Saturday, November 30, 2013

እስራኤል ስደተኞችን ከሃገሯ አስወጣለሁ አለች:: ኢትዮጵውያኑም የገፈቱ ቀማሽ እንደሚሆኑ ተገልጿል፡

 30 בNovember 2013
Israeli immigration officers escort an African migrant in south Tel Avivእስራኤል ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ 60ሺህ የሚጠጉ አፍሪካውያን ስደተኞችን ከሃገሯ እንደምታስወጣ ያስታወቀች ሲሆን በህገወጥ መንገድ በሊቢያ የሚኖሩ ከ120 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ደግሞ ወደ ሃገራቸው ይመለሳሉ ተብሏል፡፡ የእስራኤል ካቢኔ ባለፈው እሁድ ስደተኞቹን የሚያስወጣ አዲስ ህግ ካፀደቀ በኋላ የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያዊን ኔትያሁ፣ ህገወጥ ስደተኞቹን ከሀገራቸው እንደሚያስወጡ አስታውቀዋል፡፡
የአገሪቱ ካቢኔ ባፀደቀው መመሪያ መሰረት እስራኤል በመጀመሪያው ዙር 4ሺ ስደተኞችን የምታስወጣ ሲሆን በቀጣይም በዘላቂነት ህገወጥ ስደተኞች ወደ ሀገሯ እንዳይገቡ በዘላቂነት ለመከላከል ከግብጽ የምትዋሰንበትን ድንበር ጥበቃ እንደምታጠናክር ገልፃለች፡፡ ከሀገሪቱ ይወጣሉ ተበለው የሚጠበቁት አብዛኞቸ ሱዳናውያንና ኤርትራውያን ሲሆኑ ኢትዮጵውያኑም የገፈቱ ቀማሽ እንደሚሆኑ ተገልጿል፡፡

Thursday, November 28, 2013

በቤሩት የተከናወነ አሰቃቂ ድርጊት

"በወገኖቻችን ላይ የሚደርሰውን ግፍ እና ሰቆቃ ፈጣሪ በቃ ይበለንን"
በሳውዲ ብቻ ሳይሆን ዛሬ በቤሩትም  በአሰቃቂ ሁኔታ በህታችን አዳነች ላይ የተከናወነውን ዘግናኝ ድርጊት በወቅቱ ኢትዩጽያኖቹ ለማጋለጥ ቢሞክሩም ቤይሩት ከሚገኘው ከኢትዩጽያ ቆንስላ አርፋችው ተቀመጡ የሚል መልስ  ማግንኘታቸውን አሳውቀዋል።
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/10112

Wednesday, November 27, 2013

ለኔ ግን ወገን ማለት........

ዛሬ ዛሬ ኛ ሌላ ዜጋ ነን ብለው ለሚያምኑ የወገን ጥቃት ምንም ላልመሰላቸው ማንነታቸውን ሳይጠየቁ ኢትዩጽያዊ አይድለንም እያሉ በህቶቻችንና በወንድሞቻችን እየደረሰባቸው ያለው ስቃይና ሞት ምንም ሳይሰማቸው የራሳቸውን ነገር ብቻ ለሚያራምዱ ለራስ ወዳዶች አዝናለው......!!!!
ለኔ ግን ወገን ማለት ወገኑ ሲነካ እንደ ንብ  ሆሆሆሆሆሆሆሆሆሆሆሆ......... ብሎ ለወገኑ መከታ የሚሆን ፣ህመማቸውና ስቃያቸው የሚሰማሁ....ይህ ነው ወገን ማለት ። 


Tuesday, November 26, 2013

በንፁሃን ላይ ያለ አግባብ ሲወሰድ የነበረው የቅጥረኞች እርምጃ አንጀቱ ላረረው ሕዝብ እምባ ያበሰ እንደሆነም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርና የጋምቤላ ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ ሰራዊት በጋራ ወታደራዊ ጥቃት ፈፀሙ

የጋራ ትግል አስፈላጊ መሆኑን በፅኑ የሚያምኑት የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር /ኢሕአግ

Ethiopian freedom fighters
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርና የጋምቤላ ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ /ጋሕነን/ በሕዳር 13/2006 ዓ.ም በሁመራ ሉግዲ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1፡00 ለሶስት ሰዓት ያህል በወሰደው ውጊያ የወያኔው 24ኛ ክፍለ ጦር ድባቅ ተመቷል።
ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በ24ኛው ክፈለ/ ጦር ላይ በተመሳሳይ ሥፍራ  ከፍተኛ ድል መቀዳጀቱ ይታወሳል።
በሕዳር 13/2006 ዓ.ም የኢሕአግና የጋህነን ሰራዊት በወሰዱት ድንገተኛ ወታደራዊ ጥቃት 66 /ስልሳ ስድስት/ ገድለው 113 /አንድ መቶ አስራ ሶስት/ በማቁሰል እንዲሁም ቁጥራቸው የበዛ የጦር መሳሪያዎችን ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ማርከዋል።
ሁለቱ ድርጅቶች በጋራ በተለያየ የትግል መስክ ሲተጋገዙና ሲተባበሩ ቆይተዋል የግንኙነታቸውን እድገትና ለውጥ የሚያሳይ ወታደራዊ ጥቃትም ፈፅመዋል።
ይህ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚመኘውና የሚፈልገው የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ስምምነትና አንድነት መገለጫ ሊሆን የሚችል አኩሪ ጥቃት መሆኑ ይታመንበታል ። በጥቃቱ የተካፈሉ የሁለቱ ድርጅቶች ታጋዮች እንዳብራሩት ዛሬ በጋራ የጀመርነው ወታደራዊ ጥቃት በዚሁ የሚያበቃ ሳይሆን የጋራ ዓላማና ራዕይ እስካለን ድረስ ወደኋላ የማይቀለበስ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ከዚህም አክለው የዚህ ወታደራዊ ዘመቻ ዓላማ አገር እንደሌለው ሁሉ በሰው አገር ፍዳውን እያየና እየተሰቃየ እንዲሁም ለሞት እየተዳረገ የሚገኙውን በሳውዲ አርቢያ ለተፈፀመው በደል ለመበቀልና ሕዝባዊ ወገንተኝነታችንን ለማሳየት ታስቦ የተወሰደ ወገናዊ እርምጃ ነው በማለት አብራርተዋል።
በውጊያው ከሞት ተርፎ ለከባድ ቁስልና የአካል ጉዳት የተዳረገው የወያኔው ቅጥረኛ የ24ኛ ክፈለ ጦር አባላትን ከሁመራ አንስቶ እስከ ትግራይ የሕክምና ማዕከሎች ማጋጋዝ ዋነኛ ተግባሩ ሆኗል።
ይህንን የጀግና ጥቃትና ድል የተመለከቱ የአካባቢው ነዋሪዎች ሰራዊቱን እንኳን ደህና መጣችሁ ብሎ በመቀበልና ስንቅና ትጥቅ በማቅረብ አጋርነቱን ያስመሰከረ ሲሆን የተጀመረው ወታደራዊ ጥቃት በተለያዩ አካባቢዎች ላይ እንዲደገም ያላቸውን ልባዊ ምኞት ገልፀው በንፁሃን ላይ ያለ አግባብ ሲወሰድ የነበረው የቅጥረኞች እርምጃ አንጀቱ ላረረው ሕዝብ እምባ ያበሰ እንደሆነም ተናግረዋል።
በመጨረሻም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር/ ኢሕአግ/ እና የጋምቤላ ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ /ጋህነን/ ወያኔ ለ22 ዓመት ያህል አገሪቷን ሲበዘብዝና ሕዝቡ የዲሞክራሲያዊ መብቱ ተጠቃሚ እንዳይሆን በሃይል የመግዛቱ ሂደት እንዲያከትም የተቻላቸውን ሁሉ ለማድረግ ቆርጠው መነሳታቸውን አስታውቀዋል።

Monday, November 25, 2013

ወገን ከምንለው የማህበረሰባችን አካል ይሄን መስማቱ ከጥቃቱ ይበልጥ ያማል....!!!!

ተዋርደን አንቀርም!!!
ሳውዲ አረቢያ በዜጎቻችን ላይ እያደረሰች ያለውን ግፍና በደል በሰላማዊ ሰልፍ ለመቃወም ፓርቲያችን በወሰነው መሰረት ለሚመለከተው ክፍል አሳውቀን ነበር፡፡መቸም ህዝባችን በጭቆና ውስጥ ስለኖረ በመብቱና በግዴታው መሀል ያለውን ድንበር በውል ካለመረዳቱ የተነሳ ሰልፉ እንዲደረግ ስለመፈቀዱ በተደጋጋሚ ስንጠየቅ ነበር፡፡ህጉ የሚለው ግን ማስፈቀድ ሳይሆን ማሳወቅ ብቻ ነው፡፡በተቃራኒው መንግስት በተለያዩ ጉዳዮች ሳቢያ በእለቱ ለሰላማዊ ሰልፉ የደህንነት ከለላ መስጠት የማይችልበት ሁኔታ ከገጠመው ሰልፉን ለጠራው አካል ችግሩን ገልጾ ቀኑ እንዲተላለፍለት ይጠይቃል፡፡በመሆኑም ይህን መሰል ጥያቄ ከሚመለከተው መስሪያ ቤት ለፓርቲያችን ባለመቅረቡ በሙሉ ልብ ቅድመ-ዝግጅት ማድረጉን ተያያዝን፡፡
ሁሌም ቢሆን መንግስት ሰበብ ፈልጎ ሊወነጅለንና ከመስመር ሊያስወጣን እንደሚፈልግ በሚገባ እናውቃለንና በጥቃቅን ጉዳዮች ላይ ሳይቀር ጥንቃቄ እናደርጋለን፡፡ለሚመለከተው መስሪያ ቤት ባሳወቅን በአስራ ሁለት ሰአታት ውስጥ ምላሽ ስላልመጣ ሙሉ በሙሉ ህጋዊነታችንን አረጋግጠናል ማለት ነው፣እነሱ ደግሞ ጠብ-መንጃ በእጃቸው አለና የፈለጉትን ሁሉ ማድረግ ይችላል፡፡
አቶ ሽመልስ ከማል ለሚዲያወች የሰጡትን ፍጹም ከእውነት የራቀ ውንጀላና ሰበብ አዳምጨዋለው፡፡ “ሰላማዊ ሰልፉን ያገድንበት ምክንያት ጸረ-አረብ መፈክሮች ስለነበሩ ነው“ብለዋል፡፡መጀመሪያ ደረጃ ሰልፉ ገና ከግቢው ፈቅ ሳይል ነው ያፈኑት፣ሆኖም የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም አንድ በአንድ እየሆንን ወደ ሰላማዊ ሰልፉ መዳረሻ ለመሄድ ስንሞክር የተወሰኑ አመራሮችን አራት ኪሎ አካባቢ ያዙን፣እነሱ ቀድሞውኑ ሰልፉ እንዳይካሄድ ስለወሰኑ ነው እንጅ ትንሽ እንኳ ተንቀሳቅሶ የሰልፉን ባህሪ ለመገምገም ምንም እድል አልሰጡንም፡፡ለምሳሌ ሰልፉን እንደምናደርግ ይፋ ባደረግን ማግስት ከራዲዮ ፋና ተደውሎ አንዳንድ ጥያቄዎች ተጠይቄ ነበር፡፡በቃለ-መጠይቁ ሰላማው ሰልፉ በዜጎቻችን ላይ የሚደርሰውን በደል በመቃወም እንደምናደርግ ተናግረናል፡፡ጋዜጠኛው ለሰላማዊ ሰልፉ ተሳታፊዎች መልዕክት ካለ ብሎ በጠየቀኝ ወቅት የሳውዲ አረቢያ ሰንደቅ አላማ ላይ ያለው ምልክትና ጽሁፍ ሀይማኖትን የሚመለከት በመሆኑ ዜጎች በስሜታዊነት ባንዲራ እንዳያቃጥሉ፣እነሱ ቢያዋርዱንም እኛ ግን ክብር ያለን ዜጎች ስለሆንን ተቃውሟችንን ጨዋነት በተሞላበት ሁኔታ ማካሄድ እንዳለብን ተናግሬ ነበር፡፡ከሰላማዊ ሰልፉ በፊት በዚህና በተለያየ መንገድ በማያሻማ ሁኔታ መልዕክት ባስተላልፍም እነሱ ግን ይህን በመቁረጥ አላስተላለፉትም፡፡እነዚህና ሌሎች ምክንያቶች ሲደመሩ የአቶ ሽመልስ ከማል ንግግር ነጭ ውሸት መሆኑን ያስገነዝባል፡፡
ሁለተኛ የአንድ ሀገር መንግስት ዜጎቹ እየተደፈሩ፣በማጎሪያ ካምፕ በረሀብና በውሃ ጥም፣ሌላው ቢቀር መጸዳጃ ቤት እንኳ ተከልክለው ፍጹም ከሰውነት ክብራቸው ወርደው እየተበደሉ፣እየተገደሉ ባለበት ወቅት ገና ለገና ተቃዋሚ ፓርቲ በጠራው ሰልፍ ላይ በሚንጸባረቅ ጥላቻና ተቃውሞ የዲፕሎማሲ ግንኙነቴ ይበላሽብኛል ብለን መናገር እንችላለን?ሌላው ይቅር አንድ ክፉና ደጉን የለየ ሰው የሚያስበው ጤነኛ ሃሳብ ነው ማለትስ ይቻላል?
ከእገዳው ባሻገር የሚደንቀው ነገር ደግሞ በፓርቲያችን አመራሮችና አባላት ላይ የተደረገው ድብደባ ነው፣የሆነ ማስተላለፍ የፈለጉት ነገር ያለ ይመስላል፡፡የጭካኔያቸውን መጠን እንድናውቅ የሚደበድቡት አቅመ-ደካሞችን፣ሽማግሌወችንና ሴቶችን እየመረጡ በፍጹም አረመኔነት ነበር፡፡ይህን ተግባራቸውን ስመለከት የደረሱበትን የዝቅጠት ደረጃ መታዘብ ችያለው፡፡ከፖለቲካ ልዩነትም፣ከአምባገነንነትም በላይ ሰወቹ እንደታመሙ ነው ለመረዳት የቻልኩት፣ስር የሰደደ የቁስ ሰቀቀንና የስልጣን ጥም የተጣባቸው፣ለዚያ ሲሉም የትኛውንም አይነት ውርደት ለመቀበል የቆረጡና የሞራል ልዕልናቸውን ሙሉ በሙሉ ያጡ ሰዎች ናቸው፡፡ስነ-ልቦናቸው ክፉኛ ተቃውሷል እንጂ ሀገር እመራለው የሚል ቡድን እንዲህ ያለ ተግባር ይፈጽማል ለማለት እቸገራለው፡፡በአባላቶቻችን ላይ ክፍኛ ድብደባ ተፈጽሟል፣እስከዛሬም እግሮቻቸው መራመድ የማያስችላቸው፣የሚያነክሱ ሰዎች አሉ፡፡እውነት ለመናገር ይሄ እብደት ነው፡፡አንዲት እራሷን መከላከል የማትችል ሴትን ለሶስት መደብደብን ከዚህ በተሸለ ልገልጸው አልችልም፡፡አንድ ማስገንዘብ የምፈልገው ነገር ለኛ ዋነው ጉዳይ የዜጎቹ ህጋዊነት ወይም ህጋዊ ያለመሆን ጉዳይ አይደለም፡፡በምንም አይነት መንገድ ሴቶች እየተደፈሩ፣ወንዶች በየስርቻው እንደ ውሻ ተቀጥቅጠው እየተገደሉ እንዲሁም በተለያዩ ቦታዎች ታጉረው ይህን ሁሉ መከራ መቀበላቸውን ልንታገሰው፣ወይም ከህጋዊነት አንጻር እየተራቀቅን ልንመለከተው አንችልም፣ስለ ህግም ከተወራ የሳውዲ አረቢያ መንግስት ጭፍጨፋው ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ባላቸው ላይ ጭምር ሲፈጸም እንደነበር አምኗል፡፡
ባለንበት የግሎባላይዜሽን ዘመን የአንዱ ሀገር ዜጋ ካለ ሀገሩ መገኘት አገር ይያዝ የሚያስብል አይደለም፡፡መውጣት ካለባቸው ጊዜ በመስጠት፣ከመንግስታቸው ጋር በመነጋገር በዘዴ ነገሩን መከዎን እየተቻለ አንድ ሀገርና መንግስት በሰዎች ላይ እንዲህ የጭካኔ ጥግ የሆነን አቋም ይዘው መንቀሳቀሳቸው ፍጹም ኢ-ሰብአዊነት ነው፡፡
ለኢትዮጵያውያን እንዲህ ያለ አስከፊ ጊዜ የለም፣እውነቱን ለመናገር ለአገዛዙ ሰዎች የነበረኝ ጭላንጭል ተስፋም አፈር ተደፍቶባታል፣እንዲህ ግልጽ የሆነ ጭፍጨፋ እየደረሰብን እንኳ በድፍረት ለመናገር አልፈለጉም፡፡ስለ ኢትዮጵያውያን መገደል ለማውራት ሲፈልጉ ሌላ ሀገር ይጠቅሱና እነሱም እኮ እየተገደሉ ነው ይላሉ፣ወገን ከምንለው የማህበረሰባችን አካል ይሄን መስማቱ ከጥቃቱ ይበልጥ ያማል፡፡
ለምሳሌ ኢቲቪ ስጉዳዩ ሲያወራ ህገ ውጥ ሊባል የሚችል ድርጊት ተፈጽሟል በማለት ነው፡፡ተመልከቱ! እንዴት ያለ ባዕድነት ነው?ኢትዮጵያውያን በድህነትም ውስጥ እንኳ ለክብራችን የመሞት ባህሪ አለን፣ይሄ ከቀደሙት አንጡራ ኢትዮጵያውያን የወረስነውና ዛሬም ያለን ሀብታችን ነው፡፡
ትናንት ፍየል ጠባቂ የነበረ በረኸኛ ይህን ክብራችንን ገፍፎ እንደውሻ ቀጥቅጦ ስርቻ ሲጥለን ያልተቆጣ መንግስት ኢትዮጵያዊ ነው?ከዜጎቹ የወጣና ለህዝቡ የቆመ እውነተኛ መንግስት ከዚህ የበለጠ የሚቆጣበት ጉዳይ ከወዴት ይመጣል?
እውነተኛ መንግስት ቢሆን ኖሮ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የሳውዲ ካምፓኒዎችን በሰአታት ውስጥ ማባረር፣ኢምባሲውን ዘግቶ አምባሳደሩን ማሰናበትን የመሳሰሉ ውሳኔዎችን ያሳልፉ ነበር፡፡የሆነው ግን በተቃራኒው ነው፣የድፕሎማሲ ግንኙነቴ ሊበላሽ ይችላል ብሎ እኛ ድምጻችን እንዳናሰማ ደበደበን፣አፈነን፡፡በግልጽ እንደሚታየው የጥቅም ትስስሩ ነው አፋቸውን ያዘጋቸው፣ይህች ጥቅማቸው እንዳትቋረጥ በዜጎች ህይዎት መደራደርን መርጠዋል፡፡
ስነ ልቦናቸው የተቃወሰ በመሆኑና ተራ ስስታሞች በመሆናቸው እንጂ ኢንቨስትመንትም ሆነ ዲፕሎማሲ ግብአትነታቸው ለሰው ልጅ ነው፣እንደ አህያ ሲያፈጋ ከርሞ ሬሳቸውን ለላከ መንግስት እንዴት ተመጣጣኝ ምላሽ ለመመለስ ይገዳል?እንዴት እንደ ኢትዮጵያ ያለች ታሪካዊትና ለአፍሪካ የነጻነትና የኩራት ተምሳሌት የሆነች ሀገርን እየመሩ እንዴት ትናንት የነዳጅ ዘይት ባቆማቸው እረኞች ስትዋረድ ዝም ይላሉ?!::
እንዴት!
በዜጎች ህይወት የተደራደረው አገዛዝ ማለፉ አይቀርም፣ለዚህ ጥርጥር የለኝም፡፡ታሪክ ለመጥቀስ ብዙ ርቀት መሄድ አያስፈልግኝም፡፡የቅርብ የሰሜን አፍሪካ አምባገነኖች የከፋ ፍጻሜ አለና፡፡ኢትዮጵያውያን ፍቅርም ጸብም እናውቃለን፣ሳውዲወችም የፈጸሙትን ግፍ ማወራረዳቸው አይቀርም፡፡በዚህ ክፉ ጊዜ ስለስብአዊ መብት ቆመናል የሚሉ አለም አቀፍ ተቋማት ዝምታን መምረጣቸው እውነተኝነታቸውን ለመመርመር ጥሩ እድል ይሰጠናል፡፡
መንግስት ቢኖረን ኖሮ ይሄ ሁሉ ውርደት ይፈጸምብን ነበር ብየ አላስብም፡፡በዚህ ሰአት ርዕሰ-መንግስት ብሆን ኖሮ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ትልቅ ድርጅት እንደመሆኑ፣ወደየትኛውም ሀገር የሚደረገውን ጉዞ አቋርጨ ዜጎቸን ማስወጣትን አስቀድም ነበር፡፡ያሄ ጥቂት ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ ሊያመጣብን ቢችልም ከከፋው የዜጎች ስቃይ ጋር ግን በአንድ ሚዛን ላይ አይቀመጥም፡፡የአደጋ መከላከያና ዝግጁነት ኮሚሽን የሚባል ድርጅት አለ፡፡በዜጎቻችን ላይ ጎርፍና ድርቅ ሲመጣ ብቻ ነው የሚንቀሳቀሰው? ይሄም ሰው ሰራሽ አደጋ ነው ሙሉ ሀይሉን ወደዚህ አዙሮ ሊንቀሳቀስ ይገባው ነበር፡፡እርግጥ ነው ባቀድነው መሰረት ሰላማዊ ሰልፉ ሙሉ በሙሉ ስኬታማ እንዳይሆን አድርገውታል፡፡ጩኸቱ ግን ይቀጥላል……ባለን አቅም ሁሉ አፈናውንም፣ወከባውንም ተቋቁመን ለዜጎቻችንና ለኢትዮጵያዊነት እንታገላለን፡፡
አገዛዙ ይሄን ሰላማዊ ሰልፍ ሲያፍን ለኢትዮጵያ ህዝብ እንድ መልእክት አስተላልፏል፣ይህን መልእክት እንዲያስትላልፍ ማስገደዳችንም ለኛ ትልቅ ስኬት ነው፡፡የሳውዲ መንግስት ያሻውን ያደርግ ዘንድ የፈቀድኩት እኔ ነኝ፣በመሆኑም እሱን በመቃወም ግንኙነቴን አታበላሹ ብሎ እርምጃ በመውሰዱ ህዝቡ የነገሩ ቁልፍ የት እንዳለ፣የአጥቂወቹ በራስ መተማመን ምን ላይ እንደቆመ በጠራ ሁኔታ ለመመልከት እንዲችል ሆኗል፡፡
ይሄ ሁሉ ነገር እየተፈጸመ የተስተዋለ አንድ ነገር አለ፡፡የጠቅላይ ሚኒስትሩ ዝምታ እውነተኛ ማንነታቸው፣እውነተኛ በአገዛዙ ውስጥ ያላቸውን ቦታ ያሳየን ክስተት ነው፡፡እንደሚታወቀው እሳቸው በኢህአዲግ እንጂ በኢትዮጵያ ህዝብ የተመረጡ አይደሉም፡፡ኢህአዲግ የሚናገረው ከሌለ እርሳቸው የሚሉት አይኖርም፡፡እንደ አንድ ሀገርና ህዝብ መሪ ግን የመኮነንም ሆነ የማጽናናት ቃል ይጠበቅባቸው ነበር፡፡
ባሉበት ቦታ ያስቀመጣቸው ህወሀት ነው፤ድርጅቱ ደግሞ ይሄን አቋም አልወሰደም፡፡ስለዚህ እንደሚቆጣቸው ስለሚያውቁ ዝምታን መረጡ፣ቸልታንም አስበለጡ፡፡በሀገርም ሆነ በግለሰብ ደረጃ ከዚህ በላይ ሽንፈት ያለ አይመስለኝም፡፡
(ይህ ጽሁፍ በፋክት መጽሄት ተስተናግዷል፣ነገር ግን መጽሄቱ ላልደረሳቸው ሰዎች ይደርስ ዘንድ እዚህ ለማስተናገድ ወደድኩ፡፡)

Sunday, November 24, 2013

የተማራቂ ተማሪዎች “ጌት ቱጌዘር”

በጎንደር ዩንቨርስቲ ውጥረቱ እንደቀጠለ ነው .አንድ ተማሪ በታጣቂዎች ተገድሏል

ነገሩ የተፈፀመው የተማራቂ ተማሪዎች “ጌት
ተጌዘር” አዘጋጅተው ያንን ፖሮግራም ጨርሰው ከምሽቱ ሁለት ሰአት ተኩል አካባቢ ወይም ከዛ ረፈድ ብሎ በቁጥር ወደ
ሀምሳ የሚሆኑ ተማሪዋች ወደ ዩኒቨርስቲው በር አካባቢ ሲደርሱ ሞች እና በወቅቱ ከሟች ጋር አብራ የነበረች ተማሪ ቀድመው
ወደ ጥበቃ በመድረሳቸው ጥበቃው እንዲቆሙ በሚያዛቸው ወቅት ሟች የለም ከግቢው በር ውጭ ልታስቆመን መብቱ
የለህም እንደውም መታወቂያህን አሳየኝ በማለት በመባባል ነገሩ እንደተጀመረ እና በወቅቱ ተማሪዎቹ መጠጥ መቀማመሳቸውን
፣ ሟችም በስካር መንፈስ ሆኖ ግብግብ መፈጠሩን ጥበቀውም ከሟች ጋር የነበረችውን ምንዋን እንደመቱዋት
ባልታወቀ ሁኔታ እራሱዋን መሳትዋን እና መውደቁዋ ፣ በዚህ መሀል ተማሪዋቹ ለማገላገል በሚጠበጉበት ወቅት ጥይት
በመተኰሱ በድንጋጤ (ሶሰት ግዜ መተኰስሱን ልብበሉ) መበታተናችወን እና ጠዋት ሟች በተባለው ቦታ ደም ፈሶት
ሟቶ ስለመገኘቱ በጉንደር ዪኒቨርሰቲ የሳስተኛ አመት ማርኬቲንግ ተማሪ የሆነው እና በወቅቱ ቦታው ላይ የነበረው ወንድሜ
የነሀረኝን ሳልጨምር ሳልቀንስ!! በጣም የሚያመውና
የሚያቆስለው ሟች የተገደለው እርስ በርስ በጩቤ ተወጋግተው ነው በማለት አንድን ተጠርጣሪ ነፍሰ ገዳይ
ዘበኛ ለዛውም የህክምና እርዳታ ቢያገኝ ሊድን የሚችልን ልጅ እንደውሻ ጐትተው ወንዝ ዳር በመጣል የጭካኔ አገዳደል የገደለን ለማድበስበስ
መመኮራቸው ሳያንስ ይህን ለመቃወም ሰልፍ የወጡትን ተማሪዋች በፈደራል አስደብድበው የሰአት እላፊ አውጅው አስረዋቸዋል
ወጣት አንተነህ አስፋው ለገሰ  የማርኬቲንግ ማኔጅመንት የ፫ኛ ዓመት የድግሪ ተማሪ ነበር
source: freedom4ethiopian

አንድ ጊዜ ሆድ ብሶኝ ራሴን ለማጥፋት ሞክሬ ነበር....!!

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/9831

Friday, November 22, 2013

የዜጎቻችን እንባና ደም በግደለሽነት አንየው...!!!

(ራሄል ኤፍራም)
November 22.11.2013
ስቃያቸው እንደ ወንዝ ጅረት ለበዛው እና እንደ ቀልድ እየተደፈሩ የትም ለቀሩት ህቶቻችን እንዲሁም  ሂወታቸው በየቦታው እንድዋዛ ለረገፈው ወንድሞቻችን፣ ሀዘናችው ውስጣችንን እያቃጠለው፣እያንገበገብው  ፍትህ እስከምናገኝ መቀመጫ ያልሰጠን የወገኖቻችን ጉዳይ ፖለቲካ ሳይሆን የማንነት ጥያቄ መሆኑን ሁላችንም ልንገነዘብ ይገባል።
  ማንነታችን ተደፍሮ ፣ተንቀን ፣ተዋርደን ፖለቲካ ነው እያልን የምንሸሽ ካለን ስህተት ነው። ወገኖቻችን በሰው ሀገር መደፈር ፣መደብደብ ፣መሰቃየት ፣መዋረድ እና መገደል የሁላችንም ህልውና የሚነካ ሲሆን ይሄንን የስፖርት ቤተሰብ የወገኖቻችንን ስቃይና ጉዳት እንዲሁም በአሰቃቂ ሁኔታ መሰቃየታቸው እና መገደላቸው እንደወገን ሊሰማቸው የገባል።
ጉዳታቸው ጉዳታችን ፣ስቃያቸው ስቃያችን ፣ ውርደታቸው የሁላችንም ውርደት በመሆኑ ይህንን በመገንዘብ በስቃይና በመከራ ወስጥ ያለውን የወገኖቻችንን ድምፅ ማሰማት የኢትዮጵያዊነት ግዴታችን ነው።

በእርግጥ አንድ እውነት አለ የዚህ ሁሉ የወገኖቻች መሰቃየት ፣ የህቶቻችን መደፈር ፣የወንድሞቻችን መደብደብ በተለያየ መንገድ ሂወታቸውን ማጣታቸው ዋንኛው ምክንያት ስልጣንን ከህሊናቸው በማስበለጥ ለሃገራቸው ሳይሆን ለጥቅማቸው ሲሉ እንድ እባብ በሆዳቸው እየሄዱ መርዛቸውን እየረጩ እነሱ እየኖሩ ሌላሁን የስደት ቁራኛ በማድረግ ከመኖረም በላይ በህዝቦቻቸ ደም ላይ አንደዚ እየተሳለቁ ወገን ሲዋረድ ሀገር አቀርቅራ ስታለቅስ እነሱ ሽቅብ እየሳየቁ ወገኖቻቸን ችግር ከምንም ባልቆጠሩት ቱባ ያገራችን ባለስልጣናት ምክንያት መሆኑ ግልፅ ነው ።
ሆኖም ግን ጥያቄው በዜጎቻችን ላይ የሚደርስው ጥቃትንና አሰቃቂ ግድያ እንዲያቆም እና ፍታዊ እርምጃ እንዲወሰድ እንጂ ፍጹም ከፖለታካ ጋር የሚያያይዘው አንድም ነገር አለመኖሩ እንዲሁም ባገኘነው አጋጣሚ ለወገኖቻችን መጮህ እንዳለብን ድምፃቸው እንዲሰማ የግላችንን አስትዋፆና ጥረት በማድረግ ፍትህ የሚያገኙበትን መንገድ በመፍጠር ለወገኖቻቸን መቆማችንን በታላቁ እሩጫ ላይ ጥቁር ሪቫን በማሰር አዘናችንን እና የተሰማንን የወገናዊነት  እናሳይ ።

Thursday, November 21, 2013

የኢትዮጵያዊያን ሴቶች አሰቃቂ ሂወት በሀገር ውስጥ እና በስደት ኣውደርዕይ

(ምስራቅ መንበሩ)
በሃገራችን ኢትዮጵያ ወያኔ ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ  በኣስከፊ ሁኔታ አየተባባሰ የመጣው የዜጎች መብት ረገጣ ፣ በተለይም በዚ ስርአት ዋነኛ ተጎጂ የሆኑት ሴት አህቶቻችን በሀገር ውስጥ በመንግስት አካላት በሚደርስባቸው ጥቃት ለ አካል አና ስነልቦና ጉዳት ሰለባ የተዳረጉትን እና ገዢው ፓርቲ ባመቻቸው አና በከፍተኛ ሁኔታ አየተስፋፋ የመጣው ህገወጥ የሰው ዝውውር ዘመናዊ ባርነት ወደ አረብ ህገራት በዜጎች ላይ እያደረሰ ያለው ከፍተኛ ሰቃይ፣ አንግልት፣ አስር፣ ሞት አና የመሳሰሉት ችግሮች በየጊዜው የምንሰማው እና እልባት ያልተገኘለት መራር አውነት የሚያሳይ የፎቶ ኣውደርዕይ እና ገለጻ  በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የሴቶች ክፍል ኣዘጋጅነት በኦስሎ ከተማ ተደረገ ።
በዝግጅቱ ላይ ከቀረቡት ፎቶዎች መሀከል ሴቶች በሀገር ውስጥ የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊ ናቹ በሚል በመንግስት ኣካላትeth women2የሚደርስባቸው አሰቃቂ ድብደባ በአካላቸው ላይ የደረሰባቸው ጉዳትን የሚያሳ፥ ገዢው መንግስት በልማት ሰበብ ነዋሪዎችን ያለምንም ቅድመ ዝግጅት ከመኖሪያቸው በማፈናቀል ለጎዳና ህይወት መዳረጋቸው በየሜዳው መበተናቸው የሚያሳይ (እነዚህ ዜጎች መጠለያ በማጣት ለጎዳና ህይወት መዳረጋቸው ሴቶች ለተለያየ ጾታዊ ጥቃቶች፣ መደፈር፣ ላልተፈለገ እርግዝና፣ ለተለያዩ በሽታዎች እንዲጋለጡ ብሎም ሴተኛ ኣዳሪነት አንዲስፋፋ እና ለስደት ለህገወጥ ዝውውር ምክኒያት መሆኑ ይታወቃል)።
የዚህ ዝግጅት ዋነኛ ክፍል የነበረው በህገወጥ መንገድ በተለይም ወደ አረብ ሀገራት ለርካሽ የጉልበት ስራ ብዝብዛ  በሚሰደዱበት ሀገር የሚደርሰባቸው ሰቃይ አና አሰቃቂ ሞት የሚያሳዩ የተለላዩ ፎቶውች ናቸው ።
(በ100,000  የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ሴቶች አብዛኛዎቹ እድሜአቸው ከ18 በታች የሆኑ ህጻናት ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በህገወጥ መንገድ ለጉልበት ስራ ዘመናዊ ባርነት ወደ አረብ ሀገራት ይሰደዳሉ። በተሰደዱበት ሀገር ህጋዊ ጥበቃ ከኢትዮጵያ መንግሰትም ሆነ ከተሰደዱት ሀገር መንግስት ባለማግኘታቸው ከአቅም በላይ የሆነ የጉልበስራት በቀን ከ18  ሰዓት በላይ አንዲሰርሩ በመገደድ ፣  የሚደርስባቸው ከፍተኛ ስቃይ እና እንግለት፣ ድብደባ፣ በኣሰሪዎቻቸው በተደጋጋሚ መደፈር፣ በአካል አና ስነልቦና ጉዳት ብዙዎች ለአይምሮ ህመም በሽታ በመዳረጋቸው እና ክትትል የሚያደርግልቸው ባለማግኘታቸው በባእድ ሀገር በየጎዳናው ወድቀዋል።
ይህ ስቃይ ከኣቅማቸው በላይ የሆነባቸው ሰሚ ያጡ ዋይታዎች፣ ድብደባ መቛቛም ያቃታቸው፣ በመደፈር ባዛት የደከሙ የጨቅላ ገላዎች፣በደል የበዛባቸው ብዙ እህቶች፤ መርዝ በመጠጣት፣ ከፎቅ በመፈጥፈጥ፣ በመታነቅ ሂወታቸውን ያጠፋሉ።
ከመነሻው ለዚህ ችግር ምክኒያት የሆነው ገዢው መንግስት በዜጎቸ ላይ የሚደርሰውን እንግልት እና የግፍ ሞት ግዴለሽ በመሆኑ እና ባለመጠየቁ ዛሬ ኢትዮጵያዊነት ወንጀል እስኪመስል ድረስ በሳውዲ በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለውን ስቃይ አንገልት እንዲባባስ ምክኒያት በመሆን ብሎም ለህዝቡ ያለውን ከፍተኛ ንቀት አያሳየ ይገኛል።)
በዘግጅቱ ላይቁጥራቸው በዛ ያለ   ሰዎች የተገኙ ሲሆን ተጋባዥ አንገዶችም  ንግግር ኣድርገዋል።

Tuesday, November 19, 2013

"ለመላዉ ኢትዮጲያዊያን፡- ከሰማያዊ ፓርቲ የተላለፈ ጥሪ"

Posted on 

ለመላዉ ኢትዮጲያዊያን፡- ከሰማያዊ ፓርቲ የተላለፈ ጥሪ
በሳዑዲ ለሚሞቱና ለሚንገላቱ ወገኖቻችን ያለንን ተቆርቋሪነት
አሁንም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት፡፡ ሰሞኑን በአዲስ አበባዉ
ሰልፍ የተፈፀመዉን መንግስታዊ ሽብር ሁላችንም በሀዘን
አልፈነዋል፡፡ ነገር ግን ለብሔራዊ ቡድናችን ያደረግነዉ ጥሪ
በቸልተኝነት መታለፉ ፣ በሀይማኖት ተቋማትም የሚፈለገዉን
ያህል ጥሪዉን ባለመቀበላቸዉ የዘንን ቢሆንም ህዝቡን ከጎናችን
በማቆም የደረሰበትን ነገር ሁሉ በፅናት መቀበሉ አኩርቶናል፡፡
በቀጣይነትም የተለያዩ ስራዎችን ለመስራት ታስቧል፡፡ ከነዚህ
ዉስጥ በመጪዉ እሁድ ህዳር 15 ቀን በአዲስ አበባ በሚካሄደዉ
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጲያ ላይ የምንሳተፍ ሰዎች ጥቁር ሪቫኖችን
አድርገን እንድንሳተፍ፤ በአንድነት መንፈስም አጋጣሚዉን በሳዑዲ
ስለሚሞቱና ስለሚንገላቱ ሰዎች ድምፃችንን የምናሰማበት
ሀዘናችንን የምንገልፅበት እንዲሆን ሰማያዊ ፓርቲ በግፉአን
ወገኖቻችን ስም ጥሪ ያስተላልፋል፡፡
የሰማ ላልሰማ ያሰማ!!

Saturday, November 16, 2013

“የኛ ዜጐች በሳውዲ ከሰውነት በታች ተዋርደው ግፍ የሚደርስባቸው ለዜጐች የሚቆረቆር መንግስት ስለሌለ ነው”

“ለዜጐቻችን ስቃይ የሳኡዲና የአገራችን መንግስታት ተጠያቂ ናቸው” ተቃዋሚ ፓርቲዎች

NOV 16,2013

ሠሞኑን በሳውዲ አረቢያ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ እየደረሠ ያለው ግፍና ስቃይ እንዳሳዘናቸው የገለፁ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች፤ የሣውዲ አረቢያ መንግስት እና የኢትዮጵያ መንግስት የመጀመሪያ ደረጃ ተጠያቂ ናቸው ሲሉ ተናገሩ፡፡ የመድረክ ሊቀመንበር ዶ/ር መራራ ጉዲና፣ ሣውዲ አረቢያ የራሷንም ዜጐች መብት የማታከብር ሃገር መሆኗን ገልፀው፣ በኢትዮጵያውያን ላይ የተፈፀመው አሠቃቂ ስራ ግን በ21ኛው ክ/ዘመን የማይጠበቅ ግፍ ነው ብለዋል። በተለይ በሴቶች ላይ የሚፈፀመው ድርጊት አስነዋሪ ነው በማለት መወገዝ እንዳለበት የተናገሩት ዶ/ር መራራ፤ ዋናው ተጠያቂ የሳውዲ መንግስት ነው ብለዋል፡፡
“በሌላ በኩል ኢህአዴግ ሃገሪቱን የስደት ሃገር አድርጓል” ያሉት ዶ/ር መረራ፤ በሜድትራኒያን፣ በየመንና በደቡብ አፍሪካ መስመሮች የሚሰደዱ ዜጐቻችን የአውሬ ሲሣይ እየሆኑ ነው፤ በሃገር ውስጥም በውጭም የዜጐቹን መብት ማስከበር ያልቻለው የኢትዮጵያ መንግስት ተጠያቂ መሆን አለበት” ብለዋል፡፡
በሣውዲ አረቢያ ኢትዮጵያውያን ላይ እየተፈፀመ ያለውን ግፍ በትኩረት እየተከታተሉ መሆናቸውን የሚገልፁት የመኢአድ ፕሬዚዳንት አቶ አበባው መሃሪ በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ መንግስት በዜጐቻችን ላይ የተፈፀመውን ድርጊት ለመከላከልና ለማስቆም አለመቻሉ መንግስት አልባ መሆናችንን የሚያሣይ ነው ብለዋል፡፡ አቶ አበባው እንደሚሉት፤ የሌላ ሃገር መንግስት ቢሆን ኖሮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን እዚያ ሃገር ድረስ ልኮ ሄዶ የዜጐቹን መብት ያስከብር ነበር ብለዋል – አቶ አበባው፡፡ እዚህ ሃገር የውጭ ዜጐች ከቀን ሠራተኛነት ጀምሮ በተለያዩ የስራ መስኮች ላይ መብታቸው ተከብሮላቸው ይኖራሉ ያሉት አቶ አበባው፤ “የኛ ዜጐች በሳውዲ ከሰውነት በታች ተዋርደው ግፍ የሚደርስባቸው ለዜጐች የሚቆረቆር መንግስት ስለሌለ ነው” ብለዋል፡፡ ለዜጐቻችን ሠቆቃ የመጀመሪያ ደረጃ ተጠያቂው የኢትዮጵያ መንግስት ነው በማለት የሚናገሩት አቶ አበባው፤ ዜጐች በሃገራቸው የስራ እድል የሚያገኙበትን አማራጭ ማስፋት የመንግስት ሃላፊነት ቢሆንም፤ በተቃራኒው በአዲስ አበባም ሆነ በሌሎች ከተሞች ብሎኬት የሚሠሩት፣ ሹፌር የሚሆኑት፣ አሣማ የሚያረቡትና የመሣሠሉትን ስራዎች የሚሠሩት የውጭ ሃገር ዜጐች ሆነዋል” ብለዋል አቶ አበባው።
የሣውዲ አረቢያ መንግስት “ከሃገሬ ውጡልኝ” ቢል እንኳ፤ የስደተኞችን ሰብአዊ ክብር በጠበቀ መልኩ ማስፈፀም ነበረበት ያሉት አቶ አበባው፤ “ነገር ግን ኢትዮጵያውያኑ በፖሊስ እየተገደሉና እንደ አውሬ እየተሣደዱ ነውና በዚህም የሣውዲ መንግስት ተጠያቂ ይሆናል” ብለዋል፡፡ ጉዳዩን አስመልክቶ በተለያዩ የማህበራዊ ድረ ገፆችና መገናኛ ብዙሃን ላይ የሠላማዊ ሠልፍ ጥሪዎችን ጨምሮ የተለያዩ መግለጫዎችን ሲሠጥ የነበረው የሠማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት በበኩላቸው፤ የሣውዲ አረቢያ መንግስት ህገወጥ የሚላቸውን ስደተኞች በህገ ወጥ መንገድ ማሠቃየቱ በምንም መዘዘኛ ተቀባይነት እንደሌለው ገልፀው፤ የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ ደካማነት የሚያረጋግጥና የኢትዮጵያንም ህዝብ የሚንቅ ድርጊት ነው ብለዋል።
የአገራችን ባለስልጣናት ጉዳዩን የተመለከቱበት መንገድ አሣዝኖኛል፤ አሣፍሮኛልም ያሉት ኢ/ር ይልቃል፤ “ጥንታዊ ታሪክና ክብር ካለው ሃገር መሪዎች የሚጠበቅ አይደለም” ብለዋል፡፡ በየአመቱ አንድ ሚሊዮን ስራ አጥ እየተፈጠረ መሆኑን የሚናገሩት ኢ/ር ይልቃል፤ ወጣቱን ለስራ ፈጣሪነት የሚጋብዝ ነገር አለመኖሩ አንድ የስደት መንስኤ ነው ብለዋል፡፡ “የተማረና አቅሙ የፈቀደ በቦሌ ይሄዳል፤ ያልተማረው ደግሞ ውሃ ይብላኝ እያለ በረሃ እያቋረጠ ይሄዳል” የሚሉት ኢ/ር ይልቃል፤ “አገር እያደገች ዜጐች ስደትን ይመርጣሉ የሚለው የባለስልጣናት አባባል ውሸት ነው” ይላሉ፡፡ የሣውዲ አረቢያ መንግስት በዜጐች ላይ የፈፀመው አሠቃቂ ድርጊት ሳያንስ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናትና የመንግስት ሚዲያ ለጉዳዩ የሠጡት አናሣ ትኩረት አሳዝኖኛል ብለዋል – የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር፡፡ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ዜጐቻችን ሲሰቃዩና የሰው ህይወት ሲጠፋ፣ መንግስት ለጉዳዩ በቂ ትኩረት አልሰጠም የሚሉት ኢ/ር ይልቃል፤ የኢትዮጵያ እና የሣውዲ አረቢያ መንግስት በእኩል ደረጃ ተጠያቂ ናቸው ብለዋል፡፡
የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በበኩላቸው፤ ፓርቲያቸው ጉዳዩን በአፅንኦት እየተከታተለው መሆኑን ገልፀው፤ በሳውዲ የተፈፀመው ተግባር በእጅጉ የሚያሣፍር እና የሚያሣዝን ነው ብለዋል። ማንኛውም ሃገር የራሱን ህግና መመሪያ ሊያወጣ ይችላል ያሉት ዶ/ር ነጋሶ፤ ይሁን እንጂ “ፍቃድ አላሣደሡም” በሚል ሰበብ ዜጐቻችን የሠው ልጅን ክብር በሚያዋርድ ሁኔታ ለስቃይ መዳረጋቸው ብሄራዊ ሃፍረት ነው ብለዋል። ድርጊቱን በፈፀሙት አካላት ላይ ተጠያቂነትን የሚያስከትል መሆኑን ዶ/ር ነጋሶ ጠቅሰው፤ የሣውዲ አረቢያ መንግስትና የፖሊስ ሃይሉ በህግ ሊጠየቅ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
“አሁን ግን በዜጐቻችን ላይ እየተፈፀመ ባለው ድርጊት የአገራችን ሉአላዊነት ተነክቷል፤ የኢትዮጵያ መንግስትም ይህን የማስጠበቅ ሃላፊነቱን በአግባቡ እየተወጣ አይደለም” ብለዋል ዶ/ር ነጋሶ፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ጠበቅ ያለ አቋም መውሠድ እንዳለበትና ዜጐች ደህንነታቸው ተጠብቆ ወደ ሃገራቸው እንዲገቡ በአስቸኳይ መፍትሔ መስጠት እንዳለበትም አሣስበዋል፡፡ የመልካም አስተዳደር እጦት፣ ስራ አጥነትና የመሣሠሉት ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮች የሃገሪቱን ዜጐች ለስደት እየዳረገ መሆኑን የገለፁት ዶ/ር ነጋሶ፤ መንግስት ድክመቱን እንዲያሻሽል ሁሉም ዜጋ ግፊት ማድረግ አለበት ብለዋል፡፡
addisadmass
posted by Daniel tesfaye

Saturday, November 9, 2013

"ለወገኖቻችን ዛሬ ነገ ሳንል እንድረስላቸው"

በስቃይና በመከራ ሂወታቸውን እያጡ ና ለከባድ አደጋ እየተጋለጡ ላሉ ወገኖቻችን ዛሬ ነገ ሳንል እንድረስላቸው!!
ይሄ ክፉ መንግስት ለ2 ዓስርት ዓመታት ወገኖቻችንን በተለያይ መንገድ ለስደት ሲዳርጋቸው፥ ሂወታቸው  በረሃ ውስጥ እንደ ቅጠል ወድቀው መቅረታቸው አልበቃ ብሎ፥ እንድሁም በየ ባህር ዳረቻው በየቀኑ የሞት ቁጥራቸው ከፍ በማለቱ ምክንያተ የዓለም የሚድያ መነጋገርያ ዕርስ ሆነው ሰንብተዋል።


ወገኖቻችን እንደዋዛ እየተቀጠቀጡ ሲገደሉ ማንም አቤት የሚል ጠፍቶ ፥ የሚደርስላቸው በማጣት ብቻ  እንደ ቀላል በየቦታው    ሂወታቸውን ማጣታቸው  አልበቃ ብሎ ፥
በየ አረብ አገራት ሴት እቶቻችን ላይ በተለያዩ ችግሮች ምክነያት አካላቸው እና ፥ስነልቦናቸው ተጎድቶ መታከም ባለመቻላቸው ምክንያት እራሳቸው ላይ ሞት እየፈረዱ ወተው የቀሩትን፤ ያልጋ ቁራኛ በመሆን ስሚ አተው እየተስቃዩ አልጋ ላይ ሆነው  የሚያሰሙትን የድረሱልኝ ጥሪ ሰምተን ይሄንን ስቃያቸዉን ለመታደግ ምንን  እያደረግ ነው ያለው ??


 ከሰሞኑነ በህጋዊነት  ሳውዲ የገቡትን፥ ፈጣሪ በአምሳሉ የፈጠረው የስው ልጅን እነሱ በእንሳት እየመሰሉ በሰው ልጅ ሳይሆን በአዉሬ ላይ እንኳን የማይደርግ ተግባር እየፈጰሙ ፥ወገኖቻችንን  ለስቃይ እየዳረጉ ይገግኛሉ።
አንደዚ አይነት ኢሰባዊ ተግባር የዓለም እዝብ አንዲያውቀው እና በተለያዩ መንገዶች የሚዲያ ሽፋን እንዲያገኙ የየበኩላችንን አላፊነት የመወጣት ግዴታ አለብን ፥ በስቃይና በመከራ ሂወታቸውን እያጡና ለከባድ አደጋ እየተጋለጡ ላሉ ወገኖቻችን ዛሬ ነገ ሳንል እንድረስላቸው።ራሄል ኤፍሬም


Friday, November 8, 2013

ሰበር ዜና – የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ከፍተኛ የአመራር አባላት ላይ ታቅዶ የነበረ የመግደል ሙከራ ከሸፈ


ሰበር ዜና – የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ከፍተኛ የአመራር አባላት ላይ ታቅዶ የነበረ የመግደል ሙከራ ከሸፈ
HOME » መግለጫ / PRESS RELEASE » ሰበር ዜና – የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ከፍተኛ የአመራር አባላት ላይ ታቅዶ የነበረ የመግደል ሙከራ ከሸፈ
NOV 8, 13 • BY  • 

GPF_Logo-Small

የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ከፍተኛ የአመራርአባላት ላይ ታቅዶ የነበረ የመግደል ሙከራ ከሸፈ።
በጠቅላይ ሚንስትር ተብየው ሃይለማሪያም ደሳለኝ እውቅናና ትእዛዝ የግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል ታጋዮች በሚገኙበት ቦታ ድረስ በመሄድ አመራሩን ለመግደል ሙከራ ቢደረግም ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት በሕዝባዊ ሃይሉ መረጃና ደህንነት ክፍል ከፍተኛ ክትትል ሙከራው መክሸፉን ሕዝባዊ ሃይሉ ገለጸ። ይህ ልዩ ትእዛዝ ጥቅምት 30 2006 ዓ/ም ተፈጻሚ እንዲሆን እቅድ የነበረ ቢሆንም ሕዝባዊ ሃይሉ ጥቅምት 27 2006 ዓ/ም ሊያከሽፈው ችሏል። ዝርዝሩን ይዘን እንመለሳለን።

Wednesday, November 6, 2013

Abbay dam will be owned by Egypt and Sudan

November 5, 2013

Egypt, Sudan, and Ethiopia are all committed to coordinating and cooperating in dealing with Ethiopia’s Grand Renaissance Dam, said Egypt’s Ministry of Irrigation and Water Resources on Monday.
lue Nile River in Guba, Ethiopia, during its diversion
A picture taken on 28 May 2013 shows the Blue Nile River in Guba, Ethiopia, during its diversion (AFP/File, William Lloyd-George)
Egyptian Minister of Irrigation and Water Resources Mohamed Abdel Moteleb said that it was “time to consider a new strategy for the available investment opportunity,” adding that any matter dealing with the dam must be agreed upon by the governments of the three countries.
The countries’ water ministers began meetings in the Sudanese capital of Khartoum on Monday in order to review recommendations put forth by a report formed by a tripartite committee investigating the impacts of the dam on Ethiopia’s neighbours in the north.
Abdel Moteleb added that trilateral support for the dam could set a “good example for cooperation in the region,” adding that he hoped that the outcome of the process would be the “beginning of a new era of cooperation between the three countries.”
“I would like to recall the initiative put forth by the Prime Minister of Ethiopia, a proposal considering the Renaissance Dam a joint regional project from which the three countries could benefit,” said Moteleb in his Monday address to the representatives from the three countries.
Last week Egyptian Minister of Foreign Affairs Nabil Fahmy stressed the importance of joint action and cooperation between countries when dealing with Ethiopia’s dam, saying that the water issue must not be dealt with as a “zero-sum game.”
Spokesman of the foreign ministry Badr Abdelatty said that the Prime Minister of Ethiopia Hailemariam Desalegn would come to Cairo “soon.”
“We will continue dialogue with Ethiopia and our Sudanese brothers,” added Abdelatty.
Source: Daily News

Tuesday, November 5, 2013

International Commission of Jurists (ICJ): Ethiopian Leaders to Face a Trial for Genocide



















October 30, 2013
by Betre Yacob
The International Commission of Jurists (ICJ) reported to have begun to work to bring Ethiopian authorities to justice for having committed a genocide in the Ogaden region. The International Commission of Jurists is a known international human rights organization composed of jurists (including senior judges, attorneys, and lawyers). The commission is known for its dedication to ensuring respect for international human rights standards through the law.

The report came right after different Swedish TV channels showed a movie smuggled out from Ogaden by an Ethiopian refugee, who had been a government official in the region. The 100 hours long movie is said to have many evidences of genocide committed by the Ethiopian government in the region.

Speaking to journalists, Stellan Diaphragm, the commissioner of the Commission, said that he would do everything necessary to bring the case to the International Criminal Court (ICC).

Reports indicate that although Ethiopia is not a member of the ICC, the country can possibly face trial for crimes under international law.

The Ogaden region is a territory in Eastern part of Ethiopia, and populated mainly by ethnic Somalis. Since 2007, the region has been a site of brutal struggle between the government troops and the Ogaden National Liberation Front (ONLF), a rebel group seeking for more autonomy for the region.

Different human right organizations accuse the Ethiopian government of committing grave human right violation (including genocide) against the civilians in attempt to control the ONLF’s public support.

According to the Genocide Wach, the crimes committed in the region include extrajudicial killings, arbitrary detention, rape, torture, disappearances, the destruction of livelihood, the burning of villages and the destroying of life stock.

source: ECADF

Ethiopian man lynched to death in South Africa

A group of men savagely beaten up and killed an Ethiopian man in Mpumalanga, South Africa, last Monday. The gruesome attack took place in broad day light while many people watched, according to the police. The identity of the victim has not been released yet. The police only said that he is a 30-year-old immigrant from Ethiopia.
 Ethiopian attached in South Africa

.