(ራሄል ኤፍራም)
November 22.11.2013
ስቃያቸው እንደ ወንዝ ጅረት ለበዛው እና እንደ ቀልድ እየተደፈሩ የትም ለቀሩት ህቶቻችን እንዲሁም ሂወታቸው በየቦታው እንድዋዛ ለረገፈው ወንድሞቻችን፣ ሀዘናችው ውስጣችንን እያቃጠለው፣እያንገበገብው ፍትህ እስከምናገኝ መቀመጫ ያልሰጠን የወገኖቻችን ጉዳይ ፖለቲካ ሳይሆን የማንነት ጥያቄ መሆኑን ሁላችንም ልንገነዘብ ይገባል።
ማንነታችን ተደፍሮ ፣ተንቀን ፣ተዋርደን ፖለቲካ ነው እያልን የምንሸሽ ካለን ስህተት ነው። ወገኖቻችን በሰው ሀገር መደፈር ፣መደብደብ ፣መሰቃየት ፣መዋረድ እና መገደል የሁላችንም ህልውና የሚነካ ሲሆን ይሄንን የስፖርት ቤተሰብ የወገኖቻችንን ስቃይና ጉዳት እንዲሁም በአሰቃቂ ሁኔታ መሰቃየታቸው እና መገደላቸው እንደወገን ሊሰማቸው የገባል።
ጉዳታቸው ጉዳታችን ፣ስቃያቸው ስቃያችን ፣ ውርደታቸው የሁላችንም ውርደት በመሆኑ ይህንን በመገንዘብ በስቃይና በመከራ ወስጥ ያለውን የወገኖቻችንን ድምፅ ማሰማት የኢትዮጵያዊነት ግዴታችን ነው።
በእርግጥ አንድ እውነት አለ የዚህ ሁሉ የወገኖቻች መሰቃየት ፣ የህቶቻችን መደፈር ፣የወንድሞቻችን መደብደብ በተለያየ መንገድ ሂወታቸውን ማጣታቸው ዋንኛው ምክንያት ስልጣንን ከህሊናቸው በማስበለጥ ለሃገራቸው ሳይሆን ለጥቅማቸው ሲሉ እንድ እባብ በሆዳቸው እየሄዱ መርዛቸውን እየረጩ እነሱ እየኖሩ ሌላሁን የስደት ቁራኛ በማድረግ ከመኖረም በላይ በህዝቦቻቸ ደም ላይ አንደዚ እየተሳለቁ ወገን ሲዋረድ ሀገር አቀርቅራ ስታለቅስ እነሱ ሽቅብ እየሳየቁ ወገኖቻቸን ችግር ከምንም ባልቆጠሩት ቱባ ያገራችን ባለስልጣናት ምክንያት መሆኑ ግልፅ ነው ።
ሆኖም ግን ጥያቄው በዜጎቻችን ላይ የሚደርስው ጥቃትንና አሰቃቂ ግድያ እንዲያቆም እና ፍታዊ እርምጃ እንዲወሰድ እንጂ ፍጹም ከፖለታካ ጋር የሚያያይዘው አንድም ነገር አለመኖሩ እንዲሁም ባገኘነው አጋጣሚ ለወገኖቻችን መጮህ እንዳለብን ድምፃቸው እንዲሰማ የግላችንን አስትዋፆና ጥረት በማድረግ ፍትህ የሚያገኙበትን መንገድ በመፍጠር ለወገኖቻቸን መቆማችንን በታላቁ እሩጫ ላይ ጥቁር ሪቫን በማሰር አዘናችንን እና የተሰማንን የወገናዊነት እናሳይ ።
No comments:
Post a Comment