Friday, October 11, 2013

የናቁት ያደርጋል እራቁት

ታሪክ አንዳስቀመጠልን በሃገራችን ሰው የሚኖርበትን ኣካባቢ ለቆ የሚሰደደው የተሻለ ትምህርት ለማግኘትና የሄደበትን አላማ ሲጨርስ ሀገሩን ለማገልገል እንደሆነ የታሪክ ምንጮች ይገልጻሉ። ዛሬ በተለያየ መንገድ ተሰደው የተለያዩ አሰቃቂ ችግሮች የሚደርስባቸው ሴት እህቶቻችን በ አረብ ሀገር ውስጥ የሚደርስላቸውን አጥተው እንደወጡ የሚቀሩት፣ በደቡብ አፍሪካ ስንት ወገኖቻችን የእንስሳት ሆድ መሙያ የሆኑበት፣ የሰሀራ በረሀ ስንት ወገኖቻችንን አፍኖ ያስቀረበት፣ በተለያዩ ሀገሮች እንዲህ ነው ሊባል የማይችል ስቃይ እየደረሰባቸው ሰሚ አጥተው በወጡበት የቀሩት ወገኖቻችን ማን ነው የሚያየው? ማነውስ የሚደርስላቸው? የላምፐዱሳ ደሴት ውጦ ጸጥ ያለውን የወንድሞቻችን እና የእህቶቻችንን እንዲሁም ምንም የማያውቁ ህጻናትንስ ማን ነው የሚያድነው? ማነውስ በቃ የሚለው? እሬሳቸው ሀገርና ወገን እንደሌለው ወድቀው ለሚገኙት እና የስደት መከራ በየግዜው ለሚያሰቃየን፣ ሀገራቸው ውስጥ የነጻነት መብታቸውን ተነጥቀው፣ ፍትህን አጥተው በእስር እየተሰቃዩ ላሉት፣ በሀገራቸው የመኖር መብታቸውን ተቀምተው ለሚንከራተቱት፣ ነጻነት እና ዲሞክራሲ እንደውሃ ከጠማው ህዝባችን ጋር በፍቅር እጅ ለእጅ ተያይዘን ሆድ እንጂ ጭንቅላት የሌለውን የዚህ ሁሉ ወገኖቻችን እልቂት፣ ስቃይ፣ መከራና መንከራተት ምክንያት የሆነውን ይህንን ባንዳ ከናዚ ባልተናነሰ መንገድ ሀገራችንን በተለያየ መንገድ ደብዛዋን ሊያጠፋ ቆርጦ ለራሱ ቃል የገባውን ቆርጠን ተነስተን የስልጣን ፍቅሩን በውርደት ኣስለቅቀን ለፍርድ ማቅረብ የምንችልበት ግዜ አሁን ነው!! አንድ ላይ በመሆን የናቁት እንዴት እንደሚያስቀር እራቁት በተግባር ለማሳየት የድሮው ይበቃል ብለን ቆርጠን መነሳት ይኖርብናል። ራሄል ኤፍሬም ከኖርዌይ

No comments:

Post a Comment