በሃገራችን ኢትዮጵያ ወያኔ ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ በኣስከፊ ሁኔታ አየተባባሰ የመጣው የዜጎች መብት ረገጣ ፣ በተለይም በዚ ስርአት ዋነኛ ተጎጂ የሆኑት ሴት አህቶቻችን በሀገር ውስጥ በመንግስት አካላት በሚደርስባቸው ጥቃት ለ አካል አና ስነልቦና ጉዳት ሰለባ የተዳረጉትን እና ገዢው ፓርቲ ባመቻቸው አና በከፍተኛ ሁኔታ አየተስፋፋ የመጣው ህገወጥ የሰው ዝውውር ዘመናዊ ባርነት ወደ አረብ ህገራት በዜጎች ላይ እያደረሰ ያለው ከፍተኛ ሰቃይ፣ አንግልት፣ አስር፣ ሞት አና የመሳሰሉት ችግሮች በየጊዜው የምንሰማው እና እልባት ያልተገኘለት መራር አውነት የሚያሳይ የፎቶ ኣውደርዕይ እና ገለጻ በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የሴቶች ክፍል ኣዘጋጅነት በኦስሎ ከተማ ተደረገ ።
በዝግጅቱ ላይ ከቀረቡት ፎቶዎች መሀከል ሴቶች በሀገር ውስጥ የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊ ናቹ በሚል በመንግስት ኣካላትየሚደርስባቸው አሰቃቂ ድብደባ በአካላቸው ላይ የደረሰባቸው ጉዳትን የሚያሳ፥ ገዢው መንግስት በልማት ሰበብ ነዋሪዎችን ያለምንም ቅድመ ዝግጅት ከመኖሪያቸው በማፈናቀል ለጎዳና ህይወት መዳረጋቸው በየሜዳው መበተናቸው የሚያሳይ (እነዚህ ዜጎች መጠለያ በማጣት ለጎዳና ህይወት መዳረጋቸው ሴቶች ለተለያየ ጾታዊ ጥቃቶች፣ መደፈር፣ ላልተፈለገ እርግዝና፣ ለተለያዩ በሽታዎች እንዲጋለጡ ብሎም ሴተኛ ኣዳሪነት አንዲስፋፋ እና ለስደት ለህገወጥ ዝውውር ምክኒያት መሆኑ ይታወቃል)።
የዚህ ዝግጅት ዋነኛ ክፍል የነበረው በህገወጥ መንገድ በተለይም ወደ አረብ ሀገራት ለርካሽ የጉልበት ስራ ብዝብዛ በሚሰደዱበት ሀገር የሚደርሰባቸው ሰቃይ አና አሰቃቂ ሞት የሚያሳዩ የተለላዩ ፎቶውች ናቸው ።
(በ100,000 የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ሴቶች አብዛኛዎቹ እድሜአቸው ከ18 በታች የሆኑ ህጻናት ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በህገወጥ መንገድ ለጉልበት ስራ ዘመናዊ ባርነት ወደ አረብ ሀገራት ይሰደዳሉ። በተሰደዱበት ሀገር ህጋዊ ጥበቃ ከኢትዮጵያ መንግሰትም ሆነ ከተሰደዱት ሀገር መንግስት ባለማግኘታቸው ከአቅም በላይ የሆነ የጉልበስራት በቀን ከ18 ሰዓት በላይ አንዲሰርሩ በመገደድ ፣ የሚደርስባቸው ከፍተኛ ስቃይ እና እንግለት፣ ድብደባ፣ በኣሰሪዎቻቸው በተደጋጋሚ መደፈር፣ በአካል አና ስነልቦና ጉዳት ብዙዎች ለአይምሮ ህመም በሽታ በመዳረጋቸው እና ክትትል የሚያደርግልቸው ባለማግኘታቸው በባእድ ሀገር በየጎዳናው ወድቀዋል።
ይህ ስቃይ ከኣቅማቸው በላይ የሆነባቸው ሰሚ ያጡ ዋይታዎች፣ ድብደባ መቛቛም ያቃታቸው፣ በመደፈር ባዛት የደከሙ የጨቅላ ገላዎች፣በደል የበዛባቸው ብዙ እህቶች፤ መርዝ በመጠጣት፣ ከፎቅ በመፈጥፈጥ፣ በመታነቅ ሂወታቸውን ያጠፋሉ።
ከመነሻው ለዚህ ችግር ምክኒያት የሆነው ገዢው መንግስት በዜጎቸ ላይ የሚደርሰውን እንግልት እና የግፍ ሞት ግዴለሽ በመሆኑ እና ባለመጠየቁ ዛሬ ኢትዮጵያዊነት ወንጀል እስኪመስል ድረስ በሳውዲ በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለውን ስቃይ አንገልት እንዲባባስ ምክኒያት በመሆን ብሎም ለህዝቡ ያለውን ከፍተኛ ንቀት አያሳየ ይገኛል።)
በዘግጅቱ ላይቁጥራቸው በዛ ያለ ሰዎች የተገኙ ሲሆን ተጋባዥ አንገዶችም ንግግር ኣድርገዋል።
No comments:
Post a Comment