January 9, 2014ሳዲቅ አህመድ
ወጣቷ ኢትዮጵያዊት ዶክተር ድንቅ የቀዶ-ጥገና ስራዎችን እንደምታከናዉን በአሜሪካ የመገናኛ ብዙሗን ተዘግቧል። እርሷ የሙያ ግዴታዋን ትወጣ እንጂ ያደረገቻቸዉ የቀዶ ጥገናዎች አስደናቂ ናቸዉ ብላ አትገምትም፤ ግን ቤተሰቦቿ እዉነታዉን ያረጋግጣሉ። ኒይሮ-ሰርጀኗ ዶክተር እሙን አብዱ ባለፈዉ አመት መገባደጃ ላይ ያደረገችዉ የቀዶ ጥገና ሁሉንም ያስደነቀ ነበር።
ዶ/ር እሙን አብዱ
ነፍሰጡር ባለቤቱ ለወሊድ የተቃረበችዉ ኬኔት ዊሊያም የሐያ አምስት አመት ወጣት ነዉ። የአሪዞና ግዛት ነዋሪ የሆነዉ ኬኔት በገጠመዉ ሐይለኛ የጭንቅላት ህመም ሳቢያ የመዳን ተስፋዉ ሐምሳ በመቶ ነዉ ተብሎ ነበር። የሚወለደዉን ህጻን ድምጽ የመስማትም ህጻኑንን የማየትም እድል እንዳልነበረዉ ተነግሯል። ይህ አሜሪካዊ ወጣት እድሉ ሆኖ የዶክተር እሙን አብዱ ታካሚ ይሆናል፤ እሙንም ቀዶ ጥገናዉን በተገቢዉ መልኩ ታከናዉናለች። ቀዶ ጥገናዉ በፈጣሪ እርዳታ የተሳካ ይሆንና ኬኔት ዊሊያም የሚወለደዉን ልጅ ድምጽ መስማት ብቻ ሳይሆን ለማቀፍም በቅቷል።
ምን ያህል ኢትዮጵያዉያን ኒይሮ-ሰርጀኖች እንዳሉ መረጃዉ ለግዜዉ ባይኖረንም፤ እሙን አብዱ ካሉት ጥቂት ኒይሮ-ሰርጀኖች አንዷ ናት። እሙን ለብዙ ኢትዮጵያዉያን ሴቶች ሁሉንም ማድረግ እንደሚቻል”እሙን” መሆኑንን በተምሳሊትነት የምታሳይ የሰሜን አሜሪካ ኢትዮጵያዉያን-አሜሪካዉያን ማህበረሰብ አባል ናት። ምን አልባትም እናት-አገራችን ዉስጥ በኒይሮ-ሰርጀን የቀዶ ጥገና እጦት አደጋ ላይ ለሚወድቁ ኢትዮጵያዉያን ወገኖቿ ደራሽ ትሆን ይሆናል።
No comments:
Post a Comment