Tuesday, October 15, 2013

UNITY IS POWER: Nhatty Man & Jacky Gosse - Fim Esat [NEW! Music Vi...

UNITY IS POWER: Nhatty Man & Jacky Gosse - Fim Esat [NEW! Music Vi...: በጣም ተወዳጅ የሆነው የ ናቲና የ ጃኪ ፍም እሳት የሚለውሙዚቃ በስተመጨረሻ ክሊፑ ተለቋል። በኔ አመለካከት የሙዚቃው መልእክት በኢትዮጵያ የእግር ክኳስ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረገውና  ባሁኑ ወቅት በጣም ከፍተ...

ተሸላሚ ያጣው የሞ ኢብራሂም ሽልማት

በመልካም አስተዳደር ለተመረጡ የአፍሪቃ መሪዎች ለሚሰጠው የሞኢ ኢብራሂም ሽልማት በዚህ ዓመት ተሸላሚ እንዳልተገኘ ድርጅቱ ዛሬ ለንደን ውስጥ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል ።
ሞኢ ኢብራሂም የተባለው ድርጅት በመልካም አስተዳደር ለተመረጡ የአፍሪቃ መሪዎች ለሚሰጠው ሽልማት በዚህ ዓመት መስፈርቱን ያሟላ መሪ አለማግኘቱን አስታወቀ ። ድርጅቱ ዛሬ ለንደን ውስጥ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ በዚህ ዓመት ተሸላሚ እንደሌለ አስታውቋል ። ከ52 የአፍሪቃ ሃገራት መሪዎች መካከል የድርጅቱን መስፈርት ያሟላ መሪ አለመገኘቱ በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አነጋጋሪ ጉዳይ ነበር ። ድርጅቱ ለአፍሪቃ ሃገራት የሰጠው የመልካም አስተዳደር ደረጃም ዛሬ ይፋ ሆኗል ። የለንደኑ ዘጋቢያችን ድልነሳ ጌታነህ ዝርዝሩን ልኮልናል ። ድልነሳ ጌታነህ ሂሩት መለሰ አርያም ተክሌ

ከሊቢያ ለጉዞ የተዘጋጁ ስደተኞች

አፍሪቃ ኣንዳንድ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ስደተኞች ታጉረው ከሚገኙበት ወይንም ተደብቀው ጀልባ ከሚጠባበቁበት የትሪፖሊ ማጎሪያ ቤት ለዶቸቬሌ አነጋግሯቸዋል። እንደተናገሩትም በሱዳን በኩል ኣድርገው ሊቢያ እስኪደርሱ በዚህ ረጅም የበረሃ ጉዞ የደረሰባቸውስቃይ ሳያንሳቸው ኣሁንም የባህር ላይ ኣሰቃቂ ጉዞ ይጠብቃቸዋል። በእርግጥ ስደተኞቹ እንደሚሉት ያ ከሁለት መጥፎ ይሻላል ብለው የመረጡት የተሻለ መጥፎ በመሆኑ እዚያው ሊቢያ ውስጥ በፖሊሶች የሚደርስባቸውን ዘረፋ እና እስራት ነው ይበልጥ የሚያማርሩት። ከ UNHCRየጀኔቫ ቢሮ ቃል ኣቀባዩ ሚ/ር ዳን ሚክኖኣፓኔ እንደሚሉት ለችግሩ መፍትሄ ለመሻት የሚደረገው ጥረት ማነጣጠር ያለበት መነሻው ላይ ነው። ይህ ግን ጊዜ የሚፈጅ በመሆኑ ሚ/ር ዳን እንደሚሉት የኣውሮፓ ህብረት እና ሌሎችም ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ስደተኞች ተገን የሚጠይቁበትን ቦታ እና የሚያገኙበትን ሁኔታ እንደገና ሊመረምሩ ይገባል። ከዚሁ ጎን ለጎን ደግሞ የባህር ላይ ቁጥጥሩም በእርግጥ ሊጠናከር ይገባል ባይ ናቸው ሚ/ር ዳን። ጃፈር ዓሊ ሸዋዬ ለገሰ

Sunday, October 13, 2013

ስብሃት ነጋ በአሁን ሰአት በፖሊስ እየታደኑ ነው !

በአሌክሳንደሪያ ቨርጂኒያ ከአንድ ሰአት በፊት ስብሃት ነጋና አብሯቸው የነበረ ግለሰብ በአንድ ኢትዮጲያዊ ላይ ከፍተኛ ድብደባ ፈፅመው ማምለጣቸውን ማረጋገጥ ተችሏል። መስፍንsebehat nega one of the founders of TPLF የተባለው ኢትዮጲያዊ በአሁኑ ሰአት በሆስፒታል የሚገኝ ሲሆን የሲቪሊቲ ሩም ፓልቶክ አዘጋጅ አባ መላ በስልክ አግኝቶት ስለሁኔታው ያነጋገረው ሲሆን፤ መስፍን እንደገለፀው በድብደባው ጅርባው እንደተጎዳና ብዙ ደም እንደፈሰሰው ገፆዋል። እነስብሃት ድብደባውን ሲፈፅሙ በቅርብ ርቀት ቪዲዮ እየተቀረፁ እንደነበረና ይህኑን ማስረጃ ለፖሊስ መስጠታቸው ታውቋል። ድርጊቱ ከተፈፀመ በኋላ ፖሊስ በአካባቢው ፈጥኖ የደረሰ ሲሆን፣ በአሁን ሰአት እነስብሃትን ለመያዝ ፖሊስ መሰማራቱ ታውቋል። ከኢየሩሳሌም አርአያ

Saturday, October 12, 2013

ከስክሪን ጅርባ በመሆን የሰዎችን እቅድ ለምታደናቅፉ የወያኔ ጀሌሆች

በዚህ እድገታችን እጅግ ፈጣን በሆነበት 21ኛዉ ክፍለ ዘመን እየኖርን አስተሳሰባችን እጅግ የላቀንና የማስተዋል ችሎታችን እጅግ የፈጠነ በሆነበት ሰዓት ፡ ከስዎች ጋር ተነጋግረን መረዳዳት አንደውም ጉለታችንን መማማር በምንችልብት በዚ ጊዜ፡ ከስክሪን ጅርባ በመሆን የሰዎችን እቅድ ለምታደናቅፉ የወያኔ ጀሌሆች፡ እሊና እንዳለው ሰው ሁኔታዎችን እንዳትመለከቱ ወያኔ በላቀ ደረጃ ሚናሁን እየተጫወተባችሁ ይገኛል። አብዛኞዉን ኢትዮዺያዊ እየተራበ እና እተጠማ ባለበት በዚ አስቸጋሪ ሰዓት፡ ወያኔ እንደራሳቸዉ ህሊና የሌላቸዉን ለመለምለም ሆዳችሁን ብቻ እየሞላ እሊናቸሁ ግን ባዶ አንዲሆን ጊዜ ወስዶ ሲቀርፃችሁ ነበር። አዉንም የሆድ አዳሪሁን ተግባር ለሟሟላት ለምትራራጡ እና በተለያየ መንገድ የሰሆችን ስራ ለማበላሽት ከምስኪኑ ሕዝብ ተነጥኮ ለናንተ ይሄንን ስራ እንድታከናሁኑ የተከፍላችሁ አሁን ምንም መሄጃ ስለሌላችሁ ለህለናችሁ መኖርን ብትመረጡ ይሻላችዋል። ከጀግናዉ ወገኖቻችን ጋር እጅ ለእጅ በመያያዝ ልክ እንደ ጥንቱ እንደልማዳችን ለህሊና እና ለወገን የምንኖርበትን መንገድ ማንም ለያስቆመን ስለማይችል ከንቱ ልፋታችሁን ብታቆሙ ይመረጣል። ፦ ራሄል ኤፍሬም ከኖርዌይ

Friday, October 11, 2013

የናቁት ያደርጋል እራቁት

ታሪክ አንዳስቀመጠልን በሃገራችን ሰው የሚኖርበትን ኣካባቢ ለቆ የሚሰደደው የተሻለ ትምህርት ለማግኘትና የሄደበትን አላማ ሲጨርስ ሀገሩን ለማገልገል እንደሆነ የታሪክ ምንጮች ይገልጻሉ። ዛሬ በተለያየ መንገድ ተሰደው የተለያዩ አሰቃቂ ችግሮች የሚደርስባቸው ሴት እህቶቻችን በ አረብ ሀገር ውስጥ የሚደርስላቸውን አጥተው እንደወጡ የሚቀሩት፣ በደቡብ አፍሪካ ስንት ወገኖቻችን የእንስሳት ሆድ መሙያ የሆኑበት፣ የሰሀራ በረሀ ስንት ወገኖቻችንን አፍኖ ያስቀረበት፣ በተለያዩ ሀገሮች እንዲህ ነው ሊባል የማይችል ስቃይ እየደረሰባቸው ሰሚ አጥተው በወጡበት የቀሩት ወገኖቻችን ማን ነው የሚያየው? ማነውስ የሚደርስላቸው? የላምፐዱሳ ደሴት ውጦ ጸጥ ያለውን የወንድሞቻችን እና የእህቶቻችንን እንዲሁም ምንም የማያውቁ ህጻናትንስ ማን ነው የሚያድነው? ማነውስ በቃ የሚለው? እሬሳቸው ሀገርና ወገን እንደሌለው ወድቀው ለሚገኙት እና የስደት መከራ በየግዜው ለሚያሰቃየን፣ ሀገራቸው ውስጥ የነጻነት መብታቸውን ተነጥቀው፣ ፍትህን አጥተው በእስር እየተሰቃዩ ላሉት፣ በሀገራቸው የመኖር መብታቸውን ተቀምተው ለሚንከራተቱት፣ ነጻነት እና ዲሞክራሲ እንደውሃ ከጠማው ህዝባችን ጋር በፍቅር እጅ ለእጅ ተያይዘን ሆድ እንጂ ጭንቅላት የሌለውን የዚህ ሁሉ ወገኖቻችን እልቂት፣ ስቃይ፣ መከራና መንከራተት ምክንያት የሆነውን ይህንን ባንዳ ከናዚ ባልተናነሰ መንገድ ሀገራችንን በተለያየ መንገድ ደብዛዋን ሊያጠፋ ቆርጦ ለራሱ ቃል የገባውን ቆርጠን ተነስተን የስልጣን ፍቅሩን በውርደት ኣስለቅቀን ለፍርድ ማቅረብ የምንችልበት ግዜ አሁን ነው!! አንድ ላይ በመሆን የናቁት እንዴት እንደሚያስቀር እራቁት በተግባር ለማሳየት የድሮው ይበቃል ብለን ቆርጠን መነሳት ይኖርብናል። ራሄል ኤፍሬም ከኖርዌይ

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ወደ ፖሊስ ጣብያ ተወሰዱ

October 11, 2013 በአሁኑ ወቅት በመነን አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ በቁጥጥር ስር የነበሩት የፓርቲ አመራሮች ወደ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ መወሰዳቸዉን አሁን የደረሰን መረጃ ይገልፃል፡፡ *** ጉዳዩ እንደዚህ ነው መንግስት ነኝ ባዩ በስራው ግን ከማፍያ ቡድን እምብዛም የማይለየው ህወሀት/ኢህአዴግ በተለየም የሰማያዊ ፓርቲ እና የአንድነት ፓርቲ አጠናክረው የቀጠሉት የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴ ስጋት ውስጥ ጥሎታል። “ሳይቃጠል በቅጠል” እንዲሉ ይህን ህዝብ ውስጥ በፍጥነት እየሰረጸ የመጣውን እንቅስቃሴ ድምጽ በሌለው መሳሪያ ለማዳከምና ብሎም ለማምከን ህወሀት/ኢህአዴግ እየተከተለ ያለው ስልት ቡድኑ ምን ያህል “የሞራል የበታችነት” እንደተላበሰ የሚያሳይ ነው። የሰማያዊ ፓርቲ የካቲት 12(መነን) አካባቢ አዲስ የተከራየውን ጽህፈት ቤት ለመረከብ ጥቅምት 1/2006 ዓ.ም በቦታው ይገኛል። ይሁንና ቀድመው በቦታው የተገኙ የህወሀት/ኢህአዴግ ሰዎች ቤቱን እኛ ቀደም ብለን የተከራየነው ስለሆነ የሚገባው ለኛ ነው በማለት ወዝግብ ያነሳሉ… እንግዲህ አንባብያን እራሱን መንግስት ብሎ የሚጠራው ሀይል የሰፈር “ጢቦ” ሆኖ መጣ ማለት ነው… ይህ በዚህ እንዳለ ነው አሁን በቅርቡ የክፍለ ከተማዉ ፍትህ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ጌታሁን አማረ ፤ የወረዳዉ አስተዳደር ሃላፊዎች ፤- የወረዳ 3 ስራ አስፈፃሚ አቶ አማረ ቤካ ፤ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ አማረ አቡጤ ፤ መነን አካባቢ ፖሊሶች ፤ ፌደራል ፖሊሶች እና ሲቪል የለበሱ የደህንነት አካላት በጋራ በመሆን ኢንጅነር ይልቃልን ጨምሮ ሌሎች የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችችን ወደ ወደ መነን አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የወሰዷቸው። የሰማያዊ ፓርቲ ሁኔታውን እንዲህ በማለት በፌስ-ቡክ ገጹ ላይ ጠቅሶታል፣ የኢህአዲግ አፈና በሰማያዊ አመራሮች እና አባላት ላይ ተጠናክሮ ቀጥሏል!!! በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ዉስጥ ለሰማያዊ ፓርቲ ጽህፈት ቤት ተከራይቶ የነበረዉን ቤት ከዛሬ ጥቅምት 1 2006 ጀምሮ ለመጠቀም በሄዱበት ጊዜ የክፍለ ከተማዉ ፍትህ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ጌታሁን አማረ ፤ የወረዳዉ አስተዳደር ሃላፊዎች ፤- የወረዳ 3 ስራ አስፈፃሚ አቶ አማረ ቤካ ፤ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ አማረ አቡጤ ፤ መነን አካባቢ ፖሊሶች ፤ ፌደራል ፖሊሶች እና ሲቪል የለበሱ የደህንነት አካላት በጋራ በመሆን በማይመለከታቸዉ ጉዳይ የፓርቲዉን ከፍተኛ አመራሮች 1. ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት(ሊቀ መንበር) 2. አቶ ስለሺ ፈይሳ (ምክትል ሊቀመንበር) 3. አቶ ይድነቃቸዉ ከበደ (የህግ ጉዳይ ሃላፊ) 4. አቶ እንዳሻዉ እምሻዉ (የጽህፈት ቤት ሃላፊ) 5. አቶ በቃሉ አዳነ (ምክር ቤት አባል ) 6. አቶ ዮናስ ከድር (የምክር ቤት አባል) 7. አቶ ብርሃኑ ተክለ-ያሬድ (አባል) ወደ መነን አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደዋል፡፡

Wednesday, October 9, 2013

Photos of Ben Salam Khaled | responsible for the Lampedusa tragedy.

Ben Salam is likely to be charged with human trafficking and with multiple counts of voluntary manslaughter, the prosecutor said. As the skipper, Ben Salam was responsible for allowing too many people aboard the boat and witness accounts indicate that it was he – or someone acting on his instructions – who set a piece of cloth on fire in a bid to attract attention from other vessels once the boat began taking on water near Lampedusa, Di Natale said. source - http://www.raimoq.com/photos-of-ben-salam-khaled-responsible-for-the-lampedusa-tragedy/

ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች አድማ መቱ !

በማይ አይኒ እና አድሃሩሽ (ጸለምት ወረዳ )ኢትዮጵያውያ የሚገኙ የኤርትራውያን ስደተኞች የተቃውሞ ድምጻቸውን በማሰማት ላይ ናቸው ። ኤርትራውያን ስደተኞች ድምጻቸውን ማሰማት ከጀመሩ ሶስት ቀን አልፎታል እስካሁን የወያኔ ፖሊስ በወሰደው እርምጃ ሶስት ኤርትራዊያን ስደተኞች ህይወታቸው አልፏ ። የተቃውሞው መነሻ የስደተኛው አያያዝ እንደሆነ ይነገራል ። የኤርትራውያን ስደተኞች ከኢትዮጵያ ወደ ሱዳን ከሱዳን ወደ ሊቢያ በመሄድ ለአሰቃቂው የባህር ላይ እልቂት የሚጋለጡ በኢትዮጵያ እና በሌሎች የአፍሪካ ሃገር በሚደርስባቸው የተበላሽ የስደተኛ አያያዝ እንደሆነ ብዙ የችግሩ ገፈት ቀማሽ ወገኖች ይናገራሉ ። ከዚህ በታች የሚገኘውን ሊንክ በመጫን የ አካባቢው ያለው ድባባ ይመልከቱ ። http://www.youtube.com/watch?v=J2yhldbm1YA

Tuesday, October 8, 2013

ሞዴስ ወንዶችንም ለሞት ሊያበቃ ለሚችል በሽታ ይዳርጋል

ሴቶች የወር አበባቸውን የሚያዩበት ዕድሜ በአኗኗር ሁኔታ፣ በአመጋገብና በአካባቢያዊ ሁኔታዎች ሊለያይ የሚችል ቢሆንም በአብዛኛው ከ14 ዓመት ዕድሜያቸው ጀምሮ የወር አበባቸውን ያያሉ፡፡ ምቾት ባለበት አኗኗር ውስጥ የሚያድጉ ልጆች፤ ከዚህ ዕድሜ ቀደም ብለው የወር አበባቸውን ሊያዩ ይችላሉ፡፡ ይህ ቀደም ባሉት ዓመታት የነበረው የወር አበባ ማያ የዕድሜ ገደብ ዛሬ ዛሬ እየወረደ መጥቶ ታዳጊ ሴት ህፃናቱ፣ በዘጠኝና በአስር ዓመት ዕድሜያቸው ላይ የወር አበባ ማየታቸው እየተለመደ መጥቷል፡፡ ህፃናቱ የሰውነታቸው ዕድገት ፈጣን እንደመሆኑ ሁሉ የውስጣዊ አካላቸው ዕድገትና ለውጥ እንዲሁ ፈጣን ነው፡፡ እነዚህ ታዳጊ ህፃናት የወር አበባ ምንነትና ሒደቱ በሰውነታቸው ላይ ስለሚያስከትለው ተፈጥሮአዊ ለውጥ ግንዛቤ ባላገኙበት ዕድሜያቸው ላይ ይህ ክስተት ሲገጥማቸው ለከፍተኛ ድንጋጤና የሥነልቡና ጫና መዳረጋቸው የማይቀር ነው፡፡ ችግሩ እንዳይከሰት ቤተሰብ በተለይም እናቶች ለሴት ታዳጊ ልጆቻቸው ስለወር አበባ ምንነትና የወር አበባ በሚመጣ ጊዜ ሊደረጉ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች እንዲሁም በወር አበባ ወቅት የግል ንጽህናን በአግባቡ መጠበቅ እጅግ አስፈላጊነ መሆኑን በጊዜ ማስተማርና ልጆቻቸውን ማዘጋጀት እንደሚኖርባቸው የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ። ልጆቹ ያላወቁትና ይከሰትብኛል ብለው ያላሰቡት ነገር ሲገጥማቸው ከፍተኛ ድንጋጤና የሥነልቡና ችግር እንደሚደርስባቸውም ባለሙያዎቹ ይገልፃሉ። ቀደም ባሉት ዘመናት እናቶች የወር አበባቸው በሚመጣበት ጊዜ ከነጠላና አሮጌ ቀሚሶች ቅዳጅ እየቆረጡ በሚያዘጋጇቸው ጨርቆች የወር አበባቸውን እየተቀበሉ ንጽህናቸውን ይጠብቁ ነበር። ጨርቆቹ እየታጠቡ ከአንድ ጊዜ በላይ አገልግሎት እንዲሰጡ ይደረጉ ነበር፡፡ አሁንም ቢሆን በአገራችን በርካታ አካባቢዎች ጥቅም ላይ እየዋለ ነው። ሴቶች የወር አበባቸው በሚመጣበት ወቅት የሚጠቀሙበትና ንጽህናቸውን የሚጠብቁበት መንገድ በአብዛኛው ባህላዊና ተለምዶአዊ ነው፡፡ ዘመናዊነቱ እየተስፋፋ፣ ቴክኖሎጂው እያደገ ሲሄድ ለሴቶች የወር አበባ መቀበያነት የሚያገለግሉና የሴቶቹና ንጽህና የሚጠብቁ ሞዴሶች ተሰርተው ገበያ ላይ መዋል ጀመሩ፡፡ የእነዚህ ምርቶች ገበያ ላይ መዋል ሴቶች በወር አበባ ወቅት የሚሰማቸውን የህመም እና ያለመመቸት ስሜት በእጅጉ ከመቀነሱ ባሻገር፣ ንጽህናቸው በአግባቡ ባልተጠበቁ ጨርቆች ሳቢያ የሚከሰቱ ችግሮችን ለማስቀረት አስችሏል፡፡ በፋብሪካ ደረጃ እየተመረቱ በጥቅም ላይ የሚውሉ ዘመናዊ የወር አበባ መቀበያ ፓዶችም ሆኑ የወር አበባ መቀበያ እራፊ ጨርቆቹ እጅግ አደገኛ የሆኑ ችግሮችን እንደሚያስከትሉ ጥናቶች ጠቁመዋል፡፡ “ጆርናል ኦፍ ኢንፌክሽን ዲዚዝ” ይፋ ባደረገው መረጃ፤ በወር አበባ መቀበያ ሞዴሶች ሳቢያ የሚራቡት አደገኛ ባክቴሪያዎች ከሴቶችም አልፈው ወንዶችን ለህልፈተ ህይወት እየዳረጉ ነው፡፡ በወር አበባ ወቅት በሚፈሰው ደም ውስጥ ጉሉኮስን የመሰሉ ለባክቴሪያ መራባት እጅግ አስፈላጊና ምቹ የሆኑ ነገሮች ይገኛሉ፡፡ እነዚህም በወር አበባ መቀበያ ሞዴስ ውስጥ በመግባት በቀላሉ ለመራባትና ለመሰራጨት ይችላሉ፡፡ ስታፈሎከሰስ የተባሉት እጅግ አደገኛ ችግር ሊያስከትል ለሚችል በሽታ ምክንያት የሚሆኑት ባክቴሪያዎች “ቶክሲክ ሽክ ሲንድረም” የተባለና እስከ ሞት ሊያደርስ የሚችል አደገኛ የፍትወተ አካል ኢንፌክሽን ይፈጥራሉ፡፡ በአብዛኛው ችግሩ የሚከሰተው ረዘም ላለ ጊዜ ጥቅም ላይ በሚውሉ (በወር አበባ ወቅት በሴቷ ብልት ላይ ረዥም ሰዓት በሚቆዩ) ሞዴሶች ወይንም ንጽህናቸው በአግባቡ ባልተጠበቀና በተደጋጋሚ በጥቅም ላይ በሚውሉ የወር አበባ መቀበያ ጨርቆች አማካኝነት መሆኑንም መረጃ አመልክቷል፡፡ ችግሩን እጅግ የከፋ የሚያደርገው ሌላው ጉዳይ፤ ይህ በሞዴሱ ሳቢያ የሚከሰተው አደገኛ በሽታ ለወንዶችም መትረፉ ነው፡፡ የችግሩ ሰለባ ከሆነች ሴት ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት የፈፀሙ ወንዶችም “በቶክሲክ ሾክ ሲንድረም” መጠቃታቸው አይቀሬ ነው፡፡ ችግሩ በወቅቱ ታውቆ ተገቢው ህክምና ካልተደረገለትም ለሞት ሊያደርስ እንደሚችል መረጃው አመልክቷል። የወር አበባ መቀበያ ሞዴሶች በሴቷ ሰውነት ላይ መቆየት የሚገባቸው ከ3-4 ሰዓታት መሆን ይገባዋል ያለው መረጃው፤ ከዚህ ለበለጠ ጊዜ የሚቆይ ከሆነ ለባክቴሪያ መራቢያ ምቹ ሁኔታዎች ስለሚፈጠሩ ይኸው ስታፍሎኮከስ ኦርስ የተባለው ባክቴሪያ ይራባና ”ቶክሲክ ሾክ ሲንድረም” የተባለውን አደገኛ በሽታ ሊያስከትል እንደሚችል ገልጿል፡፡ ይህ እጅግ አደገኛና በግብረሥጋ ግንኙነት ሳቢያ ከአንዱ ወደ አንዱ የሚተላለፍ በሽታ ከመከሰቱ በፊት ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባና ሴቶች በወር አበባ ወቅት የሚጠቀሙበትን ሞዴስ በንጽህና ሊጠቀሙበት እንደሚገባ “ጆርናል ኦፍ ኢንፌክሽን ዲዚዝ” አሳስቧል። addis admas

ከሜዲትራንያኑ የባህር አደጋ የተረፈው ኢትዮጵያዊ አጭር የቪዲዮ ምስክርነት

ከሜዲትራንያኑ የባህር አደጋ የተረፈው ኢትዮጵያዊ አጭር የቪዲዮ ምስክርነት http://www.youtube.com/watch?v=05dBIYSrduU

Ethnic apartheid regime of the TPLF

Ethnic apartheid regime of the TPLF is not a formidable foe when we utilize our collective strength. As we do, we do not need the permission of TPLF/EPRDF or their supporters—inside or outside Ethiopia—in order for us to come together. We also can do it at the time of our own choosing! This is not the same old game. The rules of operation have changed. The rules of change means tolerating some degree of division as part of a process of sorting out the best ways to get to a common goal. New leadership, where the leaders put humanity before ethnicity, will automatically produce some inner tensions between the goals, values and tactics of these new leaders and those who believe in ethnic divide and conquer politics. TPLF uses Article 39 for its own advancement at the cost of the destruction of the country. People are supposed to think they have autonomy, but they are under the control of the TPLF. TPLF/EPRDF does not want all the varied groups with their different approaches to have a dialogue and to come up with common goals. Yet, dialogue and compromise is the best means to be used to restore peace and harmony to Ethiopia. Because of this, we in the SMNE, and others are determined to work as hard as possible to accomplish such solidarity. We will try to make sure that all these political, civic and religious groups come together in the same room and have a dialogue for a lasting peace in Ethiopia. An atmosphere of peace is just the beginning of the road to building a future for a New Ethiopia. source -Obang Metho

የኢትዮጵያ ስደተኞች እና የላምቤዱዛው እልቂት አዲስ ዘገባ

የኢትዮጵያ ስደተኞች እና የላምቤዱዛው እልቂት አዲስ ዘገባ አንድ N R K የሚባል የኖርዎይ ቴሌቪን በላምቤዱዛው የባህር ላይ እልቂት አስመልክቶ ባወጣው ዘገባ አሳዛኝነቱ በተጨማሪ አንድ ነገር ትኩረቴን ሳበው ። ነገሩ እንዲህ ነው ብዙ የመገናኛ ብዙሃን የሚዘግቡት የኤርትራውያን ስደተኞች እያሉ ነው ። ነገር ግን N R K እንደዘገበው ከተረፉት 150 ሰዎች መቻከል 43 ቱ እድሚያቼው ከ 11 እስከ 17 የሚሆን ነው ። ከእነዚህ ውስጥ ብዙሃኑ ከኢትዮጵያ የመጡ ስደቶኞች ናቸው ሲል ዘግቡዋል ። 41 children survived the refugee boat with over 500 people on board capsized. They were between 11 and 17 years and most are from Ethiopia. Now, Save the Children helps them to move on alone. ሙሉ ዘገባውን ለማገኘት የሚከተለውን ሊንክ ከፍተው ይተርጉሙ http://www.nrk.no/verden/vil-til-norge-etter-bathavari-1.11285143 የሞቱትን ኢትዮጵያዊ እና ኤርትራዊ ወገኖቻችንን ነፍሳቸውን ይማር ። ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እመኛለሁ !

Monday, October 7, 2013

መሬት የማን ነው? (ክፍል አንድ) ፕ/ር መሰፍን ወ/ማርያም

አገር ማለት በአባቶች፣ በአያቶችና በቅድማያቶች አጥንትና ደም ተገንብቶ የታጠረ መሬት ነው፤ የዶር. በድሉ ዋቅጅራን ዋይታ እየኮረኮረ የሚያወጣውና የሚያስተጋባው የፍቅር ስሜት ምንጭ ነው። የተከሰከሰውና ተፈረካክሶ አፈር የሆነው አጥንትና የወረደው የአያቶችና የቅድማያቶች ደም እየፈሰሰ መሬቱ ላይ በሚገኙ ወንዞች ውስጥ ሁሉ ገብቶአል፤ እንዲያውም እነዚህ ወንዞች ወስደው በቀይ ባሕር፣ በሜዲቴራንያን ባሕርና በሕንድ ውቅያኖስ ጨምረውታል፤ Prof. Mesfin Woldemariam ይህ በአጥንትና በደም የታጠረ መሬት የማን ነው? በመሬቱ ላይ የባለቤትነት መብትን ለማስከበር ከውጭ ኃይሎች ጋር የተጋደሉት ጥንታውያን ነፍጠኞች ቅድሚያን የሚያገኙ ይመስለኛል፤ እነዚህ ጥንታውያን ነፍጠኞች ብቻቸውን አልነበሩም፤ ለምግብ የሚሆናቸውን ሁሉ የሚያመርቱ ገበሬዎች ነበሩ፤ ለልብስ የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ የሚፈትሉና የሚሸምኑ ባለሙያዎች ነበሩ፤ ልጆቻቸውን የሚንከባከቡና የሚያሳድጉም ለዘማቹ ምግብ የሚያቀብሉ እናቶች ነበሩ፤ በአጠቃላይ የሕዝቡን መንፈሳዊ ጤንነት ለመጠበቅ በቤተ ክርስቲያኖችና በመስጊዶች የሚጸልዩ ሰዎች ነበሩ፤ ሰላምን የሚያስከብሩና የሚያስተዳድሩ ሰዎች ነበሩ፤ … አንድ ማኅበረሰብ ለተለያዩ የመደጋገፍ ሥራዎች የሚያስፈልጉት የሰዎች ዓይነት ሁሉ ነበሩ፤ እነዚህ ሰዎች ሁሉ በአንድ ላይ አጥሩን ለመገንባት አስተዋጽኦ አድርገዋል፤ ስለዚህ መሬቱ የእነዚህ ሰዎች ሁሉ ነው። ታሪካችንን በተግባር በኩል ስንመረምረው ግን መሬቱን እኩል እንዳልተካፈሉት እናያለን፤ ዛሬ ነፍጠኛ የሚባሉት መሣሪያ የታጠቁት ሰዎች ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ እንደሚባለው ሰፋፊ መሬት የመያዝ ዝንባሌ ነበራቸው፤ ነገር ግን ለማረስ የነበራቸው የሰው ጉልበትና የጥንድ በሬ ቁጥር የተወሰነ በመሆኑ ራሱንና ቤተሰቡን ለማስተዳደር ብቻ ለሚፈልገው ገበሬ በቂ መሬት ይደርሰው ነበር፤ ሰፋፊ መሬት የያዙት ጉልበት አጥሮአቸው ሲቸገሩና ትናንሽ ማሳ ያለው ገበሬ ሰብሉ ቀንሶበት ሲቸገር በመጋዞ በማረስ ይረዳዱ ነበር (ገበሬዎችና ከብት አርቢዎችም ላሚቱ ስትወልድ ሴት ከሆነች ለከብት አርቢው፣ የከብት አርቢው ላም ወንድ ስትወልድ ለገበሬው እየተሰጣጡ ይረዳዱ ነበር፤) ሰፋፊ መሬት ያዙትም በጉልበት እጥረት ምክንያት፣ ትናንሽ ማሳ የያዙትም በትንሽነታቸው ምክንያት ከአስፈላጊው በላይ ስለማያመርቱ ትርፍ ምርት ቢኖርም በጣም ትንሽ ነበር፤ ከላይ እሰከታች ያለው ሰው ሁሉ የሚተዳደረው በመሬት ስለነበረ በጣም ጥቂት ለሆኑ ሰዎች (ቀጥቃጮች፣ አንጣሪዎች፣ ሸክላ ሠሪዎች፣ ሸማኔዎች … ወዘተ.) ለጉልበት ዋጋ ከሚከፈለውና ለአስተዳዳሪዎች ከሚከፈለው ግብር በቀር አብዛኛው ምርት ለቤት ፍጆታ ነበር። እዚህ ላይ በመሬት ጉዳይ ላይ ለመታረም ያስቸገሩ ሁለት ስሕተቶችን ሳላመለክት ለማለፍ አልፈልግም፤ ብዙ ጊዜ እንዲታረሙ ብጥርም ፈረንጆች በብዙ ሰዎች አእምሮ ውስጥ በሙጫ አጣብቀውት ሊፋቅ አልቻለም፤ አንደኛ ገባር ማለት ባለመሬት ማለት ነው እንጂ ጪሰኛ ወይም መሬት የሌለው ሰው ማለት አይደለም፤ መሬት የሌለው ገባር አይባልም፤ መገበር ማለት የባለመሬት ግዳጅ ነው፤ ገባር ማለት ግብር ወይም ታክስ የሚከፍል ባለመሬት ነው፤ ጉዳዩን አጣርተው ያልተገነዘቡት ፈረንጆች በራሳቸው አገር የመሬት ስሪት ዓይነት እንደተረጎሙት ለኢትዮጵያውያን ወጣቶች አስተማሩ፤ እነዚያም ያንኑ እንደገደል ማሚቶ እያስተጋቡ ስሕተቱን አራቡት፤ ‹‹ፊውዳሊዝም›› የሚለው ቃልም ከዚህ ስሕተት ጋር የተያያዘ ነው፤ አውሮፓ የነበረው ፊውዳሊዝም የሚባል ነገር በኢትዮጵያ ኖሮም አያውቅ። ሁለተኛው ከመሬት ጋር የተያያዘ ቃል ጉልት ነው፤ ጉልት በመሬት ላይ ያለ መብት ሳይሆን በመሬቱ ከፊል ምርት ላይ የተሰጠ መብት ነው፤ ዱሮ ገንዘብ አልነበረምና በጥሬ ገንዘብ የሚከፈል ዋጋ አልነበረም፤ ለወታደሮችም ቢሆን በደመወዝ ፈንታ የሚሰጣቸው ገባሮች ነበሩ፤ ዛሬ ባለመሬቶች በጥሬ ገንዘብ ለመንግሥት ይከፍሉና ገንዘቡ ተሰብስቦ ለወታደሮችም ሆነ ለሌሎች የመንግሥት ሠራተኞች ይከፈላል፤ ጥንት ግን ግብር ከፋዩን (ማለት ገባሩን) በቀጥታ ከመንግሥት አገልጋዩ ጋር ያገኛኙትና በእህል እንዲቀልበውና በጉልበት እንዲረዳው ይደረግ ነበር፤ ይህ ሥርዓት አልተበላሸም ለማለት አይቻልም፤ ሆኖም የመንግሥት አገልጋዮች በገባሩ መሬት ላይ ምንም መብት አልነበራቸውም፤ እንዲሁም ጉልት የተሰጣቸው የመንግሥት ባለውለታ የሆኑ መሳፍንትና መኳንንት፣ ሴት ወይዘሮዎችም በመሬቱ ላይ ሳይሆን ለመሬቱ በሚከፈለው ግብር ላይ ነበር፤ የጉልት ሥርዓት እያሉ የሚጽፉ ወይም የሚናገሩ ሰዎች አለማወቃቸውን እያራቡ ነው። የኢትዮጵያን የመሬት ስሪት ውስብስብነት በትንሹም ቢሆን ለመረዳት ሌላ ቢቀር የብላቴን ጌታ ማኅተመ ሥላሴን ዝክረ ነገር ይመልከቱት፤ የጥንቱን እንተወውና በቅርብ ዓመታት ኢትዮጵያ ከሶማልያ ጋር ቢያንስ ሁለት ጊዜ ተዋግታለች፤ ከኤርትራ ጋር የተደረገውን ጦርነት ደግሞ ብዙ ወጣቶችም የሚያውቁት ነው፤ እነዚህ ጦርነቶች የተደረጉት በመሬት ምክንያት ነበር፤ ምናልባትም ከሶማልያ ጋር ሁለት ጊዜ ከተደረጉት ጦርነቶች ይልቅ ከኤርትራ ጋር በተደረገው ጦርነት የተገደሉት የኢትዮጵያውያን ቁጥር በጣም የላቀ ሳይሆን አይቀርም፤ ከዚያም በላይ ከኤርትራ ጋር ጦርነት የተደረገበት ምክንያት ከሶማልያ ጋር ከተደረጉት ጦርነቶች ምክንያት በጣም ያነሰ ነው፤ በአጠቃላይ አገሪቱን በሙሉ ለመውረር የመጣውንም ሆነ አንዲት ትንሽ መንደር የወረረውን እኩል በመዋጋት ሀብትንና የሰው ሕይወትን ማቃጠል የማሰብ ችግር ውጤት ነው፤ ለጊዜው ዋናው ነጥባችን በነዚህ ጦርነቶች የሞቱት ሰዎች መሬቱ የኛ ነው፤ አንሰጥም፤ በማለት ነው፤ በሌላ አነጋገር የመሬቱ ባለቤት፣ የመሬቱ ባለመብት እኛ በመሆናችን ያለፈቃዳችን ሌላ አይወስደውም በማለት ነው። ባለቤትና ባለመብት ሆኖ የሞተውና በየሜዳው ላይ ሬሳው ወድቆ ሳይቀበር ለጅብና ለአሞራ ምግብ የሆነው ኢትዮጵያዊ መሬትን እንኳን ለኑሮ ለመቃብርም አላገኘም፤ በሆነው ባልሆነው መጫወቻ የሆነው መስዋእት የሚባል ቃል ትክክለኛ ትርጉሙ ይህ ነው፤ እንግዲህ ይህ ሰው መስዋእት የሆነው ለምን ዓላማ? ለማን ዓላማ ነው? የሚለው ጥያቄ መሠረታዊ ነው፤ ማንም ሰው ለመሞት በቆረጠበት ጊዜ ‹‹የምሞተው ለምን ዓላማ ነው?›› ብሎ መጠየቅ አለበት።

የነጻነት አቅድ፤ (ባጭሩ)

የሕብርት መዓብል የእምቢታ ሰራዊት የነጻንት አዉሎ ንፋስ፤ ዳዊት ጎልያድን ያንጋለለዉ አንድ ጠጠር ድንጋይ በወንጪፍ ወርውሮ ግንባሩን መቶ ነው፤ አንዱን ትልቅ ተራራ አንድ ትንሽ ወንዝ ሸርሽሮ ያፈርሰዋል፤ ስለዚህ የነጻነት ትግል በልዩ ልዩ ዘዴ የሚክናወን ሲሆን ዋና መሳርያዉ የሰፊዉ ህዝብ ትብብር ነው። ፩. ሰላማዊ ሰልፍ በተወሠነ ቦታ ብⶫ መሆን የለበትም፤ ሕዝባዊ ንቅናቄ ሁኖ በተⶫለ መጥን ትቀነባብሮ በየከተማዉ በየመንደሩ በየቀብሌዉ በየሰፈሩ ቢደረግ ለመቆጣጠር አይቻልም፤ በሚልዮን የሚቆጠር ሰራዊት ማዓበል ይሆናል፤ ይሔም ተከታትሎ ያለረፍት በየቀኑ መደረግ አለበት። ፪. የሕዝብን መብትና ነጻነት፤ ሃብቱንና መሬቱን፤ ሞያዉንና ምግባሩን፤ የዓልት እንጀራዉን የሚነሱ፤ ዜግነቱን የሚያሳጡ፤ ከኑሮ ቦታዉ የሚፈነቅሉ፤ ማናቸዉም ድንግጋትና አዋጆች ድርጊቶች በእምቢታ መቃወም፤ ማሰናከል፤ ማፍረስ፤ እንደዚህ ያለ ድርጊት የትም ቦታ በማንም ወገን ላይ ሲፋጸም በአንድነትና ብሕብረት መቃወም። የእምቢታ ሰራዊት ገንቢ ምሆን። ፫. እያንዳንዱ ዜጋ፤ እያንዳንዱ ሕብረሰብ፤ እያንዳንዱ ባለሞያ፤ ይህ የራሴ ጉዳይ ነው፣ ያገሬ ጉዳይ ነው ብሎ በንጹህ ልቦና ይሄንን ትግባር ከፈጸም፣ ማንም ምንም ሊያቆምው የማይችል የነጻነት አዉሎ ንፋስ ተነሳ ማለት ነው፤ ዉጤቱም የማያጠራር ነዉ። ያለ ትግል ያለ ምስዋትነት የሚገኝ ነጻነት የለም። ችርነቱ ያማያልቅ አምላክ ምህረቱን ይስጥን። ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር። እመሩ ዘለቀ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ጋዜጣዊ መግለጫቸው (ከፋሲል ግርማ)

ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ ከአካላዊ እንቅስቃሴያቸው እና ድምፀታቸው ጀምሮ እስከ ሚቀልዷቸው ቀልዶች እና የሚያስተላልፏቸው መልዕክቶች በሙሉ የቀድሞውን ሟች ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በሚያስታውስ መልኩ ያካሄዱት ጋዜጣዊ መግለጫ ባብዛኛው ተቃርኖ የበዛበት ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም በጋዜጣዊ መግለጫቸው ከጥያቄ እና መልሱ አስቀድመው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መንግስት ያለውን መረጃ የተናገሩ ሲሆን እንዲሁ በደፈናው አሃዝ ሳይጠቅሱ የሃገሪቱ ምጣኔሃብት እያደገ መሆኑን፤ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ዘርፉ ካለፈው አመት የተሻለ መሆኑን እና በሰላም እና ጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ከጎረቤት ሃገራት ጋር ኢትዮጵያ ያላትን ግንኙነት ለማብራራት ሞክረዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ከኤርትራ በስተቀር ከሌሎች ጎረቤት ሃገራት ጋር ያላት ግንኙነት ስትራቴጂካዊ መሆኑን ጠቅሰው፤ በተለይ የኢትዮጵያ መንግስት ከሶማሊያ መንግስት ጋር ያለውን ግንኙነት ዘርዝረዋል፡፡ እንደ እርሳቸው አገላለጽ የኢትዮጵያ መንግስት የሶማሊያ የፌዴራል መንግስት ከሃገሩ የክልል አስተዳደሮች ጋር ተስማምቶ እንዲሰራ ኢትዮጵያ የማደራደር ሚና እየተጫወተች እንደሆነ እና አልሸባብ የተባለውን አሸባሪ ሃይል ለማጥፋት በሶማሊያ ከሰፈረው የአፍሪካ ሰላም አስከባሪ ጦር ጋር በመተባበር ጥረት በማድግ ላይ ናት በማለት ሃገሪቱ በሶማሊያ ያላትን ዘርፈብዙ ጣልቃገብነት በሚያሳብቅ መልኩ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ሃይለማሪያም እንዳሉት በኢትዮጵያ ብሎም ባጠቃላዩ ምስራቅ አፍሪካ ቀጠና የደህንነት ችግር አለ፤ ነገርግን የእርሳቸው አስተዳደር በሶማሊያ የሚያደርገው ጣልቃ ገብነት ለድህንነት ችግሩ መባባስ አንዱ ምክንያት እንደሆነ ማመን የፈለጉ አይመስልም፡፡ ኤርትራን በተመለከተ በተለይ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቄ ከኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ሃይል የመግዛት እቅድ አለን ማለታቸውን አስመልክቶ ለቀረበላቸው ጥያቄ የኢትዮጵያ መንግስት ከዘጠኝ ዓመት በፊት ጀምሮ በሁለቱ ሃገራት መካከል ሰላም እንዲፈጠር ጽኑ አቋም እንደ ያዘ እና ጥረት እያደረገ ነው ያሉ ሲሆን፤ በኤርትራ በኩል ግን ይህ ዝግጁነት የለም ብለዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ መብራት ከኢትዮጵያ እንገዛለን ማለታቸውን አስመልክቶ የራሳቸው ብቻ ፍላጎት ነው ያሉ ሲሆን፣ ምናልባትም አጣብቂኝ ውስጥ ስለሚገኝ ኑዛዜ ሊሆን ይችላል ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ከኤርትራ መንግስት ጋር ሰላም መፍጠር ይፈልጋል ብለው በተናገሩበት አንደበታቸው ጠቅላሚኒስትሩ የኤርትራ መንግስት ለራሱ ሳይሆን ሌሎችን ለመርዳት እየጣረ ይገኛል በሚል ለራሷ ክንፏ ተሰብሮ ሌላ ለመደገፍ እንደምትሄድ አሞራ መስለውታል፡፡ ሃገር ቤት ውስጥ ያሉ ተቃዋሚዎች የሚያካሂዱትን የተቃውሞ ሰልፍ በተመለከተም ለቀረበላቸው ጥያቄ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስላቅ የተቀላቀለበት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ እንደ ሃይለማሪያም ንግግር ሃገር ውስጥ የሚገኙ የተቃዋሚ ሃይሎች በየሳምቱ በሚያደርጓቸው ሰላማዊ ሰልፎች ተደጋጋሚ ጥያቄ ነው የሚያነሱት፡፡ እርሳቸው እንዳሉ ለጥያቄዎቹ መንግስት ቀደም ብሎ መልስ የሰጠባቸው ስለሆነ ተጨማሪ ከመንግስት የሚመጣ ነገር የለም፡፡ ሰልፎቹ በዚህ ሁኔታ የሚቀጥሉ ከሆነም የሆነ ግዜ መንግስት ሊያስቆመው እንደሚችል ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሃገርቤት ተቃዋሚዎች የሚያሰሟቸው ጥያቄዎች የራሳቸው እንዳልሆኑ እና እንደ እርሳቸው አባባል በተለያዩ ሃገሮች ያሉ ሌሎች ሃይሎች የሰጧቸው የቤት ስራዎች ናቸው፡፡ በዚህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር፤ ለምሳሌ ሰማያዊ ፓርቲ እና አንድነት ፓርቲ የታሰሩ ጋዜጠኞች እና ፖለቲከኞች እንዲፈቱ፣ መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ላይ ጣልቃ እንዳይገባ፣ የኑሮ ውድነት የመሳሰሉት ጉዳዮች እንዲሻሻሉ ያቀረቧቸው ጥያቄዎች መልስ አያገኙም ማለት ነው፡፡ በውጭ ካሉ የተቃዋሚዎች እንቅስቃሴ በተመለከተ ግንቦት ሰባት የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ባጭሩ ህልም ነው፤ ማለም ይችላሉ ያሉ ሲሆን በፓርቲያቸው ውስጥ መሰንጠቅ ስለመኖሩም ለተነሳው ጥያቄ ምኞት ነው መመኘት ትችላላችሁ የሚል ድፍን ያለ መልስ ሰጥተዋል፡፡ ሌላው በተቃርኖ የታጀበው የጠቅላይ ሚኒስትሩ መልስ ሙስና እና ኢንቨስትመንትን በተመለከተ የቀረበላቸው ሲሆን መንግስታቸው የሙስና ቀዳዳን እያጠፋ ተወዳዳሪነት የሰፈነበት አንቨስትመንት እንዲኖር ያበረታታል ብለው የተናገሩ ሲሆን፡፡ ሙስና ውስጥ የገቡ ባለሃብቶችን መንግስት እየተከታተለ እንደሆነ እና ሙስና ጋር ያልተነካኩ ባለሃብቶች ይህ ሊያሰጋቸው እንደማይገባ የገለፁ ቢሆንም በመቀጠል ደግሞ እስካሁን ስርቆት የፈፀሙ ባለሃብቶች ካሁን በኋላ ቢያቆሙ ጥሩ ነው በማለት ከዚህ ቀደም ለተፈጸሙ ዝርፊያዎች እውቅና ሰጥተዋል፡፡ እንዲሁም የቁጠባ ቤቶችን በተመለከተ የወጣው መመሪያ የቁጠባ ቤት ተመዝጋቢዎች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ነው መቆጠብ የሚችሉት መባሉ የሌሎች የግል ባንኮችን ተወዳዳሪነት ይቀንሳል መባሉ የተሳሳተ ትንተና የተካሄደበት ትችት ነው ያሉ ሲሆን ባንኩ ሰዎች ከሚቆጥቡት 20 በመቶ ገንዘብ ላይ 80 በመቶ ጨምሮ ስለሚያበድራቸው ተጎጂ እንደሆነ ለማብራራት ሙከራ አድርገዋል፡፡ ነገርግን በዚህ መልሳቸው ባንኩ 80 በመቶ ብድር ሲሰጥ ጎን ለጎን በብቸኝነት ኢንቨስትመንት እያካሄደ ስለመሆኑ የሰጠውን ብድር መልሶ ከወለድ ጋር እንደሚያገኘው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዘነጉት ይመስላል፡፡ በመሰረተ ልማት ላይ ስለሚገኙ ዘርፈ ብዙ ችግሮች ለተጠየቁት ጥያቄ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ከፖለቲካዊ ችሎታቸው ይልቅ የምህንድስና ሙያ እውቀታቸውን ተጠቅመው ለማብራራት ሙከራ ያደረጉ ሲሆን እዚህም ላይ ግራ አጋቢ መልሶች እና ማብራሪያዎች ሰጥተዋል፡፡ የተፋሰስ ችግር በመኖሩ የአስፋልት መንገዶችን እያበላሻቸው መሆኑን የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀድሞ ነገር መንገዶቹ ሲሰሩ ተፋሰሱንም አብሮ መስራት ለምን እንዳልተቻለ አልጠቆሙም፡፡ በተመሳሳይ መልኩ የመብራት ችግር በተለይ በመኖሪያ አካባቢዎች መብራት የሚቋረጠው አዳዲስ ማሽን ቤቶች በብዛት ስለሚከፈቱ እና በየአካባቢው ያሉ ማከፋፋያዎች ለእነዚህ የሚሆን ሃይል የመሸከም አቅም ስለሌላቸው ነው በሚል ቴክኒካል መልስ የሰጡ ሲሆን እንደ ቃሊት አካባቢ ለሚገኙ የኢንዱስትሪ አካባቢ የሚባሉ አካባቢዎችም ችግሩ ተመሳሳይ እንደሆነ ነው ያብራሩት፡፡ የሞባይል ኔትዎርክ መጣበብ ችግርም ተጠቃሚ ከታቀደው በላይ ስለበዛ ነው ያሉ ሲሆን ይህ የእቅድ እና ነባራዊ ሁኔታ አለመጣጣም እንዲሁም በተደጋጋሚ የሚያነሱት የአፈጻፀም ችግር በቀድሞውም ጠቅላይ ሚኒስትር ሲሰጥ የነበረ ሲሆን ይህ የማቀድ እና የማስፈጸም ችግር ከመንግስት ብቃት ማነስ ጋር ስለመያያዙ ማንሳት የፈለጉ አይመስሉም፡፡ ባጠቃላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስተዳደራቸውን ምዕሉ በኩለሄ አይነት አድርገው የሳሉት ሲሆን ለተፈጠሩ ችግሮች ሁሉ ሰበብ አስባብ ከመደርደር የዘለለ መልስ አልሰጡም፡፡ ከአጠቃላይ መግለጫው ግን አንድ ነገር በእርግጠኝነት እንድንገነዘብ አድርገውናል፤ ኢህአዴግ ሌላው ቢቀር የአቀራረብ ለውጥ እንኳ እንደማይኖረው፡፡

Saturday, October 5, 2013

ሙስና ያጋለጠ የህወሓት አባል ተባረረ

ሙስና ያጋለጠ የህወሓት አባል ተባረረ በትግራይ እንደርታ ወረዳ ነው። የህወሓት አባላት የሆኑ የወረዳው አስተዳዳሪዎች (የዞኑ ሓላፊ ባለበት) እርስበርሳቸው እየተገማገሙ ሳለ አንድ አባል የወረዳው አስተዳዳሪ የ10 ሺ ብር ሙስና ከህዝብ መቀበሉ ያጋልጣል። የህወሓት ባለስልጣናትም እርስበርስ ተነጋግረውና ተባብረው የ10 ሺ ብር ሙስና ያጋለጠ አባል እንዲባረር ወሰኑ። ተባረረ። አዎ! አብዛኛው አባል በሙስና ከተጨማለቀ የቅጣት ሰለባ የሚሆን ሙስና ያልሰራ ሰው ነው። ህወሓቶች ሙስና ያጋለጠ አባል ከአባልነት በማባረር ድርጅቱ የሙስና ካምፕ ለማድረግ ያሰቡ ይመስላል። መቼም ሙስና የሚያጋልጡ ሰዎች በማራቅ ሙስናን ማንገስ እንጂ መታገል የሚቻል አይመስለኝም። ለነገሩ ህወሓቶች ሙስናን ላለመጋለጥ ተስማምተው የለ። ሙሰኛ መቅጣት ከተጀመረ ማን ማንን ሊቀጣ? አስቸጋሪ ነው። ሙሰኛ ለሙሰኛ እንዴት መቅጣት ይቻለዋል? እንደውም ሙሰኞች ተሰባስበው ሙሰኛ ላልሆነ አባል መቅጣት ይቀላቸዋል። እንዲህም እያደረጉ ነው። ሙሰኛ ስርዓት ሙስናን መቃወም አይችልም። ምክንያቱም ሙስና ለማጥፋት ሙሰኞች ማጥፋት ግድ ይላል። ለገዢዎች ራስ ማጥፋት ከባድ ነው። It is so!!! source -Abraham desta

No Human Rights = No Development

No Human Rights = No Development September 26, 2013 Oakland Institute and the Housing and Land Rights Network Submit Human Rights Report on Ethiopia to the United Nations OAKLAND CA- In a report submitted to the UN Human Rights Council’s Universal Periodic Review (UPR) on September 15, 2013, the Oakland Institute and the Housing and Land Rights Network outlined the human rights and international law violations perpetrated by the government of Ethiopia in the name of country’s development strategy. Drawing clear links between recorded testimonies on the ground and breaches of specific international covenants and articles in Ethiopia’s constitution, the joint submission to the UN Human Rights Council also responds to Ethiopia’s draft National Human Rights Action Plan for 2013-2015. “Rather than working to build a development strategy grounded in human rights, the Ethiopian government is attempting to hoodwink its human rights record, leaving unmentioned its villagization program and the Anti-Terrorism Proclamation-both used by the government as significant justifications for forced resettlement, arbitrary detentions, and politically motivated arrests,” said Anuradha Mittal, Executive Director of the Oakland Institute. As previous Oakland Institute reports have chronicled, the Ethiopian government’s efforts to clear land for large-scale foreign investment has entailed widespread violations of human, social, economic, and political rights. Violations of citizen’s rights to self-determination, housing, land for subsistence production, and free political association–enshrined in the Ethiopian constitution, the Rural Land Administration and Land Use Proclamation, and in United Nations international covenants–are carried out in the name of development. The joint UPR submission suggests that the ruling party’s ability to implement country’s unpopular villagization program rests in its monopoly on force and dominance over the allocation of humanitarian assistance. “Authoritarian governance and the methods used in implementing development projects have combined to violate human rights to livelihood and culture for land-based peoples, especially in the peripheral regions,” said Joseph Schechla, Coordinator of the Housing and Land Rights Network. “Involuntary resettlement, a form of forced evictions, accompanies deprivation of the right to food, including the right to feed oneself, particularly for agropastoralists. On the other hand, the ability to control information and stifle dissent has enabled the ruling party to present a positive face to the international community, which has dubbed Ethiopia a nation in “renaissance”, he continued. The joint submission presents undeniable evidence that should compel the international community to advocate for a human rights centered development strategy that would benefit all Ethiopians. Download the joint Oakland Institute/HIC-HLRN submission source - http://ecadforum.com/2013/09/26/no-human-rights-no-development/

ከለውጡ በኋላስ?

ከለውጡ በኋላስ? (ጋዜጠኛ ተመሰገን ደሳለኝ )

ኢህአዴግ ወደ መጨረሻው ምዕራፍ (በውስጥም በውጪም ተግዳሮቶች) መገፋቱን በሚያመላክቱ የፖለቲካ አጀንዳዎች ላይ የሚያጠነጥን አንድ ፅሁፍ (‹የአብዮቱ የምፅዓት ቀን ምልክቶች›› በሚል ርዕስ) አቅርቤ እንደነበር ይታወሳል፤ ይዘቱም በመጪዎቹ ወራት ወይም ዓመት ስርዓቱ ‹ምርጫ› አሊያም ‹ህዝባዊ› እምቢተኝነት ከሚያመጣው ‹ማዕበል› (እንደበረከት ስምዖን አገላለፅ ‹ናዳን በሚገታ ሩጫ›) የማምለጥ ዕድሉ የጠበበ መሆኑን የሚያመላክት ነው፤ ይሁንና አንድ አብዮት ታላቅ (ውጤታማ) ሊባል የሚችለው አምባገነን ስርዓትን በመቀየሩ ብቻ ስላልሆነ (ሥር-ነቀል ለውጥ የሚፈጥር አብዮት ዋጋ የሚኖረው የዲሞክራሲ ተቋማትን መሰረት መጣል ሲችል ነውና) በቀጣይ መፃኢ ዕድሉ ላይ መነጋገሩ አስፈላጊ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡Journalist Temasegan Dasaleg

በዚህ ፅሁፍህ ተጠየቅም ‹ከስርዓቱ ለውጥ በኋላ፣ ማን ነው አማራጩ?› የሚለው ጥያቄ ትኩረት ይደረግበት ዘንድ አመላክታለሁ፡፡
ምክንያቱም በጠለፉ መንገድ ከቀሩ አብዮቶች ታሪክ ተምረን፣ ‹መጥነን ካልደቆስን› የሚከፈለውን ዋጋ በብላሽ የሚያስቀር አሳዛኝ ሁናቴ ሊፈጠር ይችላልና (ቭላድሚር ኤሊች ሌኒን ‹‹አብዮት፣ ለአብዮት ብቻ ሲባል መካሄድ የለበትም›› እንዲል፣ ከኢህአዴግ መገላገሉ መልካም ቢሆንም፣ የአገላጋዩን ማቀፊያ ከወዲሁ መምረጡ ወይም የምንጠይቀውን ማወቁ ብልህነት ነው)

አማራጩ ተወልዷልን?

ከኢህአዴግ በኋላ የሚተካው አማራጭ ተዘጋጅቷል? …ይህንን ቀዳዳ አስቀድሞ መድፈኑን አስቸኳይ ያደረገው፣ ለውጡ የሚመጣበት መንገድ ‹ከህዝባዊ እምቢተኝነት› ይሆናል የሚለው ቅደመ-ግምት ነው፡፡ ከታዓማኒና በዕኩል አሳታፊ ምርጫ የሚነሳ ሽግግር (‹ሕዝብ የሚፈልገውን ያውቃልና ውሳኔው መከበር አለበት› ከሚለው የዲሞክራሲ ፅንሰ-ሃሳብ በመነሳት) አሳሳቢነቱ ከአደባባይ ተቃውሞ የሚመነጨውን ያህል አይደለም፤ ስለዚህም ከስጋት ነፃ መሆን የሚቻለው በሰላማዊ መንገድ ለመታገል መሰረታቸውን ሀገር ቤት አድርገው በህግ የተመዘገቡ የፖለቲካ ድርጅቶች የቤት ስራቸውን ሰርተው ዝግጁ ሆነው ሲጠብቁ ብቻ ነው፡፡ ይህ ግን የድርጅቶቹን ቁጥር ከሰማኒያ በላይ ከማሻቀብ ያለፈ አስተዋፅኦ የሌላቸውን አሰስ-ገሰስ ‹ፓርቲ›ዎች በሙሉ እንደሚመለከት ተደርጎ መወሰድ የለበትም፡፡
ነፍስ ይማርና በ‹‹ልዕልና ጋዜጣ›› እልፍ አእላፍ ችግሮቹን ማረም ከቻለ መድረክ ተስፋ ሊጣልበት ይችላል ብዬ እንደማስብ መፃፌን አስታውሳለሁ፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የመድረክ አሰላለፍ ሊቀየር በማጋደሉ (ከአንድነት ጋ አብሮ መቀጠሉ ማጠራጠሩ) እና ሰማያዊ ፓርቲ አዎንታዊ እንቅስቃሴ ከማድረጉ አኳያ ተፎካካሪ ሊሆን የሚችልበት ዕድል በመፍጠሩ፣ በአጀንዳው ላይ ማካትቱን ተገቢ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡ ይሁንና ሌሎች ፓርቲዎችን እዚህ ጋ ያላነሳሁበት፣ ከላይ ከጠቀስኩት በተጨማሪ ሶስት ምክንያቶች አሉኝ፤ ቅቡልነትን ማጣት፣ እንቅስቃሴ አልባ መሆን እና በገዥው ፓርቲ ስፖንሰርነት መተንፈስ የሚሉ፡፡

መድረክ

የስድስት ፓርቲዎች ስብስብ ነው፤ በምርጫ ሁለት ሺህ ሁለት (ምንም እንኳ ከአንድ የምክር ቤት ወንበር በላይ ባይሳካለትም) ከሁሉም
ተቀናቃኞች በላይ ጐልቶ መውጣት ችሎ እንደነበር ይታወሳል፡፡ የአምስተኛውን ዙር ሀገር አቀፍ ምርጫም ተስፋ አድርጎ ለመጠበቁ
ማሳያዎቹ፡- አንድም ስብስቡ ዛሬም ህላዊ መሆኑ፣ ሁለትም ለበርካታ አባላቱና ደጋፊዎቹ ወደ ‹ግንባር ተሻጋገሩ› ግፊት ምላሽ መስጠት
መቻሉ ነው፡፡

በምስረታው ዋዜማና ማግስት ብዙ የተነገረለት መድረክ እርስ በእርሱ (በአንድ ጠርዝ-የአንድነት አመራሮች፤ በሌላኛው-ኦፌኮ እና
ኢሶዴፓ) የፈጠረው ውዝግብ በዙሪያው ለተሰለፉ አባላትና ደጋፊዎች ተስፋ አስቆራጭ ነው፡፡ ለግንባሩ ቅርብ የሆነ ወዳጄ የችግሩን
መጦዝ የገለፀው ‹‹ሁለቱ ጎራዎች በስብሰባ ወቅት ‹በውሃ ቀጠነ› ለፀብ ሲገባበዙ የሚያይ እና ለስድብ የሚጠቀሙባቸውን ቃላት የሚሰማ በአንድ ግንባር የተሰለፉ ናቸው ብሎ ከሚያምን ‹ግመል በመርፌ ቀዳዳ መሽሎኩን› ቢቀበል ይቀለዋል›› በሚል ምፀት ነው፡፡ አደጋውን የከፋ የሚያደርገው ደግሞ ኩነቶቹ ከመለዘብ ይልቅ መባባሳቸው ይመስለኛል፡፡

በመሬት ያለው እውነታ ይህ ቢሆንም፣ ፓርቲው በ2005 ዓ.ም ወርሃ መጋቢት ወደ ‹ግንባር› መሻገሩን ከማብሰሩም በላይ፣
‹‹የኢትዮጵያን ወቅታዊና መሰረታዊ ችግሮች የመፍቻ አጋጣሚዎች›› በሚል ርዕስ ይፋ ባደረገው ባለአራት ገፅ ‹ማኔፌስቶ›፣ የሀገሪቱን
ችግር በሙሉ በአራት ክፍል ቀንብቦ ካስቀመጠ በኋላ፣ ጉዳዩን ፈረንጅኛው ‹የሲኒ ማዕበል› እንደሚለው አድርጎ በማለፍ የ‹ደግፉኝ›
ጥሪውን እንዲህ ሲል አስተላልፏል፡-‹‹ይህንን ፀረ-ህዝብና ፀረ-ሀገር የሆነውን ኢህአዴጋዊ ስርዓት በሰላማዊ አግባብ በምታደርገው ብርቱ ትግልህ መለወጥ እንደምትችል ካለፈው የትግል ተሞክሮህ ሆነ የአለም ህዝቦች ለነፃነት፣ ለዕኩልነትና ለፍትህ ብሎም ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት እውን መሆን ከሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎችና ከሚያስመዘግቧቸውም ድሎች ትገነዘባለህ፡፡ ስለሆነም መድረክ ይህንን ክቡር ትግልህን በመምራት ባለቤትነት እንድትበቃ በፅናትህ ከጎንህ ሆኖ ለመታገለ መወሰኑን ተገንዝበህ ከምንጊዜም በላይ ሁለንተናዊ ድጋፍህን እንድትሰጥ ጥሪያችንን በከፍተኛ አክብሮትና በአንተም ላይ ባለን ሙሉ እምነት እናስተላልፋለን፡፡››በግሌ መድረክ ራሱ በሁለት ምክንያቶች እምነት ሊጣልበት የሚችል አልመስለኝም፡፡

የመጀመሪያው ከአንድነት ጋር የገባበት ድምፅ የለሽ ውዝግብ ከዕለት ወደ እለት እያደገ መሄዱ ነው፤ አዲሱ የዶክተር መረራ ጉዲና መጽሐፍም ቅራኔውን ቢያሳፋው አይገርምም፤ ዶ/ሩ ስለ2002ቱ ምርጫ ባወሳበት ምዕራፍ ‹‹የ1997ቱ የቅንጅት ወራሽ ነው ብለን የተማመንበት አንድነት እውነተኛ ወራሽ ለመሆን በጣም ብዙ እንደሚቀረው ተረዳው›› ያለበት ግምገማ እና ‹‹ያልገባኝና የሚከነክነኝ አንድነት ኦሮሚያ ላይ በብዛት ያወዳደራቸው ኦህዴድ ያሰማራቸው ወሮበሎች ነበሩ›› ፍረጃው ‹ትችት›ን በቅንነት ለመቀበል ልምድ ከሌለው የሀገሪቱ ፖለቲካ አንጻር አቧራ ማስነሳቱ አይቀሬ ለመሆኑ መገመቱ አይከብድም፡፡ ይህ እንግዲህ አንድነትን የአማራ (የከተማ ልሂቃን) ተወካይ የሚያደረገውን ወቀሳ ሳይጨመር ነው (እዚህ ጋ የሚነሳው አስቂኙ ጉዳይ ወቀሳውን የሚሰነዝሩት አባል ፓርቲዎች አንድነት የብሔር ድርጅት ቢሆን ይበልጥ ተጠቃሚ ከመሆናቸው በተጨማሪ ለአብዛኛው ችግሮቻቸው በቀላሉ መፍትሄ የመስጠቱ ጉዳይ ሲታሰብ ነው) ሁለተኛው መድረኩ ከለውጡ በኋላ ሀገር ለመምራት የሚያስችል የጠራ የፖለቲካ አመለካከት አለመከተሉ ነው፤ በውስጡ ያሉ ፓርቲዎች ቢያንስ ሁለት የተለያዩ ፕሮግራም የሚያራምዱ መሆናቸው ይታወቃል፡፡

የአንድነትን እና የኦፌኮን ፕሮግራም ብንወስድ

የችግሩን ግዝፈት ያሳየናል፤ አንድነት መልካ ምድር ላይ ስለተመሰረተ ፌደራሊዝም አስተዳደር ጠቀሜታ ሲያብራራ፤ የኦፌኮ ባለስድስት ገፅ
ፕሮግራም ደግሞ በማንነት ላይ ስለተመሰረተ ፌደራሊዝም ይሰብካል፡፡ በግልባጩ ውድሀት ይፈፅሙ እንዳይባል ደግሞ የእነ ዶ/ር መረራ
‹ከተዋህድን ኦሮሞ ተውጦ ይጠፋል› ስጋት ጋሬጣ ነው፡፡ አንዳንድ የአመራር አባላቱ ‹‹ዓላማችን ቅድሚያ ዴሞክራሲያዊ ተቋማትን
መገንባት ነው›› የሚል መከራከሪያ ሲያቀርቡ ቢደመጡም፣ ከዚህ በኩል ከሚነሳው ተግዳሮት በቀላሉ የሚመለጥ አይመስለኝም
(በነገራችን ላይ መድረኩ በወቅታዊው ቁመና ‹ግንባር› ለመመስረት የሚያስችለውን መስፈርት ሟሟላቱ ራሱ አጠራጣሪ ነው)

አንድነት

የአንድነት ተግዳሮት ወደ መድረክ ከመግባት ጋ ተያይዞ የመጣ ነው (ከጠዋቱ ሰማያዊ ፓርቲን የመሰረቱት ወጣቶች ከድርጅቱ
ለመውጣት አንዱ ምክንያታቸው ይህ እንደሆነ ይታወሳል)፤ ትብብሩን ‹ያልተባረከ ጋብቻ› የሚያስብለው ደግሞ የዛሬ አራት ዓመት ‹ወደ
መድረክ ካልገባን ትግሉን እናደናቅፋለን› ሲሉ የነበሩ አንዳንድ የአንድነት አመራሮች የውዝግቡ ተሳፊ መሆናቸውን ስንመለከት ነው፤
መተነኳኮሱ በ2002ቱ ምርጫ ማግስት የተጀመረ ቢሆንም፣ ባለፈው ዓመት ወደ መጦዝ ተሸጋግሯል፡፡ በተለይም አንድነት ‹‹የሚሊዮኖች
ድምፅ ንቅናቄ›› በሚል መርህ ያካሄደው የሶስት ወር ዘመቻ መድረክን አለማካተቱ የሚያስተላልፈው መልዕክት ግልፅ ነው፡፡ በ‹‹ፀረ-
ሽብር›› አዋጁ ላይ (ኢህአዴግንና ኢዴፓን ጨምሮ) በተደረገው ክርክርም አንድነት እና መድረክ በተለያዩ ሰዎች ተወክለው መቅረባቸው
ግንኙነቱን እንደ ቀድሞ ለማየት አስቸጋሪ አድርጎታል፡፡

ይህም ሆኖ አንድነት በራሱ የተሻለ ፓርቲ ሆኖ ሊወጣ የሚችልበት ዕድል አለው፡፡ ምሁራዊ ስብስቡም ሆነ የኢኮኖሚ አቅሙ
(የዲያስፖራ ድጋፉ) አንፃራዊ ጥንካሬ እንዲያገኝ ረድቶታል፤ ርዕዮተ-ዓለሙንም ከተቀናቃኝ ፓርቲዎች በጠበቀ መልኩ ማዘጋጀቱ
ለቅቡልነቱ አስተዋፅኦ ሊያደርግለት ይችላል፤ ከመኢአድ ጋር የጀመረውን ውህደት (‹የአማራ ተወካይ› የሚለውን ፍረጃ ቢያጠናክረውም)
ከዳር ካደረሰ ደግሞ ከአቻዎቹ ጋ ያለው ልዩነት በእጅጉ መስፋቱ አይቀሬ ነው (መኢአድ የፈራረሰው ከአናት ነውና ግዙፍ መዋቅሩ ‹እረኛ አልባ› በመሆኑ፣ አንድነት በውህደት ስም ቢሰበስበው በከፍተኛ ደረጃ ይጠቅመዋል)

የወል-መንገድ

በቀጣይ የተሻለ አማራጭ ሆኖ ለመገኘት መድረክና አንድነት መቻቻላቸው ወሳኝ ነው፡፡ ይሁንና ኩነቱን በታዛቢነት መመልከት
የመረጡት የአረና ሰዎቸ በግንባሩ ቢሮ ሰላም ለማውረድ የአስታራቂነት ሚና ቢጫወቱ ጠቃሚነቱ ለእነርሱም ነው፡፡ አንድነቶችም፣
በመድረክ ስም እዚህ ድረስ ለመጓዝ የከፈሉት ዋጋ ብላሽ ከሆነ ማንንም አያተርፍም፡፡ በአናቱም ወቅታዊው የኢትዮጵያ ፖለቲካ አስገዳጅ
መሆኑ መረሳት የለበትም፡፡ ምክንያቱም አንድነት የሰበሰባቸው ልሂቃኖችም ሆኑ በሀገሪቱ የተለያዩ ከተሞች ያነበረው መዋቅር (ጥንካሬው
ላይ ያለኝ ጥርጣሬ እንደተጠበቀ ሆኖ) ቅድሚያ ለብሔር ፖለቲካ ከሚሰጡ አካባቢዎች በ‹መድረክ ባርኔጣ› በሚገኝ ድጋፍ (ድምፅ)
ካልታገዘ በቀር አየር ላይ ተንጠልጥሎ ከመቅረት አይታደገውም፡፡

የመድረክ ተግዳሮትም ተመሳሳይ ነው፤ በፖለቲካው ላይ ውጤት የሚያዛባ ተፅዕኖ ማሳረፍ የሚቻላቸውንና አንድነት የራሱ
ያደረጋቸውን ከተሜዎች ‹ቡራኬ› ሳይቀበል ወደ ውድድር መግባቱ ‹ውሃ በወንፊት…› አይነት ሊሆንበት ይችላል፡፡ የመድረክንና
የአንድነትን የወል ቀዳዳ መዘርዘሩን እዚሁ ገትቼ፣ የተሻለ ጥንካሬና የመግባባት መንፈስ ለማስረፅ በቅድሚያ የችግሮቻቸውን መንስኤ
ለይተው ማወቅ አለባቸው ብዬ ስለማስብ፣ በግሌ ‹ያለመግባባቱ መነሻ› ከምላቸው ዋና ጉዳዮች ሶስቱን በአዲስ መስመር እጠቅሳለሁ፡፡

፩- የፕሮግራም መጋጨት ያመጣው ጣጣ አንዱ ነው፤ ይኸውም የፀቡ የቡድን አባቶች የ‹ሕብረ ብሔር› እና የ‹ክልል› ፖለቲካ አቀንቃኝነት፣ ሁሉም አባል ፓርቲዎች መድረኩን ሲፈጥሩ የየራሳቸውን ፕሮግራም እንደያዙ መሆኑ፣ ጥቂት የማይባሉ ልዩነታቸውን ሳይፈቱ ‹በይደር› ማስቀመጣቸው… እንደ ማሳያ ይጠቀሳሉ፡፡ ይህ ሁኔታም የእርስ በእርስ መተማማን እንዳይኖራቸው ያደረገ ይመስለኛል(ከዚህ አኳያም ለመፍትሄው ቅድሚያ ከልሰጡ በመድረክ በኩል ‹መጪው ጊዜ ብሩህ ይሆናል› ብሎ መጠበቅ ‹የዋህ› ሊያስብል ይችላል) የጫናው ተፅእኖ ደግሞ በሁለቱም በኩል (በአንድነትና በብሄር ድርጅቶቹ) ከሚከተሉት የፖለቲካ አመለካከት አንፃር ወደ ስልጣን የመምጣቱ አጋጣሚ ቢፈጠር፣ የታገሉለትን ስርዓት ማንበሩ ፍፁም አዳጋች መሆኑን በማስታወስ ነው፤ አንድነቶች ፓርቲያቸው ከመድረክ እንዲወጣ ይጎተጉታሉ፤ ብሔር ተኮሮቹ ደግሞ ‹አንድነት የነፍጠኛውን ስርዓት የሚመለስ በመሆኑ፣ ወይ ወደ ብሄር ድርጅት ራሱን ይቀየር፣ አሊያም ፕሮግራሙን ይከልስ› የሚለው ሙግታቸው በአሳማኝ ሁኔታ መፍትሄ አለማግኘቱ ራሱን የቻለ ሌላ ትግል ከሚፈልግ አጀንዳ ጋ አላትሟቸዋል፡፡

፪-አንድነት በሚያራምደው የሊብራል ዲሞክራሲ እና አብዛኛው የመድረክ አባል ድርጅቶች በሚከተሉት የሶሻል ዲሞክራሲ መካከል ያለውን ልዩነት የማሰታረቅ ስራ አለመሰራቱ ነው፡፡ ‹‹የአንድነት ፓርቲ ስትራቴጂና የአምስት ዓመት ዕቅድ›› በሚል ርዕስ 246 ገፅ ይዞ በታተመው መፅሀፍ ላይ ‹‹አንድነት የሚመሰረትበት ርዕዮተ-ዓለም ሊበራሊዝም ሆኖ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፖሊሲዎች የሶሻል ዲሞክራሲን ጠቃሚ ገፅታዎች ይወስዳል›› የሚለው አንቀፅ ቢጤን ለመልካም ግንኙነት መደላድል መሆን ይችላል (በነገራችን ላይ‹እንዲህ የችግር ቋት ተሸክመው ስለምን በጋራ ለመስራት ተስማሙ?› የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀርምና ግምቴን ላስቀምጥ፤ የብሔር ድርጅቶቹን እስትንፋስ የሚቆጣጠሩት ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ እና ዶ/ር መረራ ጉዲና ምርጫ 97ን ከሁለት አቅጣጫ ገምግመው ከደረሱበት ድምዳሜ ጋ የሚያያዝ ይመስለኛል፤ ይኸውም ‹አንድነት፣ የቅንጅት ወራሽ ነው› የሚለው የተሳሳተው ትንተና አንዱ ሲሆን፣ ሁለተኛው በዛው ምርጫ ተቀማጭነታቸው አውሮፓና አሜሪካ ከሆኑ አስራ ሁለት ፓርቲዎች ጋር መስርተውት የነበረው ‹‹ህብረት››፣ ፓርላማ በመግባታቸው፣ ከውግዘት ጋር እንዲባረሩ በማድረጉ ያሳደረባቸው መገለል ሊሆን ይችላል፤ በአንድነት በኩል ደግሞ ‹የመድረኩ መሀንዲስ› ተደርገው የተወሰዱት ዶ/ር ነጋሶና አቶ ስዬ አብርሃ አንድነትን ለመቀላቀል ወደ መድረክ መግባትን እንደ መደራደሪያ በማቅረባቸው ሲሆን፣ ሌላኛው ደግሞ ዛሬም ያልተሸነፈው የ‹ተባበሩ ወይም ተሰባበሩ› ግልብ ግፊት ነው ብዬ አስባለሁ፤ የዚህ ድምር ውጤትም ከነርዕዮተ-ዓለም እና የፕሮግራም ልዩነት ወደ መድረኩ አምጥቷቸው አይን የሚገባ ሥራ እንዳይሰሩ አግዷቸዋል)

፫-የመድረክ አባል ድርጅቶች መተዳደሪያ ደንብን አለማክበር ‹የፖለቲካ ብልጠት› በማድረጋቸው፣ ለራሳቸው ተጨማሪ የመናተረኪያአጀንዳ ፈጥረዋል፡፡ ይህ አይነቱ ስርዓት አልበኝነት በጋራም በተናጥልም ተፈፅሟል፡፡ አንድነትን ጨምሮ የመድረኩ ስራ አስፈፃሚ ደጋግሞከመርሁ ሲያፈነግጥ ታይቷል፤ ለምሳሌ በደንቡ ላይ መሻሻል ያለበትን አንቀፅ የሚወስነውም ሆነ ከፍተኛው ስልጣን የጠቅላላ ጉባዔውመሆኑ በግልፅ ተቀምጦ ሳለ፣ ጉባዔው ከተሰበሰበባቸው በአንዱ ዕለት ‹የመድረኩ ሊቀ-መንበረ በዙር ከሚሆን፣ በብቃት ይሁን›፤እንዲሁም ‹አዲስ ፓርቲ በአባልነት የምንቀበልበት መንገድ መሻሻል አለበት› የሚሉ አቋሞች ላይ ቢደርስም፣ ስራ አስፈፃሚው ቃል በቃል‹ይህንን አሰራር ጉባኤው ሊቀይረው አይችልም› ሲል ውድቅ ያደረገበትን አጋጣሚ መጥቀስ ይቻላል፡፡

በተናጥል አንድነት፣ ኦፌኮ እና ኢሶዴፓ በአንቀፅ 21 ‹የአባል ድርጅቶች ግዴታ› በሚል ርዕስ ስር የተቀመጡትን፡- ‹ከአፍራሽና
ተቃራኒ ከሆኑ እንቅስቃሴዎች መቆጠብ›፣ ‹በአባላት መካከል አለመተማመን ከሚፈጥሩ ማናቸውም ተግባር መቆጠብ›፣ ‹የግንባሩን አቋም
የሚፃረር አቋም ያለማራመድ› እና መሰል ደንቦችን ደጋግመው በአደባባይ ሲጥሱ ታይተዋል፤ ይህ አይነቱ ስርዓተ-አልበኝነት መፍትሄ
ሳያገኝ የተሻለና ጠንካራ ሆኖ መውጣቱ አዳጋች ይመስለኛል፡፡

ሰማያዊ

ሰማያዊ ፓርቲ አዲስ በመሆኑ ለወቀሳ መቸኮሉ አግባብ እንዳልሆነ ቢሰማኝም፣ ፓርቲው እያሳየ ካለው ፈጣን እንቅስቃሴ አኳያ፣
በፍጥነቶቹ መካከል የሚፈጥራቸውን ድክመቶቹን ቢያሻሽል ጠቀሜታው ለሀገር ስለሆነ የግል አስታየየት መስጠቱን አስፈላጊ ሆኖ
አግኝቸዋለሁ፡፡የሰማያዊ ዋናው ድክመት ከ‹ግንፍሌ ፓርቲ›ነት አልፎ የመሄድ ፍላጎት ያለው አለመምሰሉ ነው (ጽ/ቤቱ አራት ኪሎ /ግንፍሌ/ አካባቢ ይገኛል)፡፡

ከአዲስ አበባ ውጪ ለመንቀሳቀስ ሲሞክር አይታይም፤ በሌሎቸ የሀገሪቱ ከተሞች የተከፈተ ተጨማሪ ቢሮ ካለ፣ ከምስረታው
በኋላ የአባላቱ ቁጥር ምን ያህል እንደደረሰ፣ እና መሰል መረጃዎችን ለማግኘት ወደ ፓርቲው ጽ/ቤት ሄዶ የነበረው የመፅሄቱ ሪፖርተር
‹እንዴት እንደምትጠቀሙበት ስለማናውቅ አንናገርም› በሚል ክልከላ በመመለሱ ስለወቅታዊው ቁመና እዚህ ጋ መጥቀስ አልተቻለም
(ከዚህ ውጪ ሊቀ-መንበሩ ይልቃል ጌትነት ከ‹ሰንደቅ› ጋዜጣ ጋር ባደረገው ቃለ-መጠይቅ ‹‹ባለፉት 40 ዓመታት ከመጣው የፓርቲዎች ጥንካሬ ይልቅ፣ በአንድ ዓመት ውስጥ ሰማያዊ ፓርቲ ብቻውን አምጥጦታል›› ያለው ሀረግ ስህተት ቢሆንም፣ አንድም በሂደት የሚታረም፣ሁለትም የአፍ ወለምታ፣ ሶስትም ከልምድ ማነስ የሚያጋጥም በመሆኑ ‹ፀጉር መንጨቱ› ፓርቲው ፍርሃትን ለመስበር ከሚያደርገው እንቅስቃሴ አኳያ ገንቢ አይደለምና አልፈዋለሁ፡፡)

‹እምነት ጨምሩልን›

‹ለውጥ! ለውጥ!› የሚል ድምፅ በመላ ሀገሪቱ የበረከተው የ‹ቡርዣ› ወይም ‹አድሀሪ› አብዮትን በመናፈቅ አይደለም፤ እንዲህ አይነት
አብዮት፣ ከሰው ለውጥ በቀር ሕዝባዊ ጠቀሜታ የለውማና፡፡ የደርግም ሆነ የኢህአዴግ ‹አብዮት› የዚህ አምሳያ በመሆኑ ነው፣ ዛሬም
ዘመን ተጋሪዎቼ ‹ፋኖ ተሰማራ!› ከማለት ነፃ ያልወጡት፡፡ ‹ሶስተኛው አብዮት› የማይሸነፍ እና የማይንበረከክ እንዲሆንልን ከምንመኘው
በላይ ወደ ‹መፈንቅለ-መንግስት›ነት እንዳይቀየር መጠንቀቁንም ግዴታ ያደረገው ጠንካራ ፓርቲና የነቃ ማህበረሰብ ያለመኖሩ ስጋት ነው፡
፡ ይህ ደግሞ ከወዲሁ ከአማራጩ ኃይል ጎን መቆም ይቻል ዘንድ ‹እምነት ጨምሩልን!› (ሀገር የመረከብ አቅማቸውን አሳዩን?) እንድንል አስገድዷል (‹ጀግናው› ኢህአዴግ ወደ ማይቀረው ሽንፈት መንገዱን ከጀመረ ጥቂት ክረምቶች በማለፋቸው፣ ከለውጡ በኋላ የሚመጣው ኃይል ሁለንታው የተቃና መሆኑን ማስመስከር አለበት)መድረክ፣ አንድነት እና ሰማያዊ ወደራሳቸው ይመለከቱ ዘንድ ከሞላ ጎደል የወል ‹ክፍተቶች› ወይም ‹ድክመቶች› የምላቸውን ሶስት ጉዳዮች ከዚህ ቀጥሎ እጠቅሳለሁ፡፡

ሃሳብ-አልባ

ፓርቲዎቹ በምስረታቸው ዘመን ቅድሚያ የሚሰጡት ለምርጫ ቦርድ የእውቅና ሰርተፍኬት እና ‹ተቃዋሚ ድርጅት› ተብለው
ለመጠራት በመሆኑ አንድም የሀገሪቱን አንኳር ችግሮች አጥንተው መፍትሄ በመያዝ አልተዘጋጁም፤ ሁለትም ከነባር ድርጅቶች ድክመትና
ጥንካሬ ተምረው አልመጡም፤ በዚህም የሚፈልጉትን ሳያወቁ እና የተለየ አማራጭ ሳይይዙ ወደ ፖለቲካው ገብተዋል ወደሚል ጠርዝ
እየገፋን ነው፤ ጠንካራና የተፍታታ የፖለቲካ ፕሮግራም የላቸውም፤ በንፅፅር ‹‹አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ›› የተሻለ ፕሮግራም
ለመቅረፅ ከመሞከሩ ውጪ፣ የመንግስቱ ስልጣን ‹ገጭ-ቋ› ቢል ‹አማራጭ ሊሆኑ ይችላሉ› የሚባሉት ፓርቲዎች ‹እያሾፉ ነው› በሚል
ችላ ካልተባሉ በቀር ‹ፕሮግራሜ› ብለው ያቀረቡትን ለተመለከተ ምን ያህል ሃሳብ አልባ እንደሆኑ ለመረዳት አይቸገርም፡፡

የሆነው ሆኖ ይህንን ፅሁፍ ሳዘጋጅ የነበረኝ አመለካከት ስለመድረክና አንድነት የፖለቲካ ፕሮግራም ደካማነት ከዚህ ቀደም ስለጠቀስኩ፣
ዛሬ ሰማያዊ ፓርቲን ብቻ አንስተን ብንነጋገር ይሻላል የሚል ነበር፤ ይሁንና የድርጅቱን ፕሮግራም ካነበብኩ በኋላ ግን ምንም ማውራት
እንደማይቻል ተረዳው (ያውም ያየሁት ወረቀት ‹ፕሮግራም› ተብሎ ሊጠራ ከቻለ ማለት ነው)፡፡ ፓርቲው ለስልጣን የመብቃት ዕድል
ካገኘ፣ ለዘመናት ሲንከባለልና ሲደራረብ የመጣውን ዘርፈ ብዙ የሀገሪቷን ችግር የሚፈታው ‹‹የሰማያዊ ፓርቲ ፕሮግራም›› በማለት ርዕስ
ባዘጋጀው ባለአስራ አምስት ገፅ ወረቀት ነው፡፡ መቼም በዚህ ፕሮግራም ‹ከሌሎች የተሻልኩ ነኝ-ምረጡኝ› የማለቱ ድፍረት ግራ አጋቢ
ይመስለኛል፤ ምናልባት ‹የፖለቲካ ሳይንስ ምሁሩ ዶ/ር መረራ ጉዲና ካዘጋጀው አራት ገፅ ፕሮግራም፣ የእኛ የበለጠ ነው› የሚል
መከራከሪያ ካልቀረበ፡፡

ስለርዕዮተ-ዓለሙም ቢሆን ‹ለዘብተኛ ሌብራሊዝም› ከማለት ያለፈ ያብራራልን ጉዳይ የለም (በዚህ በኩል ኢዴፓ ከሁሉም በተሻለ የተብራራና የጠበቀ ፕሮግራም አለው፤ ግና! ለአንድ ፓርቲ ከምንም በላይ አስፈላጊ የሆነውን ‹ታአማኒነት› አፍርሷልና ፕሮግራሙ ጠቀመ አልጠቀመ ፋይዳ አለው ማለት አይቻልም) በተቀረ ያለ ርዕዮተ-ዓለም ፓርቲ መስርቶ፣ ‹ሀገሬን፣ ሀገሬን…› ማለቱን
ከቀረርቶ ለይቶ መረዳት ይቸግራል፡፡ መድረክ፣ አንድነት እና ሰማያዊ አሁንም ጊዜውም ዕድሉም አላቸውና ስልጣን ቢይዙ በዋና ዋና ሀገራዊ አጀንዳዎች፣ በፖሊሲዎች፣ በማህበራዊ ፍትህ እና መሰል ጉዳዮች ላይ ያላችውን የመፍትሄ ሃሳብ እና የተሻለ አማራጭ በትክክል ተንትነው ማዘጋጀቱን ቢያስቀድሙ መልካም ይመስለኛል፡፡

ቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ በ1997 ዓ.ም ‹‹የምርጫ ማኒፌስቶ›› ብሎ ያዘጋጀው ሰነድ እንኳ ከ130 ገፅ በላይ የፈጀ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው፡፡ እናም ፓርቲዎቹ ‹ፕሮግራሜ› የሚሉትንም ሆነ፣ ከተራራ የገዘፈ ችግሮቻችንን በደቃቃ ግምገማ ለማብራራት መዳከሩን አርቀው በመስቀል ወደ ቁም-ነገሩ ቢያዘንብሉ ጠቀሜታው ለራሳቸው ነው፤ ‹የትም ፍጪው…› መረሳት አለበት፤ ለፖለቲካ ፓርቲ ሃሳብ ከምንም በላይ ወሳኝ ነው፡፡ ዳሩስ! በሰላማዊ መንገድ ለመታገል የተዘጋጀ ፓርቲ፣ የሚሸጥ ርዕዮተ-ዓለም ካላዘጋጀ በቀር ወታደራዊ ድርጅት አይደለምና ‹በኃይል ተጠቅሜ ፍላጎቴን አሳካለሁ› ሊል አይችልም፡፡ እውነት እውነት እላችኋለውም በዚህ በኩል ቀድሞ የነቃ፣ እርሱ አትራፊ ነው፤ ረቢው እንዳለውም ‹ላለው ይጨመርለታል›ና፡፡

ምሁር አልባ

የተፎካካሪ ድርጅቶች ሌላኛው ክፍተት ምሁራንን /ሙያተኞችን/ አለማቀፍ እንደሆነ ተደጋግሞ ቢነገርም፣ ዛሬም በዚህ በኩል የተሰራ
ሥራ የለም፡፡ ይህንን ቀዳዳ ለመድፈን አመራሩና አባለቱ ከጽ/ቤት በመውጣት መቀስቀስ፣ ማሳመን፣ ማግባባት… አለባቸው ብዬ
አስባለሁ፤ መቼም በሁሉም ዘርፍ ‹እኔ ብቻ ነኝ የማውቀው› ግብዝነትን የወረሱት ነፍሱን ይማረውና ከአቶ መለስ ይመስለኛል፤ ይህ
አይነቱ አመለካከት ግን ወንዝ አያሻግርም፡፡ በርግጥ ‹ፖለቲካና ኮረንቲ…› በሚባልበት አገር፣ በደፍረት፣ ድርጅት እስከመመስረት መድረስ
ትልቅ ታሪክ ቢሆንም፣ ጠንካራ መሆን ካልተቻለ ዞሮ ዞሮ ያው ክሽፈት ነው፡፡ አደባባዩም እንደቀድሞ ‹ድንጋይ ዳቦ ነው› ብለው
ለሚከራከሩ አፈ-ጮማ ፖለቲከኞች ቦታ የሌለው መሆኑ ግልፅ ይመስለኛል፡፡ በተለያየ ሙያ የሰለጠኑ ምሁራኖችን ወደ ፓርቲያችሁ
ለመሳብ መደላደሉን አመቻቹ፤ ፍርሃት መሰበር እንዳለበት አሳምኗቸው፤ አንኳኩ፤ ከልከፈቱም ደጋግሙት፡፡

የሴራ ፖለቲካ

ሌላው ድርጅቶቹ የሚጠነክሩት፡- ከሴራ፣ ከስርቻ ስር ፖለቲካ፣ ከጠልፎ መጣል ጨዋታ፣ ከአፍቅሮተ-ስልጣን አና ከመሳሰሉት ነፃ
ሲሆኑ ነው፡፡ በአናቱም የጥናትና ምርምር ዘርፍ መሰል እያቋቋሙ እውቀትና መረጃን ወደላይም ወደታችም በማሰራጨት አመራሩንና
አባላትን ማብቃት፣ እንዲሁም ግልፅነትን በመተግበር፣ የ‹ጀርባ ፖለቲካ›ን ማዳካም ይቻላል፡፡ ይህ ሲሆን ነው ኩነቶችን ከመበለጥና
ያለመበለጥ፤ ከመሸነፍና ያለመሸነፍ አኳያ ብቻ የማየቱ አባዜ የሚለወጠው፡፡ ከእዚህ ሁሉ ስንክሳር በላይ ደግሞ በምሬቷ ብዛት
በአማራጩ ኃይል ላይ ተስፋ የጣለች ሀገር መኖሯም ከእያንዳንዷ እንቅስቃሴ ጋ መታወስ ይኖርበታል፡፡

በመጨረሻም-የአልባራዲ መንገድ

ሀገሪቱ ካለችበት ወሳኝና ታሪካው ወቅት አኳያ ቢያንስ በመንግስት ጥቁር መዝገብ ስማቸው ያልሰፈረ፣ እውቀትና አቅም ያላቸው፣
በየትኛውም ሀገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በራሳቸው መንገድ ወደ ሀገራቸው ገብተው ትግሉን ማገዝ የሀገሪቱ ወቅታዊ ሁናቴ
የሚያስገድደው ነው፡፡ በተለይም በእንዲህ አይነት ጉዳዮች ከትምህርትም ሆነ ከመስክ ልምድ ያካበቱ ወንድምና እህቶች የግብፃዊውን
መሀመድ አልባራዲ መንገድ ቢከተሉ፣ አንድም ሁኔታዎች ከቁጥጥር እንዳይወጡ ማገዝ ይችላሉ፤ ሁለትም አብዮቱን ከሽንፈትና ቅልበሳ
ይታደጋሉ፡፡
(ጋዜጠኛ ተመሰገን ደሳለኝ )
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ

Amnesty International: Ethiopian repression of Muslim protests must stop

“We are extremely concerned at reports coming out of Ethiopia this morning of further widespread arrests of Muslim protesters. The Ethiopian government’s ongoing repressive crackdown on freedom of speech and the right to peacefully protest has to end now.”
Claire Beston, Amnesty International’s Ethiopia researcher.


The Ethiopian government must end its use of repressive tactics against demonstrators, following initial reports of widespread arrests of Muslim protestors during this morning’s Eid al-Fitr celebrations, said Amnesty International today.
“We are extremely concerned at reports coming out of Ethiopia this morning of further widespread arrests of Muslim protesters. The Ethiopian government’s  ongoing repressive crackdown on freedom of speech and the right to peacefully protest has to end now,” said Claire Beston, Amnesty International’s Ethiopia researcher.
Last week, another incident related to the protests reportedly ended in the deaths of an unconfirmed number of people in the town of Kofele in Oromia region.
During the 18 month-long protest movement against alleged government interference in Islamic affairs, the vast majority of demonstrations have been peaceful. However, there have been at least four incidents involving serious allegations of the excessive use of force by security forces against demonstrators in the long-running movement.  While a few isolated incidents of violence involving protestors have occurred, these have taken place during episodes where excessive police force is alleged.
“These reports of further deaths in the context of the Muslim protest movement are deeply worrying. There must be an immediate, independent and impartial investigation into the events in Kofele, as well as into the four incidents last year which resulted in the deaths and injuries of protestors,” said Claire Beston.
“With further protests planned, it is imperative that the behaviour of the security forces is scrutinised and if enough admissible evidence of crimes is found, suspected perpetrators should be prosecuted in trial proceedings that meet international standards.”
Accounts of last week’s incident in Kofele from the protestors and the government differ widely.
Protestors report that the security forces opened fire on unarmed people who were protesting against the arrests of members of the local Muslim community. One resident of Kofele told Amnesty International that 14 people were shot dead by the army, including at least three children. Another said that 11 people had been killed.
According to media reports, the authorities have said that the protestors were armed, leading to an outbreak of violence which resulted in the deaths of three protestors and injuries to a number of police officers. Government representatives refused to respond to Amnesty International’s queries about the incident.

What is it like to get everything you need but to lose everything you know?"



Girl, Adopted



Girl, Adopted is a contemporary coming-of-age story that follows Weynsht, a 13-year-old Ethiopian girl, from an orphanage in Africa to an adoptive American family in rural Arkansas. An irrepressible adolescent, Weynsht searches for identity in an effort to find out who she is in the aftermath of her adoption. The film follows her struggle for love among strangers and to understand what to make of this love on an unexpected return trip to Ethiopia. 

Weynsht’s story offers a rare, child’s-eye view of being adopted across race and culture. Taking neither a pro- or anti-adoption stance, the film acknowledges the complexities involved and gives a real voice to the experience. The central question that Girl, Adopted asks is, "What is it like to get everything you need but to lose everything you know?"