንድ መቀቃርን በመፍጠር በትምህርት ዘርፉ ላይ ግዙፍ የጥራት ኪሳራ አሳይታል።እኔም ከዚህ በላይ የጠቀስኋቸዉን/የተጠቀሱትን የአደረጃጀት ጋጋታዎች በመዳሰስ አዎንታዉና አሉታዊ አካሄዳቸዎን ለማስቀመጥ እሞክራለሁ።
1/ የትምህርት ጥራት ፓኬጆች በአምስት ዋናዋን ክፍሎች ይከፈላሉ
ሀ/ የትምህርት ቤት መሸሻል መርሃ ግብር፡-ምቹ፤የተዋበና ለመማር ማስተማሩ ማራኪና የተዋበ ማድረግና
የህብረተሰቡን ተሳትፎ ማጎልበት ነዉ።
ለ/ የመምህራን ልማት መርሃ ግብር፡-የመምህራንን አመለካከት መለወጥ፤የመምህራንን አቅም ማሳደግና አዳዲስ
አሰራሮችን በመምህራንና በባለሙያዎች በማስጠናት ለትምህርቱ እድገት የሚበጁትን አሰራሮች መተግበር።
ሐ /የኢንፎርሜሽንን ቴክኖሎጅ ማሻሻያ መርሃ ግብር፡-መምህራንና ተማሪዎችን ከዘመኑ መረጃና እዉቀት ጋር
ማስተዋወቅና በዚሁ መርሃ ግብር በመጠቀም እዉቀታቸዉን ማሳደግ።
መ/  የስነ ዜጋና ስነምግባር ትምህርት መርሃ ግብር፡-የሀገሪቱን ህገ መንግስት ማዉቅና ለተማሪዎች በማስረጽ
የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብም በእኩልነት ላይ፤ በማንነት ላይ፤በህግ የነላይነት ላይ በመሳሰሉት ላይ የነቃን
የበሰለ ግንዛቤ መዉሰድ።
ሠ/  የስርዓተ ትምህርት መርሃ ግብር፡-ስርዓተ ትምህርቱን በመፈተሽ ግድፈቶችን አስወግዶ የማሰተካከል እርምጃ
መዉሰድ፤ተማሪዎችን ያሳተፈና ክህሎታቸዉን በሚያዉጣ መንገድ ማሰተማር፤የተማሪዎች ዉጤት
የሚሸሻልበትን መንገድ መተለም፤ተማሪዎችን ሊመዝንና የባህሪ ለዉጥ ሊያመጣ የሚችል መንገድ መተለም።
ረ/  የትምህርት አደረጃጀትንና አሰራር ማሸሻያ መርሃ ግብር፡-የትምህርት አስተዳደር ከማነኛዉም የፖለቲካ
አስተሳሰብ በመዉጣት መምህራንና ተማሪዎችን በማቀራረብ የትምህርቱን ስራ ለማጎልበት ወቅታዊ
አሰራሮችን መተግበር።
ከዚህ በላይ የጠቀስኋቸዉ ሳይንሳዊ ትንታኒያቸዉ ሲሆን ኢህአድግ እየተጥቀመበት ያለዉ በጠረጴዛዉ ገጽ ላይ እነዚህ ያማሩና አለም አቀፍ አደረጃጅቶችን በማስቀመጥ የጠረጴዛዉን ዉስጥ/under the table/የራሱን የፖለቲካ ማራመጃና ማስፋፋያ በማድረግ የሃገሪቱ ትምህርት እንደፋሽን በፈለገዉ ግዜ በመቀያየርና በመጫን የትምህርቱን ጥራት በእጅጉ ጎድቶት ይገኛል።
2/ ኮማንድ ፖስት፡-ት/ቤቶችን ከህዝብና ከመንግስት ክንፎች ጋር በማስተባበር መማር ማስተማሩን ሴኩላር በማድረግ ትምህርቱ የሚጎለብትበትንና ጥራቱ ጠብቆ የሚሄድበትን መንገድ መተለምና መተግበር ሲሆን መንግስትእየተጠቀመበት ያለዉ አሉታዊ የአደረጃጀት መምህራን ዋናዉን ጉዳይ በመርሳት መንግስት በሚሰጣቸዉ የአሉታዊ አደርጃጀት ኩልኩሌ በመጠመድ ከትምህርት ጥራት ወደ ሪፖርት ጥራት ተሽጋግሯል።
3/ አንድ ለአምስት፡- ተማሪዎችን በቡድን በማደራጀት ማህበራዊ ግንኙነታቸዎን በማጎልበት አብሮ የመስራትና የመተሳሰብ ክህሎታቸዎን ማሳደግ ሲሆን ገዥዎ መንግስት እየተጠቀመበት ያለዎዉ በቡድኑ ዉስጥ የራሱን አባሎች በመመደብ የራሱን የፖለቲካ አቋም የማይደግፉትን በመለየትና በተለያየ መንገድ ተማሪዎችን በማሸማቀቅ አልፎዎም የቤተሰቦቻቸዎን የፖለቲካ አቋም መገምገሚያ ሲሆን ይታያል።
4/ BPR/Business process reengineering/መሰረታዊ የስራ ሂደት ለዉጥ:-
  • አንድን ድርጅት ወይም ተቋም ለዉጥ ሊያመጣ የሚችልበትን የሰዉ ሀይል ግንባታ ለትምህርቱ ለዉጥ ሊያመጡ የሚያስችሉትን/ኮፒተር፤ICT፤ቤተሙከራ፤ቤተመጽሐፍት፤ትምህርት ማበልጸጊያና የመማሪያ ቁሳቁሶችን ግባት በማሟላት በትምህርት ቤቱ/በተቋሙ/ ዉስጥ በሚገኙት ሰራተኞች ፍላጎትና እምነት መሆን አለበት።
  • መልካም አስተዳደር በማመቻቸት የትምህርቱን ጥራትና ዉጤት የተሻለ ደረጃ ማድረስ
  • ሜዛናዊ የመምህራን ዉጤትተኮር አስራር ማስፈን
  • የመምህራንና የተማሪዎችን ቅሬታ አግባባዊ በሆነ መንገድ መፍታት
  • በሙያዉ ብቁ የሆኑና ግልጸኝነትን የተላበሱ አመራሮችን መመደብ
  • የደንበኞችን እርካታ ማሳደግ
  • የሰራተኞችን እዉቀትና ክህሎት መጨመር
  • ተጨባጭ ለዉጥ ሊያመጣ የሚያስችል ጥናት በሙያተኛዉ በማስጠናት ዉጤቱን በሚያስጠብቅ መንገድ መተግበረ
  • ለመምህራን የማትጊያና የማበረታቻ ስራዓት በመዘርጋት የትምህርቱን ጥራት ማጎልበት
ከላይ በአንኳርነት የጠቀስሗቸዉ በትምህርቱ ስርዓት ዉስጥ በመሰካት ትምህርቱን በማጎልበት የሚገኙ ሲሆን የኢህድግ መንግስት የአደረጃጀት ጋጋታ በመፍጠር መምህርንና ተማሪዎችን በማቃቃር ሀገሪቷ ትምህርትን ካልተጠቀሙበት ሀገር አንዷ ሆናለች።
ለዚህ ጉልህ ማሳያ የሚሆን ወያኔ በትግራይ ክልል መማር ማስተማርን በተመለከተ አንድ ማሳያ ማቅረብ እፈልጋለሁ።
በመቀሌ ከተማ መቀሌ ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጅና ቀዳሚኖ 1ኛና 2ኛ ደረጃ /ቤት አድሀሪ የሆኑት
  • ዉስጥ አደረጃጀታቸዉ የአዉሮፓንና የአሜሪካን ስታንደርድ የያዙ
  • መምህራን በዉጭ ሀገር መምህራንና በሙያዉ ከፍተኛ ብቃት ያላቸዉ
  • የተማሪዎች ቅበላ ከትግራይ ብቻ የሆነ
ሲሆን ተማሪዎች ትምህርታቸዉን በሚጨርሱበት ጊዜ በኢትዮጵያ ባሉ ቁልፍ መስሪያቤቶች ያለምንም ዉድድርና ማስቲዎቅያ  የተለየ እስኬል በማስቀመጥ በቀጥታ ሲመደቡ የተቀሩት በዉጭ ሀገር በሚገኙ እንባሴዎችን በሀገር ዉስጥ የስለላ መረቡን ተብትበዎ ይገኛሉ የተቀሩት ደግም በእንግሊዝን ፤ በአዉሮፓና በአሜሪካ በመንግስት ልዩ ትእዛዝ ለከፍተኛ ትምህርት ይላካሉ።መንግስት /ወያኔ/ ህገመንግስቱን ከሽኖ በወረቀት በማስቀመጥ ዉስጥዉስጡን የሚሰራዉ ገሀዱ ይህ ነዉ።ለዚህ አፍራሽ ተግባር ሁላችንም በመረባረብ የሁሉም ክልል የትምህርት አሰጣጥ ፍታዊነቱን ማረጋገጥ አለብን።