Saturday, November 9, 2013

"ለወገኖቻችን ዛሬ ነገ ሳንል እንድረስላቸው"

በስቃይና በመከራ ሂወታቸውን እያጡ ና ለከባድ አደጋ እየተጋለጡ ላሉ ወገኖቻችን ዛሬ ነገ ሳንል እንድረስላቸው!!
ይሄ ክፉ መንግስት ለ2 ዓስርት ዓመታት ወገኖቻችንን በተለያይ መንገድ ለስደት ሲዳርጋቸው፥ ሂወታቸው  በረሃ ውስጥ እንደ ቅጠል ወድቀው መቅረታቸው አልበቃ ብሎ፥ እንድሁም በየ ባህር ዳረቻው በየቀኑ የሞት ቁጥራቸው ከፍ በማለቱ ምክንያተ የዓለም የሚድያ መነጋገርያ ዕርስ ሆነው ሰንብተዋል።


ወገኖቻችን እንደዋዛ እየተቀጠቀጡ ሲገደሉ ማንም አቤት የሚል ጠፍቶ ፥ የሚደርስላቸው በማጣት ብቻ  እንደ ቀላል በየቦታው    ሂወታቸውን ማጣታቸው  አልበቃ ብሎ ፥
በየ አረብ አገራት ሴት እቶቻችን ላይ በተለያዩ ችግሮች ምክነያት አካላቸው እና ፥ስነልቦናቸው ተጎድቶ መታከም ባለመቻላቸው ምክንያት እራሳቸው ላይ ሞት እየፈረዱ ወተው የቀሩትን፤ ያልጋ ቁራኛ በመሆን ስሚ አተው እየተስቃዩ አልጋ ላይ ሆነው  የሚያሰሙትን የድረሱልኝ ጥሪ ሰምተን ይሄንን ስቃያቸዉን ለመታደግ ምንን  እያደረግ ነው ያለው ??


 ከሰሞኑነ በህጋዊነት  ሳውዲ የገቡትን፥ ፈጣሪ በአምሳሉ የፈጠረው የስው ልጅን እነሱ በእንሳት እየመሰሉ በሰው ልጅ ሳይሆን በአዉሬ ላይ እንኳን የማይደርግ ተግባር እየፈጰሙ ፥ወገኖቻችንን  ለስቃይ እየዳረጉ ይገግኛሉ።
አንደዚ አይነት ኢሰባዊ ተግባር የዓለም እዝብ አንዲያውቀው እና በተለያዩ መንገዶች የሚዲያ ሽፋን እንዲያገኙ የየበኩላችንን አላፊነት የመወጣት ግዴታ አለብን ፥ በስቃይና በመከራ ሂወታቸውን እያጡና ለከባድ አደጋ እየተጋለጡ ላሉ ወገኖቻችን ዛሬ ነገ ሳንል እንድረስላቸው።ራሄል ኤፍሬም


No comments:

Post a Comment