Tuesday, October 15, 2013

ከሊቢያ ለጉዞ የተዘጋጁ ስደተኞች

አፍሪቃ ኣንዳንድ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ስደተኞች ታጉረው ከሚገኙበት ወይንም ተደብቀው ጀልባ ከሚጠባበቁበት የትሪፖሊ ማጎሪያ ቤት ለዶቸቬሌ አነጋግሯቸዋል። እንደተናገሩትም በሱዳን በኩል ኣድርገው ሊቢያ እስኪደርሱ በዚህ ረጅም የበረሃ ጉዞ የደረሰባቸውስቃይ ሳያንሳቸው ኣሁንም የባህር ላይ ኣሰቃቂ ጉዞ ይጠብቃቸዋል። በእርግጥ ስደተኞቹ እንደሚሉት ያ ከሁለት መጥፎ ይሻላል ብለው የመረጡት የተሻለ መጥፎ በመሆኑ እዚያው ሊቢያ ውስጥ በፖሊሶች የሚደርስባቸውን ዘረፋ እና እስራት ነው ይበልጥ የሚያማርሩት። ከ UNHCRየጀኔቫ ቢሮ ቃል ኣቀባዩ ሚ/ር ዳን ሚክኖኣፓኔ እንደሚሉት ለችግሩ መፍትሄ ለመሻት የሚደረገው ጥረት ማነጣጠር ያለበት መነሻው ላይ ነው። ይህ ግን ጊዜ የሚፈጅ በመሆኑ ሚ/ር ዳን እንደሚሉት የኣውሮፓ ህብረት እና ሌሎችም ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ስደተኞች ተገን የሚጠይቁበትን ቦታ እና የሚያገኙበትን ሁኔታ እንደገና ሊመረምሩ ይገባል። ከዚሁ ጎን ለጎን ደግሞ የባህር ላይ ቁጥጥሩም በእርግጥ ሊጠናከር ይገባል ባይ ናቸው ሚ/ር ዳን። ጃፈር ዓሊ ሸዋዬ ለገሰ

No comments:

Post a Comment